Related Video and Audio

VIDEO 1 MINUTE 44 SECONDSVIDEO 1 MINUTE 44 SECONDS1:44
Play video በሐማስ ጥቃት የሞቱ ወታደሮችን አስከሬን ለማግኘት እስራኤል እንዴት የንስር ወፍን ተጠቀመች? from BBCበሐማስ ጥቃት የሞቱ ወታደሮችን አስከሬን ለማግኘት እስራኤል እንዴት የንስር ወፍን ተጠቀመች?
- BBC
Play video በሐማስ ጥቃት የሞቱ ወታደሮችን አስከሬን ለማግኘት እስራኤል እንዴት የንስር ወፍን ተጠቀመች? from BBC

VIDEO 1 MINUTE 18 SECONDSVIDEO 1 MINUTE 18 SECONDS1:18
Play video ሕይወት በጋዛ፡ “ጦርነቱ መቶ ዓመታትን ወደኋላ መልሶናል” from BBCሕይወት በጋዛ፡ “ጦርነቱ መቶ ዓመታትን ወደኋላ መልሶናል”
- BBC
Play video ሕይወት በጋዛ፡ “ጦርነቱ መቶ ዓመታትን ወደኋላ መልሶናል” from BBC

VIDEO 2 MINUTES 31 SECONDSVIDEO 2 MINUTES 31 SECONDS2:31
Play video ‘ቢያንስ ሆስፒታሉ ጥቃት አይደርስበትም ብለን አስበን ነበር’፡ ከሆስፒታል የሸሹ የጋዛ ነዋሪዎች from BBC‘ቢያንስ ሆስፒታሉ ጥቃት አይደርስበትም ብለን አስበን ነበር’፡ ከሆስፒታል የሸሹ የጋዛ ነዋሪዎች
- BBC
Play video ‘ቢያንስ ሆስፒታሉ ጥቃት አይደርስበትም ብለን አስበን ነበር’፡ ከሆስፒታል የሸሹ የጋዛ ነዋሪዎች from BBC

VIDEO 2 MINUTESVIDEO 2 MINUTES2:00
Play video ጋዛን የጎበኘው ቢቢሲ የዓለም አቀፍ ኤዲተር ጄረሚ ቦውን እይታ from BBCጋዛን የጎበኘው ቢቢሲ የዓለም አቀፍ ኤዲተር ጄረሚ ቦውን እይታ
- BBC
Play video ጋዛን የጎበኘው ቢቢሲ የዓለም አቀፍ ኤዲተር ጄረሚ ቦውን እይታ from BBC

VIDEO 1 MINUTE 30 SECONDSVIDEO 1 MINUTE 30 SECONDS1:30
Play video አሜሪካ ከ60 በላይ አውሮፕላን ተሸካሚ ሁለተኛ መርከቧን ወደ እስራኤል አስጠጋች from BBCአሜሪካ ከ60 በላይ አውሮፕላን ተሸካሚ ሁለተኛ መርከቧን ወደ እስራኤል አስጠጋች
- BBC
Play video አሜሪካ ከ60 በላይ አውሮፕላን ተሸካሚ ሁለተኛ መርከቧን ወደ እስራኤል አስጠጋች from BBC

VIDEO 1 MINUTE 48 SECONDSVIDEO 1 MINUTE 48 SECONDS1:48
Play video ሐማስ ጋዛ ውስጥ የገነባቸው ወደ እስራኤል የሚያሻግሩት ዋሻዎች from BBCሐማስ ጋዛ ውስጥ የገነባቸው ወደ እስራኤል የሚያሻግሩት ዋሻዎች
- BBC
Play video ሐማስ ጋዛ ውስጥ የገነባቸው ወደ እስራኤል የሚያሻግሩት ዋሻዎች from BBC

VIDEO 3 MINUTES 27 SECONDSVIDEO 3 MINUTES 27 SECONDS3:27
Play video ሕይወት በጋዛ፡ ከቤታቸው ወጥተው መጠለያ ፍለጋ መንከራተት from BBCሕይወት በጋዛ፡ ከቤታቸው ወጥተው መጠለያ ፍለጋ መንከራተት
- BBC
Play video ሕይወት በጋዛ፡ ከቤታቸው ወጥተው መጠለያ ፍለጋ መንከራተት from BBC
ጭምቅ ሃሳብ
- ሐማስ እና እስራኤል ‘ጊዜያዊ የተኩስ አቁም’ ለማድረግ ወደ ስምምነት ተቃርበዋል ተባለ
- ዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት ኔታንያሁ ላይ የእስር ትዕዛዝ እንዲያወጣ ደቡብ አፍሪካ ጠየቀች
- በጋዛ የተገደሉ ፍልስጤማውያን ቁጥር 13 ሺህ ደረሰ- የጋዛ ጤና ሚኒስቴር
