
- የእስራኤል ጦር የተቆጣጠረው የጋዛ ትልቁ ሆስፒታል አል ሺፋ ‘የሞት ቀጠና’ ሆኗል ሲል የዓለም ጤና ድርጅት አስታወቀ። የቦምብ ድብደባዎችን ባስተናገደው ሆስፒታሉ መግቢያ ላይ “ የጅምላ መቃብር” ማየቱን እና በስፍራው ከ80 በላይ ሰዎችም ተቀብረዋል መባሉንም ተቋሙ አስታውቋል።
ጭምቅ ሃሳብ
- የእስራኤል ጦር በተቆጣጠረው የጋዛው ሆስፒታል ውስጥ ያሉ በርካቶች በሞት አፋፍ ላይ ናቸው ተባለ
- ኔታንያሁ የእስራኤል ታጋቾች በአልሺፋ ሆስፒታል እንደነበሩ ‘ጠንካራ ፍንጮች እንዳሉ’ ተናገሩ
- የእስራኤል ጦር በዌስት ባንክ በሚገኝ ሆስፒታል ወረራ ማካሄዱ ተነገረ
- የእስራኤል ጦር ከአል-ሺፋ ሆስፒታል የተገኘ ነው ያለውን ወታደራዊ ቁስ አሳየ
- ደቡብ አፍሪካ በጋዛ ጥቃት እስራኤልን ወደ ዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት ወሰደች
- ኔታኒያሁ ስልጣን እንዲለቁ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪ ጠየቁ
- አል ሺፋ ሆስፒታል በታንክ ተከቧል
- ባይደን አል-ሺፋ ሆስፒታል ጥበቃ ሊደረግለት ይገባል አሉ
- የጋዛ ጉዳይ ወታደራዊ መፍትሄ የለውም- የዮርዳኖስ ንጉስ አብዱላህ
- በእስራኤል ጥቃት የተገደሉ ፍልስጤማውያን ቁጥር 11 ሺህ 240 ደረሰ- የጋዛ ጤና ሚኒስቴር
- እስራኤል በጋዛ ትልቁ ሆስፒታል ላይ ጥቃት ፈጽማለች መባሏን አስተባበለች
- አሜሪካ በሶሪያ በሚገኙ የኢራን ጦር ሰፈሮች ላይ ጥቃቶች ፈጸመች
ቀጥታ ዘገባ
- የታተመዉ 7:237:23የኳታር ጠቅላይ ሚኒስትር ታጋቾችን የማስለቀቅ ስምምነት ላይ ‘መተማመን መጨመሩን’ ተናገሩ
EPACopyright: EPAየኳታር ጠቅላይ ሚኒስትር መስከረም መጨረሻ ላይ የተወሰዱ ታጋቾችን ለማስፈታት በሚደረገው ድርድር ላይ የሚቀሩ ችግሮች ‘በጣም ጥቃቅን’ እንደሆኑ ተናገሩ።መሃመድ ቢን አብዱልራህማን አል ታኒ በእስራኤል እና በሐማስ መካከል ስምምነት ላይ ሊደረስ እንደሚችል ‘እምነታቸው ከፍ ማለቱን’ ነው ያስረዱት።በኳታር በሚደረገው ውይይት አሜሪካ ታጋቾችን ለማስለቀቅ የስምምነት ውል እንዳቀረበች የዘገበው ዋሽንግተን ፖስት ስምምነት ላይ እንደሚደረስም አስፍሯል።የዋይት ሐውስ የጸጥታው ምክር ቤት ቃለ አቀባይ አድሪያን ዋትሰን በኤክስ ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት ጽሁፍ እስካሁን ስምምነት ላይ እንዳልተደረሰ ጠቅሰው ነገር ግን “ስምምነት ላይ ለመድረስ ጠንክረን መስራታችንን እንቀጥላለን” ብለዋል።የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ታጋቾች ከተለቀቁ ጦርነቱን በጊዜያዊነት ለማቆም እንደሚያስቡበት ቢናገሩም ሙሉ በሙሉ የተኩስ አቁም ስምምነት እንደማይደረስ አስታውቀዋል።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 2:522:52ስድስት ሳምንታትን ያስቆጠረው የጋዛ ጦርነት የቅርብ ክስተቶች
