ጭምቅ ሃሳብ

  1. የእስራኤል ጦር በተቆጣጠረው የጋዛው ሆስፒታል ውስጥ ያሉ በርካቶች በሞት አፋፍ ላይ ናቸው ተባለ
  2. ኔታንያሁ የእስራኤል ታጋቾች በአልሺፋ ሆስፒታል እንደነበሩ ‘ጠንካራ ፍንጮች እንዳሉ’ ተናገሩ
  3. የእስራኤል ጦር በዌስት ባንክ በሚገኝ ሆስፒታል ወረራ ማካሄዱ ተነገረ
  4. የእስራኤል ጦር ከአል-ሺፋ ሆስፒታል የተገኘ ነው ያለውን ወታደራዊ ቁስ አሳየ
  5. ደቡብ አፍሪካ በጋዛ ጥቃት እስራኤልን ወደ ዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት ወሰደች
  6. ኔታኒያሁ ስልጣን እንዲለቁ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪ ጠየቁ
  7. አል ሺፋ ሆስፒታል በታንክ ተከቧል
  8. ባይደን አል-ሺፋ ሆስፒታል ጥበቃ ሊደረግለት ይገባል አሉ
  9. የጋዛ ጉዳይ ወታደራዊ መፍትሄ የለውም- የዮርዳኖስ ንጉስ አብዱላህ
  10. በእስራኤል ጥቃት የተገደሉ ፍልስጤማውያን ቁጥር 11 ሺህ 240 ደረሰ- የጋዛ ጤና ሚኒስቴር
  11. እስራኤል በጋዛ ትልቁ ሆስፒታል ላይ ጥቃት ፈጽማለች መባሏን አስተባበለች
  12. አሜሪካ በሶሪያ በሚገኙ የኢራን ጦር ሰፈሮች ላይ ጥቃቶች ፈጸመች

ቀጥታ ዘገባ

  1. የታተመዉ 5:145:14በርካቶች ከአል-ሺፋ ሆስፒታል ለቀው ሲወጡ የተወሰኑት እዚያው ቀርተዋልአል-ሺፋ ሆስፒታልAHMED EL MOKHALLALATICopyright: AHMED EL MOKHALLALATIበእስራኤል ወታደሮች ከቀናት በፊት ከተወረረው የጋዛ ትልቁ ሆስፒታል አል-ሺፋ በርካታ ሰዎች ነጭ ጨርቅ እያሳዩ ጊቢውን ለቀው መውጣታቸውን በሆስፒታሉ ውስጥ ያለ ጋዜጠኛ ለቢቢሲ ተናገረ።ጋዜጠኛ ኻዴር አል ዛኑን እንዳለው ከቀናት በፊት የእስራኤል ወታደሮች በሆስፒታሉ ውስጥ አሰሳ ሲያካሂዱ ከባድ ተኩስ እና ምርመራ መካሄዱን ገልጿል።“ሆስፒታሉ መንቀሳቀስ ከማይችሉት ሕሙማን እና ከጥቂት ዶክተሮች በስተቀር ሁሉም ሰው ቀደም ብሎ ለቆ ወጥቷል” ብሏል።በሐማስ የሚመራው የጋዛ ጤና ሚኒስቴር በበኩሉ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ከአል-ሺፋ ሆስፒታል ዛሬ ጠዋት በእግራቸው ለቀው ወጥተዋል ስለማለቱ ኤኤፍፒ ዘግቧል።ጨምሮም በአሁኑ ወቅትም 120 ቁስለኛ ህሙማን ቁጥራቸው ካልተገለጸ ከጊዜያቸው ቀድመው ከተወለዱ ጨቅላ ሕጻናት ጋር በሆስፒታሉ ውስጥ ይገኛሉ።ቀደም ሲል የጤና ባለሥልጣናት ለፈረንሳዩ የዜና ወኪል እንደተናገሩት “450 የቆሰሉ እና በጽኑ የታመሙ” መንቀሳቀስ የማይችሉ ህሙማን እነሱን ከሚመከታተሉ የተወሰኑ የሕክምና ባለሙያዎች ጋር በሆስፒታሉ ይቆያሉ ብለው ነበር።የተጠቀሱትን አሃዞች ቢቢሲ ከገለልተኛ ወገን ለማረጋገጥ አልቻለም።Article share tools
