ተዋናይት ሜሊሳ ባሬራ

ከ 3 ሰአት በፊት

የሆሊውዷ ተዋናይት ሜሊሳ ባሬራ ፍልስጤምን በመደገፍ ማህበራዊ ሚዲያ ያሰፈረቻቸው ጽሑፎች ጸረ ሴማዊ ናቸው በማለት ከምትሠራበት ፊልም እንድተባረረ ተደረገ።

ተዋናይቷ በጋዛ እየተካሄደ ስላለው ጦርነት የሚገልጹ ጽሁፎችን በማህበራዊ ሚዲያዋ ገጿ አጋርታለች። ከነዚህም ጽሁፎችን አንዱ እስራኤልን “በዘር ማጥፋት እና ዘር ማጽዳት’ የሚከሰው አንዱ ነው።

የፊልም ኩባንያው ስፓይግላስ “ለፀረ-ሴማዊነት ምንም ትዕግስት የለኝም” ብሏል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ሱዛን ሳራንደን የተባለቸውው ተዋናይት ለፍልስጤም አጋርነት በተደረገ ሰልፍ ላይ ንግግር ካደረገች በኋላ በሆሊውድ ኤጀንሲዋ ተባራለች።

ሳራንደንም ሆነች ሜክሲኳዊቷ ተዋናይ ባሬራ በሁኔታቸው ላይ አስተያየት አልሰጡም።

ባሬራ መባረሯ ከመገለጹ በፊት ባሬራ ኢንስታግራም ላይ ልትባረር እንደምትችል የሚጠቁም ጽሁፍ አጋርታለች።

ባሬራ በቀደሙት ሁለት የስክሪም ተከታታይ ፊልሞች ላይ በተዋናይነት ተሳትፋለች። በፊልም ለዕይታ በበቃው በካርመን እና ዘ ሃይትስ ላይም ተጫውታለች።

ሜሊሳ ባሬራ እና የስክሪም 6 አባላት

ባሬራ በቅርብ ሳምንታት ውስጥ ካጋራቻቸው ልጥፎች በአንዱ ሆሎካስትን በማዛባት “የእስራኤልን የጦር መሳሪያ ኢንዱስትሪ ለማካበት” ውሏል ይላል። ሌላው ልጥፍ ደግሞ ጋዛ “በአሁኑ ጊዜ እንደ ማጎሪያ ካምፕ እየታየች ነው” ይላል።

የስክሪም 7 አዘጋጅ የሆነው የስፓይግላስ ቃል አቀባይ ለቫራይቲ በሰጡት መግለጫ አቋማቸው “በማያሻማ መልኩ ግልጽ” ነው ብሏል።

“የዘር ማጥፋት፣ የዘር ማፅዳት፣ እልቂትን ማዛባት ወይም ወደ ጥላቻ ንግግር የሚያልፍ ማንኛውንም ነገር ጨምሮ ለፀረ-ሴማዊነትም ሆነ ለጥላቻ ማነሳሳት ምንም ዓይነት ትዕግስት የለንም” ብሏል።

የስክሪም 7 ዳይሬክተር ይሆናል ተብሎ የሚጠበቀው ክሪስቶፈር ሎንዶን በማህበራዊ ሚዲያ ላይ አስተያየቱን አስፍሯል።

በኋላ ላይ ከኤክስ ላይ በጠፋው ልጥፉ “ሁሉም ነገር ያማል። መጮህ አቁሙ። ይህ የእኔ ውሳኔ አይደለም” ብሏል።

ሱዛን ሳራንደን

ስክሪም ተከታታይ ፊልም በአውሮፓውያኑ 2022 የጀመረ ሲሆን፣ አምስተኛው ክፍል በቦክስ ኦፊስ 137 ሚሊዮን ዶላር. ስድስተኛው ደግሞ 169 ሚሊዮን ዶላር አስገብቷል።

ባሬራ በፊልሞቹ ውስጥ ሳም ካርፔንተር የተሰኘ ገጸ ባህርይ ተጫውታለች።

ተዋናይት ሳራንደን በወኪሏ ዩቲኤ እንደተባረረች የሚገልጸው ዜና መሰማቱን ተከትሎ ነው ባሬራ የተባረረችው።

ሳራንደን ባለፈው ሳምንት በተከናወነ የአጋርነት ሰልፍ ላይ “በዚህ ጊዜ አይሁዳዊ መሆንን የሚፈሩ ሰዎች በዚህች ሀገር ሙስሊሞች ለዘመናት ያለፉበትን መከራ እየቀመሱ ይገኛሉ” ስትል ተናግራለች።

“ሰዎች ራሳቸውን እያስተማሩ ነበር፣ በርካቶች በልጅነታቸው ጀምረው ከተሞሉበት አስተሳሰብ እየወጡ ነው” ብላለች።

ሳራንደን ለሰልፈኞቹ “ጠንካራ፣ ታጋሽ፣ ግልጽ እንዲሆኑ እና ለመናገር ድፍረት ካለው ከማንኛውም ሰው ጋር እንዲቆሙ” አበረታታለች።

ቶም ክሩዝ

ሲኤኤ የተባለው የሆሊውድ ኤጀንሲ ከፍተኛ ባለስልጣን የሆኑት ማሃ ዳኺል ስለ ግጭቱ በኢንስታግራም ባቀረቡት ጽሁፎች ተቃውሞ ገጥሟቸዋል።

“የዘር ማጥፋት ወንጀል ከመመልከት የበለጠ ምን አሳዛኝ ነገር አለ? የዘር ማጥፋት እየተፈጸመ መሆኑን ክህደት ሲፈጸም እየተመለከትን ነው” ሲሉ በአንድ ጽሑፋቸው አስፍረዋል።

በዚህ ምክንያት ዳኺል ከተንቀሳቃሽ ምስል ዲፓርትመንት ዋና ዳይሬክተር ከኃላፊነታቸው ቢነሱም ወኪል ሆነው እንዲያገለግሉ ተፈቅዶላቸዋል።

ከታዋቂ ደንበኞቿ አንዱ የሆነው ቶም ክሩዝ ዳኪልን እንደሚደግፍ ለሲኤኤ ማሳወቁ ተዘግቧል።

ለዳኺል ያለውን ድጋፍ ለማሳየት ክሩዝ ባለፈው ሳምንት በኤጀንሲው ቢሮ በአካል በመገኘት እንዳገኛቸው ተዘግቧል።