November 15, 2023 – Konjit Sitotaw 

አሜሪካ ከመጪው ወር ጀምሮ በመላው ኢትዮጵያ የምግብ እርዳታ ማቅረብ እንደምትጀምር አስታውቃለች።

በኢትዮጵያ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተለይም ከሁለት ሶስት አመታት ወዲህ የሰላም እጦትና የኑሮ ውድነት ፈተና እየሆነ ነው። የኢትዮጵያ ሰሜኑ ክፍል በጦርነት ወድሟል እየወደመም ነው። ስራ አጥነት የሀገሪቱ ራስ ምታት ከሆነ ሰነባብቷል።

በ30 ዓመታት ታይቶ አይታወቅም በተባለ ድርቅና በሰሜኑ ጦርነት ምክንያት በኢትዮጵያ 20 ሚሊዮን የሚሆኑ ሰዎች የምግብ እርዳታ ፈላጊ መሆናቸውም ተረጋግጧል።

ሀገሪቱ ከ850 ሺህ በላይ ስደተኞችን በማስተናገድ ላይ ስትሆን ፥ ከ35 ሺህ በላይ ሱዳናውያን ጦርነትን ሽሽት ወደ ኢትዮጵያ ገብተዋል።

የአለም ምግብ ፕሮግራምና የአሜሪካ ዓለም አቀፍ ልማት ተራድኦ ድርጅት በእርዳታ ስርቆት ምክንያት ድጋፍ አቋርጠው መቆየታቸውም ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱ ተረድተው ሰብዓዊ እርዳታቸውን ሊያቀርቡ መሆኑን ይፋ አድርገዋል።

የአሜሪካ መንግስት ከዚህ ቀደም የሚያደርገውን ድጋፍ ያቆመው መንግስት የእርዳታ እህሉን ለተጎጅዎች ሳያደርስ ለግል ጥቅም አውሎታል ፣ ሰርቆ በልቶታል በሚል እንደነበር የሚታወስ ነው።