Getty ImagesCopyright: Getty Imagesየእስራኤል ከአልሺፋ ሆስፒታል ውጡ ትዕዛዝ፦ የእስራኤል ጦር በተቆጣጠረው እና ከበባ ውስጥ ባስገባው የጋዛው ትልቁ ሆስፒታል የአል ሺፋ ዳይሬክተር ጦሩ ህሙማኑን እንዲወጡ ትዕዛዝ ማስተላለፋቸውን ተናግረዋል። እስራኤል ይህንን ያስተባበለች ሲሆን ዳይሬክተሩ እንውጣ ብለው ባቀረቡት ጥያቄ መሰረት ፈቃድ ሰጥቻለሁ ብላለች።በመቶዎች የሚቆጠሩ ፍልስጤማውያን ከአልሺፋ እየሸሹ ነው፦ በመቶዎች የሚቆጠሩ ፍልስጤማውያን የእስራኤል ጦር ከተቆጣጠረው የጋዛ ሆስፒታል እየወጡ እና እየሸሹ ይገኛሉ። የእስራኤል መከላከያ ስራዊት በሆስፒታሉ እዝ ስር የሐማስ እዝ አለ በማለት ሆስፒታሉን በቁጥጥሩ ስር አድርጎ ፍተሻ እያደረገም ይገኛል። የሐማስ ዋሻ እና የጦር መሳሪያዎች ናቸው ያላቸውንም ምስሎች አሳይቷል።ተመድ ባቋቋመው የትምህርት ቤት መጠለያ የደረሰው ጥቃት፦እስራኤል ተመድ ባቋቋመው እና ወደ ተፈናቃዮች መጠለያ በተቀየረ ትምህርት ቤት ባደረሰችው ጥቃት በርካቶች መገደላቸውን የጋዛ ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።እስራኤል ወደ መጠለያነት በተቀየረው ትምህርት ቤት ላይ ጥቃት ማድረሷን ባታረጋግጥም እየመረመርኩ ነው ብላለች።የሐማስ የጤና ባለስልጣናት በሰሜን ጋዛ ጃባሊያ በደረሱ ሁለት ጥቃቶች 80 ሰዎች መገደላቸውን አስታውቀዋል።የቆሰሉ ህጻናት ወደ አረብ ኤምሬትስ አቀኑ፦ 15 የሚደርሱ የተጎዱ ፍልስጤማውያን ህጻናት እና ቤተሰቦቻቸውን ያሳፈረው የመጀመሪያው አውሮፕላን አቡዳቢ ደርሷል። የተበባሩት አረብ ኤምሬቶች ባለስልጣናት በሚቀጥሉት ጥቂት ሳምንታት ውስጥ 1 ሺህ ፍልስጤማውያን ህጻናት እና ሴቶችን ከጋዛ አስወጥቶ በአገሩ ወደሚገኙ የጤና ማዕከላት ለማምጣት ማቀዱን አስታውቋል።ወደ እየሩሳሌም የተደረገው የተቃውሞ ሰልፍ፦ በሐማስ የተወሰዱ ከ200 በላይ ታጋቾች ቤተሰቦች እና ደጋፊዎቸቻቸው ከቴል አቪቭ ወደ እየሩሳሌም በመሄድ ተቃውሟቸውን አሰምተዋል። በርካቶች መፈክሮችን እና ሰንደቅ አላማም ይዘው ነበር። አንዳንዶችም የታገቱትን ሰዎች ምስል ይዘው የነበረ ሲሆን ታጋቾችን ለማስለቀቅ የእስራኤል መንግሥት የተቻለውን እያደረገ አይደለም ሲሉም ተሰምተዋል።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 1:341:34እስራኤል ተመድ ባቋቋመው የትምህርት ቤት መጠለያ ባደረሰችው ጥቃት በርካቶች መገደላቸው ተነገረ
Getty ImagesCopyright: Getty Imagesእስራኤል ተመድ ባቋቋመው እና ወደ ተፈናቃዮች መጠለያ በተቀየረ ትምህርት ቤት ባደረሰችው ጥቃት በርካቶች መገደላቸውን የጋዛ ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።እስራኤል ወደ መጠለያነት በተቀየረው ትምህርት ቤት ላይ ጥቃት ማድረሷን ባታረጋግጥም እየመረመርኩ ነው ብላለች።የሐማስ የጤና ባለስልጣናት በሰሜን ጋዛ ጃባሊያ በደረሱ ሁለት ጥቃቶች 80 ሰዎች መገደላቸውን አስታውቀዋል።ቢቢሲ በጃባሊያ አል ፋክሁራ ትምህርት ቤት የተቀረጸ ቪዲዮን ያገኘ ሲሆን በከፋ የተጎዱ እና እንቅስቃሴ አልባ ሰዎችንም በወለሎች ላይ ተኝተው ያሳያል።በቪዲዮው ላይ ከ20 የሚበልጡ ተጎጂዎች የሚታዩ ሲሆን ያሉበትም ክፍል ህንጻ በከባዱ እንደተጎዳ ያሳያል።የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፍልስጤም ስደተኞች ኤጀንሲ ኃላፊ ፊሊፕ ላዛሪኒ ወደ መጠለያነት በተቀየረው ትምህርት ቤታቸው በሺዎች የሚቆጠሩ ፍልስጤማውያን ተፈናቃዮች እንደሚገኙ ጠቅሰው “በርካታ የተገደሉ እና የተጎዱ ሰዎችን የሚያሳዩ ዘግናኝ ቪዲዮዎችን እና ምስሎችን ማየታቸውን” ተናግረዋል።