ቀጥታቀጥታ
Related Video and Audio

VIDEO 1 MINUTE 44 SECONDSVIDEO 1 MINUTE 44 SECONDS1:44
Play video በሐማስ ጥቃት የሞቱ ወታደሮችን አስከሬን ለማግኘት እስራኤል እንዴት የንስር ወፍን ተጠቀመች? from BBCበሐማስ ጥቃት የሞቱ ወታደሮችን አስከሬን ለማግኘት እስራኤል እንዴት የንስር ወፍን ተጠቀመች?
- BBC
Play video በሐማስ ጥቃት የሞቱ ወታደሮችን አስከሬን ለማግኘት እስራኤል እንዴት የንስር ወፍን ተጠቀመች? from BBC

VIDEO 1 MINUTE 18 SECONDSVIDEO 1 MINUTE 18 SECONDS1:18
Play video ሕይወት በጋዛ፡ “ጦርነቱ መቶ ዓመታትን ወደኋላ መልሶናል” from BBCሕይወት በጋዛ፡ “ጦርነቱ መቶ ዓመታትን ወደኋላ መልሶናል”
- BBC
Play video ሕይወት በጋዛ፡ “ጦርነቱ መቶ ዓመታትን ወደኋላ መልሶናል” from BBC

VIDEO 2 MINUTES 31 SECONDSVIDEO 2 MINUTES 31 SECONDS2:31
Play video ‘ቢያንስ ሆስፒታሉ ጥቃት አይደርስበትም ብለን አስበን ነበር’፡ ከሆስፒታል የሸሹ የጋዛ ነዋሪዎች from BBC‘ቢያንስ ሆስፒታሉ ጥቃት አይደርስበትም ብለን አስበን ነበር’፡ ከሆስፒታል የሸሹ የጋዛ ነዋሪዎች
- BBC
Play video ‘ቢያንስ ሆስፒታሉ ጥቃት አይደርስበትም ብለን አስበን ነበር’፡ ከሆስፒታል የሸሹ የጋዛ ነዋሪዎች from BBC

VIDEO 2 MINUTESVIDEO 2 MINUTES2:00
Play video ጋዛን የጎበኘው ቢቢሲ የዓለም አቀፍ ኤዲተር ጄረሚ ቦውን እይታ from BBCጋዛን የጎበኘው ቢቢሲ የዓለም አቀፍ ኤዲተር ጄረሚ ቦውን እይታ
- BBC
Play video ጋዛን የጎበኘው ቢቢሲ የዓለም አቀፍ ኤዲተር ጄረሚ ቦውን እይታ from BBC

VIDEO 1 MINUTE 30 SECONDSVIDEO 1 MINUTE 30 SECONDS1:30
Play video አሜሪካ ከ60 በላይ አውሮፕላን ተሸካሚ ሁለተኛ መርከቧን ወደ እስራኤል አስጠጋች from BBCአሜሪካ ከ60 በላይ አውሮፕላን ተሸካሚ ሁለተኛ መርከቧን ወደ እስራኤል አስጠጋች
- BBC
Play video አሜሪካ ከ60 በላይ አውሮፕላን ተሸካሚ ሁለተኛ መርከቧን ወደ እስራኤል አስጠጋች from BBC

VIDEO 1 MINUTE 48 SECONDSVIDEO 1 MINUTE 48 SECONDS1:48
Play video ሐማስ ጋዛ ውስጥ የገነባቸው ወደ እስራኤል የሚያሻግሩት ዋሻዎች from BBCሐማስ ጋዛ ውስጥ የገነባቸው ወደ እስራኤል የሚያሻግሩት ዋሻዎች
- BBC
Play video ሐማስ ጋዛ ውስጥ የገነባቸው ወደ እስራኤል የሚያሻግሩት ዋሻዎች from BBC

VIDEO 3 MINUTES 27 SECONDSVIDEO 3 MINUTES 27 SECONDS3:27
Play video ሕይወት በጋዛ፡ ከቤታቸው ወጥተው መጠለያ ፍለጋ መንከራተት from BBCሕይወት በጋዛ፡ ከቤታቸው ወጥተው መጠለያ ፍለጋ መንከራተት
- BBC
Play video ሕይወት በጋዛ፡ ከቤታቸው ወጥተው መጠለያ ፍለጋ መንከራተት from BBC
ጭምቅ ሃሳብ
- የእስራኤል ካቢኔ የታገቱትን ነጻ ለማውጣት የተደረሰውን ስምምነት አፀደቀ
- ሐማስ እና እስራኤል ‘ጊዜያዊ የተኩስ አቁም’ ለማድረግ ወደ ስምምነት ተቃርበዋል ተባለ
- ዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት ኔታንያሁ ላይ የእስር ትዕዛዝ እንዲያወጣ ደቡብ አፍሪካ ጠየቀች
- በጋዛ የተገደሉ ፍልስጤማውያን ቁጥር 13 ሺህ ደረሰ- የጋዛ ጤና ሚኒስቴር
- የኳታር ጠቅላይ ሚኒስትር ታጋቾችን የማስለቀቅ ስምምነት ላይ ‘መተማመን መጨመሩን’ ተናገሩ
- የጃፓን ዕቃ ጫኝ መርከብ ቀይ ባሕር ላይ በየመን ሁቲ አማጺያን ታገተ
- እስራኤል ተመድ ባቋቋመው የትምህርት ቤት መጠለያ ባደረሰችው ጥቃት በርካቶች መገደላቸው ተነገረ
ቀጥታ ዘገባ
- የታተመዉ 3:563:56ዶ/ር ቴድሮስ ባልደረባቸው ከአራት ቤተሰቧ ጋር መገደሏን አስታወቁ
