
19 ህዳር 2023, 10:30 EAT
በ19ኛው ክፍለ ዘመን የፈረንሳይ ግዛትን ሲመራ የነበረው ናፖሊዮን ቦናፓርት ባርኔጣው በፓሪስ ውስጥ በሚደረግ ጨረታ ሊሸጥ ነው።
ጥቁር ቀለም ያለው ባርኔጣ ከ600 እስከ 800 ሺህ ዩሮ ዋጋ ተቆርጦለታል።
የታሪክ ተመራማሪዎች ባርኔጣው ከናፖሊዮን ምልክቶች አንዱ ነበር ይላሉ።
ባርኔጣውን ወደ ጎን አጥልቆ በጦርነት ላይ በመዝመትም ታዋቂነትን አትርፏል።
120 የቢኮርን ኮፍያዎችን ነበሩት። አሁን 20 ኮፍያዎች ብቻ ቀርተዋል።
ባርኔጣው ባለፈው ዓመት በሞተ ከተለየ አንድ ግለሰብ ከተሰበሰቡ ሌሎች የናፖሊዮን ማስታወሻዎች ጋር ለጨረታ ይቀርባል።
የጨረታ አቅራቢዎቹ ባርኔጣው ድንቅ ቅርስ ነው ብለዋል።

የጨረታ አቅራቢው ዣን ፒየር ኦሴና “ሰዎች ይህንን ባርኔጣ የትም ይለዩታል። በጦር ሜዳ ሲያዩት ናፖሊዮን እዚያ መኖሩን ያውቁ ነበር’ ብሏል።
“ከጦርነት ውጭ ደግሞ ሁልጊዜም በራሱ ያጠልቀው ነበር። ወይም በእጁ ይይዘዋል፤ አንዳንድ ጊዜም መሬት ላይ ይጥለው ነበር። ይህ ምስል ነበር የንጉሠ ነገሥቱ ምልክት።”
አጫራቾቹ ባርኔጣ እንከን የለሽ ሆኖ እንደሚቀርብ ተናግረዋል።
በፎንታይንበለው በሚገኘው ኦሴናት ጨረታ ቤት የሚሸጠው ኮፍያ በአውሮፓውያኑ 1815 ናፖሊዮን በባርኔጣው ላይ ያስቀመጠው የጨርቅ ሪባንን ይዟል።
በ1815 በዋተርሉ ከተሸነፈ በኋላ ከናፖሊዮን ሰረገላ የተዘረፈ የብር ሳህን እና ከእንጨት ሳጥኑ ውስጥ የተገኘ ምላጭ፣ የብር የጥርስ ብሩሽ፣ መቀስ እና ሌሎች ንብረቶች በጨረታ ከሚሸጡት መካከል ይገኙበታል።