- የኳታር ጠቅላይ ሚኒስትር ታጋቾችን የማስለቀቅ ስምምነት ላይ ‘መተማመን መጨመሩን’ ተናገሩ
- የጃፓን ዕቃ ጫኝ መርከብ ቀይ ባሕር ላይ በየመን ሁቲ አማጺያን ታገተ
- እስራኤል ተመድ ባቋቋመው የትምህርት ቤት መጠለያ ባደረሰችው ጥቃት በርካቶች መገደላቸው ተነገረ
ቀጥታ ዘገባ
- የታተመዉ 8:408:40በሐማስ የታገቱትን ነጻ የማውጣት ድርድር ከጫፍ ድርሷል – የኳታር አደራዳሪ
AFPCopyright: AFPሐማስ በእስራኤል ላይ ድንገተኛ ጥቃት አድርሶ ያገታቸውን ሰዎች ለማስለቀቅ እየተደረገ ያለው ድርድር በስምምነት ሊቋጭ ከጫፍ መድረሱን የኳታር አደራዳሪ ገለጹ።የኳታር የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማጂድ አል-አንሳሪ ከስምምነት ለመድረስ ከጫፍ ደርሰናል ብለዋል።ኳታር ሐማስ የያዛቸውን ታጋቾች እንዲለቅ፤ እስራኤልም እየተጠየቀች ላለችው የተኩስ አቁም ስምምነት አዎንታዊ ምላሽ እንድትሰጥ እስራኤል እና ሐማስን ስታደራድር ቆይታለች።ቃል አቀባዩ “. . . ስምምነት ላይ ለመድረስ ተቃርበናል” ያሉ ሲሆን ድርድሩ አሁን ያለበትን ድረጃ “ወሳኝ እና የመጨረሻው” ላይ ነው ሲሉ ገልጸውታል።ኳታር በጠላትንት የሚተያዩት የእስራኤል እና የሐማስ ‘ወዳጅ’ እንዲሁም በሁለቱ ወገኖች እምነት የሚጣልባት አገር ሆና ብቅ ብላለች።ለመሆኑ ኳታር ምዕራባውያን አሸባሪ ያሉትን ሐማስ ለምን አስጠለለች? ማደራደሩስ ይሳካላታል? ዝርዝሩን እዚህ ያንብቡ ኳታር ምዕራባውያን አሸባሪ ያሉትን ሐማስ ለምን አስጠለለች? ማደራደሩስ ይሳካላታል?Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 8:228:22ሐማስ የእስራኤል የአየር ጥቃት መቆም የስምምነት አካል እንዲሆን ፍላጎት አለው ተባለ
ReutersCopyright: Reutersየእስራኤል መገናኛ ብዙኃን በእስራኤል እና በሐማስ መካከል እየተደረገ ባለው ተኩስ የማቆም ንግግር ውስጥ እስራኤል በጋዛ የአየር ክልል ላይ መብረሯን እንድታቆም ሐማስ መጠየቁን ዘገቡ።ዋላ የተሰኘ መገናኛ ብዙኃን በጋዛ የሚገኙት የሐማስ መሪ ያህያ ሲንዋር እስራኤል በጋዛ የአየር ክልል ላይ ሙሉ በሙሉ በረራዋን እንድታቆም ጠይቀዋል ያለ ሲሆን፣ ያኔት የተባለ የዜና ድረ-ገጽ ደግሞ እስራኤል በሰሜን ጋዛ ላይ ብቻ በቀን ለስድስት ሰዓታት ለመብረር እንድትስማማ ሐማስ ጥረት እያደረገ ነው ሲል ዘግቧል።እስራኤል በጋዛ ላይ በምድር፣ በአየር እና በባሕር ጥቃቶች እየፈጸመች ሁለት ወራት ሊሞላት የተቃረበች ሲሆን፣ አስካሁን ጋዛ ውስጥ ከፍተኛ ውድመት እያደረሰ ያለው የአገሪቱ አየር ኃይል ጥቃት ነው።እስራኤል ከተዋጊ አውሮፕላኖች በተጨማሪ በውል የማይታቁ የስለላ እና ጥቃት አድራሽ ሰው አልባ አውሮፕላኖችን (ድሮኖች) በጋዛ አሰማርታ ቆይታለች።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 8:148:14እስራኤል በደቡብ አፍሪካ ያሉትን አምባሳደሯን ‘ለምክክር’ ጠራችእስራኤል በጋዛ ላይ እያካሄድ ባለው ወታደራዊ ዘመቻ ላይ ጠንካራ ተቃውሞዋን እያሰማች ባለችው ደቡብ አፍሪካ የሚገኙ አምባሳደሯን መጥራቷን የአገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።ተጨማሪ ያንብቡArticle share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 5:535:53በሐማስ እና እስራኤል መካከል ይደረሳል የተባለው የጊዜያዊ ተኩስ አቁም ስምምነት ምንን ይዟል?