Tedros Adhanom GhebreyesusCopyright: Tedros Adhanom Ghebreyesusዲማ አለሃጅ ከስድስት ወር ልጇ፣ ከባለቤቷ እና ከሁለት ወንድሞቿ ጋር ትናንት ተገድላለች።Image caption: ዲማ አለሃጅ ከስድስት ወር ልጇ፣ ከባለቤቷ እና ከሁለት ወንድሞቿ ጋር ትናንት ተገድላለች።የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ቴድሮስ አድሃኖም አንድ ባልደረባቸው ከአራት የቤተሰብ አባሎቿ ጋር ጋዛ ውስጥ መገደሏን አስታወቁ።ዲማ አልሃጅ የተባለችው የዓለም ጤና ድርጅት ባልደረባ ከስድስት ወር ልጇ፣ ከባለቤቷ እና ከሁለት ወንድሞቿ ጋር ትናንት ማክሰኞ መገደሏን ገልጸዋል።“ሐዘናችንን የምገልጽበት ቃላት የለኝም” ብለዋል ዋና ዳይሬክተሩ በኤክስ (ትዊተር) ገጻቸው ላይ።ዶ/ር ቴድሮስ ጨምረውም ከመስከረም 26 ወዲህ 108 የተባበሩት መንግሥታት ሠራተኞች በጋዛ መገደላቸውን ገልጸዋል።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ

- የታተመዉ 3:183:18ደቡብ አፍሪካ የእስራኤል ኤምባሲ እንዲዘጋ እና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቷ እንዲቋረጥ ወሰነችየደቡብ አፍሪካ ምክር ቤት በፕሪቶሪያ የሚገኘው የእስራኤል ኤምባሲ እንዲዘጋ እና ከእስራኤል ጋር ያለ ሁሉም ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እንዲቋረጥ ወሰነ።ተጨማሪ ያንብቡArticle share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 2:202:20እስራኤል ከእስር የምትለቃቸውን ፍልስጤማውያንን ዝርዝር አወጣች
Getty ImagesCopyright: Getty Imagesየእስራኤል እስር ቤት (ፋይል ፎቶ)Image caption: የእስራኤል እስር ቤት (ፋይል ፎቶ)እስራኤል ከሐማስ ጋር በተደረሰው ስምምነት መሠረት ከእስር የምትለቃቸውን 300 ፍልስጤማውያንን ዝርዝር ይፋ አደረገች።በእስራኤል የፍትሕ ሚኒስቴር ገጽ ላይ የወጣው ዝርዝር የታሳሪዎችን ስም፣ እድሜ እና ለእስር ተዳርገውበታል የተባለው የሕግ ጥሰትን ዘርዝሯል።አብዛኞቹ ታሳሪዎች ከ14 እስከ 18 የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ሲሆን፤ ድንጋይ መወርወር፣ ከሐማስ ጋር ግንኙነት መፍጠር ወይም የሐማስን ጥቃት ማወደስ ከሚሉ ክሶች አንስቶ ቦምብ መወርወር እንዲሁም የግድያ ሙከራ መፈጸም የሚሉ ክሶች የቀረቡባቸው ናቸው።እስራኤል 300 ፍልስጤማውያንን እለቃለሁ ብትልም በስምምነቱ መሠረት በመጀመሪያው ዙር የሚለቀቁት እስረኞች 150 ሰዎች ናቸው።ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብቶች ተከራካሪ ድርጅት ሂዩማን ራይትስ ዋች ከ7ሺህ ያላነሱ ፍልስጤማውያን በእስራኤል እስር ቤቶች ውስጥ እንደሚገኙ የገለጸ ሲሆን፣ ከእነዚህ መካከል 200 ሴቶች እና 60 ልጆች ይገኙባቸዋል።የሂዩማን ራይትስ ዋች ዳይሬክተር ሳሪ ባሺ የፍልስጤማውያን ታዳጊዎች ጉዳይ በእስራኤል ወታደራዊ ሕግ እንዲታይ በመደረጉ ወላጆች ወይም ጠበቆች በሌሉበት እንዲመረመሩ እና ለተራ ጥፋቶች ለረዥም ሰዓት በእስር እንዲቆዩ ይደረጋሉ ብለዋል።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 0:090:09ኳታር የሐማስ እና እስራኤል የደረሱት ስምምነት መቼ ተግባራዊ እንደሚደረግ ይፋ ይደረጋል አለች
Getty ImagesCopyright: Getty Imagesበእስራኤል እና በሐማስ መካከል ስምምነት እንዲደርስ ያስቻለችው ኳታር ሐማስ እና እስራኤል የደረሱት ስምምነት መቼ ተግባራዊ እንደሚደረግ ይፋ አድርጋለች።በዚህም የባሕረ ሰላጤዋ አገር “የተኩስ አቁም የሚጀምርበት ጊዜ በሚቀጥሉት 24 ሰዓታት ውስጥ ይፋ ይሆናል” ብላለች።የተኩስ አቁሙ ለአራት ቀናት ይቆያል ከማለት ባለፈ “ሊራዘም ይችላል” ስትል አስታውቃለች።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 0:030:03ሐማስ 150 ፍልስጤማውያን ከእስራኤል እስር ነጻ ይወጣሉ አለሐማስ ከእስራኤል ጋር በደረሰው ስምምነት መሠረት 150 ፍልስጤማውያን ከእስራኤል እስር ቤት ይወጣሉ አለ።ሐማስ ከእስራኤል አግቶ ከያዛቸው መካከል 50 ሰዎችን ለመልቀቅ መስማማቱ ይታወሳል። 50ዎቹ ታጋቾች በእስራኤል እስር ቤቶች ውስጥ ባሉ 150 ፍልስጤማውያን ሴቶች እና ህጻናት ምትክ እንደሚለቀቁ ገልጿል።በስምምነቱ መሠረት በመቶዎች የሚቆጠሩ የሰብዓዊ እርዳታ፣ የህክምና ቁሳቁስ እና ነዳጅ የጫኑ የጭነት መኪናዎች ወደ ጋዛ እንዲገቡ ያስችላል ሲል ሐማስ ገልጿል።እስራኤል ለጦርነቱ ፋታ በምትሰጥበት ወቅት በጋዛ ማንንም እንደማታጠቃ እና እንደማታሰር መግለጿን መግለጫው አክሏል።በአራቱ ቀናት በደቡባዊ ጋዛ የአየር ትራፊክ ሙሉ በሙሉ ይቆማል። በሰሜን ጋዛ ደግሞ ለስድስት ሰዓታት እንደሚቆም ተናግሯል።ዩናይትድ ኪንግደም እና አሜሪካን ጨምሮ በበርካታ አገራት አሸባሪ ተብሎ የተፈረጀው ሐማስ መስከረም 26 አሰቃቂ ጥቃት ከመፈጸም ባለፈ ወደ 230 የሚጠጉ ሰዎችን አፍኖ ወስዷል።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 23:46 21 ህዳር 202323:46 21 ህዳር 2023ባይደን ታጋቾችን ለማስለቀቅ የተደረሰውን ስምምነት አወደሱ