  2. የታተመዉ 4:134:13ፍልስጤማውያን ከደቡባዊ የጋዛ ክፍሎች ለቀው እንዲወጡ እስራኤል አዘዘችበእስራኤል የአየር ጥቃት የወደመ ሕንጻ ኻን ዩኒስ ውስጥAFPCopyright: AFPበእስራኤል የአየር ጥቃት የወደመ ሕንጻ ኻን ዩኒስ ውስጥImage caption: በእስራኤል የአየር ጥቃት የወደመ ሕንጻ ኻን ዩኒስ ውስጥፍልስጤማውያን በደቡባዊ ጋዛ ከሚገኘው የኻን ዩኒስ አካባቢ ለቀው እንዲወጡ እስራኤል አዲስ ባወጣችው ትዕዛዝ አስጠነቀቀች።የጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታኒያሁ አማካሪ የሆኑት ማርክ ሬጌቭ ኤምኤስኤንቢሲ ለተባለ የአሜሪካ ቴሌቪዥን እንደተናገሩት በአካባቢው ያሉ ነዋሪዎች ለቀው እንዲወጡ እንደተነገራቸው ገልጸዋል።“ለሰዎቹ ቀላል እንደማይሆን አውቃለሁ፣ ነገር ግን ሲቪሎች በተባራሪ ጥይት መካከል ጉዳት እንዲደርስባቸው አንፈልግም” ብለዋል አማካሪው።ጦርነቱ እንደጀመረ ለራሳቸው ደኅንነት ሲሉ ነዋሪዎች ከሰሜናዊ ጋዛ ለቀው እንዲወጡ በእስራኤል መታዘዙን ተከትሎ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች ወደ ደቡብ መውጣታቸው ይታወቃል። ነገር ግን ደቡባዊው የጋዛ ክፍልም በእስራኤል ከባድ ጥቃት ውስጥ ነው የቆየው።አስራኤል ከሦስት ቀናት በፊት የኻን ዩኒስ ነዋሪዎች ለቀው እንዲወጡ የሚያስጠነቅቁ መልዕክቶችን የያዙ በራሪ ወረቀቶችን የበተነች ሲሆን፣ አሁን ደግሞ ሌላ ማስጠንቀቂያ ለከተማዋ ነዋሪዎች ተላልፏል።ኻን ዩኒስ በደቡባዊ ጋዛ ከሚገኙ ከተሞች መካከል ትልቁ ሲሆን፣ የእስራኤልን ጥቃት በመሸሽ ከሰሜናዊ ጋዛ የተፈናቀሉ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ይገኙበታል።በከተማዋ ሰብዓዊ ቀውስ እየተባባሰ ሲሆን፣ የእስራኤልን ማስጠንቀቂያ ተከትሎ ወታደራዊ ዘመቻ በኻን ዩኒስ ላይ መካሄዱ አይቀሬ ነው ተብሏል።Article share tools
  3. የታተመዉ 0:420:42በኤሌክትሪክ መቋረጥ ሕጻናትን ጨምሮ የ40 ሰዎች ሕይወት አለፈበአል-ሺፋ ያሉ ታካሚዎችGetty ImagesCopyright: Getty Imagesበአል-ሺፋ ያሉ ታካሚዎችImage caption: በአል-ሺፋ ያሉ ታካሚዎችየተባበሩት መንግሥታት አል-ሺፋ ሆስፒታል በኤሌክትሪክ ኃይል መቋረጥ ምክንያት 4 ከጊዜያቸው ቀድመው የተወለዱ ጨቅላ ሕጻናትን ጨምሮ የ40 ታማሚዎች ሕይወታቸው ማለፉን አስታወቀ።የሆስፒታሉ አስተዳዳሪዎች በእስራኤል ጦር ተደጋጋሚ ድብደባ ሲደርስበት የነበረው እና በጦሩ ቁጥጥር ስር በሚገኘው ሆስፒታል ባለፉት 7 ቀናት የሟች ታማሚዎች ቁጥር 44 መሆኑን ተናግረዋል።የተባበሩት መንግሥት የሰብዓዊ እርዳታዎች ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ጋዛን በተመለከተ ባወጣው ዕለታዊ ሪፖርት መሠረታዊ አቅርቦቶች በቀሟጠጡባት ጋዛ በውሃ ጥም እና በምግብ እጥረት የተጎዱ ሰዎች ስለመኖራቸው ሪፖርት እየደረሰኝ ነው ብሏል።Article share tools
  4. የታተመዉ 0:400:40እስራኤል በቀን ሁለት ቦቴ ነዳጅ ወደ ጋዛ እንዲገባ እፈቅዳለሁ አለችነዳጅBBCCopyright: BBCእስራኤል በአሜሪካ የደረሰባትን ጫና ተከትሎ በየቀኑ ሁለት ቦቴ ነዳጅ ወደ ጋዛ እንዲገባ እንደምትፈቅድ አስታወቀች።የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ኃላፊ በየሁለት ቀኑ 140ሺህ ሊትር ነዳጅ ጋዛ እንዲገባ ይፈቃል ብለዋል።