ጭምቅ ሃሳብ

  1. ደቡብ አፍሪካ በጋዛ ጥቃት እስራኤልን ወደ ዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት ወሰደች
  2. የእስራኤል ጦር ከአል-ሺፋ ሆስፒታል የተገኘ ነው ያለውን ወታደራዊ ቁስ አሳየ
  3. ኔታኒያሁ ስልጣን እንዲለቁ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪ ጠየቁ
  4. አል ሺፋ ሆስፒታል በታንክ ተከቧል
  5. ባይደን አል-ሺፋ ሆስፒታል ጥበቃ ሊደረግለት ይገባል አሉ
  6. የጋዛ ጉዳይ ወታደራዊ መፍትሄ የለውም- የዮርዳኖስ ንጉስ አብዱላህ
  7. በእስራኤል ጥቃት የተገደሉ ፍልስጤማውያን ቁጥር 11 ሺህ 240 ደረሰ- የጋዛ ጤና ሚኒስቴር
  8. እስራኤል በጋዛ ትልቁ ሆስፒታል ላይ ጥቃት ፈጽማለች መባሏን አስተባበለች
  9. አሜሪካ በሶሪያ በሚገኙ የኢራን ጦር ሰፈሮች ላይ ጥቃቶች ፈጸመች

ቀጥታ ዘገባ

  1. የታተመዉ 11:0211:02በጋዛ የቴሌኮም ግንኙነት አማራጮች በሙሉ ተቋረጡNetBlocksNetBlocksCopyright: NetBlocksበጋዛ የሞባይል ስልክ፣ የሞባይል ዳታ ኢንተርኔት፣ ዋይፋይ እንዲሁም መደበኛ የስልክ መስመሮች መቋረጣቸው ተገለጸ።የፍልስጤም ኮሚኒኬሽን ኩባንያ የሆነው ጃዋል በጋዛ ሁሉም የቴሌኮም አማራጮች መቋረጣቸውን አስታውቋል።“በጋዛ የቴሌኮም አግልግሎቶችን የሚያንቀሳቀሱ የኃይል ምንጮች ተሟጠው በማለቃቸው ሁሉም የቴሌኮም አማራጮች ተቋረጠዋል” ብሏል ኩባንያው።በመላው ዓለም የኔትዎርክ ግንኙነትን የሚከታተለው ኔትብሎክስ የተሰኘው ድርጅትም ይህንኑ ያረጋገጠ ሲሆን ጋዛ የጠቅላላ የኢንተርኔት መቋረጥ ውስጥ ትገኛለች ብሏል።Article share tools
  2. የታተመዉ 10:5210:52የእስራኤል ጦር አል-ሺፋ ሆስፒታልን ፈትሾ ለመጨረስ ሳምንታት ሊወስድብኝ ይችላል አለከሆስፒታሉ ተገኘ የተባለ የሐማስ ወታደራዊ ርዕዮተ ዓለምBBCCopyright: BBCከሆስፒታሉ ተገኘ የተባለ የሐማስ ወታደራዊ ርዕዮተ ዓለምImage caption: ከሆስፒታሉ ተገኘ የተባለ የሐማስ ወታደራዊ ርዕዮተ ዓለምየእስራኤል ጦር በጋዛ ትልቁ የሆነውን ሆስፒታል ፈትሾ ለመጨረስ ጥቂት ሳምንታት ሊወስዱበት እንደሚችል አስታወቀ።የጦሩ ቃል አቀባይ ሌተናል ኮሌኔል ጆናታን ኮንሪከስ ለቢቢሲ ሲናገሩ ሐማስ ከሆስፒታሉ ስር የሰራውን ግንባታ ስፋት መጠን ለማሳየት ጥቂት ሳምንታት ሊወስድብን ይችላል ብለዋል።እስራኤል እና አሜሪካ ሐማስ ከሆስፒታሉ ስር ወታደራዊ ማዘዣ ጣቢያ እና ዋሻ ግንብቷል ይላሉ።ሐማስ እና የጤና ተቋሙ ግን ይህን ሲያስተባብሉ ቆይተዋል።የእስራኤል ጦር ባለፉት ሁለት ቀናት ሆስፒታሉን ተቆጣጥሮ ብርበራዎችን እያደረገ ሲሆን እስካሁን ድረስ ጥቂት ክላሺንኮቭ መሳሪያዎችን እና ወታደራዊ የደንብ ልብሶችን አግኝቻላሁ ከማለቱ ወጪ የተገነባ ዋሻ አላሳየም።“ሁሉንም የሆስፒታለ ክፍል ፈትሸን አልጨረስንም- ገና አልተጀመረም ማለት ይቀላል” ብለዋል ቃል አቀባዩ ኮንሪከስ።Article share tools