EPACopyright: EPAጆ ባይደን “ለሳምንታት በእስር እና በቃላት ሊገለጽ የማይችል መከራ” ሲያሳልፉ ከነበሩ ታጋቾች መካከል አንዳንዶቹ ከቤተሰቦቻቸው ጋር ሊቀላቀሉ መሆኑ “በጣም አስደስቶኛል” ብለዋል።የአሜሪካው ፕሬዝዳንት የኳታር እና የግብጽ መሪዎች ስምምነቱ እንዲደረስ ላሳዩት “ወሳኝ አመራር እና አጋርነት” አመስግነዋቸዋል።የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ለጦርነቱ ፋታ ለመስጠት ላሳዩት “ቁርጠኝነት” አድናቆታቸውን ችረዋቸዋል።”የዚህ ስምምነት ሃሳቦች ሙሉ በሙሉ መተግበራቸው አስፈላጊ ነው” ሲል አጽንኦት ሰጥተዋል።በስምምነቱ መሠረት በርካታ ሰብዓዊ ድጋፍ ወደ ጋዛ እንዲገባ በማገዛቸውም ኔታንያሁን አመስግነዋቸዋል።“ይህም በጋዛ የሚገኙ ንጹሐን ፍልስጤማውያን ቤተሰቦችን ያግዛል” ብለዋል።በመቶዎች የሚቆጠሩ መድኃኒት እና ነዳጅ የጫኑ ተሽከርካሪዎች በስምምነቱ መሠረት ጋዛ እንዲገቡ ይፈቀድላቸዋል።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 23:36 21 ህዳር 202323:36 21 ህዳር 2023የእስራኤል ካቢኔ የታገቱትን ነጻ ለማውጣት የተደረሰውን ስምምነት አፀደቀ
Getty ImagesCopyright: Getty Imagesየእስራኤል ካቢኔ በሐማስ ታግተው የሚገኙ 50 ሰዎችን ነጻ ለማውጣት የተደረሰውን ስምምነት አጸደቀ።የእስራኤል ጠቅላይ ሚንስትር ጽህፈት ቤት 50 ታጋቾች በአራት ቀናት ውስጥ እንደሚለቀቁ አስታውቋል።በምላሹ እስራኤል የተኩስ አቁም ለማድረግ ተስማምታለች።በስምምነቱ መሠረት በመጀመሪያዎቹ አራት ቀናት ከሚለቀቁ 50 ታጋቾች በተጨማሪ “10 ታጋቾች በተለቀቁ ቁጥር አንድ ተጨማሪ የተኩስ አቁም ቀን ይኖራል” ተብሏል።ሐማስ መስከረም 26 በእስራኤል ላይ ድንገተኛ ጥቃት ፈጽሞ ከ230 ያላነሱ ሰዎችን አግቶ መውሰዱ ይታወሳል።ሐማስ እና እስራኤል በደረሱት ስምምነት መሠረት በቅድሚያ ታግተው የሚገኙ ሴቶች እና ሕጻናት ነጻ ይወጣሉ ተብሏል።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 9:10 21 ህዳር 20239:10 21 ህዳር 2023ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታኒያሁ “ታጋቾች ነጻ ይወጣሉ ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ” አሉ
ReutersCopyright: Reutersየእስራኤል ጠቅላይ ሚንስትር ቤኒያሚን ኔታኒያሁImage caption: የእስራኤል ጠቅላይ ሚንስትር ቤኒያሚን ኔታኒያሁየእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታኒያሁ ታጋቾችን ለማስለቀቅ በሚደረገው ጥረት በቅርቡ መልካም ዜና እጠብቃለሁ አሉ።ሮይተርስ የዜና ወኪል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጋዛ የሚገኙ ታጋቾችን በተመለከተ “መልካም ዜና ይኖራል ብዬ ተስፋ አድርጋለሁ” ስለማለታቸው ዘግቧል።ሐማስ መስከረም 26/2016 ዓ.ም. በእስራኤል ላይ ድንገተኛ ጥቃት አድርሶ ከ240 ያላሱ ሰዎች አግቶ ወደ ጋዛ መውሰዱን እስራኤል አሳውቃለች።ሐማስ እነዚህ ታጋቾች እንዲለቅ፣ እስራኤልም በበኩሏ የተኩስ አቁም እንድታደርግ የባሕረ ሰላጤዋ አገር ኳታር ስታደራድር ቆይታለች።ከዚህ ድርድር መልካም ውጤት እንደሚጠብቁ የኳታር የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ገልጸው ነበር።የሐማስ መሪም እንዲሁ ከእስራኤል ጋር ጊዜያዊ የተኩስ አቁም ለማድረግ ወደ ስምምነት ተቃርበናል ብለዋል።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 8:40 21 ህዳር 20238:40 21 ህዳር 2023በሐማስ የታገቱትን ነጻ የማውጣት ድርድር ከጫፍ ድርሷል – የኳታር አደራዳሪ