አብዛኛው ነዳጅ ጥቅም ላይ የሚውለው እርዳታ ለሚያጓጉዙ ደረቅ ተሸከርካሪዎች እና የተባበሩት መንግሥታት የንጹህ ውሃ አቅርቦት እና ንጽህና ሥራን ለማስኬድ ነው።የተቀረው ደግሞ በነዳጅ እጥረት የተቋረጠውን የሞባይል እና ኢንተርኔት አገልግሎትን ለማስቀጠል ጥቅም ላይ ይውላል።ተመድ በነዳጅ እጥረት እና የቴሌኮሚኒኬሽን ግንኙነት አማራጮች አለመኖር አግልግሎቴን ለማቆም ተገድጃለሁ ብሎ ነበር።እስራኤል በጋዛ የተደበቀ የተከማቸ ነዳጅ አለ ብላ የምትከራከር ሲሆን ነዳጅ ወደ ጋዛ እንዲገባ የምፈቅደው ታጋቾች ነጻ ሲወጡ መሆን አለባት ስትልም ቆይታለች።Article share tools
  5. የታተመዉ 0:380:38በሐማስ ታግቶ የነበረው ታንዛኒያዊ መገደሉ ተረጋገጠየታንዛኒያ ዜጋMASHAV ISRAELCopyright: MASHAV ISRAELየታንዛኒያ መንግሥት በሐማስ ታግቶ የነበረው ዜጋው መገደሉን ይፋ አደረገ።ክሌመንስ ፌሊክ ምቴንጋ የተባለው የ22 ዓመት ወጣት ታንዛኒያዊ ሐማስ መስከረም 26/2016 ዓ.ም. ድንገተኛ ጥቃት በፈጸመበት ወቅት ነበር ከሌላ የአገሩ ዜጋ ጋር ታግቶ የነበረው።በእስራኤል የግብርና ትምህርት ሲከታተል የነበረው ምቴንጋ እንዴት ሕይወቱ ሊያልፍ እንደቻለ የተባለ ነገር የለም።የታንዛኒያ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር የቀሪውን ታጋች ታንዛኒያዊ ዕጣ ፈንታ በተመለከተ እና የሟቹን አስክሬን ወደ አገር ለማምጣት ከእስራኤል መንግሥት ጋር እየተነጋገርኩ ነው ብሏል።በእስራኤል ወደ 260 የሚጠጉ የግብርና ትምህርት የሚከታተሉ ታንዛኒያውያን ተማሪዎች ይገኛሉ።ሐማስ መስከረም 26 ላይ ከ230 ያላሱ ሰዎችን ከእስራኤል አግቶ ወደ ጋዛ መውሰዱ ይታወሳል።Article share tools
  6. የታተመዉ 9:12 17 ህዳር 20239:12 17 ህዳር 2023ባለፉት ጥቂት ሰዓታት ከጋዛ የወጡ ምስሎችባለፉት ጥቂት ሰዓታት ጋዛ ያለችበትን ሁኔታ የሚያሳዩ ምስሎች በዜና ወኪሎች ተልከዋል።ምስሎቹ የእስራኤል ጦር በጋዛ ወታደራዊ ዘመቻውን ስለማስቀጠሉ ያሳያሉ።በደቡባዊ ጋዛ ካን ዩኒስ በጥቃት ከወደመ ተሸከርካሪ ጎን የሚራመድ ፍልስጤማዊReutersCopyright: Reutersበደቡባዊ ጋዛ ካን ዩኒስ በጥቃት ከወደመ ተሸከርካሪ ጎን የሚራመድ ፍልስጤማዊImage caption: በደቡባዊ ጋዛ ካን ዩኒስ በጥቃት ከወደመ ተሸከርካሪ ጎን የሚራመድ ፍልስጤማዊበደቡብ ጋዛ የወደመ ሕንጻReutersCopyright: Reutersበደቡብ ጋዛ የወደመ ሕንጻImage caption: በደቡብ ጋዛ የወደመ ሕንጻሰሜናዊ ጋዛEPACopyright: EPAሰሜናዊ ጋዛImage caption: ሰሜናዊ ጋዛበኢንዶኔዢያው ሆስፒታል ሰዎች የሕክምና አገልግሎት ሲሰጣቸውReutersCopyright: Reutersበኢንዶኔዢያው ሆስፒታል ሰዎች የሕክምና አገልግሎት ሲሰጣቸውImage caption: በኢንዶኔዢያው ሆስፒታል ሰዎች የሕክምና አገልግሎት ሲሰጣቸውArticle share tools