  3. የታተመዉ 9:229:22ጀርመን ለሄዝቦላ ድጋፍ በመስጠት በጠረጠረችው ማዕከል ላይ ድንገተኛ ፍተሻ አደረገችየጀርመን ፖሊስReutersCopyright: Reutersየጀርመን ፖሊስ በሰባት ግዛቶች ውስጥ ለሄዝቦላ ድጋፍ ያደርጋል ብሎ በጠረጠረው እስላማዊ ማዕከል ላይ ድንገተኛ ፍተሻ አደረገ።የጀርመን የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚንስቴር እንዳለው የሃምቡርግ እስላማዊ ማዕከል ለታጣቂው ቡድን ሄዝቦላ ድጋፍ ያደርጋል በሚል ፍተሻ ተደርጎበታል።ፖሊስ ከ300 ያላሱ አባላቱን አሰማርቶ ከማዕከሉ ጋር ግንኙነት አላቻው በተባሉ 50 ቦታዎች ብርበራ ማድረጉ ተሰምቷል።የባለስልጣናት ትኩረት ተቋሙ ለሄዝቦላ ድጋፍ እንደሚሰጠ የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማግኘት ስለነበረ ብርበራውን ተከትሎ በቁጥጥር ስር የዋለ የለም ሲል ሮይተርስ የዜና ወኪል ዘግቧል።በጀርመን ከእአአ 2020 ጀምሮ የሄዝቦላ ንብረቶች ተወርሰው እንቅስቃሴዎቹ በሙሉ ታግደዋል።Article share tools
  4. የታተመዉ 7:087:08ኔታኒያሁ ስልጣን እንዲለቁ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪ ጠየቁየተቃዋሚ ፓርቲ መሪው ላፒድReutersCopyright: Reutersየተቃዋሚ ፓርቲ መሪው ላፒድImage caption: የተቃዋሚ ፓርቲ መሪው ላፒድየተቃዋሚ ፓርቲ መሪው ያይራ ላፒድ ጠቅላይ ሚንስትር ቤኒያሚን ኔታኒያሁ ስልጣን መልቀቅ አለባቸው አሉ።ላፒድ የእስራኤል መንግሥት ከሐማስ ጋር የተገባውን ግጭት በአግባቡ መያዝ ባለመቻሉ ኔታኒያሁ በአስቸኳይ ስልጣን መልቀቅ አለባቸው ብለዋል።ቻናል 12 ለተባለ ቴሌቪዥን ጣቢያ ሲናገሩ፤ “ኔታኒያሁ አሁን መሰናበት አለባቸው። መንግሥት ኃላፊነቱን መወጣት አልቻለም። . . . ሕዝብ አመኔታ ባጣበት መሪ ልንመራ አንችልም” ብለዋል።ከዚህ ቀደም የውጭ ጉዳይ ሚንስትር እና ተጠባባቂ ጠቅላይ ሚንስርት የነበሩት ላፒድ ፓርቲያቸው ዬሽ አቲድ ከገዢው ሊኩድ ፓርቲ ጋር በመጣመር ግዚያዊ መንግሥት ለማቋቋም ዝግጁ መሆኑን ተናግረው ኔታኒያሁ ግን መሪ ሆነው መቀጠል አይችሉም ብለዋል።Article share tools
  5. የታተመዉ 6:556:55የእስራኤል ጦር ከአል-ሺፋ ሆስፒታል የተገኘ ነው ያለውን ወታደራዊ ቁስ አሳየክላሽንኮቭBBCCopyright: BBCየእስራኤል ጦር ለሁለት ቀናት ተቆጣጥሮ በያዘው የጋዛ ትልቁ ሆስፒታል የተገኙ ናቸው ያላቸውን ወታደራዊ ቁሳቁሶች አሳየ።ጦሩ ሐማስ ከአል-ሺፋ ሆስፒታል ስር የጦር ማዘዣ እና ወታደራዊ መሳሪያዎችን የሚያከማችበት ዋሻ ገንብቷል ሲል ቆይቷል።ባለፉት ሁለት ቀናትም የእስራኤል ጦር በአስተርጓሚዎች ታጅቦ እያንዳንዱን የሆስፒታል ክፍሎች እየበረበረ፤ ሐኪሞችን እና ታካሚዎችን ጥያቄ ሲጠይቅ ቆይቷል።የእስራኤል ጦር የቢቢሲን ጋዜጠኛ ይዞ ወደ ሆስፒታሉ የገባ ሲሆን የሐማስ የሆኑ እና ከሆስፒታሉ የተገኙ ናቸው የተባሉ ጦር መሳሪያዎችን አሳይቷል።ክላሽንኮቭ መሳሪያ ከኤምአርአይ ማሽን ጀርባ ተደብቆ መገኘቱን እንዲሁም የሐማስን ወታደራዊ የደንብ ልብሶች እና ወታደራዊ ርዮአተ ዓለም የሚገልጹ ጽሑፎች መገኘቱን የጦር አባላቱ ገልጸዋል።Article share tools
