Related Video and Audio

VIDEO 1 MINUTE 44 SECONDSVIDEO 1 MINUTE 44 SECONDS1:44

Play video በሐማስ ጥቃት የሞቱ ወታደሮችን አስከሬን ለማግኘት እስራኤል እንዴት የንስር ወፍን ተጠቀመች? from BBCበሐማስ ጥቃት የሞቱ ወታደሮችን አስከሬን ለማግኘት እስራኤል እንዴት የንስር ወፍን ተጠቀመች?

Play video በሐማስ ጥቃት የሞቱ ወታደሮችን አስከሬን ለማግኘት እስራኤል እንዴት የንስር ወፍን ተጠቀመች? from BBC

VIDEO 1 MINUTE 18 SECONDSVIDEO 1 MINUTE 18 SECONDS1:18

Play video ሕይወት በጋዛ፡ “ጦርነቱ መቶ ዓመታትን ወደኋላ መልሶናል” from BBCሕይወት በጋዛ፡ “ጦርነቱ መቶ ዓመታትን ወደኋላ መልሶናል”

Play video ሕይወት በጋዛ፡ “ጦርነቱ መቶ ዓመታትን ወደኋላ መልሶናል” from BBC

VIDEO 2 MINUTES 31 SECONDSVIDEO 2 MINUTES 31 SECONDS2:31

Play video ‘ቢያንስ ሆስፒታሉ ጥቃት አይደርስበትም ብለን አስበን ነበር’፡ ከሆስፒታል የሸሹ የጋዛ ነዋሪዎች from BBC‘ቢያንስ ሆስፒታሉ ጥቃት አይደርስበትም ብለን አስበን ነበር’፡ ከሆስፒታል የሸሹ የጋዛ ነዋሪዎች

Play video ‘ቢያንስ ሆስፒታሉ ጥቃት አይደርስበትም ብለን አስበን ነበር’፡ ከሆስፒታል የሸሹ የጋዛ ነዋሪዎች from BBC

VIDEO 2 MINUTESVIDEO 2 MINUTES2:00

Play video ጋዛን የጎበኘው ቢቢሲ የዓለም አቀፍ ኤዲተር ጄረሚ ቦውን እይታ from BBCጋዛን የጎበኘው ቢቢሲ የዓለም አቀፍ ኤዲተር ጄረሚ ቦውን እይታ

Play video ጋዛን የጎበኘው ቢቢሲ የዓለም አቀፍ ኤዲተር ጄረሚ ቦውን እይታ from BBC

VIDEO 1 MINUTE 30 SECONDSVIDEO 1 MINUTE 30 SECONDS1:30

Play video አሜሪካ ከ60 በላይ አውሮፕላን ተሸካሚ ሁለተኛ መርከቧን ወደ እስራኤል አስጠጋች from BBCአሜሪካ ከ60 በላይ አውሮፕላን ተሸካሚ ሁለተኛ መርከቧን ወደ እስራኤል አስጠጋች

Play video አሜሪካ ከ60 በላይ አውሮፕላን ተሸካሚ ሁለተኛ መርከቧን ወደ እስራኤል አስጠጋች from BBC

VIDEO 1 MINUTE 48 SECONDSVIDEO 1 MINUTE 48 SECONDS1:48

Play video ሐማስ ጋዛ ውስጥ የገነባቸው ወደ እስራኤል የሚያሻግሩት ዋሻዎች from BBCሐማስ ጋዛ ውስጥ የገነባቸው ወደ እስራኤል የሚያሻግሩት ዋሻዎች

Play video ሐማስ ጋዛ ውስጥ የገነባቸው ወደ እስራኤል የሚያሻግሩት ዋሻዎች from BBC

VIDEO 3 MINUTES 27 SECONDSVIDEO 3 MINUTES 27 SECONDS3:27

Play video ሕይወት በጋዛ፡ ከቤታቸው ወጥተው መጠለያ ፍለጋ መንከራተት from BBCሕይወት በጋዛ፡ ከቤታቸው ወጥተው መጠለያ ፍለጋ መንከራተት