  7. የታተመዉ 8:10 17 ህዳር 20238:10 17 ህዳር 2023በምስል፡ የእስራኤል ጦር በጋዛየእስራኤል መከላከያ ኃይል በሰሜናዊ ጋዛ የሚያደርገውን ወታደራዊ ዘመቻ አጠናክሮ ቀጥሏለ።ጦሩ የሠራዊቱ አባላት በጋዛ ሆነው ዘመቻ ሲያካሂዱ የሚያሳዩ ምስሎችን ለመገናኛ ብዙሃን አጋርቷል።በአሁኑ ወቅት በተለይ በሰሜናዊ ጋዛ የግንኙነት መስመሮች ሙሉ በሙሉ በመቋረጣቸው ከስፍራው መረጃዎችን ማግኘት አዳጋች ሆኗል።የእስራኤል ሠራዊት አባላት በሰሜናዊ ጋዛIsraeli Defense ForcesCopyright: Israeli Defense Forcesየእስራኤል ሠራዊት አባላት በሰሜናዊ ጋዛImage caption: የእስራኤል ሠራዊት አባላት በሰሜናዊ ጋዛየእስራኤል ሠራዊት አባል በሰሜናዊ ጋዛIsraeli Defense ForcesCopyright: Israeli Defense Forcesየእስራኤል ሠራዊት አባል በሰሜናዊ ጋዛImage caption: የእስራኤል ሠራዊት አባል በሰሜናዊ ጋዛየእስራኤል ሠራዊት አባላት በሰሜናዊ ጋዛIsraeli Defense ForcesCopyright: Israeli Defense Forcesየእስራኤል ሠራዊት አባላት በሰሜናዊ ጋዛImage caption: የእስራኤል ሠራዊት አባላት በሰሜናዊ ጋዛArticle share tools
  8. የታተመዉ 8:02 17 ህዳር 20238:02 17 ህዳር 2023ተመድ ሰብዓዊ እርዳታ ወደ ጋዛ ማድረስ አልቻልኩም አለጋዛGetty ImagesCopyright: Getty Imagesየተባበሩት መንግሥታት በጋዛ የግንኙነት መስመሮች በመቋረጣቸው ዓርብ ለማድረስ የታቀውን የሰብዓዊ እርዳታ ማድረስ አልቻልኩም አለ።በጋዛ ለሁለተኛ ቀን የሞባይል ስልክ፣ የሞባይል ዳታ ኢንተርኔት፣ ዋይፋይ እንዲሁም መደበኛ የስልክ መስመሮች ተቋርጠው ይገኛሉ።በጋዛ የተመድ ተወካይ ጁሊዬት ቱማ በጋዛ ካሉ ሠራተኞቻቸው ጋር መገናኘት አለመቻላቸውን ገልጸው፤ የግንኙነት አማራጮች እና የነዳጅ አቅርቦት ቢኖር እርዳታ ማድረስ ይቻላናል ብለዋል።የእስራኤል እና ሐማስ ጦርነት መስከረም 26/2016 ዓ.ም. ከተጀመረ በኋላ በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ ነዳጅ ወደ ጋዛ እንዲገባ እስራኤል ለመጀመሪያ ጊዜ መፍቀዷ ይታወሳል።ይህ ነዳጅ ግን በፍጥተን እለቋል።የተመድ የዓለም ምግብ ፕሮግራም በጋዛ የምግብ አቅርቦት የለም የሚባል ደረጃ ላይ መድረሱን የገለጸ ሲሆን የጋዛ ነዋሪዎች የመራብ አደጋ ተጋርጦባቸዋል ብሏል።Article share tools
  9. የታተመዉ 7:35 17 ህዳር 20237:35 17 ህዳር 2023የዓለም ጤና ድርጅት በጋዛ በሽታ በፍጥነት እየተሰራጨ ነው አለጋዛEPACopyright: EPAየዓለም ጤና ድርጅት በጋዛ ሰዎች በመጠላያ ጣቢያዎች ተጨናንቀው መኖራቸው በሽታ ከተገመተው ፍጥነት በላይ እየተሰራጨ ነው አለ።ድርጅቱ ከ70ሺህ በላይ የመተፈንሻ ስርዓት ሕመም እና ከ44ሺህ በላይ የተቅማጥ በሽት ኬዞችን መመዝገቡን ገልጾ የቀዝቃዛማ ወራት መግቢያ መቃረቡ ደግሞ ሁኔታውን የበለጠ አሳሰቢ ያደርገዋል ብሏል።“የቀዝቃዛ ወራት እየቀረቡ ባለበት ወቅት የበሽታ ስርጭቱ እጅጉን አሳስቦናል” ብለዋል በጋዛ እና ዌስት ባንክ የዓለም ጤና ድርጅት ተወካይ ሪቻርድ ፒፕርኮርን።በጋዛ የነዳጅ እጥረት የውሃ ማጣሪያ ማሽኖች ስራ እንዲያቆሙ በማድረጉ ሰዎች የተበከለ ውሃ ለመጠጣት በመገደዳቸው ለተቅማት በሽታ የመጋለጥ ዕድላቸውን ከፍ አድርጎታል ተብሏል።በጋዛ ቆሻሻ የመሰብሰብ ስራም በመቆሙ በሽታ ተሸካሚ የሆኑ ተባዮች እና አይጦች እንዲፈጠሩ ምቹ ሁኔታ ተፈጥሯል ይላል የዓለም ጤና ድርጅት።Article share tools