  6. የታተመዉ 6:436:43ደቡብ አፍሪካ በጋዛ ጥቃት እስራኤልን ወደ ዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት ወሰደችራማፎሳReutersCopyright: Reutersደቡብ አፍሪካ እስራኤል በጋዛ እየወሰደች ባለችው እርምጃ አገሪቱን ወደ ዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት (አይሲሲ) ወሰደች።ፕሬዝዳንት ራማፎሳ የእስራኤል መንግሥት በጋዛ እየፈጸመ ያለው ተግባር በዓለም አቀፉ የወንጀለ ፍርድ ቤት መዳኘት እንዳለበት ከሌሎች በርካታ አገራት ጋር ተግባብተናል በለዋል።ራማፎሳ የእስራኤል እርምጃ በፍርድ ቤቱ መታየት አለበት ያሉት ቀሪ አገራት የትኞቹ እንደሆኑ ያሉት ነገር ባይኖርም፤ በጋዛ “የጦር ወንጀለኞች እየተፈጸሙ እንደሆነ እናምናል” ብለዋል።በእስራኤል-ጋዛ ጦርነት እስራኤልን አጥብቆ በመተቸት እና ለፍልስጤማውያን ግልጽ ድጋፍ እየሰጡ ካሉ ጥቂት አገራት መካከል ደቡብ አፍሪካ አንዷ ነች።ሐማስ በእስራኤል ላይ ያደረሰውን ጥቃት ያለወገዙት ራማፎሳ፤ እስራኤል በጋዛ እያደረገች ያለችው ወታደራዊ ዘመቻ በዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት እንድትታይ ያደርጋታል ብለዋል።አይሲሲ ዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት ሲሆን እንደ ጦር ወንጀል እና ዘር ማጥፋት ባሉ ክሶች የተከሰሱ ግለቦችን ይዳኛል።Article share tools
  7. የታተመዉ 3:203:20ባይደን የጋዛ ታጋቾች እንደሚለቀቁ ተስፋ እንዳላቸው ተናገሩየአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደንReutersCopyright: Reutersየአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ወደ ጋዛ የተወሰዱ ታጋቾችን ለማስለቀቅ ስምምነት ላይ እንደሚደረስ “ተስፋ አለኝ” አሉ።ቀደም ሲል በካሊፎርኒያ በነበራቸው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ሁኔታው ሳይበስል ያለጊዜው መናገር እንደማይፈልጉ ገልጸው ነገር ግን አገራቸው በእስራኤል እና በሐማስ መካከል የተጀመረውን ድርድር ስትመራ ከነበረችው ኳታር “ታላቅ ትብብር” አይታለች ብለዋል።እስራኤል በጋዛ ትልቁ ሆስፒታል አልሺፋ ያደረገችውንም ወታደራዊ ዘመቻ ደግፈው የተናገሩት ፕሬዚዳንቱ ሐማስ ስፍራውን ለወታደራዊ ዓላማ በመጠቀም “የጦር ወንጀል” ፈጽሟል ብለዋል።እስራኤል ከሆስፒታሉ ውስጥ ተገኙ ያለቻቸውን የሐማስ የጦር መሳሪያ እና ወታደራዊ ቁሶች ምስሎች እና ቪዲዮዎች አሳይታለች።ሐማስ የህክምና ተቋማትን በሽፋንነት እንደማይጠቀም ተናግሯል። ፕሬዚዳንቱ እስራኤል የሐማስ ምሽጎችን ለመፈለግ በምትታደርገው ጥረት ሰላማዊ ሰዎች ጥንቃቄ እንዲደረግም አሳስበዋል።Article share tools