AFPCopyright: AFPሐማስ በእስራኤል ላይ ድንገተኛ ጥቃት አድርሶ ያገታቸውን ሰዎች ለማስለቀቅ እየተደረገ ያለው ድርድር በስምምነት ሊቋጭ ከጫፍ መድረሱን የኳታር አደራዳሪ ገለጹ።የኳታር የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማጂድ አል-አንሳሪ ከስምምነት ለመድረስ ከጫፍ ደርሰናል ብለዋል።ኳታር ሐማስ የያዛቸውን ታጋቾች እንዲለቅ፤ እስራኤልም እየተጠየቀች ላለችው የተኩስ አቁም ስምምነት አዎንታዊ ምላሽ እንድትሰጥ እስራኤል እና ሐማስን ስታደራድር ቆይታለች።ቃል አቀባዩ “. . . ስምምነት ላይ ለመድረስ ተቃርበናል” ያሉ ሲሆን ድርድሩ አሁን ያለበትን ድረጃ “ወሳኝ እና የመጨረሻው” ላይ ነው ሲሉ ገልጸውታል።ኳታር በጠላትንት የሚተያዩት የእስራኤል እና የሐማስ ‘ወዳጅ’ እንዲሁም በሁለቱ ወገኖች እምነት የሚጣልባት አገር ሆና ብቅ ብላለች።ለመሆኑ ኳታር ምዕራባውያን አሸባሪ ያሉትን ሐማስ ለምን አስጠለለች? ማደራደሩስ ይሳካላታል? ዝርዝሩን እዚህ ያንብቡ ኳታር ምዕራባውያን አሸባሪ ያሉትን ሐማስ ለምን አስጠለለች? ማደራደሩስ ይሳካላታል?Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 8:22 21 ህዳር 20238:22 21 ህዳር 2023ሐማስ የእስራኤል የአየር ጥቃት መቆም የስምምነት አካል እንዲሆን ፍላጎት አለው ተባለ
ReutersCopyright: Reutersየእስራኤል መገናኛ ብዙኃን በእስራኤል እና በሐማስ መካከል እየተደረገ ባለው ተኩስ የማቆም ንግግር ውስጥ እስራኤል በጋዛ የአየር ክልል ላይ መብረሯን እንድታቆም ሐማስ መጠየቁን ዘገቡ።ዋላ የተሰኘ መገናኛ ብዙኃን በጋዛ የሚገኙት የሐማስ መሪ ያህያ ሲንዋር እስራኤል በጋዛ የአየር ክልል ላይ ሙሉ በሙሉ በረራዋን እንድታቆም ጠይቀዋል ያለ ሲሆን፣ ያኔት የተባለ የዜና ድረ-ገጽ ደግሞ እስራኤል በሰሜን ጋዛ ላይ ብቻ በቀን ለስድስት ሰዓታት ለመብረር እንድትስማማ ሐማስ ጥረት እያደረገ ነው ሲል ዘግቧል።እስራኤል በጋዛ ላይ በምድር፣ በአየር እና በባሕር ጥቃቶች እየፈጸመች ሁለት ወራት ሊሞላት የተቃረበች ሲሆን፣ አስካሁን ጋዛ ውስጥ ከፍተኛ ውድመት እያደረሰ ያለው የአገሪቱ አየር ኃይል ጥቃት ነው።እስራኤል ከተዋጊ አውሮፕላኖች በተጨማሪ በውል የማይታቁ የስለላ እና ጥቃት አድራሽ ሰው አልባ አውሮፕላኖችን (ድሮኖች) በጋዛ አሰማርታ ቆይታለች።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 8:14 21 ህዳር 20238:14 21 ህዳር 2023እስራኤል በደቡብ አፍሪካ ያሉትን አምባሳደሯን ‘ለምክክር’ ጠራችእስራኤል በጋዛ ላይ እያካሄድ ባለው ወታደራዊ ዘመቻ ላይ ጠንካራ ተቃውሞዋን እያሰማች ባለችው ደቡብ አፍሪካ የሚገኙ አምባሳደሯን መጥራቷን የአገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።ተጨማሪ ያንብቡArticle share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 5:53 21 ህዳር 20235:53 21 ህዳር 2023በሐማስ እና እስራኤል መካከል ይደረሳል የተባለው የጊዜያዊ ተኩስ አቁም ስምምነት ምንን ይዟል?
EPA-EFE/REX/ShutterstockCopyright: EPA-EFE/REX/Shutterstockየሐማስ መሪ ከእስራኤል ጋር ጊዜያዊ የተኩስ አቁም ለማድረግ ወደ ስምምነት መቃረቡን ባወጡት መግለጫ አስታውቀዋል።እስራኤል በጉዳዩ ላይ የሰጠችው አስተያየት የለም። እንደ አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ጊዜያዊ የተኩስ አቁም ስምምነቱ የሚከተሉትን ሊያካትት ይችላል።
- ኢስማኢል ሃኒዬ ጊዜያዊ የተኩስ አቁሙ ምን ያህል ጊዜ እንደሚቆይ አልተናገሩም ነገር ግን እየተካሄደ ያለው ድርድር ጊዜያዊ የተኩስ አቁሙ ለምን ያህል ጊዜ እንደሚቆይ፣ እርዳታ ወደ ጋዛ ለማድረስ እና ታጋቾችን በፍልስጤማዊ እስረኞች መለዋወጥ ላይ ያተኮረ እንደሆነ ተናግረዋል። ሁለቱም አካላት ሴቶችን እና ህጻናትን ያካትታሉ ብሏል።
- የስምምነቱ ዝርዝር ሁኔታ በሃማስ እና በእስራኤል መካከል አሸማጋይ በነበረችው ኳታር ይፋ እንደሚሆንም ተናግረዋል።
- የእስራኤል ጦር በጋዛ ሰርጥ ያለውን ውጊያ ለአምስት ቀናት እንዲያቆም እንዲሁም በደቡባዊ ጋዛ ላይ የእስራኤል የአየር እንቅስቃሴን የሚገድብ።
- የፍልስጤም ቡድኖች ከ50-100 ታጋቾችን የሚለቁ ሲሆን እነዚህም የእስራኤል ሰላማዊ ዜጎች፣ የሌላ አገር ተወላጆች የሚሆኑ ሲሆን ነገር ግን ወታደሮች አይሆኑም።