  10. የታተመዉ 7:25 17 ህዳር 20237:25 17 ህዳር 2023ኔታኒያሁ ለሰላማዊ ሰዎች ሞት ምክንያት ሐማስ ነው አሉየእስራኤል ጠቅላይ ሚንስትር ቤኒያሚን ኔታኒያሁEPACopyright: EPAየእስራኤል ጠቅላይ ሚንስትር ቤኒያሚን ኔታኒያሁ እስራኤል በጦርነቱ የሰላማዊ ሰዎች ጉዳትን ለመቀነስ ብትጥርም ስኬታማ አልሆነችም አሉ።ጠቅላይ ሚንስትሩ አገራቸው ሰላማዊ ሰዎች እንዳይጎዱ ጥንቃቄ ብታደርግም “ሐማስ ግን የተቻለውን በማድረግ ለጉዳት እየዳረጋቸው ነው” ሲሉ ለሲቢኤስ ተናግረዋል።ኔታኒያኑ እንደሚሉት እስራኤል በራሪ ወረቀቶችን በመበተን እና የስልክ ጥሪ በማድረግ ሰላማዊ ሰዎች ደኅንነቱ ወደተጠበቀ ቦታ እንዲያመሩ የምትገልጽ ቢሆንም ሐማስ ግን ደኅንነቱ የተጠበቀ ነው ከሚባለው ቦታ ላይ ሆኖ ይተኩሳል ብለዋል።በሐማስ የሚተዳደረው የጤና ሚንስቴር መስከረም 26 በጀመረው ጦርነት እስካሁን በእስራኤል ጥቃት ከ11ሺህ 500 በላይ ሰዎች በጋዛ መገደላቸውን አስታውቋል።Article share tools
  11. የታተመዉ 5:02 17 ህዳር 20235:02 17 ህዳር 2023ሕይወት በጋዛ፡ “ጦርነቱ መቶ ዓመታትን ወደኋላ መልሶናል”በእስራኤል እና ሐማስ ጦርነት ሳቢያ ከቤታቸው ተፈናቅለው ወደ ደቡባዊ ጋዛ እንዲሸሹ የተገደዱ ፍልስጤማውያን “ጦርነቱ 100 ዓመታትን ወደኋላ መልሶናል” ይላሉ።ተጨማሪ ያንብቡArticle share tools
  12. የታተመዉ 4:45 17 ህዳር 20234:45 17 ህዳር 2023እስራኤል የሁለተኛዋን ታጋች አስክሬን በጋዛ ማግኘቷን አስታወቀችኖራ ማርሲያኖIDFCopyright: IDFየእስራኤል መከላከያ ሰራዊት የ19 አመቷን ታጋች ወታደር አስከሬን በጋዛ ማግኘቱን ገልጿል።የእስራኤላዊቷ ኖራ ማርሲያኖ አስከሬንም የተገኘው በጋዛ ትልቁ ሆስፒታል አልሺፋ አጠገብ በሚገኝ ስፍራ እንደሆነም ጦሩ አስታውቋል።ወታደሯ መሞቷ ከተገለጸ ከቀናትም በኋላ ነው አስከሬኗ የተኘው።ወታደሯ ሐማስመስከረም 26 በእስራኤልላይጥቃትበፈጸመበትወቅትከተወሰዱ 200 ታጋቾችመካከልአንዷነበረች።አስከሬኗ ወደ እስራኤል ከተወሰደ በኋላም ማንነቷን የሚያረጋግጡ ምርመራዎች መካሄዳቸው ተገልጿል።እስራኤል በትናንትናው ዕለት በአልሺፋ አጠገብ በሚገኝ ስፍራ ይሁዲት ዌይስ የተባለችው ታጋች አስከሬን ተገኝቷል ብላለች።Article share tools
  13. የታተመዉ 4:11 17 ህዳር 20234:11 17 ህዳር 2023የእስራኤል መከላከያ በሆስፒታሉ ስር አሉ ያላቸውን “ዋሻዎች” ምስል አሳየእስራኤል የሐማስ ናቸው ያለቻቸው ዋሻዎችIDFCopyright: IDFየእስራኤል መከላከያ በጋዛው ትልቁ ሆስፒታል አልሺፋ ስር የሐማስ ናቸው ያላቸውን ‘ዋሻዎች’ ምስል በኤክስ ገጹ አውጥቷል።ቢቢሲ የእነዚህን ምስሎች ትክክለኛነት ገና አላረጋገጠም። “በአልሺፋ ሆስፒታል ቅጽር ግቢ ውስጥ የአሸባሪው ሐማስ ዋሻ ተገኝቷል” ሲል መከላከያው በትዊተር ገጹ ለጥፏል።በተጨማሪም በሆስፒታል ግቢ ውስጥ በመሬት ስር ያለ መተላለፊያ መግቢያንም ያሳያል ያለውንም ቪዲዮ አውጥቷል።