  8. የታተመዉ 3:023:02እስራኤል በኳታር ተቀማጭነታቸውን ያደረጉትን የሐማስ መሪ የጋዛ ቤታቸውን እንደመታች አስታወቀችየሐማስ ከፍተኛ አመራር እስማኤል ሐኒዬህReutersCopyright: Reutersየእስራኤል ጦር በኳታር ተቀማጭነታቸውን ያደረጉትን የሐማስ ከፍተኛ አመራር እስማኤል ሐኒዬህ የጋዛ መኖሪያ ቤታቸውን እንደመታ አስታወቀ።የሐማስ የፖለቲካ ቢሮ ኃላፊን መኖሪያ ቤት ለምምታት ተዋጊ ጄቶች መጠቀማቸውንም የእስራኤል መከላከያ ኃይል በኤክስ ገጹ አስፍሯል።የእስራኤል ጦር የአመራሩ መኖሪያ ቤት “ለሽብር መሰረተ ልማትነት ” እንዲሁ “ለድርጅቱ ከፍተኛ ባለስልጣናት መሰብሰቢያ ቦታ ነበር” ብሏል። ቢቢሲ የእስራኤል ጦር ያቀረባቸውን ክሶች በገለልተኛነት ማረጋገጥ አልቻለም።እስማኤል ሐኒዬህ ማን ናቸው?ሃኒዬህ በአውሮፓውያኑ 2017 የሐማስ የፖለቲካ ቢሮ ኃላፊ ሆነው ቢመረጡም ኑሯቸውን በኳታር ካደረጉ ዓመታት አስቆጠሩ።በአውሮፓውያኑ 1980ዎቹ ከሐማስ ስመ ጥር አመራሮች አንዱ የነበሩ ሲሆን እስራኤልም ለሶስት ዓመታት አስራቸዋለች። ከእስር ተፈትተው ለግዞት የታደረጉ ሲሆን ከዚያም ወደ ጋዛ ተመልሰዋል።በአውሮፓውያኑ 1997 የሐማስ መንፈሳዊ ጽህፈት ሐላፊ ሆነው ተሾሙ። ሃኒዬህ በአውሮፓውያኑ 2006 የፍልስጤም ጠቅላይ ሚነስትር ሆነው በፕሬዚዳንት ማህሙድ አባስ ሆነው ቢሾሙም ነገር ግን ከአንድ ዓመት በኋላ ከስልጣን ተባረዋል።ሐማስ የፕሬዚዳንት አባስ ፓርቲ የሆነውን ፋታህን ከጋዛ ሰርጥ እንዲወጣ ካደረገ በኋላም ነው ከኃላፊነታቸው የተነሱት።ሃኒዬህ ከስልጣን የተባረሩበትን መንገድ ህገ መንግሥታዊ አይደለም በማለት ውድቅ ያደረጉ ሲሆን መንግሥታቸው “ለፍልስጤም ህዝብ ያለውን አገራዊ ኃላፊነት አይተውም”Article share tools
  9. የታተመዉ 2:132:13በእስራኤል-ጋዛ የተከሰቱ የቅርብ ጉዳዮችየጋዛ ጥቃትGetty ImagesCopyright: Getty Images
    • የእስራኤል ጦር በሰሜናዊ ጋዛ በሚገኘው አልሺፋ ሆስፒታል በታንክ ታግዞ ወታደራዊ ዘመቻ ማካሄዱን አስታውቋል። ሐማስ ሆስፒታሉን ለወታደራዊ ትዕዛዝ ማዕከልነት እየተጠቀመበት ነው ስትል እስራኤል ትከሳለች። ሐማስም ሆነ የሆስፒታሉ ሐላፊዎች ይህንን ፍጹም ሐሰት ነው ሲሉ ውድቅ አድርገውታል።
    • በሆስፒታሉ ውስጥ የሚገኝ ጋዜጠኛ ለቢቢሲ እንደተናገረው የእስራኤል ወታደሮች ሆስፒታሉን ለቀው መውጣታቸውን የጠቀሰ ሲሆን ነገር ግን ቢቢሲ ይህንን በገለልተኛነት ማረጋገጥ አልቻለም።
    • የእስራኤል መከላከያ ሰራዊት ወታደሮች ወደ ሆስፒታሉ ዋና ድንገተኛ ክፍል ገብተው ታካሚዎችን መመርመራቸውም ይኸው ጋዜጠኛ ተናግሯል።
    • ጦሩ በአል ሺፋ ውስጥ የሐማስ ያላቸውን የጦር መሳሪያዎች እና ወታደራዊ ቁሶች የሚያሳዩ ምስሎችን እና ቪዲዮዎችንም አውጥቷል።
    • በደቡባዊ ጋዛ በምትገኘው ኻን ዩኒስ ከባድ ዝናብ እየዘነበ ሲሆን ጦርነቱ ከተጀመረ በኋላም ለመጀመሪያ ጊዜ 25 ሺህ ሊትር ነዳጅ በግብጽ በኩል ባለችው የድንበር ማቋረጫ ራፋህ በኩል ገብቷል።
    • የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት የጋዛው ጦርነት ‘የተራዘመ ሰብዓዊ ፋታ’ እንዲሰጠው ውሳኔ አሳልፏል። ተመድ በአስቸኳይ ተግባራዊ እንዲሆን ያሳለፈው ውሳኔ በሙሉ ከበባ ውስጥ ባለችው ጋዛ እርዳታ እንዲገባ ለማድረግ ‘ለበቂ ቀናት’ የሚቆይ እንደሆነም ተገልጿል።
    • በዩናይትድ ኪንግደም በጋዛ የተኩስ አቁም ጥሪን በመቃወም የተወካዮች ምክር ቤት ድምጽ ሰጥተዋል። ጥሪው በ293 ተቃውሞ እና በ125 ድጋፍ ውድቅ ተደርጓል። የሌበር ፓርቲ መሪ ሰር ኬይር ስታርመን የፓርላማ አባላት ድምጸ ተዓቅቦ እንዲያካሂዱ ጥሪ ማድረጋቸውን ተከትሎ ከፍተኛ ተቃውሞ ገጥሟቸዋል።
    Article share tools
  10. የታተመዉ 0:220:22ከእስራኤል ወረራ በኋላ የአልሺፋ ሆስፒታል ከፍተኛ ውድመት ደርሶበታል- የሆስፒታሉ ኃላፊየአልሺፋ ሆስፒታልIDFCopyright: IDFየእስራኤል ጦር በታንክ ታግዞ የወረረው የጋዛው ትልቁ ሆስፒታል የከፋ ውድመት እንደደረሰበት የሆስፒታሉ የቀዶ ጥገና ኃላፊ ዶ/ር ማርዋን አቡ ሳዳ ተናገሩ።በተለይም የራዲዮሎጂ (የራጅ) ክፍሉ የከፋ እንደሆነም ነው የገለጹት። ‘የእስራኤል ጦር በልዩ የቀዶ ህክምና ውስጥ የሚገኘው የራጅ ክፍሉ ላይ ወረራ ፈጽሟል” ሲሉም ለቢቢሲ በላኩት መልዕክት ልከዋል።”ወንዶቹን እጃቸውን አስረው በአንድ ክፍል ለዩዋቸዋው። በሲቲ ስካነር፣ በኤምአርአይ ማሺን እና በበርካታ የአልትራ ሳውንድ የህክምና መሳሪያዎች እና እቃዎች ላይ የከፋ ውድመት አድርሰዋል” ብለዋል።”የጥገና ቡድን አባላት የሆኑ ሁለት ሰዎችም በቁጥጥር ስር መዋላቸውንም” አክለው ገልጸዋል።Article share tools
  11. የታተመዉ 0:100:10ተመድ የጋዛው ጦርነት ‘ሰብዓዊ ፋታ’ እንዲሰጠው ውሳኔ አሳለፈየአልሺፋ ሆስፒታልGetty ImagesCopyright: Getty Imagesየተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት የጋዛው ጦርነት ‘የተራዘመ ሰብዓዊ ፋታ’ እንዲሰጠው ውሳኔ አሳለፈ።ተመድ በአስቸኳይ ተግባራዊ እንዲሆን ያሳለፈው ውሳኔ በሙሉ ከበባ ውስጥ ባለችው ጋዛ እርዳታ እንዲገባ ለማድረግ ‘ለበቂ ቀናት’ የሚቆይ እንደሆነም ተገልጿል።በማልታ የቀረበውን የውሳኔ ሐሳብም 12 አገራት ሲደግፉት የምከር ቤቱ ሶስቱ ቋሚ አባላት አሜሪካ፣ ዩናይትድ ኪንግደም እና ሩሲያ ድምጸ ተአቅቦ አድርገዋል።ውሳኔው በሐማስ እና በሌሎች ቡድኖች የተወሰዱ ታጋቾች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በአስቸኳይ እንዲለቀቁም ጠይቋል።በተጨማሪም ሁሉም አካላት በአለም አቀፍ ህግ የተጣለባቸውን ግዴታዎች እንዲወጡ የሚጠይቅ ሲሆን የተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸሐፊ ሁኔታውን እየተከታተሉ አፈጻጸሙን ሪፖርት እንዲያደርጉም ወስኗል።የጸጥታው ምክር ቤት ከዚህ ቀደም በጋዛ የተኩስ አቁም ወይም የሰብዓዊነት ፋታ እንዲሰጥ የሚጠይቁ ውሳኔዎችን ለአራት ጊዜ ያህል ማሳለፍ ተስኖት ነበር።Article share tools