- በምላሹም እስራኤል ሴቶች እና ህጻናትን ጨምሮ 300 ፍልስጤማውያንን ከእስር ቤቶቿ የምትለቅ ይሆናል። አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ስማቸው ያልጠቀሳቸውን የሐማስ፣ እስላማዊ ጂሃድ ባለስልጣናትን ዋቢ አድርጎም ድርጅቶቹ በስምምነቱ ሐሳብ መስማማታቸውን ዘግቧል።
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- የታተመዉ 4:08 21 ህዳር 20234:08 21 ህዳር 2023ሰባተኛ ሳምንቱን በያዘው የጋዛ ጦርነት አዳዲስ ክሰተቶች
Getty ImagesCopyright: Getty Images
- የሐማስ መሪ ከእስራኤል ጋር ጊዜያዊ የተኩስ አቁም ለማድረግ ወደ ስምምነት መቃረቡን ባወጡት መግለጫ አስታውቀዋል።
- ኢስማኢል ሃኒዬ ጊዜያዊ የተኩስ አቁሙ ምን ያህል ጊዜ እንደሚቆይ ባይናገሩም ነገር ግን ለአልጀዚራ እንደተናገሩት ድርድሩ ለምን ያህል ጊዜ እንደሚቆይ፣ እርዳታ ወደ ጋዛ ለማድረስ እና ታጋቾችን በፍልስጤማዊ እስረኞች መለዋወጥ ላይ ያተኮረ እንደሆነ ተናግረዋል።
- የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት ታጋቾችን ለመልቀቅ ሲደረግ የነበረው ውይይት ወደ ስምምነት መቃረቡን ነው።
- የቢቢሲ የመካከለኛው ምስራቅ ጋዜጠኛ ቶም ባትማን ታጋቾችን ደረጃ በደረጃ የሚለቁበትን ሁኔታ እንደሚመለከቱም ተናግሯል።
- እስራኤል በማዕከላዊ ጋዛ በሚገኘው ኑሴራት የስደተኞች ካምፕ ላይ ባደረሰችው የአየር ጥቃት ቢያንስ 17 ሰዎች መገደላቸውን የፍልስጤም የዜና ወኪል ዋፋ ዘግቧል። እስራኤል ጥቃቱን አስመልክቶ ያለችው ነገር የለም።
- የጦርነቱ ማዕከል የሆነው የጋዛው የኢንዶኔዥያ ሆስፒታል ዳይሬክተር ተኩስ እስከ ምሽቱ ድረስ ቀጥሏል ብለዋል።
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- የታተመዉ 1:35 21 ህዳር 20231:35 21 ህዳር 2023ዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት ኔታንያሁ ላይ የእስር ትዕዛዝ እንዲያወጣ ደቡብ አፍሪካ ጠየቀችዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት በጠቅላይ ሚንስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ላይ የእስር ትዕዛዝ እንዲያወጣ የደቡብ አፍሪካ መንግሥት ጠየቀ። እስራኤልን የጦር ወንጀል ፈጽሟል በማለት እየከሰሰች ያለችው ደቡብ አፍሪካ እስከ ታህሳስ አጋማሽ ድረስም ትዕዛዙ መውጣት አለበት ብላለች። የፕሬዝዳንቱ ጽህፈት ቤት ሚንስትር ኩምቡድዞ ሳቬኒ እንዳሉት ፍርድ ቤቱ ይህንን ማድረግ ካልቻለ የዓለምአቀፉ አስተዳደር “ጠቅላላ ውድቀት” ምልክት ይሆናል ብለዋል።ተጨማሪ ያንብቡArticle share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 23:54 20 ህዳር 202323:54 20 ህዳር 2023ሐማስ እና እስራኤል ‘ጊዜያዊ የተኩስ አቁም’ ለማድረግ ወደ ስምምነት ተቃርበዋል ተባለ
ReutersCopyright: Reutersሐማስ እና እስራኤል ውጊያውን በጊዜያዊነት ለማቆም እና ታጋቾች እንዲለቀቁ ለማመቻት ወደ ስምምነት እንደተቃረቡ ሪፖርቶች እየወጡ ይገኛሉ።በኳታር አሸማጋይነት መሰረት ሁለቱ ወገኖች ውይይት ሲያደርጉም ቆይተዋል።የሐማስ መሪ እስማኤል ሃኒዬህ እንዳሉት ድርጅታቸው ምላሹን “በኳታር ላሉት ወንድሞቻችን እና ለአሸማጋዮች ሰጥቷል። ውጊያውን ለማቆም ስምምነት ላይ ለማድረስ ተቃርበናል” ሲሉም መናገራቸውን የዜና ወኪሎች እና የፍልስጠም የዜና አውታሮች ዘግበዋል።እስራኤል በጉዳዩ ላይ የሰጠችው ምላሽ የለም።የአሜሪካ ከፍተኛ ባለስልጣንም በሐማስ የተወሰዱ ታጋቾችን ለማስለቀቅ እየተደረገ ያለው ውይይት ወደ ስምምነት መቃረቡን እንዲሁም በምላሹም ውጊያውም በጊዜያዊነት እንዲገታ ሊደረግ መሆኑምም ሰኞ እለት ገልጸው ነበር።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 9:27 20 ህዳር 20239:27 20 ህዳር 2023የጃፓን ዕቃ ጫኝ መርከብ ቀይ ባሕር ላይ በየመን ሁቲ አማጺያን ታገተበኢራን በሚደገፉት የየመን ሁቲ አማጺያን የእስራኤል ነው ያሉትን የጃፓን ግዙፍ የዕቃ ጫኝ መርከብ ቀይ ባሕር አገቱ።ተጨማሪ ያንብቡArticle share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 7:42 20 ህዳር 20237:42 20 ህዳር 2023በጋዛ ያለጊዜያቸው ከተወለዱ 31 ጨቅላ ሕጻናት 28ቱ ብቻ ለምን ወደ ግብፅ ተላኩ?
