Skip to content
ጭምቅ ሃሳብ
- አል ሺፋ ሆስፒታል በታንክ ተከቧል
- ባይደን አል-ሺፋ ሆስፒታል ጥበቃ ሊደረግለት ይገባል አሉ
- የጋዛ ጉዳይ ወታደራዊ መፍትሄ የለውም- የዮርዳኖስ ንጉስ አብዱላህ
- በእስራኤል ጥቃት የተገደሉ ፍልስጤማውያን ቁጥር 11 ሺህ 240 ደረሰ- የጋዛ ጤና ሚኒስቴር
- እስራኤል በጋዛ ትልቁ ሆስፒታል ላይ ጥቃት ፈጽማለች መባሏን አስተባበለች
- አሜሪካ በሶሪያ በሚገኙ የኢራን ጦር ሰፈሮች ላይ ጥቃቶች ፈጸመች
- በጋዛ ትልቁ ሆስፒታል ያለው ሁኔታ አስከፊ እንደሆነ ዶ/ር ቴድሮስ ገለጹ
- በጋዛ ያሉ ሆስፒታሎች ጥቃት እንደተፈጸመባቸው ተመድ አስታወቀ
- ተመድ በጋዛ የሚገኘው ቢሮው ጥቃት እንደደረሰበት አስታወቀ
- በጋዛ ትልቁ ሆስፒታል ሥራ ለማቆም ተቃርቧል
- የእስራኤል መከላከያ ቤይሩት የጋዛ እጣ ፈንታ ሊገጥማት ይችላል ሲል ሄዝቦላህን አስጠነቀቀ
- በአልሺፋ ሆስፒታል ጨቅላ ማሞቂያ ውስጥ ያሉ ሕጻናት በሞት አፋፍ ላይ ናቸው ተባለ
- የታተመዉ 11:1411:14ከአል-ሺፋ ለመውጣት የሚሞክሩ በጥይት እየተመቱ ነው ተባለበእስራኤል ጦር ከበባ ስር ከሚገኘው ከጋዛ ትልቁ ሆስፒታል ለመውጣት ሙከራ የሚያደርጉ ከወገባቸው በታች በጥይት እየተመቱ ነው ተባለ።የቢቢሲው ጋዜጠኛ ቁስም ሆነ ሰው ላለፉት 48 ሰዓታት ወደ ሆስፒታሉ እንዳይገባም ሆነ እንዳይወጣ የእስራኤል ጦር መከልከሉን በስፍራው ከሚገኙ ምንጮቹ ሰምቷል።በሆስፒታሉ ከሚገኘው ጋዜጠኛ እንደሰማው ከአል-ሺፋ ሆስፒታል ለመውጣት የሞከሩ አራት ሰዎች እግራቸው ላይ ተመትተው ደም እየፈሰሳቸው እርዳታ ጥበቃ እስከ ሁለት ሰዓታት በመንገድ ላይ ውድቀው ነበር።የሆስፒታሉ ጤና ባለሙያዎች ሕይወታቸውን አደጋ ላይ ጥለው አራቱን ሰዎች ለሕክምና ወደ ሆስፒታሉ መልሰው አስገብተዋል።እስራኤል ሐማስ ከአል-ሺፋ ሆስፒታል ስር የማዘዣ ጣቢያ አለው ትላለች። ይህን ግን ሐማስም ሆነ የጤና ተቋሙ ሐሰት ነው ይላሉ።Article share tools
- የታተመዉ 8:168:16እውቅ ፖለቲከኞች ኔታኒያሁ ላይ የዘር ማጥፋት ወንጀል ምርመራ እንዲከፈተ ጠየቁ
ReutersCopyright: Reutersጠቅላይ ሚንስትር ቤኒያሚን ኔትኒያሁImage caption: ጠቅላይ ሚንስትር ቤኒያሚን ኔትኒያሁበአውሮፓ እና ደቡብ አሜሪካ የሚገኙ ፖለቲከኞች የእስራኤል መንግሥት የዘር ማጥፋት ወንጀል ምርመራ እንዲከፈትበት ጠየቁ።60 የሚሆኑት ግራ ዘመም ፖለቲከኞች እስራኤል በጋዛ እያካሄድ ባለችው ወታደራዊ ዘመቻ የዘር ማጥፋት ወንጀል ስለመፈጸሟ ዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ምርመራ እንዲያደርግ ፊርማ ማሰባሰብ ጀምረዋል።የስፔን የማኅበራዊ መብቶች ሚንስትሯ አዮን ቤላራ እንዲሁም የዬኬው ሌበር ፓርቲ አመራር እና የፓርላማ አባል ጄሬሚ ኮርቤይ ጥያቄውን ካቀረቡት ፖለቲከኞች መካከል ይገኙበታል።ፖለቲከኞቹ ጠቅላይ ሚንስትር ቤኒያሚን ኔትኒያሁን፣ መከላከያ ሚንስትሩ ዮአቭ ጋላንትን እንዲሁም የፋይናንስ ሚንስትሩ ቤዛሌል ስሞትሪችን በዘር ማጥፋት እና በሰብዓዊነት ላይ በሚፈጸም ወንጀል ከሰዋቸዋል።Article share tools
- የታተመዉ 7:227:22ባለፉት ጥቂት ሰዓታት በጋዛ ያጋጠሙ ዋና ዋና ክስተቶች
EPACopyright: EPAእስራኤል በሐማስ ላይ የምትወስደውን የአጸፋ እርምጃ አጠናክራ የቀጠለች ሲሆን ባለፉት ቀናት ዋነኛ ትኩረት ሆኖ የቆየው የእስራኤል ጦር በዋነኛ ሆስፒታሎች ዙሪያ የሚያደርገው ዘመቻ ነው።የቢቢሲው ዘጋቢ በጋዛ ካሉት ምጮቹ እንደሰማው በጋዛ ትልቁ በሆነው አል-ሺፋ ሆስፒታል 170 አስክሬኖችን ለመቅበር የጅምላ መቃብር እየተቆፈረ ነው።እስራኤል በተለይ አል-ሺፋ ሆስፒታልን ዒላማ አላደረጉም በትልም ሐማስ የማዘዣ ጣቢያ ከሆስፒታሉ ስር ስለገነባ በሆስፒታሉ ዙሪያ ዘመቻ እያካሄድኩ ነው ትላለች።ሐማስ እና የሕክምና ተቋሙ ግን ይህ ሐሰት ነው ይላሉ።በሌላ ዜና የእስራኤል ጦር መስከረም 26 በሐማስ ከታገቱት መካከል አንዲት የ19 ዓመት እስራኤላዊት መገደሏን አረጋግጫለሁ ብሏል። ጦሩ የወጣቷ ሞት መንስዔ ምን እንደሆነ ያለው ነገር የለም።Article share tools