  12. የታተመዉ 9:50 15 ህዳር 20239:50 15 ህዳር 2023ኳታር ለሦስት ቀናት የተኩስ አቁም እንዲደረግ እያደራደረች ነው ተባለእስራኤል ለሦስት ቀናት ያክል በጋዛ የተኩስ አቁም አድርጋ በምላሹ 50 ታጋቾች እንዲላቀቁላት ኳታር እያደራደረች ነው ተባለ።በውይይት ላይ የሚገኘውን ስምምነት የአሜሪካ መንግሥት እያስተባበረው ሲሆን የእስራኤል ጦር ለሦስት ቀናት በጋዛ የሚያደርገውን ወታደራዊ ዘመቻ ካቆመ መስከረም 26 በሐማስ ከታገቱት መካከል 50 የሚሆኑት ይለቀቃሉ ተብሏል።ስምምነቱ ተፈጻሚ ከሆነ እስራኤል ተጨማሪ የሰብዓዊ እርዳታ ወደ ጋዛ እንዲገባ የምትፈቅድ ሲሆን በእስራኤል እስር ቤቶች ተይዘው የሚገኙ ሴቶች እና ሕጻናትም ነጻ ይወጣሉ።ሮይተርስ የዜና ወኪል ለድርድሩ ቅርበት ያላቸውን ምንጮች ጠቅሶ እንደዘገበው ሐማስ በድርድሩ የተስማማ ሲሆን እስራኤል ግን ገና እንዳልተስማማች እና በዝርዝር ጉዳዮች ላይ እየተደራደረች ነው።Article share tools
  13. የታተመዉ 9:01 15 ህዳር 20239:01 15 ህዳር 2023የስፔን ጠቅላይ ሚንስትር እስራኤል “የዘፈቀደ ግድያን” ታቁም አሉየስፔን ጠቅላይ ሚንስትር ፔድሮ ሳንቼዝAFPCopyright: AFPየስፔን ጠቅላይ ሚንስትር ፔድሮ ሳንቼዝImage caption: የስፔን ጠቅላይ ሚንስትር ፔድሮ ሳንቼዝየስፔን ጠቅላይ ሚንስትር ፔድሮ ሳንቼዝ እስራኤል በጋዛ እየፈጸመች ያለችውን የዘፈቀደ ግድያ ማቆም አለባት አሉ።ጠቅላይ ሚንስትሩ እስራኤል ዓለም አቀፍ “የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን በመጣስ ፍልስጤማውያንን በጋዘ በዘፈቀደ እየገደለች ነው” ስለማለታቸው የፈረንሳይ የዜና ወኪል ዘግቧል።ጠቅላይ ሚንስትሩ በጋዛ አስቸኳይ የተኩስ አቁም እንዲደረግ እና ዓለም አቀፍ ሕግጋቶች እንዲከበሩ ጠይቀዋል።ጠቅላይ ሚንስትር ፔድሮ ሳንቼዝ እስራኤል እራሷን የመከላከል መብት እንዳላት እናምናል፤ ሐማስም አግቶ የያዛቸውን በአስቸኳይ መልቀቅ አለበት የሉ ሲሆን የዘፈቀ ግድያዎችን ግን መንግሥታቸው እንደሚቃወም አስታውቀዋል።ከጠቅላይ ሚንስትሩ ንግግር በኋላ የስፔን የማኅበራዊ መብቶች ሚንስትሯ አዮን ቤላራ አገራቸው ስፔን ከእስራኤል ጋር ያላትን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እንድታቋርጥ እና እስራኤል ላይ ምጣኔ ሃብታዊ ማዕቀብ እንድትጥል ጥሪ አስተላልፈዋል።Article share tools