ReutersCopyright: Reutersበሰሜን ጋዛ ከሚገኘው አል ሺፋ ሆስፒታል እንዲወጡ ከተደረጉ 31 ያለጊዜያቸው የተወለዱ ጨቅላ ሕጻናት መካከል 28ቱ ብቻ ወደ ግብፅ ተላኩ።እነዚህ ጨቅላ ሕጻናት የእስራኤል ጦር ከተቆጣጠረው እና የሞት ቀጠና ከሆነው የጋዛ ትልቁ ሆስፒታል አል ሺፋ በሕይወት ተርፈው የወጡ ሲሆን፣ ወደ አል አህሊ ኤምሬትስ ሆስፒታል ተወስደው የነበሩ ናቸው።ከእነዚህ ሕጻናት መካከል አብዛኞቹ ለሕክምና ወደ ግብፅ የተላኩ ሲሆን፣ ጥቂቶቹ አሁንም ድረስ እዚያው ሆስፒታል ውስጥ ይገኛሉ።ይህ ለምን ሆነ ሲል ቢቢሲ በአል አህሊ ኤምሬትስ ሆስፒታል ውስጥ የጨቅላ ሕጻናት ክፍል ኃላፊ የሆኑትን ዶ/ር መሐመድ ሳላማን ጠይቋቸዋል።ዶ/ር መሐመድ የተወሰኑት የሕጻናቱ ወላጆች ልጆቻቸውን ለመለየት እሁድ ዕለት አል አህሊ ኤምሬትስ ሆስፒታል መድረሳቸውን ገልጸው፣ ልጆቻቸው ለሕክምና ወደ ግብፅ እንዲሄዱ የፈቃድ ፎርም እንዲሞሉ እንደጠየቋቸው እና ፈቃድ ያገኙትን መላካቸውን ተናግረዋል።“አሁን ላይ ማንነቱ ያልተለየ እና ወላጆቹ ያልታወቁ አንድ ሕጻን ይገኛል። ይህ ሕጻን አሁንም ከእኛ ጋር ነው ያለው ። ሕጻኑ በጥሩ የጤንነት ሁኔታ ላይ ስለሚገኝ እና ለሕክምና ወደ ሌላ ቦታ መሄድ ስለማያስፈልገው በጋዛ ጤና ሚኒስቴር ውሳኔ እዚህ እንዲቆይ ተደርጓል” ብለዋል።ሁለት ሌሎች ሕጻናት ደግሞ ወላጆቻቸው በግል ጉዳይ ምክንያት ለመላክ ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ሳይላኩ የቀሩ መሆናቸውን ገልጸዋል።ዶክተር ሳላማ እንዳሉት ሦስቱም ሕጻናት በጥሩ ሁኔታ ላይ ይገኛሉ።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 4:47 20 ህዳር 20234:47 20 ህዳር 2023የእስራኤል ታንኮች በሰሜናዊ ጋዛ ወደሚገኘው ሆስፒታል ገቡየእስራኤል ታንኮች በሰሜን ጋዛ ወደሚገኘው የኢንዶኔዥያ ሆስፒታል ገቡ።እስራኤል ዛሬ ማለዳ በሆስፒታል ባደረሰችው ጥቃት ወደ 12 የሚጠጉ ሰዎች መገደላቸውም ተዘግቧል።ከጥቂት ሰዓታት በፊት የሆስፒታሉ ዳይሬክተር ዶ/ር ማርዋን አል ሱልጣን ለቢቢሲ እንደተናገሩት የእስራኤል ጦር ከሆስፒታሉ ህንጻ 20 ሜትሮች ያህል ርቀት ነበረው።በአካባቢው ከፍተኛ የተኩስ ድምጽ ይሰማ እንደነበር እና የቀዶ ጥገና ማገገሚያ ክፍል መመታቱን ተናግረው ነበር።የእስራኤል ጦር በቅርቡ በሰጠው መግለጫ በሆስፒታሉ ላይ ስላለው ነገር ምንም አላለም። “የእስራኤል መከላከያ ወታደሮች በጋዛ ሰርጥ የሚያደርጉትን ዘመቻ ቀጥለዋል። አውሮፕላኖቻችን አሸባሪዎች ላይ፣ አሸባሪዎች መሰረተ ልማት ላይ እንዲሁም የጦር መሳሪያዎቻችን እና ወታደራዊ ቁሳቁሶችን በማፈላለግ ስራቸውን ቀጥለዋል” ብሏል።የሐማስ ሶስት አዛዦችም ተገድለዋል ተብሏል። የሆስፒታሉ ዳይሬክተር እስራኤል ባደረሰችው የአየር ጥቃት ቢያንስ 10 ሰዎች መገደላቸውን ገልጸዋል።ጋዛ የጤና ሚኒስቴር በበኩሉ 12 ሰዎች መገደላቸውን ተናግሯል። የሚኒስቴሩ ቃለ አቀባይ አሽራፍ አል ቁድራ ለአጃንስ ፍራንስ ፕሬስ የዜና ወኪል ከተገደሉት በተጨማሪም በርካቶች ቆስለዋል ብለዋል።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 3:43 20 ህዳር 20233:43 20 ህዳር 2023ቻይና ከአረብ አገራት ሚኒስትሮች ጋር ተወያየች
ReutersCopyright: Reutersቻይና ከአረብ አገራት ጋር ባደረገችው ውይይት የሁለት አገራት፣ የፍልስጤምና የእስራኤል መንግሥት ምስረታን እንደምትደግፍ አስታወቀች።ቻይና ይህንን ያስታወቀችው ከአረብ እና ሙስሊም አገራት የተወጣጡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ልዑካን በቻይና መደበኛ ጉብኝት እያደረጉ ባለበት ወቅት ነው።ሳዑዲ አረቢያ፣ ዮርዳኖስ፣ ግብጽ፣ ኢንዶኔዥያ እና ከፍልስጤም አስተዳደር እና የእስልምና ትብብር ድርጅት መሪን ያካተተ ልዑካን በቻይና ይገኛሉ።ጉብኝቱ ቻይና በጋዛ ያለውን ጦርነት ለማርገብ፣ ሰላማዊ ዜጎችን ለመጠበቅ እና የፍልስጤም ጥያቄ ፍትሃዊ በሆነ መንገድ የሚፈታበትን ሁኔታም ላይ ለመምከርም እንደሆነ የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዋንግ ዩ በቅርቡ በሪያድ በተካሄደው የአረብ እና ሙስሊም አገራት መሪዎች ጉባዔ ላይ የቀረበውን ጥሪ በመደገፍ አገራቸው የሁለት አገራት ምስረታን እንደ መፍትሄ እንደምታየው ተናግረዋል።አለም አቀፉ ማህበረሰብ ‘በአፋጣኝ እርምጃ መውሰድ እንዳለበት እና የሰብዓዊ ጥፋቱም እንዲያከትም ውጤታማ እርምጃዎች መውሰድ አለበት’ ሲሉም ተደምጠዋል።ሚኒስትሩ በመክፈቻ ንግግራቸውም ” በጋዛ ያለውን ጦርነት ለማርገብ እና የመካከለኛውን ምስራቅ ሰላምንም በተቻለ ፍጥነት ለመመለስ በጋራ እንስራ” ሲሉም ለሚኒስትሮቹ ተናግረዋል።ቻይና በጋዛ የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲደረግ በቀዳሚነት ጥሪ ካቀረቡ አገራት መካከል ስትሆን ቀደም ሲልም ውይይትን ለማበረታት እና ሰላምንም ለማስፈን አስፈላጊውን ሁሉ ለማድረግ ፈቃደኛ መሆኗንም ስትናገር ቆይታለች።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 2:19 20 ህዳር 20232:19 20 ህዳር 2023ሰባተኛ ሳምንቱን በያዘው የጋዛ ጦርነት የተከሰቱ የቅርብ ጉዳዮች
