November 15, 2023 

ኢሳይያስ አፈወርቂ ሰሞኑን በሳውዲ አረቢያ በነበራቸው ቆይታ ከአንድ የአረቢኛ ጊዜጣ ጋር ቃለምልልስ አድርገዋል።

በዚህ ቃለምልልሳቸው የተለያዩ ጉዳዮችን ያነሱ ሲሆን ስለቀይባህር ጉዳይ የሚከተለውን ብለዋል።
ቀይባህርን የምንጋራ ሀገራት በጋራ መቆም አለብን ሲሉ ነው የመለሱት።

የቀይባህር ዳርቻ ሀገራትን ሉዓላዊነት ለማስከበር እና የቀይባህርን ደህንነት ለማስጠበቅ በጋራ መቆም አለብን ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል።ይህ ከሆነ ከሌሎች ጣልቃ ገቦች ለመጠበቅ ያስችለናል ሲሉ ተደምጠዋል።

ለሌሎች ሀገራትን ተጠቃሚነት በተመለከተ ለተነሳላቸው ጥያቄ የቀይባህር ወደብን ለመጠቀም የሚፈልጉ ሌሎች ሀገራት በውይይት እና በምክክር ብቻ ሊሆን እንደሚችል ጠቅሰው ይህን ከማለም በፊት ግን በቀጠናው ያሉብንን የፀጥታ መደፍረስ፣ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን መፍታት ይኖርብናል ብለዋል።