መከላከያው በጋዛ የህጻናት ሆስፒታል አል ራንቲሲ ውስጠኛው ክፍል “ሌላ የአሸባሪ ዋሻ” ነው በሚልም ሌሎች ምስሎችን አጋርቷል።ጦሩ በዚሁ ሆስፒታል ውስጥ ተገኝተዋል ያላቸውን የጦር መሳሪያዎች እና ፈንጂዎችም ቪዲዮ በቅርቡ ማውጣቱ ይታወሳል።በተጨማሪም በአልቁድስ ሆስፒታል “ከፍተኛ መጠን ያለው የጦር መሳሪያ እና ጥይቶች” ተገኝተዋል ሲልም ፎቶ አጋርቷል።እስራኤል ሐማስ ሆስፒታሎቹን ለወታደራዊ ዓላማ ይጠቀምበታል በማለት የምታቀርበውን ክስ አሜሪካ ትደግፈዋለች። ሐማስም ሆነ የሆስፒታሉ ባለሙያዎች የእስራኤል ውንጀላ ፍጹም ሀሰት ነው ሲሉ አይቀበሉትም።Article share tools
  14. የታተመዉ 3:20 17 ህዳር 20233:20 17 ህዳር 2023ኔታንያሁ የእስራኤል ታጋቾች በአልሺፋ ሆስፒታል እንደነበሩ ‘ጠንካራ ፍንጮች እንዳሉ’ ተናገሩየእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁCBSCopyright: CBSየእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ወደ ጋዛ የተወሰዱ ታጋቾች በአልሺፋ ሆስፒታል እንደነበሩ የሚጠቁሙ ‘ጠንካራ ፍንጮች’ እንዳሉ ተናገሩ።ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከአሜሪካው ሚዲያ ሲቢኤስ ጋር ባደረጉት ቆይታ ጦሩ ወደ “ሆስፒታሉ ከገባበትም ምክንያቶች አንዱ ነው” ብለዋል።ኔታንያሁ ወታደሮቻቸው ረቡዕ ዕለት ወደ ሆስፒታሉ ሲገቡ ታጋቾቹ አልነበሩም ብለዋል። ” [ታጋቾቹ] ካሉም ወደውጭ ተወስደዋል” ሲሉም ገልጸዋል።እስራኤል ስለታሰሩት ሰዎች ተጨማሪ መረጃ አለኝ ብትልም ኔታንያሁ ግን “ስለ ጉዳዩ ትንሽ መረጃ መስጠቴ የተሻለ ነው” ብለዋል።እስራኤል በጋዛ በሚገኘው ትልቁ ሆስፒታል አልሺፋ ሐማስ ወታደራዊ ጣቢያ ስትል በተደጋጋሚ የምትከስ ሲሆን ሐማስም ሆነ የሆስፒታሉ ኃላፊዎች ይህንን ፍጹም ሐሰት ነው ሲሉ አይቀበሉትም። ኔታንያሁ አገራቸው በአልሺፋ ታጋቾች እንደነበሩ አለኝ ስለምትለው መረጃ ከመስጠት ተቆጥበዋል።Article share tools
  15. የታተመዉ 3:07 17 ህዳር 20233:07 17 ህዳር 2023የእስራኤል ጦር በዌስት ባንክ በሚገኝ ሆስፒታል ወረራ ማካሄዱ ተነገረጄኒን የስደተኞች መጠለያReutersCopyright: Reutersእስራኤል በኃይል በያዘቻት ዌስት ባንክ ውስጥ በምትገኘው ጄኒን የስደተኞች መጠለያ ወረራ በማካሄድ ኢብን ሲና በተሰኘው ሆስፒታል ውስጥ መግባታቸው ተነገረ።በርካታ ወታደሮች በከተማዋ በሚገኘው የስደተኞች መጠለያ ወረራ መፈጸማቸውን አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ የዜና ወኪል ዘግቧል።እስራኤል በፈጸመችው የድሮን ጥቃትም ሶስት ፍልስጤማውያን መገደላቸውን ሮይተርስ የፍልስጤም አምቡላንስ አገልግሎት ዋቢ አድርጎ ዘግቧል።የእስራኤል ወታደሮች ወደ ከተማዋ ኢብን ሲና ሆስፒታል ሲገቡም አምቡላንሶችን እንዲቆሙ እና የህክምና ሰራተኞችም ለቀው እንዲወጡ ማስገደዳቸውንም በርካታ የፍልስጤም የዜና ምንጮች ዘግበዋል።ቀይ መለዮ የለበሱ ሰራተኞች እጃቸውን ወደላይ አድርገው የሚያሳዩ ቪዲዮ የተጋራ ሲሆን ቢቢሲ ቪዲዮውን ማረጋገጥ አልቻለም።የፍልስጤም ቀይ ጨረቃ በሆስፒታሉ የሚገኙ ሰራተኞቻቹ መታሰራቸውን ማስታወቁንም እነዚህ የዜና ማዕከላት ዘግበዋል።እስራኤል በጄኒን የስደተኞች ጣቢያ ላይ ተደጋጋሚ ወረራዎችን ፈጽማለች። ባለፈው ሳምንት ብቻ በእስራኤል ወረራ 14 ፍልስጤማውያን ሲገደሉ በጣቢያው በቅርብ ጊዜ ከተከሰቱትም የከፋው ነው ተብሏል።Article share tools