  14. የታተመዉ 8:40 15 ህዳር 20238:40 15 ህዳር 2023የእስራኤል ወታደሮች በሺፋ ሆስፒታል ብርበራ እያደረጉ መሆኑ ተገለጸየእስራኤል ጦርReutersCopyright: Reutersየእስራኤል መከላከያ ኃይል በጋዛ እያደረገ ያለውን ዘመቻ በተመለተ በሰጠው መግለጫ በጋዛ ትልቁ ሆስፒታል ፍተሻ እያደረገ መሆኑን አስታውቋል።ጦሩ በአስተርጓሚዎች ታጅቦ እያንዳንዱን የሆስፒታል ክፍሎች እየበረበረ፤ ሐኪሞችን እና ታካሚዎችን ጥያቄ እየጠየቀ እንደሆነ የቢቢሲ ጋዜጠኛ በስፍራው ከሚገኙ ምንጮች ሰምቷል።ጦሩም ባወጣው መግለጫ በሺፋ ሆስፒታል ውስጥ ሐማስን ዒላማ ያደረገ ዘመቻ እየተካሄደ ነው ብሏል። ጦሩ ጨምሮ እንደገለጸው ወደ ሆስፒታሉ ሲገባ የሕጻናት ምግብ እና የሕጻናት ማሞቂያ ማሽኖችን ይዞ ነው።እስራኤል እና አሜሪካ ታጣቂ ቡድኑ የጦር ማዘዣ ጣቢያ እና መጋዘን ከሆስፒታሉ ስር ገንብቶ ይገኛል የሚሉ ሲሆን ሐማስ እና የጤና ተቋሙ ግን ይህ ሐሰት ነው ይላሉ።Article share tools
  15. የታተመዉ 5:03 15 ህዳር 20235:03 15 ህዳር 2023‘ሆስፒታሎች የጦር ሜዳዎች አይደሉም’ የመንግሥታቱ ድርጅት ከፍተኛ ባለሥልጣንማርቲን ግሪፊትስReutersCopyright: Reutersማርቲን ግሪፊትስImage caption: ማርቲን ግሪፊትስየእስራኤል ወታደሮች ጋዛ ውስጥ ወደሚገኘው ትልቁ ሆስፒታል አል-ሺፋ መግባታቸውን ተከትሎ የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ ጉዳዮች ኃላፊ ማርቲን ግሪፊትስ ተቃውሟቸውን አሰሙ።“በጋዛው አል-ሺፋ ሆስፒታል ውስጥ የተካሄደውን ወታደራዊ ወረራን በተመለከተ እየወጡ ባሉት ዘገባዎች አዝኛለሁ” ሲሉ ግሪፊትስ በኤክስ (የቀድሞው ትዊተር) ገጻቸው ላይ ጽፈዋል።ጨምረውም “የጨቅላ ሕጻናትን፣ የህሙማንን፣ የሕክምና ባለሙያዎችን እንዲሁም የሲቪሎችን ደኅንነት መጠበቅ ከምንም በላይ አሳሳቢ ጉዳይ ነው። ሆስፒታሎች የጦር ሜዳዎች አይደሉም” ብለዋል።ቀደም ሲል እንደተዘገበው የእስራኤል ጦር ኃይል አባላት ወደ ሆስፒታሉ የገቡ ሲሆን፣ በሆስፒታሉ ውስጥ ላገኗቸው ሰዎች ጥያቄ እያቀረቡ ምርመራ እያካሄዱ ነው። በተጨማሪም በሆስፒታሉ ውስጥ ያሉ ወንዶችን በአንድ ቦታ ላይ እያሰባሰቧቸው መሆኑ ተነግሯል።የእስራኤል ጦር ሠራዊት ሐማስ ከሆስፒታሉ ስር የዕዝ ማዕከል እንዳለው በመግለጽ ቢከስም ሐማስ ግን ይህንን ያስተባብላል።ሠራዊቱ እንደሚለው በአሁኑ ወቅት በአል-ሺፋ ሆስፒታሉ ውስጥ “የተመረጡ ዘመቻዎችን” እያከሄደ ነው።Article share tools
  16. የታተመዉ 3:26 15 ህዳር 20233:26 15 ህዳር 2023እስራኤል የተወሰኑ የተባበሩት መንግሥታት መኪኖች ዛሬ ነዳጅ እንደሚሞሉ ገለፀችየእስራኤል ወታደራዊ ኃይል ወደ ጋዛ እርዳታ የሚያጓጉዙ የተወሰኑ የተባበሩት መንግሥታት ከባድ መኪኖች ዛሬ ነዳጅ እንደሚሞላላቸው ገለፀ።በግዛቲቱ የመንግሥታቱን እንቅስቃሴ የሚያስተባብሩት እና በፍልስጤማውያን ሲቪል ጉዳዮችን የሚከታተለው የእስራኤል ሚኒስትር መሥሪኣ ቤት፣ መኪኖቹ ነዳጅ የሚሞላላቸው በአሜሪካ መንግሥት ጥያቄ መሰረት መሆኑን ገልጾ በግብጻውያን ድንበር ራፋ አካባቢ ነዳጅ እንደሚሞሉ ተናግሯል።ሚኒስትር መሥርያ ቤቱ አክሎም “ከአስፈላጊ የደህንነት ተቋማት ጋር በጥምረት በመሆን” እንደሚሰራ ተናግሯል።