በጃባሊያ ሌላ ስፍራ እስራኤል በፈጸመችው ጥቃት የአንድ ቤተሰብ አባል የሆኑ ከ30 በላይ ፍልስጤማውያን መገደላቸውን በሐማስ የሚመራው የጤና ሚኒስቴር ገልጿል።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 1:031:03በመቶዎች የሚቆጠሩ ከአል-ሺፋ ሆስፒታል ሲሸሹ፤ በርካቶች በመጠለያ ጣብያ ውስጥ ተገደሉታማሚዎችን ጨምሮ በመቶዎች የሚቆጠሩ ፍልስጤማውያን ቅዳሜ ዕለት ጋዛ ከተማ ከሚገኘው ትልቁ ሆስፒታል ለቀው እየሸሹ ይገኛሉ። አንዳንድ የሕክምና ባለሙያዎች ሆስፒታሉን ለቀው እንዲወጡ እንደተነገራቸው ቢገልጹም እስራኤል ግን አስተባብላለች። የተኩስ ድምጽ እየተሰማ ብዙዎች በፈራረሱት መንገዶች ሲጓዙ ታይተዋል።ተጨማሪ ያንብቡArticle share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 0:200:20የጋዛ ትልቁ ሆስፒታል አልሺፋ ‘የሞት ቀጠና’ ሆኗል- የዓለም ጤና ድርጅት
Getty ImagesCopyright: Getty Imagesየእስራኤል ጦር የተቆጣጠረው የጋዛ ትልቁ ሆስፒታል አል ሺፋ ‘የሞት ቀጠና’ ሆኗል ሲል የዓለም ጤና ድርጅት አስታወቀ።የቦምብ ድብደባዎችን ባስተናገደው ሆስፒታሉ መግቢያ ላይ ” የጅምላ መቃብር” ማየቱን እና በስፍራው ከ80 በላይ ሰዎችም ተቀብረዋል መባሉንም ተቋሙ አስታውቋል።የጤና ተቋሙን ሁኔታ የገመገመው የዓለም ጤና ድርጅት ሁኔታውን ‘ተስፋ አስቆራጭ’ ሲል ጠርቶታል።የእስራኤል ጦር በሆስፒታሉ ስር የሐማስ የእዝ ማዕከል አለ በሚልም ወረራ የፈጸመ ሲሆን ለቀናትም ያህል ፍተሻ እያደረገ ይገኛል።ሆስፒታሉ የቦምብ ድብደባ እና የተኩስ ልውውጦችንም ማስተናገዱን መረጃዎች አግኝቻለሁ ብሏል። ሆስፒታሉ መብራት፣ ውሃ እና ነዳጅ የተቋረጠበት ሲሆን በዚህም በርካቶች መሞታቸው ተገልጿል።በመቶዎች የሚቆጠሩ ፍልስጤማውያንም ከአልሺፋ ሆስፒታል ወጥተው በእግራቸው እየሸሹ ይገኛሉ።አንዳንዶችም በመንገዳቸው ላይ ነጭ ሰንደቅ ዓላማ እያውለበለቡም የሚያሳዩ ፎቶዎች ታይተዋል። ከሆስፒታሉ ከወጡት መካከል የሆነው አንድ ጋዜጠኛ እንደተናገረው ሌሊት ላይ የተኩስ ድምጽ እና ፍንዳታዎች ነበሩ ብሏል።በተጨማሪም የእስራኤል ቡልዶዘሮች በሆስፒታሉ ቅጥር ግቢ ውስጥ ትላልቅ ጉድጓዶች መቆፈራቸውንም ተናግሯል።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 0:100:10እስራኤል በሐማስ የተገደሉ ሰዎችን አስከሬን ለማግኘት ንስርን እንዴት ተጠቀመች?በመስከረም ወር ማብቂያ ላይ ሐማስ የፈጸመውን ጥቃት ተከትሎ ደብዛቸው የጠፋ ወታደሮቿን አስከሬን ለመፈለግ እስራኤል ባለ ነጭ ጭራ ንስሮችን ተጠቅማለች። በዚህ ሂደትም አንድ ንስር ቢያንስ አራት አስከሬኖችን ለማግኘት አስችሏል። ይህ እንዴት ሆነ?ተጨማሪ ያንብቡArticle share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 5:14 18 ህዳር 20235:14 18 ህዳር 2023በርካቶች ከአል-ሺፋ ሆስፒታል ለቀው ሲወጡ የተወሰኑት እዚያው ቀርተዋል
