November 13, 2023 – Konjit Sitotaw
አስቸኳይ ማሳሰቢያ!
የብልፅግና ፓርቲ አገልጋይ የሆነው መከላከያ ሰራዊቱ በአሁን ሰዓት በራያ ቆቦ ወረዳ ከቆቦ ከተማ በቅርብ ርቀት ልዩ ቦታው ሆርማት ወንዝ ዙሪያ ባለው ካምፑ ነፍሰ ጡር ሴቶችን ጨምሮ የሚልሻ ቤተሰቦችን ሰብስቦ በማስገደድ “የሚልሻ ቤተሰብ በመሆናችን ብቻ ፋኖ ደበደበን፣ ዘረፈን” በሉ በሚል በቪድዮ እየቀረፀ ይገኛል።
የጋዜጠኞች ቡድን በማስመጣት
ማርፈጃውን ጀምሮ የሚሊሻ ቤተሰቦችን በማስገደድ የሚናገሩትን ካስጠና በኋላ ነው ለዜና ግብዓት እየቀረፀ የሚገኘው ሲሉ የአይን እማኞች ለአማራ ድምፅ ሚድያ ገልፀዋል።
ተገደው ሀሰት የሆነ ነገር እየተናገሩ ከተቀረፁት መካከል ነፍሰጡር ሴቶች ይገኙበታል የተባለ ሲሆን፡ እነዚህን ነፍሰ ጡር ሴቶች “የሚልሻ ቤተሰብ በመሆናችን ብቻ ለሊት ላይ ፋኖ ወደ ቤታችን መጥቶ አፍኖ ወደ ጫካ ከወሰደን በኋላ ደበደበን በመጨረሻም መከላከያ ደረሰልንና አዳነን” የሚል ንግግር እንዲናገሩ ተደርገዋል ነው የተባለው።
መረጃውን ለአማራ ድምፅ ሚድያ ያደረሱት የአይን እማኞች፡ ይህ የተቀረፀው ምስልም ዛሬ ማታ አልያም ነገ በመንግስት ሚድያዎች ሊተላለፍ ይችላል ሲሉ ጠቁመዋል።
ስለሆነም ይህ ሀሰተኛ ድርጊት ከመተላለፉ በፊት ይመለከተኛል የሚል ሁሉ አስቀድሞ እንዲያጋልጥ እና ነገሩን እንዲያከሽፍ ጥሪ ቀርቧል።