- የታተመዉ 7:107:10የዓለም ጤና ድርጅት ከግማሽ በላይ የጋዛ ሆስፒታሎች ከአገልግሎት ውጪ ሆነዋል አለ
ReutersCopyright: Reutersየዓለም ጤና ድርጅት በጋዛ ከሚገኙ 36 ሆስፒታሎች መካከል 22 የሚሆኑት አገልግሎት መስጠት ማቆማቸውን አስታወቀ።ድርጅቱ ሆስፒታሎቹ ሥራ ለማቆም የተገደዱት በነዳጅ እጥረት፣ በደኅንነት ስጋት ወይም ውድመት አጋጥሟቸው ነው ብሏል።በሥራ ላይ የሚገኙ 14 ሆስፒታሎችም ቢሆኑ ከፍተኛ የሕክምና ቁሳ ቁስ እጥረት እንዳለባቸው የገለጸው ተቋሙ፤ በጋዛ አስቸኳይ የሆነ የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲደረግ ዳግም ጠይቋል።Article share tools
- የታተመዉ 5:025:02የጋዛ ጉዳይ ወታደራዊ መፍትሄ የለውም- የዮርዳኖስ ንጉስ አብዱላህ
ReutersCopyright: Reutersእስራኤል የተወሰነውን የጋዛ ክፍል ለመቆጣጠር ወይም በግዛቲቱ ውስጥ የጸጥታ ቀጠና ለመመስረት ያቀደችውን እቅድ እንደማይቀበሉ የዮርዳኖሱ ንጉስ አብዱላህ ተናገሩ።በእስራኤል እና በፍልስጤም መካከል ላለው ግጭት “ወታደራዊም ሆነ የጸጥታ መፍትሄ” እንደማይኖሩ ንጉሱ ለከፍተኛ ፖለቲከኞች መናገራቸውን የመንግሥት መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።የቀውሱ መንስኤ እስራኤል የፍልስጤማውያንን “ህጋዊ መብት መካዷ” እንደሆነም ተናግረዋል። “መፍትሔው ከዚህ ይጀምራል። የትኛውም ሌላ መንገድ የማይሳካ እና የበለጠ የብጥብጥ እና ውድመት አዙሪት የሚያስከትል ነው” ብለዋል።የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ እስራኤል በጋዛ ሰርጥ ላልተወሰነ ጊዜ “አጠቃላይ የጸጥታ ኃላፊነት” እንደሚኖራት ባለፈው ሳምንት በሰጡት ቃለ ምልልስ ተናግረው ነበር።ዮርዳኖስ በርካታ የፍልስጤም ስደተኞች መኖሪያ ነች።Article share tools
- የታተመዉ 4:344:34ባይደን አል-ሺፋ ሆስፒታል ጥበቃ ሊደረግለት ይገባል አሉ
Al Drago/POOL/EPA-EFE/REX/ShutterstockCopyright: Al Drago/POOL/EPA-EFE/REX/Shutterstockየአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን እስራኤል የጋዛ ትልቁን ሆስፒታል አል ሺፋን እንድትጠብቅ አሳሰቡ።ፕሬዚዳንቱ ትናንት በሰጡት መግለጫ መንግሥታቸው ከእስራኤል ጋር እየተነጋገረ እንደሆነ እና በሆስፒታሉ ላይ የምትወስደው እርምጃ “ተገቢ” በሆነ መልኩ እንደሚሆንም ተስፋቸውን ገልጸዋል።”ሆስፒታሉ ጥበቃ ሊደረግለት ይገባል” ሲሉም ለጋዜጠኞች ተናግረዋል።የዓለም ጤና ድርጅት ትልቁ የጋዛ ሆስፒታል አል ሺፋ ወደ መቃብርነት ስፍራ እየተቀየረ እንደሆነ ማሳሰቡን ተከትሎም ነው ፕሬዚዳንቱ ይህንን የተናገሩት።በሆስፒታሉ አቅራቢያ ጦርነት እየተፋፋመ ሲሆን እስራኤል ሆስፒታሉን ከበባ ውስጥ አስገብታዋለች ተብሏል።በርካታ አገራት ዕርዳታ እንዲገባ እና ነዋሪዎች ወደ ጋዛ እንዲገቡ እና እንዲወጡ ለማስቻል ጦርነቱ እንዲገታ ሲጠይቁ ሌሎች ደግሞ አስቸኳይ የተኩስ አቁም እንዲደረግ እየጠየቁ ይገኛሉ።እስራኤል በጋዛ የምታደርገውን ጥቃት በተቀናጀ ሁኔታ የቀጠለች ሲሆን በየቀኑ ለአራት ሰዓታት የሚቆይ የእፎይታ ጊዜ እንደሚኖርም ተናግራለች።Article share tools
- የታተመዉ 4:074:07አል ሺፋ ሆስፒታል በታንክ ተከቧል