EPA-EFE/REX/ShutterstockCopyright: EPA-EFE/REX/Shutterstockየሐማስ መሪ ከእስራኤል ጋር ጊዜያዊ የተኩስ አቁም ለማድረግ ወደ ስምምነት መቃረቡን ባወጡት መግለጫ አስታውቀዋል።እስራኤል በጉዳዩ ላይ የሰጠችው አስተያየት የለም። እንደ አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ጊዜያዊ የተኩስ አቁም ስምምነቱ የሚከተሉትን ሊያካትት ይችላል።
- ኢስማኢል ሃኒዬ ጊዜያዊ የተኩስ አቁሙ ምን ያህል ጊዜ እንደሚቆይ አልተናገሩም ነገር ግን እየተካሄደ ያለው ድርድር ጊዜያዊ የተኩስ አቁሙ ለምን ያህል ጊዜ እንደሚቆይ፣ እርዳታ ወደ ጋዛ ለማድረስ እና ታጋቾችን በፍልስጤማዊ እስረኞች መለዋወጥ ላይ ያተኮረ እንደሆነ ተናግረዋል። ሁለቱም አካላት ሴቶችን እና ህጻናትን ያካትታሉ ብሏል።
- የስምምነቱ ዝርዝር ሁኔታ በሃማስ እና በእስራኤል መካከል አሸማጋይ በነበረችው ኳታር ይፋ እንደሚሆንም ተናግረዋል።
- የእስራኤል ጦር በጋዛ ሰርጥ ያለውን ውጊያ ለአምስት ቀናት እንዲያቆም እንዲሁም በደቡባዊ ጋዛ ላይ የእስራኤል የአየር እንቅስቃሴን የሚገድብ።
- የፍልስጤም ቡድኖች ከ50-100 ታጋቾችን የሚለቁ ሲሆን እነዚህም የእስራኤል ሰላማዊ ዜጎች፣ የሌላ አገር ተወላጆች የሚሆኑ ሲሆን ነገር ግን ወታደሮች አይሆኑም።
- በምላሹም እስራኤል ሴቶች እና ህጻናትን ጨምሮ 300 ፍልስጤማውያንን ከእስር ቤቶቿ የምትለቅ ይሆናል። አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ስማቸው ያልጠቀሳቸውን የሐማስ፣ እስላማዊ ጂሃድ ባለስልጣናትን ዋቢ አድርጎም ድርጅቶቹ በስምምነቱ ሐሳብ መስማማታቸውን ዘግቧል።
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- የታተመዉ 4:084:08ሰባተኛ ሳምንቱን በያዘው የጋዛ ጦርነት አዳዲስ ክሰተቶች
Getty ImagesCopyright: Getty Images
- የሐማስ መሪ ከእስራኤል ጋር ጊዜያዊ የተኩስ አቁም ለማድረግ ወደ ስምምነት መቃረቡን ባወጡት መግለጫ አስታውቀዋል።
- ኢስማኢል ሃኒዬ ጊዜያዊ የተኩስ አቁሙ ምን ያህል ጊዜ እንደሚቆይ ባይናገሩም ነገር ግን ለአልጀዚራ እንደተናገሩት ድርድሩ ለምን ያህል ጊዜ እንደሚቆይ፣ እርዳታ ወደ ጋዛ ለማድረስ እና ታጋቾችን በፍልስጤማዊ እስረኞች መለዋወጥ ላይ ያተኮረ እንደሆነ ተናግረዋል።
- የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት ታጋቾችን ለመልቀቅ ሲደረግ የነበረው ውይይት ወደ ስምምነት መቃረቡን ነው።
- የቢቢሲ የመካከለኛው ምስራቅ ጋዜጠኛ ቶም ባትማን ታጋቾችን ደረጃ በደረጃ የሚለቁበትን ሁኔታ እንደሚመለከቱም ተናግሯል።
- እስራኤል በማዕከላዊ ጋዛ በሚገኘው ኑሴራት የስደተኞች ካምፕ ላይ ባደረሰችው የአየር ጥቃት ቢያንስ 17 ሰዎች መገደላቸውን የፍልስጤም የዜና ወኪል ዋፋ ዘግቧል። እስራኤል ጥቃቱን አስመልክቶ ያለችው ነገር የለም።