Play video ሕይወት በጋዛ፡ ከቤታቸው ወጥተው መጠለያ ፍለጋ መንከራተት from BBC

ጭምቅ ሃሳብ

  1. በጋዛ የተገደሉ ፍልስጤማውያን ቁጥር 13 ሺህ ደረሰ- የጋዛ ጤና ሚኒስቴር
  2. የኳታር ጠቅላይ ሚኒስትር ታጋቾችን የማስለቀቅ ስምምነት ላይ ‘መተማመን መጨመሩን’ ተናገሩ
  3. እስራኤል ተመድ ባቋቋመው የትምህርት ቤት መጠለያ ባደረሰችው ጥቃት በርካቶች መገደላቸው ተነገረ

ቀጥታ ዘገባ

  1. የታተመዉ 4:474:47የእስራኤል ታንኮች በሰሜናዊ ጋዛ ወደሚገኘው ሆስፒታል ገቡየእስራኤል ታንኮች በሰሜን ጋዛ ወደሚገኘው የኢንዶኔዥያ ሆስፒታል ገቡ።እስራኤል ዛሬ ማለዳ በሆስፒታል ባደረሰችው ጥቃት ወደ 12 የሚጠጉ ሰዎች መገደላቸውም ተዘግቧል።ከጥቂት ሰዓታት በፊት የሆስፒታሉ ዳይሬክተር ዶ/ር ማርዋን አል ሱልጣን ለቢቢሲ እንደተናገሩት የእስራኤል ጦር ከሆስፒታሉ ህንጻ 20 ሜትሮች ያህል ርቀት ነበረው።በአካባቢው ከፍተኛ የተኩስ ድምጽ ይሰማ እንደነበር እና የቀዶ ጥገና ማገገሚያ ክፍል መመታቱን ተናግረው ነበር።የእስራኤል ጦር በቅርቡ በሰጠው መግለጫ በሆስፒታሉ ላይ ስላለው ነገር ምንም አላለም። “የእስራኤል መከላከያ ወታደሮች በጋዛ ሰርጥ የሚያደርጉትን ዘመቻ ቀጥለዋል። አውሮፕላኖቻችን አሸባሪዎች ላይ፣ አሸባሪዎች መሰረተ ልማት ላይ እንዲሁም የጦር መሳሪያዎቻችን እና ወታደራዊ ቁሳቁሶችን በማፈላለግ ስራቸውን ቀጥለዋል” ብሏል።የሐማስ ሶስት አዛዦችም ተገድለዋል ተብሏል። የሆስፒታሉ ዳይሬክተር እስራኤል ባደረሰችው የአየር ጥቃት ቢያንስ 10 ሰዎች መገደላቸውን ገልጸዋል። የጋዛ የጤና ሚኒስቴር በበኩሉ 12 ሰዎች መገደላቸውን ተናግሯል። የሚኒስቴሩ ቃለ አቀባይ አሽራፍ አል ቁድራ ለአጃንስ ፍራንስ ፕሬስ የዜና ወኪል ከተገደሉት በተጨማሪም በርካቶች ቆስለዋል ብለዋል።Article share tools
  2. የታተመዉ 3:433:43ቻይና ከአረብ አገራት ሚኒስትሮች ጋር ተወያየችየውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዋንግ ዩReutersCopyright: Reutersቻይና ከአረብ አገራት ጋር ባደረገችው ውይይት የሁለት አገራት፣ የፍልስጤምና የእስራኤል መንግሥት ምስረታን እንደምትደግፍ አስታወቀች።ቻይና ይህንን ያስታወቀችው ከአረብ እና ሙስሊም አገራት የተወጣጡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ልዑካን በቻይና መደበኛ ጉብኝት እያደረጉ ባለበት ወቅት ነው።ሳዑዲ አረቢያ፣ ዮርዳኖስ፣ ግብጽ፣ ኢንዶኔዥያ እና ከፍልስጤም አስተዳደር እና የእስልምና ትብብር ድርጅት መሪን ያካተተ ልዑካን በቻይና ይገኛሉ።ጉብኝቱ ቻይና በጋዛ ያለውን ጦርነት ለማርገብ፣ ሰላማዊ ዜጎችን ለመጠበቅ እና የፍልስጤም ጥያቄ ፍትሃዊ በሆነ መንገድ የሚፈታበትን ሁኔታም ላይ ለመምከርም እንደሆነ የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዋንግ ዩ በቅርቡ በሪያድ በተካሄደው የአረብ እና ሙስሊም አገራት መሪዎች ጉባዔ ላይ የቀረበውን ጥሪ በመደገፍ አገራቸው የሁለት አገራት ምስረታን እንደ መፍትሄ እንደምታየው ተናግረዋል።