AHMED EL MOKHALLALATICopyright: AHMED EL MOKHALLALATIበእስራኤል ወታደሮች ከቀናት በፊት ከተወረረው የጋዛ ትልቁ ሆስፒታል አል-ሺፋ በርካታ ሰዎች ነጭ ጨርቅ እያሳዩ ጊቢውን ለቀው መውጣታቸውን በሆስፒታሉ ውስጥ ያለ ጋዜጠኛ ለቢቢሲ ተናገረ።ጋዜጠኛ ኻዴር አል ዛኑን እንዳለው ከቀናት በፊት የእስራኤል ወታደሮች በሆስፒታሉ ውስጥ አሰሳ ሲያካሂዱ ከባድ ተኩስ እና ምርመራ መካሄዱን ገልጿል።“ሆስፒታሉ መንቀሳቀስ ከማይችሉት ሕሙማን እና ከጥቂት ዶክተሮች በስተቀር ሁሉም ሰው ቀደም ብሎ ለቆ ወጥቷል” ብሏል።በሐማስ የሚመራው የጋዛ ጤና ሚኒስቴር በበኩሉ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ከአል-ሺፋ ሆስፒታል ዛሬ ጠዋት በእግራቸው ለቀው ወጥተዋል ስለማለቱ ኤኤፍፒ ዘግቧል።ጨምሮም በአሁኑ ወቅትም 120 ቁስለኛ ህሙማን ቁጥራቸው ካልተገለጸ ከጊዜያቸው ቀድመው ከተወለዱ ጨቅላ ሕጻናት ጋር በሆስፒታሉ ውስጥ ይገኛሉ።ቀደም ሲል የጤና ባለሥልጣናት ለፈረንሳዩ የዜና ወኪል እንደተናገሩት “450 የቆሰሉ እና በጽኑ የታመሙ” መንቀሳቀስ የማይችሉ ህሙማን እነሱን ከሚመከታተሉ የተወሰኑ የሕክምና ባለሙያዎች ጋር በሆስፒታሉ ይቆያሉ ብለው ነበር።የተጠቀሱትን አሃዞች ቢቢሲ ከገለልተኛ ወገን ለማረጋገጥ አልቻለም።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 4:13 18 ህዳር 20234:13 18 ህዳር 2023ፍልስጤማውያን ከደቡባዊ የጋዛ ክፍሎች ለቀው እንዲወጡ እስራኤል አዘዘች
AFPCopyright: AFPበእስራኤል የአየር ጥቃት የወደመ ሕንጻ ኻን ዩኒስ ውስጥImage caption: በእስራኤል የአየር ጥቃት የወደመ ሕንጻ ኻን ዩኒስ ውስጥፍልስጤማውያን በደቡባዊ ጋዛ ከሚገኘው የኻን ዩኒስ አካባቢ ለቀው እንዲወጡ እስራኤል አዲስ ባወጣችው ትዕዛዝ አስጠነቀቀች።የጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታኒያሁ አማካሪ የሆኑት ማርክ ሬጌቭ ኤምኤስኤንቢሲ ለተባለ የአሜሪካ ቴሌቪዥን እንደተናገሩት በአካባቢው ያሉ ነዋሪዎች ለቀው እንዲወጡ እንደተነገራቸው ገልጸዋል።“ለሰዎቹ ቀላል እንደማይሆን አውቃለሁ፣ ነገር ግን ሲቪሎች በተባራሪ ጥይት መካከል ጉዳት እንዲደርስባቸው አንፈልግም” ብለዋል አማካሪው።ጦርነቱ እንደጀመረ ለራሳቸው ደኅንነት ሲሉ ነዋሪዎች ከሰሜናዊ ጋዛ ለቀው እንዲወጡ በእስራኤል መታዘዙን ተከትሎ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች ወደ ደቡብ መውጣታቸው ይታወቃል። ነገር ግን ደቡባዊው የጋዛ ክፍልም በእስራኤል ከባድ ጥቃት ውስጥ ነው የቆየው።አስራኤል ከሦስት ቀናት በፊት የኻን ዩኒስ ነዋሪዎች ለቀው እንዲወጡ የሚያስጠነቅቁ መልዕክቶችን የያዙ በራሪ ወረቀቶችን የበተነች ሲሆን፣ አሁን ደግሞ ሌላ ማስጠንቀቂያ ለከተማዋ ነዋሪዎች ተላልፏል።ኻን ዩኒስ በደቡባዊ ጋዛ ከሚገኙ ከተሞች መካከል ትልቁ ሲሆን፣ የእስራኤልን ጥቃት በመሸሽ ከሰሜናዊ ጋዛ የተፈናቀሉ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ይገኙበታል።በከተማዋ ሰብዓዊ ቀውስ እየተባባሰ ሲሆን፣ የእስራኤልን ማስጠንቀቂያ ተከትሎ ወታደራዊ ዘመቻ በኻን ዩኒስ ላይ መካሄዱ አይቀሬ ነው ተብሏል።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 0:42 18 ህዳር 20230:42 18 ህዳር 2023በኤሌክትሪክ መቋረጥ ሕጻናትን ጨምሮ የ40 ሰዎች ሕይወት አለፈ