Getty ImagesCopyright: Getty Imagesየጋዛው ትልቁ ሆስፒታል አል ሺፋ በታንክ መከበቡን በሆስፒታሉ ውስጥ ካለ ሰው ቢቢሲ ሰምቷል።በሆስፒታሉ አካባቢ ያለው ውጥረት አሁንም ተፋፍሞ እንደቀጠለ እና በትናንትናው ሌሊትም የፍንዳታ እና የተኩስ ልውውጥ መስማታቸውን እኚሁ ግለሰብ ተናግረዋል።በተጨማሪም ታንኮች ሆስፒታሉን ከየአቅጣጫው እንደከበቡትና ወደ ሆስፒታሉ መግባትም ሆነ መውጣት እንደማይቻል ገልጸዋል።በሆስፒታሉ ቅጥር ግቢም ቢሆን ከአንዱ ህንጻ ወደ ሌላው መንቀሳቀስ ከፍተኛ አደጋ እንደጋረጠም ተናግረዋል። በሆስፒታሉ መብራት፣ ውሃ እና በቂ መድኃኒት ባለመኖሩ በርካቶች ለሞት ተዳርገዋል ብለዋል።የዓለም ጤና ድርጅት ሆስፒታሉ ወደ መቃብር ስፍራነት እየተቀየረ እንደሆነ እና በርካታ አስከሬኖችም በሆስፒታሉ ውስጥ እና ቅጽር በአሰቃቂ ሁኔታ ተከምረዋል ብሏል።የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ከፍተኛ አማካሪ ማርክ ሬጅቭ መንግሥታቸው እሁድ እለት 300 ሊትር ነዳጅ ለሆስፒታሉ ለማድረስ ያደረገው ሙከራ ሐማስ ሊቀበለው ባለመቻሉ ሳይሳካ ቀርቷል ብለዋል።ሐማስ ይህንን ሐሰት ነው ብሏል።እኚሁ በሆስፒታሉ ውስጥ ያሉት ግለሰብ አልሺፋ ያለው ነዳጅ ለግማሽ ሰዓት ብቻ የሚያቆይ ነው ብለዋል። ሆስፒታሉ አገልግሎቱን ለማከናወን በየቀኑ ቢያንስ 10 ሺህ ሊትር እንደሚያስፈልገው ገልጸው መፍትሄ እንዲፈለግም ጥሪያቸውን አቅርበዋል።እስራኤል በአልሺፋ መሬት ስር የሐማስ ማዘዣ እና የቁጥጥር ማዕከል አለ ትላለች። ሐማስ ይህንን ውንጀላ አይቀበለውም። እንዲሁም የሆስፒታሉ ዶክተሮችም ፍጹም ሐሰት ነው ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል።”በመቶዎች ለሚቆጠሩ ጊዜያት ወደዚህ ሆስፒታል መጥቼያለሁ። እዚሁ ነው የተወለድኩት። ልጄ የተወለደው በእዚህ ሆስፒታል ውስጥ ነው። እናቴ ከመሞቷ በፊት በመጨረሻዎቹ ሁለት ወራት በኩላሊት የእጥበት ማዕከል ተኝታ ትታከም ነበር። በየቀኑም እጎበኛት ነበር””ከሆስፒታሉ ስር ያለውን አላውቅም። በሆስፒታሉ ህንጻዎች ምንም አይነት ወታደራዊ እንቅስቃሴ በአይኔ አይቼ አላውቅም”Article share tools
- የታተመዉ 1:271:27በእስራኤል-ጋዛ የተከሰቱ የቅርብ ጉዳዮች
Getty ImagesCopyright: Getty Images- የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን እስራኤል በሙሉ ከበባ ውስጥ ባስገባቻት የጋዛ ሰርጥ የሚገኙ ሆስፒታሎች ጥበቃ ሊደረግላቸው እንደሚገባ ተናግረዋል። እስራኤል በሆስፒታሎቹ ላይ የምትወስደው እርምጃ “ተገቢ” በሆነ መልኩ እንደሚሆንም ተስፋቸውን ገልጸዋል። የዓለም ጤና ድርጅት ትልቁ የጋዛ ሆስፒታል አል ሺፋ ወደ መቃብርነት ስፍራ እየተቀየረ እንደሆነ ማሳሰቡን ተከትሎም ነው ፕሬዚዳንቱ ይህንን የተናገሩት።
- እስራኤል ሐማስ አል ሺፋ ሆስፒታልን እንደ ወታደራዊ ማዕከል እየተጠቀመበት ነው ስትል እየወነጀለች ትገኛለች። የእስራኤል ጦር ቃለ አቀባይ ዳንኤል ሐጋሪ ሐማስ በጋዛ የሚገኘውን የህጻናት ሆስፒታል ለጦር መሳሪያ ማከማቻነት እየተጠቀመበት ነው ሲሉ ማስረጃ ለቢቢሲ አቅርበዋል። ቢቢሲ ይህንን ማስረጃ ማረጋገጥ አልቻለም። ሐማስ ሆስፒታሎችን ለወታደራዊ አገልግሎት ይጠቀምበታል የሚለውን ክስ አይቀበለውም።
- እስራኤል በጋዛ እየፈጸመቻቸው ባለው የተቀናጀ የአየር፣ የመሬት እና የባህር ጥቃቶች የተገደሉ ፍልስጤማውያን ቁጥር 11 ሺህ 240 መድረሱን የጋዛ ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል። ከነዚህም ውስጥ አብዛኛዎቹ 4 ሺህ 630 ህጻናት መሆናቸው ተገልጿል። በተጨማሪም በእስራኤል ጥቃት ከተገደሉት 3 ሺህ 130 ሴቶች መሆናቸውን ሐማስ የሚቆጣጠረው የመንግሥት የሚዲያ ጽህፈት ቤት አስታውቋል። በጥቃቱ የቆሰሉ ፍልስጤማውያን ከ28 ሺህ በላይ መሆኑንም ጽህፈት ቤቱ አስታውቋል። ሐማስ መስከረም 26 በፈጸመው ጥቃት 1 200 ሰዎች ሲገደሉ፣ ከ200 በላይ ታጋቾችም ተወስደዋል።
- የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት (ዩኤን ኦቻ) 200 ሺህ የሚገመቱ ፍልስጤማውያን በቅርቡ ከሰሜን ጋዛ ወደ ደቡብ መሸሻቸውን ገልጿል። በደቡባዊ ጋዛ የመጠለያ፣ የምግብ እና የውሃ አቅርቦት በከፍተኛ ሁኔታ ውስን እንደሆነ እና አሳሳቢ መሆኑንም አስጠንቅቋል።
- የዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚኒስትር ሪሺ ሱናክ እስራኤል ራሷን ለመከላከል እና ታጋቾቿን ለማስለቀቅ የምታደርገው ጥረት አለም አቀፉን ህግ የተከተለ ሊሆን ይገባል ብለዋል። ንጹሃን ዜጎችን ለመጠበቅ ሁሉንም እርምጃዎችን መውሰድ እንደሚገባት ያሳሰቡት ሱናክ ከነዚህም ውስጥ በሆስፒታሎች ላይ ጥቃት እንዳይፈጸም እንዲሁም በዌስት ባንክ ግዛት አክራሪ ሰፋሪዎች በፍልስጤማውያን ላይ እየፈጸሙት ያሉትን ጥቃት ማስቆም አለባት ብለዋል። እንዲሁ ጦርነቱ በተጨባጭ መንገድ እንዲገታም ጠይቀዋል።
Article share tools
- የታተመዉ 0:220:22የጋዛው ትልቁ ሆስፒታል በአስከሬኖች እንደተጨናነቀ ተገለጸበጋዛ በሚገኘው ትልቅ ሆስፒታል ጦርነት ሸሽተው ከተጠለሉ በሺዎች ከሚቆጠሩ ነዋሪዎች በተጨማሪ አስከሬኖች እየተከማቹ መሆኑን ባለስልጣናት አስጠንቅቀዋል። ከኃይል መቆራረጥ እና ከነዳጅ እጥረት ጋር ግብግብ ውስጥ የገባው አል ሺፋ ሆስፒታል መደ “መቃብር ስፍራነት ተቀይሯል” ሲል የዓለም ጤና ድርጅት አስጠንቅቋል። የሆስፒታሉ ስራ አስኪያጅ በእስራኤል ከበባ ውስጥ በመሆናቸው ምክንያት ያሉት ውሾች አስከሬን መብላት መጀመራቸውን ተናግረዋል።ተጨማሪ ያንብቡArticle share tools
- የታተመዉ 23:53 13 ህዳር 202323:53 13 ህዳር 2023አሜሪካ ሶሪያ በሚገኙ በኢራን በሚደገፉ የጦር ሰፈሮች ላይ ጥቃት ማድረሷን ቀጥላለችዩናይትድ ስቴትስ፤ ሶሪያ የሚገኙ በኢራን አብዮታዊ ዘብ ጥቅም ላይ የሚውሉ ወታደራዊ ቁሳቁሶችን በአየር ጥቃት ማውዷሟን ፔንታገን ገልጧል። የመከላከይ ሚኒስትሩ ሎይድ ኦስቲን ይህ ምላሽ የተሰጠው ኢራቅና ሶሪያ ውስጥ በአሜሪካ መቀመጫዎች ላይ በኢራን የተደገፉ ኃይሎች ላደረሱት ጥቃት ነው ብለዋል። መቀመጫውን ዩናይትድ ኪንግደም ያደረገው አንድ የጦርነት ሂደቶች ተቆጣጣሪ ቢያንስ ስምንት የኢራን ደጋፊ ታጣቂዎች ተገድለዋል ብሏል።ተጨማሪ ያንብቡArticle share tools
- የታተመዉ 23:41 13 ህዳር 202323:41 13 ህዳር 2023በእስራኤል ጥቃት የተገደሉ ፍልስጤማውያን ቁጥር 11 ሺህ 240 ደረሰ- የጋዛ ጤና ሚኒስቴር
Getty ImagesCopyright: Getty Imagesእስራኤል በጋዛ እየፈጸመቻቸው ባለው የተቀናጀ የአየር፣ የመሬት እና የባህር ጥቃቶች የተገደሉ ፍልስጤማውያን ቁጥር 11 ሺህ 240 መድረሱን የጋዛ ጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።ከነዚህም ውስጥ አብዛኛዎቹ 4 ሺህ 630 ህጻናት መሆናቸው ተገልጿል። በተጨማሪም በእስራኤል ጥቃት ከተገደሉት 3 ሺህ 130 ሴቶች መሆናቸውን ሐማስ የሚቆጣጠረው የመንግሥት የሚዲያ ጽህፈት ቤት አስታውቋል።በጥቃቱ የቆሰሉ ፍልስጤማውያን ከ28 ሺህ በላይ መሆኑንም ጽህፈት ቤቱ አስታውቋል።የዓለም ጤና ድርጅት ሐማስ የሚመራው ባለስልጣናት በሚያቀርቡት የተገደሉ ፍልስጤማውያን አኃዝ ላይ እምነት እንዳለው ገልጿል።Article share tools
- የታተመዉ 10:37 13 ህዳር 202310:37 13 ህዳር 2023የተባበሩት መንግሥታት ኤጀንሲ በጋዛ የሚገኝ የነዳጅ ዴፖውን አሟጦ መጠቀሙን ገለጸ
