November 22, 2023 – Konjit Sitotaw

የፋኖ ብትር  በግዴታ ስለሰላም ያናግራል።

በአማራ ክልል አሸባሪዉ የአብይ መንግስት ጦርነት ካወጀ ወራቶች ተቆጥረዋል ። የአማራ ህዝብ እንደ ህዝብ በዚህ ሰአት በገዢዉ መንግስት ግፍ እና በደል ብሎም መሳደድ ፣በጅምላ በገደል እና የተለያዩ ታሪክ የማይረሳቸዉ ግፎች እያስተናገደ ይገኛል።

የገዳዩን አብይን ሀሳብ በማራገብ ደረጃ በአዴን ሁነኛ ተላላኪ ቢሆንም ከሰሞኑ የሰላም አንባሳደር ለመምሰል በየቀኑ መግለጫ ያወጣል።

አማራ እንደሰለጠነ ማህበረሰብ ሰላማዊ በሆነ መንገድ ለህዝብ የሚገባዉን ነገር ቢጠይቅም አሸባሪዉ አብይ ጦር አዝምቶበታል። በየትኛዉም የአሸባሪም ሆነ ገዳይ ቡድን አዕምሮ የለለዉን ተግባር የአብይ ሰራዊት ፈፅሟል።
የደረሰ ሰብል አቃጥሏል ፣ ህፃናትን ገሏል ደፍሯል፣ እናቶችን ከቃያቸዉ አፈናቅሏል።

ይህንን ተግባር ሲፈፅም የነበረ ሀይል ግፍ እና በደል ያፀናዉ አማራ ፋኖ ሁነኛ በትር ሲጥልበት እና አይቀጡ ቅጣት ሲቀጣዉ ብልፅግና ባዘጋጃቸዉ የሀሰት ሚዲያዎች ብአዴኖች አጥብቀዉ ሲጮሁ እያየን ነዉ።

ደሳለኝ ጣሰዉ የተባለዉ የብልፅግና አሽከር ካለቃዉ የተቀበለዉን ትርክት በሚዲያ በመቅረብ የሚያለያየንን በመተዉ የሚያቀራርበንን  በመዉሰድ ታላቅ አገር ልንገነባ ይገባል ብሏል።
ነገር ግን ሀገር ሀገር እንዳትሆን የሀገርን በጀት ለጦር በጅቶ በንፁሀን ህዝብ ላይ እሳት ሲያዘንብ እንደሚዉል የአማራ ህዝብ ተረድቷል።

የአማራ ህዝብ ሀገሩን በክንዱ እየሰራ ይገኛል መዳረሻዉንም አዉቆ ተነስቷል።

“ወይ ፍንክች የአባቱ ልጅ”