ማክሰኞ ማለዳ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት መኪኖቹ በነዳጅ እጥረት ምክንያት እርዳታ ማመላለስ አለመቻላቸውን ገልጾ ነበር።ጁሊዬቴ ቶኡማ፣ በተባበሩት መንግሥታት በፍልስጤም ስደተኞች ቃል አቀባይ ለቢቢሲ እንደተናገሩት ነዳጅ ገና ሊቀበሉ መሆኑን ገልጸው “እንቅስቃሴያችንን በከፍተኛ ሁኔታ ልንቀንስ የምንችልበት ጫፍ ላይ ደርሰናል” ሲሉ ተናግረዋል።እስራኤል በሐማስ ሊሰረቅ ይችላል በሚል ምክንያት ወደጋዛ የሚገባ ነዳጅን ካገደች ሳምንታት ያለፉ ሲሆን፣ ሆስፒታሎች፣ ዳቦ መጋገርያዎች፣ ለኤሌትሪክ ጄነረተሮች እና ውሃ ፓምፖች ስራቸውን ማከናወን መቸገራቸው ሲነገር ቆይቷል።የእርዳታ ቁሳቁስ የጫኑ ከባድ መኪኖች በራፋ ድንብ ላይ ረዥም ሰልፍ ይዘው ይታያሉReutersCopyright: ReutersArticle share tools
  17. የታተመዉ 2:53 15 ህዳር 20232:53 15 ህዳር 2023‘ሕይወቷ በማስታገሻ መድኃኒት ላይ ተንጠልጥሏል’- የጋዛ ህጻናት አሰቃቂ ታሪክበጋዛ ጦርነት ከተቀሰቀሰ ጊዜ ጀምሮ ከ26 ሺህ በላይ ሰዎች ቀላል እና ከባድ ጉዳት አስተናግደዋል።ከእነዚህ መካከል አብዛኞቹ ሕይወታቸውን ሊያሳጣ የሚችል ጉዳት የደረሰባቸው ናቸው።ተጨማሪ ያንብቡArticle share tools
  18. የታተመዉ 2:53 15 ህዳር 20232:53 15 ህዳር 2023ሐማስ በአል-ሺፋ ሆስፒታል ላይ ‘የተፈጸመው ወረራ በሰብዓዊነት ላይ የተፈፀመ ወንጀል ነው’ አለአል-ሻፊ ሆስፒታልGetty ImagesCopyright: Getty Imagesየሐማስ መንግሥት መገናኛ ብዙኀን እስራኤል በጋዛ በሚገኘው አል-ሻፊ ሆስፒታል የፈጸመችው “የጦር ወንጀል” ነው ሲል በመግለጫው ላይ ኮንኖታል።መግለጫው አክሎም የእስራኤልን ወረራ “ከግብረ ገብ ያፈነገጠ” እንዲሁም “በሰብዓዊነት ላይ የተፈጸመ ወንጀል” ሲል ጠርቶታል።ሐማስ በሆስፒታሉ ወረራ በተፈጸመ ወቅት 9000 ሕሙማን፣ የሕክምና ባለሙያዎች እንዲሁም የተፈናቀሉ ሰላማዊ ዜጎች እንደሚገኙ አስታውቋል።በቀድሞው ትዊተር፣ ኤክስ፣ማህበራዊ ሚዲያ ላይ የፍልስ=ጤማውያን መረጃ ማዕከል መሪ ኢዛት አል-ሪሺቅ፣ እስራኤል ወታደራዊ ማዕከል ሳይሆን የሰለማዊ ዜጎች ተቋምን ነው ያጠቃችው ሲሉ ተናግረዋል።ሐማስ ከዚህ ቀደም ብሎ ዋሺንግተንን እና ፕሬዝዳንት ጆ ባይደንን ለተፈጸመው ወረራ ተጠያቂ አድርጓል።እስራኤል እና አሜሪካ ከአል-ሻፊ ሆስፒታል ስር የሐማስ ማዘዣ ጣብያ እንደሚገኝ ይገልጻሉ።Article share tools
  19. የታተመዉ 2:41 15 ህዳር 20232:41 15 ህዳር 2023አሜሪካ ሐማስ በአል-ሺፋ ሆስፒታል ስር ማዘዣ ጣብያ አለው ስትል ገለጸችአሜሪካ ሐማስ በጋዛ ከተማ በሚገኘው እና ትልቅ በሆነው አል-ሺፋ ሆስፒታል ስር የማዘዣ ማዕከል እንዳለው የሚያሳይ መረጃ እንዳላት ገለፀች።ተጨማሪ ያንብቡArticle share tools
  20. የታተመዉ 1:54 15 ህዳር 20231:54 15 ህዳር 2023‘ቢያንስ ሆስፒታሉ ጥቃት አይደርስበትም ብለን አስበን ነበር’፡ ከሆስፒታል የሸሹ የጋዛ ነዋሪዎችተጨማሪ ያንብቡArticle share tools