Getty ImagesCopyright: Getty Imagesየፍልስጤማውያንን ስደተኞች የሚከታተለው የተባበሩት መንግሥታት ኤጀንሲ በነዳጅ ማከማቻው የሚገኘው ነዳጅ ተሟጦ ማለቁን ተናገረ።ይህ በጋዛ የሚገኙ በርካታ አገልግሎቶችን የሚደግፈው ኤጀንሲ በነዳጅ ዴፖዬ እንጥፍጣፊ ነዳጅ የለም ማለቱን የዘገበው ሮይተርስ ነው።የስደተኞች ኤጀንሲው ኃላፊ ፊሊፔ ላዛሪኒ ለለጋሾች እንደገለጹት፣ በጥቂት ቀናት ውስጥ ኤጀንሲው ለሆስፒታሎችን የሚያስለፍገውን ማቅረብ፣ ፍሳሾችን ማስወገድ እንዲሁም የመጠጥ ውሃ ማቅረብ አይችልም።ከጥቂት ሰዓታት በፊት በጋዛ የስደቶች ኤጀንሲው ዳይሬክተር የሆኑት፣ ቶም ዋይት፣ በኤክስ ገጻቸው ላይ “በጋዛ የሚካሄደው ሰብዓዊ እርዳታ በሚቀጥሉት 48 ሰዓታት ውስጥ ወደ ጋዛ ነዳጅ እንዳይገባ በመደረጉ ምክንያት ይቆማል” ሲሉ አስፍረዋል።ዳይሬክተሩ አክለውም ዛሬ ማለዳ ሁለት የኤጀንሲው መጠጥ ውሃ አከፋፋዮችስራቸውን አቁመዋል ሲሉ ተናግረዋል።ይህም ለ200ሺህ ነዋሪዎች የመጠጥ ውሃ እንዳይቀርብ አድርጓል።ውሃ አከፋፋዮቹ “ነዳጅ ጨረሰዋል” ነው ያሉት ዳይሬክተሩ።እስራኤል ሐማስ ጥቃት ከፈጸመበት ከመስከረም 26 ጀምሮ የሐማስን ወታደራዊ እንቅስቃሴ ያግዛል በሚል ወደ ጋዛ ነዳጅ እንዳይገባ ከልክላለች።እስራኤል አክላም በጋዛ በቂ ነዳጅ እንዳለ እና ሐማስ እያከማቸ ነው ስትል ትወነጅላለች።እስራኤል ለአል-ሺፋ ሆስፒታል 300 ሊትር ነዳጅ ማቅረቧን ተናግራ ነበር።ከሳምንታት በፊት የአሜሪካ ባለሥልጣናት በፍልስጤም የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ኤጀንሲ በግዛቱ የሚገኝ የነዳጅ መጠባበቅያን መጠቀም አለመቻሉን ገልጸው ነበር።በፍልስጤም የስደተኞች ጉዳይን የሚከታተለው የተባበሩት መንግሥታት ኤጀንሲ ቀስ በቀስ በጋዛ እና እስራኤል ድንበር አካባቢ ያለውን የነዳጅ ዲፖ አሟጦ እየተጠቀመ መሆኑን በመግለጽ፣ እንዲሞላለት ለእስራኤል መንግሥት ያቀረበው ጥያቄ ሰሚ ጆሮ ማጣቱን ሮይተርስ ላዛሪኒን ጠቅሶ ዘግቧል።Article share tools
- የታተመዉ 9:43 13 ህዳር 20239:43 13 ህዳር 2023የእስራኤል ጦር በአል-ሺፋ ሆስፒታል ነዳጅ ላለመኖሩ ሐማስን ተጠያቂ አደረገ
BBCCopyright: BBCየእስራኤል መከላከያ ኃይሎች ቃል አቀባይ ለቢቢሲ በአል-ሺፋ ሆስፒታል ከጊዜያቸው ቀድመው የተወለዱ ሕጻናት ሕይወትን ለመታደግ በአስቸኳይ የሚያስፍለገው ነዳጅ እንዳይደርስ ያደረገው ሐማስ ነው ሲሉ ወነጀሉ።“ድጋፍ አቅርበናል፣ ለሆስፒታሉ የሚያስፈልገው ነዳጅን አቅርበናል። ነዳጁ ያልተወሰደው በሐማስ ትዕዛዝ መሰረት ነው” ሲሉ ተናግረዋል ሌተናንት ኮሎኔል ጆናታን ኮንሪከስ።ኮርኒከስ የሆስፒታሉ ሰራተኞች እስራኤል ያቀረበችውን 300 ሊትር ነዳጅ ለመቀበል ከሆስፒታሉ ቅጥር ግቢ ውጪ ከወጡ በእስራኤል ጦር ጥቃት ይደርስብናል ሲሉ መግለጻቸውን “ሙሉ በሙሉ ውድቅ” አድርገውታል።“ይህ ሙሉ በሙሉ ሐሰት ነው። ደህንነታቸው አስተማማኝ ባይሆን እንኳ በእስራኤል ጦር የተነሳ ሳይሆን በሐማስ ምክንያት ነው የሚሆነው” ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል።ኮንሪከስ ሐማስ ለአል-ሺፋ ሆስፒታል ስራ አስኪያጅ “ነዳጁን እንዳይወስዱ” መናገሩን አስረድተዋል። አክለውም “ምናልባት በሆስፒታሉ የሚገኙ ሠራተኞች ላይ እየተኮሰ ሕይወታቸውነ አደጋ ላይ የጣለው ይኸው ሐማስ ይሆናል” ብለዋል።የእሰራኤል ጦር ለሆስፒታሉ የሚያስፈልግ ያለውን 300 ሊትር ነዳጅ ቢያቀርብም፣ አል-ሺፋ ሆስፒታል ግን በሰዓት ለመንቀሳቀስ 500 ሊትር ነዳጅ እንደሚያስፈልገው ይገልጻል።Article share tools
- የታተመዉ 9:11 13 ህዳር 20239:11 13 ህዳር 2023እስራኤል እግረኛ ጦሯን በጋዛ ካሰማራች ጀምሮ የሞቱ ወታደሮቿ ቁጥር 44 መድረሱን አስታወቀች