- የጦርነቱ ማዕከል የሆነው የጋዛው የኢንዶኔዥያ ሆስፒታል ዳይሬክተር ተኩስ እስከ ምሽቱ ድረስ ቀጥሏል ብለዋል።
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- የታተመዉ 1:351:35ዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት ኔታንያሁ ላይ የእስር ትዕዛዝ እንዲያወጣ ደቡብ አፍሪካ ጠየቀችዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት በጠቅላይ ሚንስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ላይ የእስር ትዕዛዝ እንዲያወጣ የደቡብ አፍሪካ መንግሥት ጠየቀ። እስራኤልን የጦር ወንጀል ፈጽሟል በማለት እየከሰሰች ያለችው ደቡብ አፍሪካ እስከ ታህሳስ አጋማሽ ድረስም ትዕዛዙ መውጣት አለበት ብላለች። የፕሬዝዳንቱ ጽህፈት ቤት ሚንስትር ኩምቡድዞ ሳቬኒ እንዳሉት ፍርድ ቤቱ ይህንን ማድረግ ካልቻለ የዓለምአቀፉ አስተዳደር “ጠቅላላ ውድቀት” ምልክት ይሆናል ብለዋል።ተጨማሪ ያንብቡArticle share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 23:54 20 ህዳር 202323:54 20 ህዳር 2023ሐማስ እና እስራኤል ‘ጊዜያዊ የተኩስ አቁም’ ለማድረግ ወደ ስምምነት ተቃርበዋል ተባለ
ReutersCopyright: Reutersሐማስ እና እስራኤል ውጊያውን በጊዜያዊነት ለማቆም እና ታጋቾች እንዲለቀቁ ለማመቻት ወደ ስምምነት እንደተቃረቡ ሪፖርቶች እየወጡ ይገኛሉ።በኳታር አሸማጋይነት መሰረት ሁለቱ ወገኖች ውይይት ሲያደርጉም ቆይተዋል።የሐማስ መሪ እስማኤል ሃኒዬህ እንዳሉት ድርጅታቸው ምላሹን “በኳታር ላሉት ወንድሞቻችን እና ለአሸማጋዮች ሰጥቷል። ውጊያውን ለማቆም ስምምነት ላይ ለማድረስ ተቃርበናል” ሲሉም መናገራቸውን የዜና ወኪሎች እና የፍልስጠም የዜና አውታሮች ዘግበዋል።እስራኤል በጉዳዩ ላይ የሰጠችው ምላሽ የለም።የአሜሪካ ከፍተኛ ባለስልጣንም በሐማስ የተወሰዱ ታጋቾችን ለማስለቀቅ እየተደረገ ያለው ውይይት ወደ ስምምነት መቃረቡን እንዲሁም በምላሹም ውጊያውም በጊዜያዊነት እንዲገታ ሊደረግ መሆኑምም ሰኞ እለት ገልጸው ነበር።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 9:27 20 ህዳር 20239:27 20 ህዳር 2023የጃፓን ዕቃ ጫኝ መርከብ ቀይ ባሕር ላይ በየመን ሁቲ አማጺያን ታገተበኢራን በሚደገፉት የየመን ሁቲ አማጺያን የእስራኤል ነው ያሉትን የጃፓን ግዙፍ የዕቃ ጫኝ መርከብ ቀይ ባሕር አገቱ።ተጨማሪ ያንብቡArticle share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 7:42 20 ህዳር 20237:42 20 ህዳር 2023በጋዛ ያለጊዜያቸው ከተወለዱ 31 ጨቅላ ሕጻናት 28ቱ ብቻ ለምን ወደ ግብፅ ተላኩ?
