November 13, 2023 – Zemedkun Bekele

ወሎ ደሴ…!  – ዘመድኩን በቀለ

“…በደሴ ጨው ተራ በሚገኘው የገበያ ማዕከል የሚገኙ ነጋዴዎች በሕይወት ዘመናቸው አይተውት የማያውቁት ከፍተኛ የሆነ የግብር ክፍያ በድኑ ብአዴን አምጥቶ ስለቆለለባቸው በግብሩ በመደንገጥም፣ በመቆጣትም የንግድ ቦታ ሱቃቸውን ጥርቅምቅም አድርገው በመዝጋት የሥራ ማቆም አድማ አድርገው መዋላቸው ተነግሯል።

“…ጎጃም እና ሸዋ፣ ላስታና ደቡብ ጎንደር፣ ጎጃም ከባህርዳር በቀር፣ ጎንደር ከተማው ካልሆነ በቀር ግብር ለመንግሥት መገበር ካቆሙ ቆይተዋል። ደሴና ኮምቦልቻ በኦሮሞ ብልጽግና ሰዎች የሚመሩ ስለሆነ በፋኖ ትግልም ላይ ሲያሾፉ፣ ሲያላግጡ መክረማቸውም ይታወቃል። የብር ጠኔ በአፍጢሙ እያዳፋው የሚገኘው ኦሮሙማ ከሙሉ ዐማራ ያጣውን የግብር ገንዘብ በሙሉ አስልቶ ለስላሴዋ ደሴ ላይ በመከመር በአንደዜ ትንፋሽ አሳጥሮ ሱቅ አዝግቷታል። ደሴን።

“…ዐማራ እንዲህ ሲቀጠቀጥ ነው መልክ የሚይዘው። ጎጃም ዛሬ አራስ ነብር ሆኖ የብራኑ ጁላን ጦር የሚያደባየው ማዳበሪያና ምርጥ ዘርም ስለተከለከለ ጭምር ነው። ጎንደርም ትንሽ ይቀራታል። እንደጋለ ብረት ተቀጥቅጣ መልክ መያዟ አይቀርም። ወሎ እየቀመሰች ነው። ገና ይቀራታል። በዚህ በኩል አማራን በማንቃቱ በኩል የብአዴን ዱላ እጅግ ወሳኝ ነው። በቅስቀሳም፣ በሰበካም የማይንቀሳቀሰውን ዐማራ እንዲህ ሲዠልጡት ነው እንደ ነብር እንደ አቦ ሸማኔ የሚወረወረው።

• ደሴ ነጋዴው ነገም ሱቄን አልከፍትም ብሏል። በዚያው ዘግቼ ቤቴ እውላለሁ ብሏል። ዘራፊው የትግሬ ነፃ አውጪ ጦርና የኦሮሞ ነፃ አውጪ ጦር እግረ መንገዱን መጥቶ ልክ እንደ ጎጃም እንደሻዋ ሰባብሮ ሱቁን ዘርፎ ቢጭንለት ደግሞ ለዐማራ ትግል ለፋኖ አሸወይና ይሆንለት ነበር። በለው ብልፄ ይሄን ለሽ ብሎ የተኛ ዐማራ። ዠልጠው። ኮምቦልቻና ደሴ አዚሙ ሊገፈፍላቸው ይመስላል።

• ጁላዬ የተኛውን ዐማራ ዠልጠው…!