Getty ImagesCopyright: Getty Imagesበአል-ሺፋ ያሉ ታካሚዎችImage caption: በአል-ሺፋ ያሉ ታካሚዎችየተባበሩት መንግሥታት አል-ሺፋ ሆስፒታል በኤሌክትሪክ ኃይል መቋረጥ ምክንያት 4 ከጊዜያቸው ቀድመው የተወለዱ ጨቅላ ሕጻናትን ጨምሮ የ40 ታማሚዎች ሕይወታቸው ማለፉን አስታወቀ።የሆስፒታሉ አስተዳዳሪዎች በእስራኤል ጦር ተደጋጋሚ ድብደባ ሲደርስበት የነበረው እና በጦሩ ቁጥጥር ስር በሚገኘው ሆስፒታል ባለፉት 7 ቀናት የሟች ታማሚዎች ቁጥር 44 መሆኑን ተናግረዋል።የተባበሩት መንግሥት የሰብዓዊ እርዳታዎች ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ጋዛን በተመለከተ ባወጣው ዕለታዊ ሪፖርት መሠረታዊ አቅርቦቶች በቀሟጠጡባት ጋዛ በውሃ ጥም እና በምግብ እጥረት የተጎዱ ሰዎች ስለመኖራቸው ሪፖርት እየደረሰኝ ነው ብሏል።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 0:40 18 ህዳር 20230:40 18 ህዳር 2023እስራኤል በቀን ሁለት ቦቴ ነዳጅ ወደ ጋዛ እንዲገባ እፈቅዳለሁ አለች
BBCCopyright: BBCእስራኤል በአሜሪካ የደረሰባትን ጫና ተከትሎ በየቀኑ ሁለት ቦቴ ነዳጅ ወደ ጋዛ እንዲገባ እንደምትፈቅድ አስታወቀች።የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ኃላፊ በየሁለት ቀኑ 140ሺህ ሊትር ነዳጅ ጋዛ እንዲገባ ይፈቃል ብለዋል።አብዛኛው ነዳጅ ጥቅም ላይ የሚውለው እርዳታ ለሚያጓጉዙ ደረቅ ተሸከርካሪዎች እና የተባበሩት መንግሥታት የንጹህ ውሃ አቅርቦት እና ንጽህና ሥራን ለማስኬድ ነው።የተቀረው ደግሞ በነዳጅ እጥረት የተቋረጠውን የሞባይል እና ኢንተርኔት አገልግሎትን ለማስቀጠል ጥቅም ላይ ይውላል።ተመድ በነዳጅ እጥረት እና የቴሌኮሚኒኬሽን ግንኙነት አማራጮች አለመኖር አግልግሎቴን ለማቆም ተገድጃለሁ ብሎ ነበር።እስራኤል በጋዛ የተደበቀ የተከማቸ ነዳጅ አለ ብላ የምትከራከር ሲሆን ነዳጅ ወደ ጋዛ እንዲገባ የምፈቅደው ታጋቾች ነጻ ሲወጡ መሆን አለባት ስትልም ቆይታለች።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 0:38 18 ህዳር 20230:38 18 ህዳር 2023በሐማስ ታግቶ የነበረው ታንዛኒያዊ መገደሉ ተረጋገጠ
MASHAV ISRAELCopyright: MASHAV ISRAELየታንዛኒያ መንግሥት በሐማስ ታግቶ የነበረው ዜጋው መገደሉን ይፋ አደረገ።ክሌመንስ ፌሊክ ምቴንጋ የተባለው የ22 ዓመት ወጣት ታንዛኒያዊ ሐማስ መስከረም 26/2016 ዓ.ም. ድንገተኛ ጥቃት በፈጸመበት ወቅት ነበር ከሌላ የአገሩ ዜጋ ጋር ታግቶ የነበረው።በእስራኤል የግብርና ትምህርት ሲከታተል የነበረው ምቴንጋ እንዴት ሕይወቱ ሊያልፍ እንደቻለ የተባለ ነገር የለም።የታንዛኒያ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር የቀሪውን ታጋች ታንዛኒያዊ ዕጣ ፈንታ በተመለከተ እና የሟቹን አስክሬን ወደ አገር ለማምጣት ከእስራኤል መንግሥት ጋር እየተነጋገርኩ ነው ብሏል።በእስራኤል ወደ 260 የሚጠጉ የግብርና ትምህርት የሚከታተሉ ታንዛኒያውያን ተማሪዎች ይገኛሉ።ሐማስ መስከረም 26 ላይ ከ230 ያላሱ ሰዎችን ከእስራኤል አግቶ ወደ ጋዛ መውሰዱ ይታወሳል።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 9:12 17 ህዳር 20239:12 17 ህዳር 2023ባለፉት ጥቂት ሰዓታት ከጋዛ የወጡ ምስሎችባለፉት ጥቂት ሰዓታት ጋዛ ያለችበትን ሁኔታ የሚያሳዩ ምስሎች በዜና ወኪሎች ተልከዋል።ምስሎቹ የእስራኤል ጦር በጋዛ ወታደራዊ ዘመቻውን ስለማስቀጠሉ ያሳያሉ።