ReutersCopyright: Reutersበሰሜን ጋዛ ከሚገኘው አል ሺፋ ሆስፒታል እንዲወጡ ከተደረጉ 31 ያለጊዜያቸው የተወለዱ ጨቅላ ሕጻናት መካከል 28ቱ ብቻ ወደ ግብፅ ተላኩ።እነዚህ ጨቅላ ሕጻናት የእስራኤል ጦር ከተቆጣጠረው እና የሞት ቀጠና ከሆነው የጋዛ ትልቁ ሆስፒታል አል ሺፋ በሕይወት ተርፈው የወጡ ሲሆን፣ ወደ አል አህሊ ኤምሬትስ ሆስፒታል ተወስደው የነበሩ ናቸው።ከእነዚህ ሕጻናት መካከል አብዛኞቹ ለሕክምና ወደ ግብፅ የተላኩ ሲሆን፣ ጥቂቶቹ አሁንም ድረስ እዚያው ሆስፒታል ውስጥ ይገኛሉ።ይህ ለምን ሆነ ሲል ቢቢሲ በአል አህሊ ኤምሬትስ ሆስፒታል ውስጥ የጨቅላ ሕጻናት ክፍል ኃላፊ የሆኑትን ዶ/ር መሐመድ ሳላማን ጠይቋቸዋል።ዶ/ር መሐመድ የተወሰኑት የሕጻናቱ ወላጆች ልጆቻቸውን ለመለየት እሁድ ዕለት አል አህሊ ኤምሬትስ ሆስፒታል መድረሳቸውን ገልጸው፣ ልጆቻቸው ለሕክምና ወደ ግብፅ እንዲሄዱ የፈቃድ ፎርም እንዲሞሉ እንደጠየቋቸው እና ፈቃድ ያገኙትን መላካቸውን ተናግረዋል።“አሁን ላይ ማንነቱ ያልተለየ እና ወላጆቹ ያልታወቁ አንድ ሕጻን ይገኛል። ይህ ሕጻን አሁንም ከእኛ ጋር ነው ያለው ። ሕጻኑ በጥሩ የጤንነት ሁኔታ ላይ ስለሚገኝ እና ለሕክምና ወደ ሌላ ቦታ መሄድ ስለማያስፈልገው በጋዛ ጤና ሚኒስቴር ውሳኔ እዚህ እንዲቆይ ተደርጓል” ብለዋል።ሁለት ሌሎች ሕጻናት ደግሞ ወላጆቻቸው በግል ጉዳይ ምክንያት ለመላክ ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ሳይላኩ የቀሩ መሆናቸውን ገልጸዋል።ዶክተር ሳላማ እንዳሉት ሦስቱም ሕጻናት በጥሩ ሁኔታ ላይ ይገኛሉ።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 4:47 20 ህዳር 20234:47 20 ህዳር 2023የእስራኤል ታንኮች በሰሜናዊ ጋዛ ወደሚገኘው ሆስፒታል ገቡየእስራኤል ታንኮች በሰሜን ጋዛ ወደሚገኘው የኢንዶኔዥያ ሆስፒታል ገቡ።እስራኤል ዛሬ ማለዳ በሆስፒታል ባደረሰችው ጥቃት ወደ 12 የሚጠጉ ሰዎች መገደላቸውም ተዘግቧል።ከጥቂት ሰዓታት በፊት የሆስፒታሉ ዳይሬክተር ዶ/ር ማርዋን አል ሱልጣን ለቢቢሲ እንደተናገሩት የእስራኤል ጦር ከሆስፒታሉ ህንጻ 20 ሜትሮች ያህል ርቀት ነበረው።በአካባቢው ከፍተኛ የተኩስ ድምጽ ይሰማ እንደነበር እና የቀዶ ጥገና ማገገሚያ ክፍል መመታቱን ተናግረው ነበር።የእስራኤል ጦር በቅርቡ በሰጠው መግለጫ በሆስፒታሉ ላይ ስላለው ነገር ምንም አላለም። “የእስራኤል መከላከያ ወታደሮች በጋዛ ሰርጥ የሚያደርጉትን ዘመቻ ቀጥለዋል። አውሮፕላኖቻችን አሸባሪዎች ላይ፣ አሸባሪዎች መሰረተ ልማት ላይ እንዲሁም የጦር መሳሪያዎቻችን እና ወታደራዊ ቁሳቁሶችን በማፈላለግ ስራቸውን ቀጥለዋል” ብሏል።የሐማስ ሶስት አዛዦችም ተገድለዋል ተብሏል። የሆስፒታሉ ዳይሬክተር እስራኤል ባደረሰችው የአየር ጥቃት ቢያንስ 10 ሰዎች መገደላቸውን ገልጸዋል።