ReutersCopyright: Reutersየእስራኤል መከላከያ ሰኞ ዕለት ሁለት ተጨማሪ ወታደሮቹ በሰሜን ጋዛ ጦርነት ምክንያት እንደሞቱበት አስታወቀ።እንደ እስራኤል ሚዲያ ዘገባ ከሆነ እስራኤል ጦሯን ወደ ጋዛ ካሰማራች ጀምሮ የሞቱት ወታደሮቿ ቁጥር 44 ደርሷል።የእስራኤል ጦር ኃይል በምዕራብ ጋዛ ከተማ በሚገኘው አል ሻቲ የስደተኞች መጠለያ አካባቢ የሚያካሄደውን ማጥቃት እንደቀጠለ ተናግሯል።እስራኤል በጋዛ ጥቃት መፈጸም የጀመረችው ሐማስ መስከረም 26 በፈጸመው ድንገተኛ ጥቃት 1ሺህ 200 ሰዎች መገደላቸውን እና ከ200 በላይ ታግተው መወሰዳቸውን ተከትሎ ነው።በሐማስ የሚመራው ጤና ሚኒስትር እንዳስታወቀው በጋዛ እስካሁን ድረስ 11 ሺህ ሰዎች የተገደሉ ሲሆን፣ ከእነዚህ ውስጥም 4ሺህ 500ዎቹ ሕጻናት ናቸው።Article share tools
- የታተመዉ 8:53 13 ህዳር 20238:53 13 ህዳር 2023ቱርክ ከራፋ ድንበር አቅራብያ ስምንት የመስክ ሆስፒታሎች ልትገነባ ነው
Getty ImagesCopyright: Getty Imagesለመስክ ሆስፒታል የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶችን የጫነች የቱርክ መርከብ ለራፋ ድንበር አቅራብያ በሚገኝ የግብጽ ወደብ ላይ መድረሷ ተሰማ።መርከቧ ላይ ጄኔሬተሮች፣ አምቡላንሶች፣ እንዲሁም የሕክምና ቁሳቁሶች የሚገኙ ሲሆን ዕቅዱ ስምንት የመስክ ሆስፒታሎችን መገንባት መሆኑን አዣንስ ፍራንስ ፕሬስ ዘግቧል።መስከረም 26 በሐማስ እና እስራኤል መካከል ጦርነት ከተቀሰቀሰ ወዲህ እንዲህ ዓይነት እርዳታ ግብጽ ሲደርስ የመጀመርያው ነው።የዓለም ጤና ድርጅት በጋዛ ከተማ የሚገኘው ትልቁ ሆስፒታል “አገልግሎት መስጠት አቁሟል” ሲል መናገሩ ይታወሳል።ሌሎች የሕክምና ተቋማትም በተመሳሳይ ነዳጅ እና የኃይል አቅርቦት ባለመኖሩ እንዲሁም በዙሪያቸው የሚካሄደው ጦርነት ምክንያት ለደህንነታቸው አስጊ በመሆኑ ስራ ያቆሙ መሆናቸው በተለያዩ አካላት ተገልጧል።የቱርክ የጤና ባለሥልጣን ለኤኤፍፒ እንደተናገሩት አናካራ ከግብጽ ባለስልጣናት በአል አሪሽ የመስክ ሆስፒታሎች ለመገንባት ይሁንታን አግኝታለች።የሚገነቡት ሆስፒታሎች ከራፋህ ድንበር 40 ኪሎሜትር ርቀት ላይ የሚገኙ ይሆናል።Article share tools
- የታተመዉ 7:00 13 ህዳር 20237:00 13 ህዳር 2023በሰሜን ጋዛ በሚገኙ ቁልፍ የሕክምና ተቋማት የተከሰተው ምንድን ነው?
REUTERSCopyright: REUTERSበጋዛ የሚገኙ ሆስፒታሎች እና የሕከምና ተቋማት እስራኤል ሐማስ ላይ በከፈተችው መጠነ ሰፊ ወታደራዊ ዘመቻ የተነሳ አጣብቂኝ ውስጥ ወድቀዋል።የበርካቶች ዋናው ትኩረት በትልቅነቱ ቀዳሚ በሆነው አል-ሺፋ ሆስፒታል ነው።በዚህ ሆስፒታል ውስጥ ከ2ሺህ 300 በላይ ሰዎች በሆስፒታሉ አቅራብያ በሚካሄዱ ግጭቶች የተነሳ መላወስ ሳይችሉ ቀርተዋል።በሌሎች የሕክምና ተቋማት ያለውም ሁኔታ ተመሳሳይ ነው።የኃይል አቅርቦት እና የሕክምና ቁሳቁስ እጥረት በሆስፒታሎቹ ሕክምና ለማግኘት የሚጠባበቁ ሰዎችን ሕይወት አደጋ ላይ ጥሎታል።እንደ ዓለም ጤና ድርጅት መረጃ ከሆነ በጋዛ ጦርነት ከተቀሰቀሰ ጊዜ ጀምሮ 22 ሆስፒታሎችን ጨምሮ፣ 36 የሕክምና ተቋማት ወድመዋል።በጣት የሚቆጠሩት ብቻ ናቸው በስራ ላይ ያሉት።እንደ ዓለም ጤና ድርጅት መግለጫ ከሆነ በጋዛ ከተማ የሚገኘው እና 700 አልጋዎች ያሉት ትልቁ ሆስፒታል አል-ሺፋ አገልግሎት መስጠት አቋርጧል።ጤና ድርጅቱ አክሎም በሆስፒታሉ ውስጥ ያለውን ሁኔታ “ አሰቃቂ እና አደገኛ” ሲል ጠርቶታል።በሆስፒታሉ ዙርያ የሚገኙ መንገዶች በሐማስ እና በእስራኤል ኃይሎች መካከል በሚካሄዱ ግጭቶች እየተናጡ ነው።እንደ ተባበሩት መንግሥታት መረጃ ከሆነ ወሳኝ የሚባሉ መሰረተ ልማቶች ወድመዋል።