ReutersCopyright: Reutersበደቡባዊ ጋዛ ካን ዩኒስ በጥቃት ከወደመ ተሸከርካሪ ጎን የሚራመድ ፍልስጤማዊImage caption: በደቡባዊ ጋዛ ካን ዩኒስ በጥቃት ከወደመ ተሸከርካሪ ጎን የሚራመድ ፍልስጤማዊ
ReutersCopyright: Reutersበደቡብ ጋዛ የወደመ ሕንጻImage caption: በደቡብ ጋዛ የወደመ ሕንጻ
EPACopyright: EPAሰሜናዊ ጋዛImage caption: ሰሜናዊ ጋዛ
ReutersCopyright: Reutersበኢንዶኔዢያው ሆስፒታል ሰዎች የሕክምና አገልግሎት ሲሰጣቸውImage caption: በኢንዶኔዢያው ሆስፒታል ሰዎች የሕክምና አገልግሎት ሲሰጣቸውArticle share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 8:10 17 ህዳር 20238:10 17 ህዳር 2023በምስል፡ የእስራኤል ጦር በጋዛየእስራኤል መከላከያ ኃይል በሰሜናዊ ጋዛ የሚያደርገውን ወታደራዊ ዘመቻ አጠናክሮ ቀጥሏለ።ጦሩ የሠራዊቱ አባላት በጋዛ ሆነው ዘመቻ ሲያካሂዱ የሚያሳዩ ምስሎችን ለመገናኛ ብዙሃን አጋርቷል።በአሁኑ ወቅት በተለይ በሰሜናዊ ጋዛ የግንኙነት መስመሮች ሙሉ በሙሉ በመቋረጣቸው ከስፍራው መረጃዎችን ማግኘት አዳጋች ሆኗል።
Israeli Defense ForcesCopyright: Israeli Defense Forcesየእስራኤል ሠራዊት አባላት በሰሜናዊ ጋዛImage caption: የእስራኤል ሠራዊት አባላት በሰሜናዊ ጋዛ
Israeli Defense ForcesCopyright: Israeli Defense Forcesየእስራኤል ሠራዊት አባል በሰሜናዊ ጋዛImage caption: የእስራኤል ሠራዊት አባል በሰሜናዊ ጋዛ
Israeli Defense ForcesCopyright: Israeli Defense Forcesየእስራኤል ሠራዊት አባላት በሰሜናዊ ጋዛImage caption: የእስራኤል ሠራዊት አባላት በሰሜናዊ ጋዛArticle share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 8:02 17 ህዳር 20238:02 17 ህዳር 2023ተመድ ሰብዓዊ እርዳታ ወደ ጋዛ ማድረስ አልቻልኩም አለ
Getty ImagesCopyright: Getty Imagesየተባበሩት መንግሥታት በጋዛ የግንኙነት መስመሮች በመቋረጣቸው ዓርብ ለማድረስ የታቀውን የሰብዓዊ እርዳታ ማድረስ አልቻልኩም አለ።በጋዛ ለሁለተኛ ቀን የሞባይል ስልክ፣ የሞባይል ዳታ ኢንተርኔት፣ ዋይፋይ እንዲሁም መደበኛ የስልክ መስመሮች ተቋርጠው ይገኛሉ።በጋዛ የተመድ ተወካይ ጁሊዬት ቱማ በጋዛ ካሉ ሠራተኞቻቸው ጋር መገናኘት አለመቻላቸውን ገልጸው፤ የግንኙነት አማራጮች እና የነዳጅ አቅርቦት ቢኖር እርዳታ ማድረስ ይቻላናል ብለዋል።የእስራኤል እና ሐማስ ጦርነት መስከረም 26/2016 ዓ.ም. ከተጀመረ በኋላ በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ ነዳጅ ወደ ጋዛ እንዲገባ እስራኤል ለመጀመሪያ ጊዜ መፍቀዷ ይታወሳል።