  16. የታተመዉ 2:48 17 ህዳር 20232:48 17 ህዳር 2023እስራኤል ከታጋቾቹ መካከል የአንዷን አስከሬን በጋዛ ማግኘቷን አስታወቀችይሁዲት ዌይስFAMILY HANDOUTCopyright: FAMILY HANDOUTየእስራኤል ጦር ከታጋቾቹ መካከል ይሁዲት ዌይስ የተሰኘችውን አስክሬን በጋዛ አልሺፋ ሆስፒታል አጠገብ በሚገኝ ስፍራ ውስጥ ማግኘቱን አስታወቀ።የ65 አመቷ ይሁዲት ሐማስ መስከረም 26 በእስራኤል ላይ ጥቃት በፈጸመበት ወቅት ከተወሰዱ 200 ታጋቾች መካከል አንዷ ነበረች።ግለሰቧ በታገተችበት ወቅት ከጡት ካንሰር ህመም እያገገመች የነበረች ሲሆን የምትወስደውን መድኃኒትም ይዛ እንዳልነበር ብሪንግ ዜም ሆም ናው የተባለው ቡድን አስታውቋል።ባለቤቷ ሻሙዔል በሐማስ ታጣቂዎች መገደሉንም የእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።Article share tools
  17. የታተመዉ 2:48 17 ህዳር 20232:48 17 ህዳር 2023በአልሺፋ ሆስፒታል ውሃ እና ኦክስጅን አለመኖሩን ዳይሬክተሩ ገለጹበእስራኤል ወታደሮች ቁጥጥር ስር በዋለው በጋዛው ትልቁ ሆስፒታል ውሃ እና ኦክስጅን ባመለመኖሩ ታካሚዎች “በውሃ ጥም እየተሰቃዩ” መሆኑን ዳይሬክተሩ ገለጹ። የሆስፒታሉን ሁኔታ “አስከፊ” ሲሉ ሙሐመድ አቡ ሳልሚያ ገልጸዋል። በሆስፒታሉ 650 ታካሚዎች፣ 500 ሐኪሞች እና 5 ሺህ በላይ ተፈናቃዮች ይገኛሉ። የእስራኤል ጦር ሆስፒታሉን መክበቡን እና ሰው አልባ አውሮፕላኖች ከላይ እንደሚያንዣብቡ ጠቁመዋል። ውስጥ የሚገኙ የእስራኤል ወታደሮች የሚያደርጉትን ፍተሻ መቀጠላቸው ተሰምቷል።ተጨማሪ ያንብቡArticle share tools
  18. የታተመዉ 1:20 17 ህዳር 20231:20 17 ህዳር 202341ኛው ቀኑን የያዘው የጋዛ ጦርነት የቅርብ ክስተቶችየአልሺፋ ሆስፒታልBBCCopyright: BBC
    • የእስራኤል ጦር ባለፉት ቀናት በጋዛ ሰርጥ ውስጥ በመሬት ስር የሚገኙ ሁለት ጣቢያዎች ላይ ጥቃት በመፈጸም የከፋ ጉዳት ማድረሱን አስታውቋል። ጥቃቱ ያነጣጠረው ተደብቀው ባሉ ከፍተኛ የሐማስ አመራሮች ላይ መሆኑንም ገልጿል። ከነዚህም መካከል የሐማስ የሮኬት ብርጌድ መሪ እና የሰሜን ጋዛ ብርጌድ መሪ ተጠቅሰዋል።
    • በጋዛ የሚገኙ የእስራኤል ወታደሮች ታግተው ከነበሩት መካከል ይሁዲት ዌይስ የተባለችውን አስከሬን ከሺፋ አጠገብ በሚገኝ ስፍራ ማግኘታቸውን ተናግረዋል። ጦሩ በገባበት የጋዛው ሆስፒታል ቅጥር ግቢ ውስጥ የዋሻ መተላለፊያ እንዲሁም የተጠመደ መኪና ማግኘታቸውን ተናግረዋል።