የሆስፒታሉ ሠራተኞች ሞትን አልያም ጉዳትን ሳይጋፈጡ ከሆስፒታሉ መውጣት የሚታሰብ አይደለም።እንደ ፍልስጤም ቀይ ጨረቃ መረጃ ከሆነ በጋዛ ሰርጥ የሚገኘው እና ከአል -ሺፋ በመቀጠል ሁለተኛ የሆነው አል-ቁድስ ሆስፒታል ስራውን አቋርጧል።የፍልስጤም ቀይ ጨረቃ ቅዳሜ ዕለት ይፋ ባደረገው መረጃ መሰረት የሆስፒታሉ ሰራተኞች ከ500 ሕሙማን እና ከ14 ሺህ ተፈናቃዮች ጋር መላወሻ አጥተው ይገኛሉ።ቅዳሜ ዕለት ሆስፒታሉ በነዳጅ አቅርቦት አለመኖር እና የኤሌትሪክ ኃይል በመቋረጡ የተነሳ አገልግሎት መስጠት ማቋረጡ ይፋ ተደርጓል።ድንበር የለሽ የሐኪሞች ማህበር ቅዳሜ ዕለት፣ በሆስፒታሉ የሚሰራ እና ከእነ ቤተሰቡ የተጠለለ የቀዶ ሕክምና ባለሙያ ጋር ያለው ግንኙነት መቋረጡን እና አሁን ስላለበት ሁኔታ ምንም ዓይነት መረጃ ማግኘት እንዳልቻለ አስታውቆ ነበር።በሰሜን ጋዛ ከተማ የሚገኙት ለሕጻናት ሕክምና የሚሰጠው ራንቲሲ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል እና በአቅራብያው የሚገኘው አል-ናስር ሆስፒታል ያሏቸውን ሕሙማን እና ሠራተኞቻቸውን ለማትረፍ ለቅቀው እንዲወጡ የተደረገው አርብ ዕለት ነበር።ራንቲሲ በጋዛ ከተማ የሕጻናት ካንሰር ሕክምና የሚሰጥ ብቸኛው ተቋም ነበር።የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ ጉዳዮች ቢሮ ቅዳሜ ዕለት በምዕራብ ጋዛ የሚገኘው የስዊዲሽ ክሊኒክ “በአየር ድብደባ መመታቱን እና መውደሙን” ይፋ አድርጓል።በክሊኒኩ 500 ሰዎች የተጠለሉ መሆናቸውን እና ስለደረሰው ጉዳት ይፋዊ መረጃ አለመኖሩንም በመግለጫው ላይ አስፍሯል።Article share tools
- የታተመዉ 5:58 13 ህዳር 20235:58 13 ህዳር 2023የአውሮጳ ሕብረት በጋዛ ‘ተጨባጭ የሆነ’ የተኩስ አቁም እንዲደረግ ጠየቀ
OLIVIER HOSLET/EPA-EFE/REX/ShutterstockCopyright: OLIVIER HOSLET/EPA-EFE/REX/Shutterstockየአውሮጳ ሕብረት በጋዛ የሚካሄደው ውግያ ‘ተጨባጭ የሆነ” የተኩስ አቁም ተደርጎ ሆስፒታሎች ተገቢውን አገልግሎት መስጠት እንዲችሉ የነዳጅ አቅርቦት መዳረስ እንዳለበት ገለጸ።የአውሮጳ ኮሚሽን ከፍተኛ ባለስልጣን የሆኑት፣ ዣኔዝ ሌናርሲስ፣ ሰኞ ዕለት በብራሰልስ በተካሄደ ስብሰባ ላይ “በጋዛ ሰርጥ የሚገኙ ከግማሽ በላይ የሚሆኑ ሆስፒታሎች በዋናነት በነዳጅ አቅርቦት አለመኖር ምክንያት ስራ አቁመዋል” ሲሉ ተናግረዋል።”የተኩስ አቁሙ ተጨባጭ መሆን አለበት” በማለት አክለዋል ሌናርሲስ።” በመጀመርያ ድርጅቶች በአግባቡ ስራቸውን እንዲያቅዱ በቅድሚያ መነገር አለበት። በመቀጠል ደግሞ ከጊዜ አንጻር በሚገባ መቀመጥ አለበት” ሲሉ ተናግረዋል።ሐማስ ጥቃት ከከፈተበት መስከረም 26 ጀምሮ ነዳጅ ወደ ጋዛ ሰርጥ እንዳይገባ ታግዷል።የአውሮጳ ሕብረት አባል አገር የሆኑ 27 አገራት እሁድ እለት “አስቸኳይ የሰብዓዊ ተኩስ አቋም” አንዲደረግ የጋራ መግለጫ ያወጡ ሲሆን ሐማስ የሕክምና ተቋማትን እና ሰላማዊ ሰዎችን “እንደ ሰብዓዊ መከላከያ” መጠቀሙንም አውግዘዋል።ባለፈው ሳምንት አሜሪካ፣ እስራኤል በየዕለቱ ለአራት ሰዓታት ያህል ወታደራዊ እንቅስቃሴዋን አንድታቋርጥ ጠይቃ ነበር።Article share tools
- የታተመዉ 5:23 13 ህዳር 20235:23 13 ህዳር 2023የተባበሩት መንግሥታት ከ100 በላይ ሰራተኞቹ በጋዛ እንደተገደሉበት አስታወቀ