ጋዛ የጤና ሚኒስቴር በበኩሉ 12 ሰዎች መገደላቸውን ተናግሯል። የሚኒስቴሩ ቃለ አቀባይ አሽራፍ አል ቁድራ ለአጃንስ ፍራንስ ፕሬስ የዜና ወኪል ከተገደሉት በተጨማሪም በርካቶች ቆስለዋል ብለዋል።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 3:43 20 ህዳር 20233:43 20 ህዳር 2023ቻይና ከአረብ አገራት ሚኒስትሮች ጋር ተወያየች
ReutersCopyright: Reutersቻይና ከአረብ አገራት ጋር ባደረገችው ውይይት የሁለት አገራት፣ የፍልስጤምና የእስራኤል መንግሥት ምስረታን እንደምትደግፍ አስታወቀች።ቻይና ይህንን ያስታወቀችው ከአረብ እና ሙስሊም አገራት የተወጣጡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ልዑካን በቻይና መደበኛ ጉብኝት እያደረጉ ባለበት ወቅት ነው።ሳዑዲ አረቢያ፣ ዮርዳኖስ፣ ግብጽ፣ ኢንዶኔዥያ እና ከፍልስጤም አስተዳደር እና የእስልምና ትብብር ድርጅት መሪን ያካተተ ልዑካን በቻይና ይገኛሉ።ጉብኝቱ ቻይና በጋዛ ያለውን ጦርነት ለማርገብ፣ ሰላማዊ ዜጎችን ለመጠበቅ እና የፍልስጤም ጥያቄ ፍትሃዊ በሆነ መንገድ የሚፈታበትን ሁኔታም ላይ ለመምከርም እንደሆነ የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዋንግ ዩ በቅርቡ በሪያድ በተካሄደው የአረብ እና ሙስሊም አገራት መሪዎች ጉባዔ ላይ የቀረበውን ጥሪ በመደገፍ አገራቸው የሁለት አገራት ምስረታን እንደ መፍትሄ እንደምታየው ተናግረዋል።አለም አቀፉ ማህበረሰብ ‘በአፋጣኝ እርምጃ መውሰድ እንዳለበት እና የሰብዓዊ ጥፋቱም እንዲያከትም ውጤታማ እርምጃዎች መውሰድ አለበት’ ሲሉም ተደምጠዋል።ሚኒስትሩ በመክፈቻ ንግግራቸውም ” በጋዛ ያለውን ጦርነት ለማርገብ እና የመካከለኛውን ምስራቅ ሰላምንም በተቻለ ፍጥነት ለመመለስ በጋራ እንስራ” ሲሉም ለሚኒስትሮቹ ተናግረዋል።ቻይና በጋዛ የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲደረግ በቀዳሚነት ጥሪ ካቀረቡ አገራት መካከል ስትሆን ቀደም ሲልም ውይይትን ለማበረታት እና ሰላምንም ለማስፈን አስፈላጊውን ሁሉ ለማድረግ ፈቃደኛ መሆኗንም ስትናገር ቆይታለች።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 2:19 20 ህዳር 20232:19 20 ህዳር 2023ሰባተኛ ሳምንቱን በያዘው የጋዛ ጦርነት የተከሰቱ የቅርብ ጉዳዮች
ReutersCopyright: Reuters
- 31 ያለጊዜያቸው የተወለዱ ጨቅላዎች ከአልሺፋ ሆስፒታል እሁድ ዕለት እንዲወጡ ተደርገው በደቡባዊ ራፋህ ከተማ ወደሚገኘው ኤምሬትስ ሆስፒታል ተወስደዋል።
- የዓለም ጤና ድርጅት ኃላፊ ዶክተር ቴድሮስ አድኃኖም ገብረእየሱስ ጨቅላዎቹ “በጣም እንደታመሙ” እና በጣም በአስቸጋሪ እና በከፋ የጸጥታ ሁኔታ ውስጥ መወሰዳቸውንም ነው የተናገሩት።