አለም አቀፉ ማህበረሰብ ‘በአፋጣኝ እርምጃ መውሰድ እንዳለበት እና የሰብዓዊ ጥፋቱም እንዲያከትም ውጤታማ እርምጃዎች መውሰድ አለበት’ ሲሉም ተደምጠዋል።ሚኒስትሩ በመክፈቻ ንግግራቸውም ” በጋዛ ያለውን ጦርነት ለማርገብ እና የመካከለኛውን ምስራቅ ሰላምንም በተቻለ ፍጥነት ለመመለስ በጋራ እንስራ” ሲሉም ለሚኒስትሮቹ ተናግረዋል።ቻይና በጋዛ የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲደረግ በቀዳሚነት ጥሪ ካቀረቡ አገራት መካከል ስትሆን ቀደም ሲልም ውይይትን ለማበረታት እና ሰላምንም ለማስፈን አስፈላጊውን ሁሉ ለማድረግ ፈቃደኛ መሆኗንም ስትናገር ቆይታለች።Article share tools
  3. የታተመዉ 2:192:19ሰባተኛ ሳምንቱን በያዘው የጋዛ ጦርነት የተከሰቱ የቅርብ ጉዳዮችየጋዛ ጦርነትReutersCopyright: Reuters
    • 31 ያለጊዜያቸው የተወለዱ ጨቅላዎች ከአልሺፋ ሆስፒታል እሁድ ዕለት እንዲወጡ ተደርገው በደቡባዊ ራፋህ ከተማ ወደሚገኘው ኤምሬትስ ሆስፒታል ተወስደዋል።
    • የዓለም ጤና ድርጅት ኃላፊ ዶክተር ቴድሮስ አድኃኖም ገብረእየሱስ ጨቅላዎቹ “በጣም እንደታመሙ” እና በጣም በአስቸጋሪ እና በከፋ የጸጥታ ሁኔታ ውስጥ መወሰዳቸውንም ነው የተናገሩት።
    • በአልሺፋ ሆስፒታል የቀሩ ህሙማንን እና ሰራተኞችን ሙሉ በሙሉ ለማስወጣት የያዘውንም እቅድ በማጠናቀቅ ላይ መሆኑንም የዓለም ጤና ድርጅት አስታውቋል። ይህም በርካታ ቀናትን እንደሚፈጅ አስታውቆ በመጀመሪያውም የኩላሊት እጥበት እየተደረገላቸው ያሉ እና የአከርካሪ አጥንት ጉዳት ያለባቸውንም ማዛወር ይሆናል።
    • የእስራኤል ጦር በአልሺፋ ሆስፒታል ስር ’55 ሜትር እርዝመት ያለው የሽብር ዋሻ” ያሳያል ያለችውን ቪዲዮ ለቋል። ጦሩ አግኜቻዋለሁ ያለውም ዋሻ በሆስፒታሉ ግቢ ውስጥ የሚገኙ በርካታ ህንጻዎች ሐማስ “ለሽብር ተግባር ሽፋንንት እንደሚጠቀምባቸው ያረጋግጣል” ብሏል። ሐማስም ሆነ የሆስፒታሉ ባለሙያዎች ይህንን ክስ አይቀበሉትም።
    • የእስራኤል መከላከያ ኃይል ሐማስ መስከረም 26 ካደረሰው ጥቃት በኋላ የወሰዳቸው ታጋቾች ወደ ጋዛ ትልቁ ሆስፒታል መወሰዳቸውን የሚያሳይ ነው ያለውን ከስፍራው የተቀረጸ ቪዲዮ (ሲሲቲቪ) አሳይቷል።
    • በኢራን የሚደገፉት የየመን ሁቲ አማጽያን የእስራኤልን የጭነት መርከብ በቀይ ባህር መያዛቸውን ያስታወቁ ሲሆን የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ “ሌላ የኢራን የሽብር ተግባር” ሲሉ ጠርተውታል። እስራኤል በጋዛ ላይ የምታደርሰውን የአየር ጥቃት ተከትሎ የሁቲ አማጽያን ወደ እስራኤል በርካታ ሚሳኤሎችን እና ድሮኖችን አስወንጭፈዋል።
    Article share tools