ReutersCopyright: Reuters
- 31 ያለጊዜያቸው የተወለዱ ጨቅላዎች ከአልሺፋ ሆስፒታል እሁድ ዕለት እንዲወጡ ተደርገው በደቡባዊ ራፋህ ከተማ ወደሚገኘው ኤምሬትስ ሆስፒታል ተወስደዋል።
- የዓለም ጤና ድርጅት ኃላፊ ዶክተር ቴድሮስ አድኃኖም ገብረእየሱስ ጨቅላዎቹ “በጣም እንደታመሙ” እና በጣም በአስቸጋሪ እና በከፋ የጸጥታ ሁኔታ ውስጥ መወሰዳቸውንም ነው የተናገሩት።
- በአልሺፋ ሆስፒታል የቀሩ ህሙማንን እና ሰራተኞችን ሙሉ በሙሉ ለማስወጣት የያዘውንም እቅድ በማጠናቀቅ ላይ መሆኑንም የዓለም ጤና ድርጅት አስታውቋል። ይህም በርካታ ቀናትን እንደሚፈጅ አስታውቆ በመጀመሪያውም የኩላሊት እጥበት እየተደረገላቸው ያሉ እና የአከርካሪ አጥንት ጉዳት ያለባቸውንም ማዛወር ይሆናል።
- የእስራኤል ጦር በአልሺፋ ሆስፒታል ስር ’55 ሜትር እርዝመት ያለው የሽብር ዋሻ” ያሳያል ያለችውን ቪዲዮ ለቋል። ጦሩ አግኜቻዋለሁ ያለውም ዋሻ በሆስፒታሉ ግቢ ውስጥ የሚገኙ በርካታ ህንጻዎች ሐማስ “ለሽብር ተግባር ሽፋንንት እንደሚጠቀምባቸው ያረጋግጣል” ብሏል። ሐማስም ሆነ የሆስፒታሉ ባለሙያዎች ይህንን ክስ አይቀበሉትም።
- የእስራኤል መከላከያ ኃይል ሐማስ መስከረም 26 ካደረሰው ጥቃት በኋላ የወሰዳቸው ታጋቾች ወደ ጋዛ ትልቁ ሆስፒታል መወሰዳቸውን የሚያሳይ ነው ያለውን ከስፍራው የተቀረጸ ቪዲዮ (ሲሲቲቪ) አሳይቷል።
- በኢራን የሚደገፉት የየመን ሁቲ አማጽያን የእስራኤልን የጭነት መርከብ በቀይ ባህር መያዛቸውን ያስታወቁ ሲሆን የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ “ሌላ የኢራን የሽብር ተግባር” ሲሉ ጠርተውታል። እስራኤል በጋዛ ላይ የምታደርሰውን የአየር ጥቃት ተከትሎ የሁቲ አማጽያን ወደ እስራኤል በርካታ ሚሳኤሎችን እና ድሮኖችን አስወንጭፈዋል።

Tedros Adhanom GhebreyesusCopyright: Tedros Adhanom Ghebreyesusዲማ አለሃጅ ከስድስት ወር ልጇ፣ ከባለቤቷ እና ከሁለት ወንድሞቿ ጋር ትናንት ተገድላለች።Image caption: ዲማ አለሃጅ ከስድስት ወር ልጇ፣ ከባለቤቷ እና ከሁለት ወንድሞቿ ጋር ትናንት ተገድላለች።የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ቴድሮስ አድሃኖም አንድ ባልደረባቸው ከአራት የቤተሰብ አባሎቿ ጋር ጋዛ ውስጥ መገደሏን አስታወቁ።ዲማ አልሃጅ የተባለችው የዓለም ጤና ድርጅት ባልደረባ ከስድስት ወር ልጇ፣ ከባለቤቷ እና ከሁለት ወንድሞቿ ጋር ትናንት ማክሰኞ መገደሏን ገልጸዋል።“ሐዘናችንን የምገልጽበት ቃላት የለኝም” ብለዋል ዋና ዳይሬክተሩ በኤክስ (ትዊተር) ገጻቸው ላይ።ዶ/ር ቴድሮስ ጨምረውም ከመስከረም 26 ወዲህ 108 የተባበሩት መንግሥታት ሠራተኞች በጋዛ መገደላቸውን ገልጸዋል።Article share tools
Getty ImagesCopyright: Getty Imagesየእስራኤል እስር ቤት (ፋይል ፎቶ)Image caption: የእስራኤል እስር ቤት (ፋይል ፎቶ)እስራኤል ከሐማስ ጋር በተደረሰው ስምምነት መሠረት ከእስር የምትለቃቸውን 300 ፍልስጤማውያንን ዝርዝር ይፋ አደረገች።በእስራኤል የፍትሕ ሚኒስቴር ገጽ ላይ የወጣው ዝርዝር የታሳሪዎችን ስም፣ እድሜ እና ለእስር ተዳርገውበታል የተባለው የሕግ ጥሰትን ዘርዝሯል።አብዛኞቹ ታሳሪዎች ከ14 እስከ 18 የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ሲሆን፤ ድንጋይ መወርወር፣ ከሐማስ ጋር ግንኙነት መፍጠር ወይም የሐማስን ጥቃት ማወደስ ከሚሉ ክሶች አንስቶ ቦምብ መወርወር እንዲሁም የግድያ ሙከራ መፈጸም የሚሉ ክሶች የቀረቡባቸው ናቸው።እስራኤል 300 ፍልስጤማውያንን እለቃለሁ ብትልም በስምምነቱ መሠረት በመጀመሪያው ዙር የሚለቀቁት እስረኞች 150 ሰዎች ናቸው።ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብቶች ተከራካሪ ድርጅት ሂዩማን ራይትስ ዋች ከ7ሺህ ያላነሱ ፍልስጤማውያን በእስራኤል እስር ቤቶች ውስጥ እንደሚገኙ የገለጸ ሲሆን፣ ከእነዚህ መካከል 200 ሴቶች እና 60 ልጆች ይገኙባቸዋል።የሂዩማን ራይትስ ዋች ዳይሬክተር ሳሪ ባሺ የፍልስጤማውያን ታዳጊዎች ጉዳይ በእስራኤል ወታደራዊ ሕግ እንዲታይ በመደረጉ ወላጆች ወይም ጠበቆች በሌሉበት እንዲመረመሩ እና ለተራ ጥፋቶች ለረዥም ሰዓት በእስር እንዲቆዩ ይደረጋሉ ብለዋል።Article share tools