    • የእስራኤል ጦር የተቆጣጠረው የጋዛ ትልቁ ሆስፒታል አልሺፋ ዳይሬክተር በመቶዎች የሚቆጠሩ ታማሚዎች በስፍራው እንደሚገኙ ገልጸዋል። ሆስፒታሉ መብራት፣ ውሃ ተቋርጦበታል እንዲሁም ኦክስጅንን ጨምሮ የህክምና ግብዓቶች የሉትም። በርካታ ህሙማንንም “በውሃ ጥም” እያቃሰቱ መሆኑንም ዳይሬክተሩ አስረድተዋል።
    • እስራኤል በሙሉ ከበባ ውስጥ ባስገባቻት ነዳጅ እንዳይገባ በመከልከሉ በመላው ጋዛ የሞባይል ስልክ እንዲሁም የኢንተርኔት አገልግሎት መቋረጡን የፍልስጤም የቴሌኮም ኩባንያዎች አስታውቀዋል።
    • በጋዛ ደቡባዊ ክፍል በአራት ከተሞች ነዋሪ የሆኑ ፍልስጤማውያን ከቤታቸው ወጥተው ወደ መጠለያዎች እንዲገቡ የሚያስጠነቅቁ በራሪ ወረቀቶች በእስራኤል ጦር ተበትኗል። ጦሩ በራሪ ወረቀቶቹን የበተነው በኻን ዪኒስ ከተማ መሆኑም ተነግሯል።
    • የእስራኤል ጦር ከዌስት ባንክ ወደ እየሩሳሌም በሚወስደው መንገድ ላይ በሚገኝ የፍተሻ ኬላ ላይ ተኩስ ከፍተዋል ባላቸው ሶስት ታጣቂዎችን መግደሉን አስታውቋል። የእስራኤል ጦር በዌስት ባንክ በሚገኘው የጄኒን የስደተኞች መጠለያ ላይ ወረራ መፈጸሙንም ዘገባዎች አመልክተዋል።
    Article share tools
  19. የታተመዉ 11:02 16 ህዳር 202311:02 16 ህዳር 2023በጋዛ የቴሌኮም ግንኙነት አማራጮች በሙሉ ተቋረጡNetBlocksNetBlocksCopyright: NetBlocksበጋዛ የሞባይል ስልክ፣ የሞባይል ዳታ ኢንተርኔት፣ ዋይፋይ እንዲሁም መደበኛ የስልክ መስመሮች መቋረጣቸው ተገለጸ።የፍልስጤም ኮሚኒኬሽን ኩባንያ የሆነው ጃዋል በጋዛ ሁሉም የቴሌኮም አማራጮች መቋረጣቸውን አስታውቋል።“በጋዛ የቴሌኮም አግልግሎቶችን የሚያንቀሳቀሱ የኃይል ምንጮች ተሟጠው በማለቃቸው ሁሉም የቴሌኮም አማራጮች ተቋረጠዋል” ብሏል ኩባንያው።በመላው ዓለም የኔትዎርክ ግንኙነትን የሚከታተለው ኔትብሎክስ የተሰኘው ድርጅትም ይህንኑ ያረጋገጠ ሲሆን ጋዛ የጠቅላላ የኢንተርኔት መቋረጥ ውስጥ ትገኛለች ብሏል።Article share tools
  20. የታተመዉ 10:52 16 ህዳር 202310:52 16 ህዳር 2023የእስራኤል ጦር አል-ሺፋ ሆስፒታልን ፈትሾ ለመጨረስ ሳምንታት ሊወስድብኝ ይችላል አለከሆስፒታሉ ተገኘ የተባለ የሐማስ ወታደራዊ ርዕዮተ ዓለምBBCCopyright: BBCከሆስፒታሉ ተገኘ የተባለ የሐማስ ወታደራዊ ርዕዮተ ዓለምImage caption: ከሆስፒታሉ ተገኘ የተባለ የሐማስ ወታደራዊ ርዕዮተ ዓለምየእስራኤል ጦር በጋዛ ትልቁ የሆነውን ሆስፒታል ፈትሾ ለመጨረስ ጥቂት ሳምንታት ሊወስዱበት እንደሚችል አስታወቀ።የጦሩ ቃል አቀባይ ሌተናል ኮሌኔል ጆናታን ኮንሪከስ ለቢቢሲ ሲናገሩ ሐማስ ከሆስፒታሉ ስር የሰራውን ግንባታ ስፋት መጠን ለማሳየት ጥቂት ሳምንታት ሊወስድብን ይችላል ብለዋል።እስራኤል እና አሜሪካ ሐማስ ከሆስፒታሉ ስር ወታደራዊ ማዘዣ ጣቢያ እና ዋሻ ግንብቷል ይላሉ።ሐማስ እና የጤና ተቋሙ ግን ይህን ሲያስተባብሉ ቆይተዋል።የእስራኤል ጦር ባለፉት ሁለት ቀናት ሆስፒታሉን ተቆጣጥሮ ብርበራዎችን እያደረገ ሲሆን እስካሁን ድረስ ጥቂት ክላሺንኮቭ መሳሪያዎችን እና ወታደራዊ የደንብ ልብሶችን አግኝቻላሁ ከማለቱ ወጪ የተገነባ ዋሻ አላሳየም።“ሁሉንም የሆስፒታለ ክፍል ፈትሸን አልጨረስንም- ገና አልተጀመረም ማለት ይቀላል” ብለዋል ቃል አቀባዩ ኮንሪከስ።