- በአልሺፋ ሆስፒታል የቀሩ ህሙማንን እና ሰራተኞችን ሙሉ በሙሉ ለማስወጣት የያዘውንም እቅድ በማጠናቀቅ ላይ መሆኑንም የዓለም ጤና ድርጅት አስታውቋል። ይህም በርካታ ቀናትን እንደሚፈጅ አስታውቆ በመጀመሪያውም የኩላሊት እጥበት እየተደረገላቸው ያሉ እና የአከርካሪ አጥንት ጉዳት ያለባቸውንም ማዛወር ይሆናል።
- የእስራኤል ጦር በአልሺፋ ሆስፒታል ስር ’55 ሜትር እርዝመት ያለው የሽብር ዋሻ” ያሳያል ያለችውን ቪዲዮ ለቋል። ጦሩ አግኜቻዋለሁ ያለውም ዋሻ በሆስፒታሉ ግቢ ውስጥ የሚገኙ በርካታ ህንጻዎች ሐማስ “ለሽብር ተግባር ሽፋንንት እንደሚጠቀምባቸው ያረጋግጣል” ብሏል። ሐማስም ሆነ የሆስፒታሉ ባለሙያዎች ይህንን ክስ አይቀበሉትም።
- የእስራኤል መከላከያ ኃይል ሐማስ መስከረም 26 ካደረሰው ጥቃት በኋላ የወሰዳቸው ታጋቾች ወደ ጋዛ ትልቁ ሆስፒታል መወሰዳቸውን የሚያሳይ ነው ያለውን ከስፍራው የተቀረጸ ቪዲዮ (ሲሲቲቪ) አሳይቷል።
- በኢራን የሚደገፉት የየመን ሁቲ አማጽያን የእስራኤልን የጭነት መርከብ በቀይ ባህር መያዛቸውን ያስታወቁ ሲሆን የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ “ሌላ የኢራን የሽብር ተግባር” ሲሉ ጠርተውታል። እስራኤል በጋዛ ላይ የምታደርሰውን የአየር ጥቃት ተከትሎ የሁቲ አማጽያን ወደ እስራኤል በርካታ ሚሳኤሎችን እና ድሮኖችን አስወንጭፈዋል።
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- የታተመዉ 0:28 20 ህዳር 20230:28 20 ህዳር 2023ታጋቾች ወደ ጋዛ ሆስፒታል መወሰዳቸውን ከስፍራው የተገኘ ቪዲዮ ማሳየቱን እስራኤል አስታወቀችሐማስ መስከረም 26 ካደረሰው ጥቃት በኋላ የወሰዳቸው ታጋቾች ወደ ጋዛ ትልቁ ሆስፒታል መወሰዳቸውን የሚያሳይ ነው ያለችውን ከስፍራው የተቀረጸ ቪዲዮ (ሲሲቲቪ) የመከላከያ ሰራዊቱ አሳይቷል። ከታጋቾቹ አንዷ የሆነችውም ወታደር በሆስፒታሉ መገደሏን የእስራኤል መከላከያ ሰራዊት ቃለ አቀባይ ተናግረዋል። የ19 ዓመቷ ኖአ ማርሲያኖ የተገደለችው ቀላል ጉዳት ደርሶባት ወደ አል-ሺፋ ሆስፒታል ከተወሰደች በኋላ ነው ሲሉ ተናግረዋል።ተጨማሪ ያንብቡArticle share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 0:07 20 ህዳር 20230:07 20 ህዳር 2023ተመድ በጋዛ ያሉ ትምህርት ቤቶቹ ላይ የደረሰው ጥቃት በከፍተኛ ሁኔታ አስደንግጦኛል አለ