  4. የታተመዉ 0:280:28ታጋቾች ወደ ጋዛ ሆስፒታል መወሰዳቸውን ከስፍራው የተገኘ ቪዲዮ ማሳየቱን እስራኤል አስታወቀችሐማስ መስከረም 26 ካደረሰው ጥቃት በኋላ የወሰዳቸው ታጋቾች ወደ ጋዛ ትልቁ ሆስፒታል መወሰዳቸውን የሚያሳይ ነው ያለችውን ከስፍራው የተቀረጸ ቪዲዮ (ሲሲቲቪ) የመከላከያ ሰራዊቱ አሳይቷል። ከታጋቾቹ አንዷ የሆነችውም ወታደር በሆስፒታሉ መገደሏን የእስራኤል መከላከያ ሰራዊት ቃለ አቀባይ ተናግረዋል። የ19 ዓመቷ ኖአ ማርሲያኖ የተገደለችው ቀላል ጉዳት ደርሶባት ወደ አል-ሺፋ ሆስፒታል ከተወሰደች በኋላ ነው ሲሉ ተናግረዋል።ተጨማሪ ያንብቡArticle share tools
  5. የታተመዉ 0:070:07ተመድ በጋዛ ያሉ ትምህርት ቤቶቹ ላይ የደረሰው ጥቃት በከፍተኛ ሁኔታ አስደንግጦኛል አለየተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሓፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝReutersCopyright: Reutersየተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሓፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ በጋዛ ሰርጥ 24 ሰዓት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ሁለት የመንግሥታቱ ድርጅት ትምህርት ቤቶች ላይ ጥቃት መፈጸሙ ‘በከፍተኛ ሁኔታ እንዳስደነገጣቸው’ ተናገሩ።”በርካቶች፣ አብዛኛዎቹ ህጻናት እና ሴቶች ተገድለዋል። በተባበሩት መንግሥታት ግቢ ውስጥ ደህንነትን ሽተው የተጠለሉ ነበሩ” ሲሉም ጉቴሬዝ በመግለጫቸው አክለዋል።”ተጠናክሮ በቀጠለው ውጊያ ምክንያት በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ፍልስጤማውያን በተባበሩት መንግሥታት ማዕከላት ተጠልለው ይገኛሉ። ግቢያችን መጣስ እንደማይገባው በድጋሚ አረጋግጣለሁ” ሲሉም ተናግረዋል።ጦርነቱ አስከፊ መሆኑን የገለጹት ዋና ጸሓፊው የሰላማዊ ሰዎች ግድያም ከፍተኛ መሆኑን ተከትሎም “ተቀባይነት የሌለው” ሲሉ ገልጸውታል። አፋጣኝ የሆነ ሰብዓዊ የተኩስ አቁምም እንዲደረግም ጥሪያቸውን አቅርበዋል።Article share tools
  6. የታተመዉ 23:51 19 ህዳር 202323:51 19 ህዳር 2023በጋዛ የተገደሉ ፍልስጤማውያን ቁጥር 13 ሺህ ደረሰ- የጋዛ ጤና ሚኒስቴርበጋዛ የተገደሉ ፍልስጤማውያንGetty ImagesCopyright: Getty Imagesሰባተኛ ሳምንቱን በያዘው የጋዛው ጦርነት በእስራኤል የተቀናጁ ጥቃቶች የተገደሉ ፍልስጤማውያን ቁጥር 13 ሺህ መድረሱን የጋዛ ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።ከነዚህም ውስጥ 70 በመቶዎቹ ህጻናት እና ሴቶች መሆናቸውን የተባበሩት መንግሥታት እንዲሁም በሐማስ አስተዳደር ስር ያለው ሚኒስቴሩ ገልጿል።ሐማስ መስከረም መጨረሻ ላይ ባደረሰው ጥቃት 1 ሺህ 200 ሰዎች ሲገደሉ፤ 200 ታጋቾች ተወስደዋል።እስራኤል ምላሽ ነው ባለችው የማያባራ ጥቃት እየፈጸመች ሲሆን የጋዛ ሰርጥንም በሙሉ ከበባ ውስጥ አስገብታታለች። መብራት፣ ውሃ እና መሰረታዊ አገልግሎቶች ተቋርጠዋል።