Getty ImagesCopyright: Getty Imagesበእስራኤል እና በሐማስ መካከል ስምምነት እንዲደርስ ያስቻለችው ኳታር ሐማስ እና እስራኤል የደረሱት ስምምነት መቼ ተግባራዊ እንደሚደረግ ይፋ አድርጋለች።በዚህም የባሕረ ሰላጤዋ አገር “የተኩስ አቁም የሚጀምርበት ጊዜ በሚቀጥሉት 24 ሰዓታት ውስጥ ይፋ ይሆናል” ብላለች።የተኩስ አቁሙ ለአራት ቀናት ይቆያል ከማለት ባለፈ “ሊራዘም ይችላል” ስትል አስታውቃለች።Article share tools
EPACopyright: EPAጆ ባይደን “ለሳምንታት በእስር እና በቃላት ሊገለጽ የማይችል መከራ” ሲያሳልፉ ከነበሩ ታጋቾች መካከል አንዳንዶቹ ከቤተሰቦቻቸው ጋር ሊቀላቀሉ መሆኑ “በጣም አስደስቶኛል” ብለዋል።የአሜሪካው ፕሬዝዳንት የኳታር እና የግብጽ መሪዎች ስምምነቱ እንዲደረስ ላሳዩት “ወሳኝ አመራር እና አጋርነት” አመስግነዋቸዋል።የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ለጦርነቱ ፋታ ለመስጠት ላሳዩት “ቁርጠኝነት” አድናቆታቸውን ችረዋቸዋል።”የዚህ ስምምነት ሃሳቦች ሙሉ በሙሉ መተግበራቸው አስፈላጊ ነው” ሲል አጽንኦት ሰጥተዋል።በስምምነቱ መሠረት በርካታ ሰብዓዊ ድጋፍ ወደ ጋዛ እንዲገባ በማገዛቸውም ኔታንያሁን አመስግነዋቸዋል።“ይህም በጋዛ የሚገኙ ንጹሐን ፍልስጤማውያን ቤተሰቦችን ያግዛል” ብለዋል።በመቶዎች የሚቆጠሩ መድኃኒት እና ነዳጅ የጫኑ ተሽከርካሪዎች በስምምነቱ መሠረት ጋዛ እንዲገቡ ይፈቀድላቸዋል።Article share tools
Getty ImagesCopyright: Getty Imagesየእስራኤል ካቢኔ በሐማስ ታግተው የሚገኙ 50 ሰዎችን ነጻ ለማውጣት የተደረሰውን ስምምነት አጸደቀ።የእስራኤል ጠቅላይ ሚንስትር ጽህፈት ቤት 50 ታጋቾች በአራት ቀናት ውስጥ እንደሚለቀቁ አስታውቋል።በምላሹ እስራኤል የተኩስ አቁም ለማድረግ ተስማምታለች።በስምምነቱ መሠረት በመጀመሪያዎቹ አራት ቀናት ከሚለቀቁ 50 ታጋቾች በተጨማሪ “10 ታጋቾች በተለቀቁ ቁጥር አንድ ተጨማሪ የተኩስ አቁም ቀን ይኖራል” ተብሏል።ሐማስ መስከረም 26 በእስራኤል ላይ ድንገተኛ ጥቃት ፈጽሞ ከ230 ያላነሱ ሰዎችን አግቶ መውሰዱ ይታወሳል።ሐማስ እና እስራኤል በደረሱት ስምምነት መሠረት በቅድሚያ ታግተው የሚገኙ ሴቶች እና ሕጻናት ነጻ ይወጣሉ ተብሏል።Article share tools
ReutersCopyright: Reutersየእስራኤል ጠቅላይ ሚንስትር ቤኒያሚን ኔታኒያሁImage caption: የእስራኤል ጠቅላይ ሚንስትር ቤኒያሚን ኔታኒያሁየእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታኒያሁ ታጋቾችን ለማስለቀቅ በሚደረገው ጥረት በቅርቡ መልካም ዜና እጠብቃለሁ አሉ።ሮይተርስ የዜና ወኪል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጋዛ የሚገኙ ታጋቾችን በተመለከተ “መልካም ዜና ይኖራል ብዬ ተስፋ አድርጋለሁ” ስለማለታቸው ዘግቧል።ሐማስ መስከረም 26/2016 ዓ.ም. በእስራኤል ላይ ድንገተኛ ጥቃት አድርሶ ከ240 ያላሱ ሰዎች አግቶ ወደ ጋዛ መውሰዱን እስራኤል አሳውቃለች።ሐማስ እነዚህ ታጋቾች እንዲለቅ፣ እስራኤልም በበኩሏ የተኩስ አቁም እንድታደርግ የባሕረ ሰላጤዋ አገር ኳታር ስታደራድር ቆይታለች።ከዚህ ድርድር መልካም ውጤት እንደሚጠብቁ የኳታር የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ገልጸው ነበር።የሐማስ መሪም እንዲሁ ከእስራኤል ጋር ጊዜያዊ የተኩስ አቁም ለማድረግ ወደ ስምምነት ተቃርበናል ብለዋል።Article share tools
AFPCopyright: AFPሐማስ በእስራኤል ላይ ድንገተኛ ጥቃት አድርሶ ያገታቸውን ሰዎች ለማስለቀቅ እየተደረገ ያለው ድርድር በስምምነት ሊቋጭ ከጫፍ መድረሱን የኳታር አደራዳሪ ገለጹ።የኳታር የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማጂድ አል-አንሳሪ ከስምምነት ለመድረስ ከጫፍ ደርሰናል ብለዋል።ኳታር ሐማስ የያዛቸውን ታጋቾች እንዲለቅ፤ እስራኤልም እየተጠየቀች ላለችው የተኩስ አቁም ስምምነት አዎንታዊ ምላሽ እንድትሰጥ እስራኤል እና ሐማስን ስታደራድር ቆይታለች።ቃል አቀባዩ “. . . ስምምነት ላይ ለመድረስ ተቃርበናል” ያሉ ሲሆን ድርድሩ አሁን ያለበትን ድረጃ “ወሳኝ እና የመጨረሻው” ላይ ነው ሲሉ ገልጸውታል።ኳታር በጠላትንት የሚተያዩት የእስራኤል እና የሐማስ ‘ወዳጅ’ እንዲሁም በሁለቱ ወገኖች እምነት የሚጣልባት አገር ሆና ብቅ ብላለች።ለመሆኑ ኳታር ምዕራባውያን አሸባሪ ያሉትን ሐማስ ለምን አስጠለለች? ማደራደሩስ ይሳካላታል? ዝርዝሩን እዚህ ያንብቡ