ይህ ነዳጅ ግን በፍጥተን እለቋል።የተመድ የዓለም ምግብ ፕሮግራም በጋዛ የምግብ አቅርቦት የለም የሚባል ደረጃ ላይ መድረሱን የገለጸ ሲሆን የጋዛ ነዋሪዎች የመራብ አደጋ ተጋርጦባቸዋል ብሏል።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 7:35 17 ህዳር 20237:35 17 ህዳር 2023የዓለም ጤና ድርጅት በጋዛ በሽታ በፍጥነት እየተሰራጨ ነው አለ
EPACopyright: EPAየዓለም ጤና ድርጅት በጋዛ ሰዎች በመጠላያ ጣቢያዎች ተጨናንቀው መኖራቸው በሽታ ከተገመተው ፍጥነት በላይ እየተሰራጨ ነው አለ።ድርጅቱ ከ70ሺህ በላይ የመተፈንሻ ስርዓት ሕመም እና ከ44ሺህ በላይ የተቅማጥ በሽት ኬዞችን መመዝገቡን ገልጾ የቀዝቃዛማ ወራት መግቢያ መቃረቡ ደግሞ ሁኔታውን የበለጠ አሳሰቢ ያደርገዋል ብሏል።“የቀዝቃዛ ወራት እየቀረቡ ባለበት ወቅት የበሽታ ስርጭቱ እጅጉን አሳስቦናል” ብለዋል በጋዛ እና ዌስት ባንክ የዓለም ጤና ድርጅት ተወካይ ሪቻርድ ፒፕርኮርን።በጋዛ የነዳጅ እጥረት የውሃ ማጣሪያ ማሽኖች ስራ እንዲያቆሙ በማድረጉ ሰዎች የተበከለ ውሃ ለመጠጣት በመገደዳቸው ለተቅማት በሽታ የመጋለጥ ዕድላቸውን ከፍ አድርጎታል ተብሏል።በጋዛ ቆሻሻ የመሰብሰብ ስራም በመቆሙ በሽታ ተሸካሚ የሆኑ ተባዮች እና አይጦች እንዲፈጠሩ ምቹ ሁኔታ ተፈጥሯል ይላል የዓለም ጤና ድርጅት።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 7:25 17 ህዳር 20237:25 17 ህዳር 2023ኔታኒያሁ ለሰላማዊ ሰዎች ሞት ምክንያት ሐማስ ነው አሉ
EPACopyright: EPAየእስራኤል ጠቅላይ ሚንስትር ቤኒያሚን ኔታኒያሁ እስራኤል በጦርነቱ የሰላማዊ ሰዎች ጉዳትን ለመቀነስ ብትጥርም ስኬታማ አልሆነችም አሉ።ጠቅላይ ሚንስትሩ አገራቸው ሰላማዊ ሰዎች እንዳይጎዱ ጥንቃቄ ብታደርግም “ሐማስ ግን የተቻለውን በማድረግ ለጉዳት እየዳረጋቸው ነው” ሲሉ ለሲቢኤስ ተናግረዋል።ኔታኒያኑ እንደሚሉት እስራኤል በራሪ ወረቀቶችን በመበተን እና የስልክ ጥሪ በማድረግ ሰላማዊ ሰዎች ደኅንነቱ ወደተጠበቀ ቦታ እንዲያመሩ የምትገልጽ ቢሆንም ሐማስ ግን ደኅንነቱ የተጠበቀ ነው ከሚባለው ቦታ ላይ ሆኖ ይተኩሳል ብለዋል።በሐማስ የሚተዳደረው የጤና ሚንስቴር መስከረም 26 በጀመረው ጦርነት እስካሁን በእስራኤል ጥቃት ከ11ሺህ 500 በላይ ሰዎች በጋዛ መገደላቸውን አስታውቋል።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 5:02 17 ህዳር 20235:02 17 ህዳር 2023ሕይወት በጋዛ፡ “ጦርነቱ መቶ ዓመታትን ወደኋላ መልሶናል”በእስራኤል እና ሐማስ ጦርነት ሳቢያ ከቤታቸው ተፈናቅለው ወደ ደቡባዊ ጋዛ እንዲሸሹ የተገደዱ ፍልስጤማውያን “ጦርነቱ 100 ዓመታትን ወደኋላ መልሶናል” ይላሉ።ተጨማሪ ያንብቡArticle share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 4:45 17 ህዳር 20234:45 17 ህዳር 2023እስራኤል የሁለተኛዋን ታጋች አስክሬን በጋዛ ማግኘቷን አስታወቀች