ReutersCopyright: Reutersየተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሓፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ በጋዛ ሰርጥ 24 ሰዓት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ሁለት የመንግሥታቱ ድርጅት ትምህርት ቤቶች ላይ ጥቃት መፈጸሙ ‘በከፍተኛ ሁኔታ እንዳስደነገጣቸው’ ተናገሩ።”በርካቶች፣ አብዛኛዎቹ ህጻናት እና ሴቶች ተገድለዋል። በተባበሩት መንግሥታት ግቢ ውስጥ ደህንነትን ሽተው የተጠለሉ ነበሩ” ሲሉም ጉቴሬዝ በመግለጫቸው አክለዋል።”ተጠናክሮ በቀጠለው ውጊያ ምክንያት በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ፍልስጤማውያን በተባበሩት መንግሥታት ማዕከላት ተጠልለው ይገኛሉ። ግቢያችን መጣስ እንደማይገባው በድጋሚ አረጋግጣለሁ” ሲሉም ተናግረዋል።ጦርነቱ አስከፊ መሆኑን የገለጹት ዋና ጸሓፊው የሰላማዊ ሰዎች ግድያም ከፍተኛ መሆኑን ተከትሎም “ተቀባይነት የሌለው” ሲሉ ገልጸውታል። አፋጣኝ የሆነ ሰብዓዊ የተኩስ አቁምም እንዲደረግም ጥሪያቸውን አቅርበዋል።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 23:51 19 ህዳር 202323:51 19 ህዳር 2023በጋዛ የተገደሉ ፍልስጤማውያን ቁጥር 13 ሺህ ደረሰ- የጋዛ ጤና ሚኒስቴር
Getty ImagesCopyright: Getty Imagesሰባተኛ ሳምንቱን በያዘው የጋዛው ጦርነት በእስራኤል የተቀናጁ ጥቃቶች የተገደሉ ፍልስጤማውያን ቁጥር 13 ሺህ መድረሱን የጋዛ ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።ከነዚህም ውስጥ 70 በመቶዎቹ ህጻናት እና ሴቶች መሆናቸውን የተባበሩት መንግሥታት እንዲሁም በሐማስ አስተዳደር ስር ያለው ሚኒስቴሩ ገልጿል።ሐማስ መስከረም መጨረሻ ላይ ባደረሰው ጥቃት 1 ሺህ 200 ሰዎች ሲገደሉ፤ 200 ታጋቾች ተወስደዋል።እስራኤል ምላሽ ነው ባለችው የማያባራ ጥቃት እየፈጸመች ሲሆን የጋዛ ሰርጥንም በሙሉ ከበባ ውስጥ አስገብታታለች። መብራት፣ ውሃ እና መሰረታዊ አገልግሎቶች ተቋርጠዋል።

AFPCopyright: AFPሐማስ በእስራኤል ላይ ድንገተኛ ጥቃት አድርሶ ያገታቸውን ሰዎች ለማስለቀቅ እየተደረገ ያለው ድርድር በስምምነት ሊቋጭ ከጫፍ መድረሱን የኳታር አደራዳሪ ገለጹ።የኳታር የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማጂድ አል-አንሳሪ ከስምምነት ለመድረስ ከጫፍ ደርሰናል ብለዋል።ኳታር ሐማስ የያዛቸውን ታጋቾች እንዲለቅ፤ እስራኤልም እየተጠየቀች ላለችው የተኩስ አቁም ስምምነት አዎንታዊ ምላሽ እንድትሰጥ እስራኤል እና ሐማስን ስታደራድር ቆይታለች።ቃል አቀባዩ “. . . ስምምነት ላይ ለመድረስ ተቃርበናል” ያሉ ሲሆን ድርድሩ አሁን ያለበትን ድረጃ “ወሳኝ እና የመጨረሻው” ላይ ነው ሲሉ ገልጸውታል።ኳታር በጠላትንት የሚተያዩት የእስራኤል እና የሐማስ ‘ወዳጅ’ እንዲሁም በሁለቱ ወገኖች እምነት የሚጣልባት አገር ሆና ብቅ ብላለች።ለመሆኑ ኳታር ምዕራባውያን አሸባሪ ያሉትን ሐማስ ለምን አስጠለለች? ማደራደሩስ ይሳካላታል? ዝርዝሩን እዚህ ያንብቡ