November 15, 2023 – Konjit Sitotaw
የኢትዮጵያን አሜሪካን ሲቪክ ካውንስል ከአሜሪካን የውጭ ጉዳይ ምክትል ሃላፊ ሞሊ ፊ ጋር ዛሬ በውቅታዊ ጉዳዮች ውይይት አደረገ።
የፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የአፍሪካ ልዩ መልእክተኛ ከሆኑት አምባሳደር ማይክ ሃመር ሲኔየር ሃላፊ እና የአሜሪካን ስቴት ዲፓርትመንት የዲያስፖራ ሃላፊ እንዲሁም የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ምክትል ሴክሬተሪ ጋር በመሆን ሰፊ ውይይት ማድረጉን የካውንስሉ ህዝብ ግንኙነት ዴሬክተር አቶ አምሳሉ ካሳው አስታውቋል።
የአፍሪካ ልዩ መልእክተኛ የሆኑት አምባሳደር ማይክ ሃመር በአሁኑ ሰኣት የአፍሪካን ጉዳይ ለመከታተል አፍሪቃ እንደሚገኙ ጠቅሰው በተለይም በኢትዮጵያ ያለውን ጉዳይ ቅድሚያ በመስጠት እየሰሩበት እንደሆነ የአሜሪካን የውጭ ጉዳይ ምክትል ሃላፊ ሞሊ ፊ ለካውንስሉ ወኪሎች ገልፀዋል።
ካውንስል አምባሳደር ማይክ ሃመር በፕሪቶርያ ያደረጉትን ጫና በአሁኑ ሰኣት በጠቅላይ ሚንስትሩ ላይ ማድረግ ይኖርባቸዋል ምክንያቱም በአሁኑ ሰኣት በርካታ የአማራ ተወላጆች በማንነታቸው ምክንያት በስርኣቱ ወታደሮችና ኦነግ እየተገደሉ በመሆኑ በአስቸኳይ መፍትሄ ሊበጅለት ይገባል።
ካውንስሉ ባለፈው ሳምንት ይህንኑ ለአፍሪካ ህብረት ተወካይ ያስረዳ ሲሆን አሁንም የፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የአፍሪካ ልዩ መልእክተኛ የሆኑት አምባሳደር ማይክ ሃመር ቀጠናው እጅግ ወደለየለት ሳይሄድ የብልጽግና መንግስትን ተጠያቂ እንዲያደርገው እንፈልጋለን። በርካታ የአማራ ተወላጆች በጦርነቱ ምክንያት በተጣለባቸው ገደብ የምግብ ፣ የመደሃኒት እና የኢንተርኔት አገልግሎት እጦት ላይ ናቸው። ስለሆነም የሰብኣዊ እርዳታ በአስቸኳይ መግባት ይኖርበታል፣ የአለም አቀፍ ማህበረሰብ አጣሪ ኮሚቴ ገብቶ ጉዳዩን መመርመር አለበት እና ይህ ይሆን ዘንድ ጫና ማድረግ ይኖርባችኋል ሲሉ የካውንስሉ ፕሬዚዳንት ዲያቆን ዮሴፍ ተፈሪ እና ኢንጅነር አይንሸት ገላጋይ አስረድተዋል።
ካውንስላችን በዘር ያልተደራጀ በርካታ የተለያዩ ብሄሮችን በአባልነት ያካተተ በአብሮ መኖር እና እኩልነት የሚያምን እና በአንድነት ላይ ጠንካራ አቋም ያለው እና አድቮኬት የሚያደርግ በመሆኑ ይህንን አብሮ የመኖር ዘይቤን ወደ አንድነት ለማምጣት ዴሞክራሲና ፍትህ እኩልነት በኢትዮጵያ ብሎም በአፍሪቃ ቀንድ ይመጣ ዘንድ ሴክሬተር ኦፍ ስቴት እና ሴቴት ዲፖርትመንት በቅርበት ከእኛ ጋር መስራት አለበት ሲሉ ዲያቆን ዮሴፍ ተፈሪ ገልፀውላቸዋል።
አምባሳደር ሞሊ ፊ ያደርጉትን መልካም ውይይት አድንቀው በቀጣይ ከካውስንሉ መፍትሄ ሊበጅለት ይገባል በሚላቸው ዙሪያ ሰፊ ውይይት እና ቀጣይነት እንዲኖረው ለማድረግ ስምምነት ላይ ደርሰዋል።