IDFCopyright: IDFየእስራኤል መከላከያ ሰራዊት የ19 አመቷን ታጋች ወታደር አስከሬን በጋዛ ማግኘቱን ገልጿል።የእስራኤላዊቷ ኖራ ማርሲያኖ አስከሬንም የተገኘው በጋዛ ትልቁ ሆስፒታል አልሺፋ አጠገብ በሚገኝ ስፍራ እንደሆነም ጦሩ አስታውቋል።ወታደሯ መሞቷ ከተገለጸ ከቀናትም በኋላ ነው አስከሬኗ የተኘው።ወታደሯ ሐማስመስከረም 26 በእስራኤልላይጥቃትበፈጸመበትወቅትከተወሰዱ 200 ታጋቾችመካከልአንዷነበረች።አስከሬኗ ወደ እስራኤል ከተወሰደ በኋላም ማንነቷን የሚያረጋግጡ ምርመራዎች መካሄዳቸው ተገልጿል።እስራኤል በትናንትናው ዕለት በአልሺፋ አጠገብ በሚገኝ ስፍራ ይሁዲት ዌይስ የተባለችው ታጋች አስከሬን ተገኝቷል ብላለች።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 4:11 17 ህዳር 20234:11 17 ህዳር 2023የእስራኤል መከላከያ በሆስፒታሉ ስር አሉ ያላቸውን “ዋሻዎች” ምስል አሳየ
IDFCopyright: IDFየእስራኤል መከላከያ በጋዛው ትልቁ ሆስፒታል አልሺፋ ስር የሐማስ ናቸው ያላቸውን ‘ዋሻዎች’ ምስል በኤክስ ገጹ አውጥቷል።ቢቢሲ የእነዚህን ምስሎች ትክክለኛነት ገና አላረጋገጠም። “በአልሺፋ ሆስፒታል ቅጽር ግቢ ውስጥ የአሸባሪው ሐማስ ዋሻ ተገኝቷል” ሲል መከላከያው በትዊተር ገጹ ለጥፏል።በተጨማሪም በሆስፒታል ግቢ ውስጥ በመሬት ስር ያለ መተላለፊያ መግቢያንም ያሳያል ያለውንም ቪዲዮ አውጥቷል።መከላከያው በጋዛ የህጻናት ሆስፒታል አል ራንቲሲ ውስጠኛው ክፍል “ሌላ የአሸባሪ ዋሻ” ነው በሚልም ሌሎች ምስሎችን አጋርቷል።ጦሩ በዚሁ ሆስፒታል ውስጥ ተገኝተዋል ያላቸውን የጦር መሳሪያዎች እና ፈንጂዎችም ቪዲዮ በቅርቡ ማውጣቱ ይታወሳል።በተጨማሪም በአልቁድስ ሆስፒታል “ከፍተኛ መጠን ያለው የጦር መሳሪያ እና ጥይቶች” ተገኝተዋል ሲልም ፎቶ አጋርቷል።እስራኤል ሐማስ ሆስፒታሎቹን ለወታደራዊ ዓላማ ይጠቀምበታል በማለት የምታቀርበውን ክስ አሜሪካ ትደግፈዋለች። ሐማስም ሆነ የሆስፒታሉ ባለሙያዎች የእስራኤል ውንጀላ ፍጹም ሀሰት ነው ሲሉ አይቀበሉትም።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 3:20 17 ህዳር 20233:20 17 ህዳር 2023ኔታንያሁ የእስራኤል ታጋቾች በአልሺፋ ሆስፒታል እንደነበሩ ‘ጠንካራ ፍንጮች እንዳሉ’ ተናገሩ
CBSCopyright: CBSየእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ወደ ጋዛ የተወሰዱ ታጋቾች በአልሺፋ ሆስፒታል እንደነበሩ የሚጠቁሙ ‘ጠንካራ ፍንጮች’ እንዳሉ ተናገሩ።ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከአሜሪካው ሚዲያ ሲቢኤስ ጋር ባደረጉት ቆይታ ጦሩ ወደ “ሆስፒታሉ ከገባበትም ምክንያቶች አንዱ ነው” ብለዋል።ኔታንያሁ ወታደሮቻቸው ረቡዕ ዕለት ወደ ሆስፒታሉ ሲገቡ ታጋቾቹ አልነበሩም ብለዋል። ” [ታጋቾቹ] ካሉም ወደውጭ ተወስደዋል” ሲሉም ገልጸዋል።እስራኤል ስለታሰሩት ሰዎች ተጨማሪ መረጃ አለኝ ብትልም ኔታንያሁ ግን “ስለ ጉዳዩ ትንሽ መረጃ መስጠቴ የተሻለ ነው” ብለዋል።እስራኤል በጋዛ በሚገኘው ትልቁ ሆስፒታል አልሺፋ ሐማስ ወታደራዊ ጣቢያ ስትል በተደጋጋሚ የምትከስ ሲሆን ሐማስም ሆነ የሆስፒታሉ ኃላፊዎች ይህንን ፍጹም ሐሰት ነው ሲሉ አይቀበሉትም። ኔታንያሁ አገራቸው በአልሺፋ ታጋቾች እንደነበሩ አለኝ ስለምትለው መረጃ ከመስጠት ተቆጥበዋል።