UNCopyright: UNየተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ከ100 በላይ ሰራተኞቹ በጋዛ እንደተገደሉበት አስታወቀ። ህይወታቸውን የተነጠቁትን ሰራተኞቹን ለማስታወስ እና “ክብሩንም ለመግለጽ” በዛሬው ዕለት ሰንደቅ ዓላማው ዝቅ ብሎ ይውለበለባል ብሏል።እስራኤል በጋዛ ላይ የቦምብ ጥቃት ከጀመረችበት ጊዜ ጀምሮ የተገደሉ ሰራተኞች ከመቶ በላይ መሆኑን የተባበሩት መንግሥታት የፍልስጤም ስደተኞች የእርዳታ ኤጀንሲ አስታውቋል።በየትኛውም ጦርነት የዚህን ያህል ቁጥር ያለው የተቋሙ ሰራተኞች ተገድለው እንደማያውቁም ተገልጿል። የሰራተኞቹ ሞት በተባበሩት መንግሥታት ታሪክ ከፍተኛው ነው ተብሏል።የተገደሉት የተመድ ሰራተኞች በጋዛ ውስጥ ከሚሰሩት 13 ሺህ ሰራተኞች መካከል ሲሆን ብዙዎቹም የተገደሉት ከቤተሰቦቻቸው ጋር መሆኑን ተመድ ገልጿል።ከተገደሉት መካከል መምህራን፣ የጤና ባለሙያዎች፣ የማህጸን ሐኪም፣ መሐንዲሶች፣ የስነ ልቦና ባለሙያ እና የድጋፍ ሰጪ ሰራተኞችም ይገኙበታል።ተቋሙ በጋዛ ሰርጥ ዙሪያ ከ150 በላይ ባሉ ማዕከላቱ ከ780 ሺህ ህዝብ በላይ እያስተናገደ ይገኛል።እነዚህ መጠለያዎችም በጋዛ በሚደረገው ጦርነት ጉዳት ደርሶባቸዋል። እስካሁን ድረስ 60ዎቹ ጥቃት የደረሰባቸው ሲሆን ከነዚህ ውስጥ አስሩ በቀጥታ ጥቃት የተፈጸመባቸው መሆኑንም ተመድ ገልጿል።Article share tools
- የታተመዉ 4:47 13 ህዳር 20234:47 13 ህዳር 2023የእስራኤል መከላከያ በአል ሻቲ የስደተኞች መጠለያ ወረራ መፈጸሙን አስታወቀየእስራኤል ጦር ከጋዛ ከተማ በስተምዕራብ በምትገኘው አልሻቲ የስደተኞች መጠለያ ላይ ድንገተኛ ወረራዎች ማካሄድ መቀጠሉን አስታውቋል።እስራኤል የምታካሂደው ወታደራዊ ዘመቻ አል ቁድስ ዩኒቨርስቲ እና አቡበከር መስጊድን ያጠቃልላል።እነዚህ ስፍራዎች ሐማስ የሚንቀሳቀስባቸው ናቸው በማለት እንደሆነም ተገልጿል። በነዚህ ወረራዎች የተያዙ በርካታ የጦር መሳሪያዎችና ወታደራዊ ቁሶችን ፎቶዎች ለቢቢሲ አጋርቷል።በተጨማሪም ስሙ ያልተገለጸ የእስላሚክ ጂሃድ ታጣቂ አባል መኖሪያ ቤትም በተፈጸመው ድንገተኛ ወረራ የጦር መሳሪያ ተይዟል ተብሏል።እስራኤል የጋዛ ከተማ ከምትገኝበት ሰሜናዊ ጋዛ የሚኖሩ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ፍልስጤማውያን ነዋሪዎች አካባቢያቸውን ለቀው እንዲሸሹ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸዋል። እስራኤል በጋዛ ሰርጥ ላይ ከምትፈጽመው የማያባራ የአየር ጥቃት በተጨማሪ እግረኛ ጦሯን ካስገባች ሳምንት አልፏል።Article share tools
- የታተመዉ 3:36 13 ህዳር 20233:36 13 ህዳር 2023የአል ሺፋ ሆስፒታል ሶስት ነርሶች መገደላቸውን ተመድ አስታወቀ
AFPCopyright: AFPበጋዛ ትልቁ ሆስፒታል አል ሺፋ አቅራቢያ የማያባሩ የአየር ጥቃቶች እና ውጊያዎች ተከትሎ ሶስት ነርሶች መገደላቸውን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስታወቀ።የሆስፒታሉ ወሳኝ የሆኑ መሰረተ ልማቶች መጎዳታቸውን ያስታወቀው ተመድ የኦክስጂን ማመንጫ፣ የውሃ ማጠራቀሚያ እና ጉድጓድ፣ የልብ እና የእናቶች ማቆያ ክፍል ጉዳት ደርሶባቸዋል ብሏል።እስራኤል በጋዛ ትልቁ ሆስፒታል አልሺፋ መሬት ውስጥ ሐማስ እንደ ማዕከል ይጠቀምበታል በማለት የምትከስ ሲሆን ሐማስ ይህንን ውንጀላ አይቀበለውም።የሆስፒታሉ የቀዶ ህክምና ኃላፊ ዶክተር ማርዋን አቡ ሳዳ ሐማስ አል ሺፋን እየተጠቀመበት እንደሆነ ተጠይቀው ውንጀላውም “ፍጹም ሐሰት ነው” ብለዋል።”እኛ ሰላማዊ ሰዎች ነን። እኔ የቀዶ ሐኪም ነኝ። ሐኪሞች የስራ ባልደረቦች አሉን። ታማሚዎች እንዲሁም ተፈናቃዮች የተጠለሉ አሉ። ሌላ ምንም የለም” ሲሉም ተናግረዋል።በቅርብ ቀናት በሰሜን ጋዛ የሚገኘው አል ሺፋ አቅራቢያ ከባድ ውጊያ እየተካሄደ ሲሆን እስራኤል ሆስፒታሉ ላይ ጥቃት ፈጽማለች ተብሏል።የእስራኤል ጦር በሆስፒታሉ አካባቢ እየተንቀሳቀሰ እንደሆነ ቢገልጽም በተቋሙ ላይ ጥቃት መፈጸሙን አስተባብሏል።