
ከ 1 ሰአት በፊት
የደቡብ አፍሪካ ምክር ቤት የተቃዋሚውን መሪ ጁሊየስ ማሌማን ለአንድ ወር አገደ።
ከማሌማ በተጨማሪም ለምጣኔ ኃብት እኩልነት የሚታገለው ፓርቲው ‘ኢኮኖሚክ ፍሪደም ፋይተርስ’ አምስት አባላትም እንዲሁ እግድ ተጥሎባቸዋል።
የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎሳ በኬፕታውን አዳራሽ ብሄራዊ ንግግር እያደረጉ በነበረበት ወቅት ጁሊየስ ማሌማ እና ሌሎች አባላቱ መድረኩን በመረበሻቸው ፓርላማውን ንቀዋል ተብሏል።
ፓርላውንም በመናቅ ጥፋተኛ ሆነው ተገኝተዋል የተባሉት የምክር ቤቱ አባላት በታገዱበት በአንድ ወር ወቅት ያለውንም ደመወዝ አይከፈላቸውም።
ማሌማ እና ሌሎች የምክር ቤቱ አባላት ከአዳራሹ በጸጥታ ኃይሎች እንዲወጡ የተደረጉ ሲሆን የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤም ሂደቱ እንዲቋረጥ አድርገዋል።
የእግዱን ውሳኔ ያስተላለፈው የፓርላማው ኮሚቴ “ የፕሬዚዳንቱን መግለጫ አቋርጠው በመበጥበጣቸው እና የአገሪቱንም ምስል በማጠልሸታቸው እነዚህ የምክር ቤቱ አባላት በአካል ፕሬዚዳንቱን ይቅርታ እንዲጠይቁ እንዲሁም አፈ ጉባኤውን እና ህዝቡንም ይቅርታ እንዲጠይቁ” ተወስኖባቸዋል።
- ጁሊየስ ማሌማ፡የደቡብ አፍሪካዊው አብዮተኛ ንግግር ለምን በኬንያ አነጋጋሪ ሆነ?13 ህዳር 2023
- በደቡብ አፍሪካ የፖለቲካ መድረክ ነውጥን በመፍጠር የሚወቀሰው ጁሊየስ ማሌማ1 ነሐሴ 2023
- ‘ የፍልስጤማውያንን ህጻናት ግድያ የደገፉት’ የኦባማ የቀድሞ ረዳት በቁጥጥር ስር ዋሉከ 4 ሰአት በፊት
ስድስቱ የምክር ቤት አባላት እግድ የሚጀምረው በመጪው ጥር ወር ሲሆን ፕሬዚዳንቱ በየካቲት ወር ሊያደርጉት ያቀዱት ብሄራዊ ንግግር የሚያመልጣቸው ይሆናል።
የምክር ቤቱ አባላቱ እግዱ እንዲተላለፍ ያቀረቡት ጥያቄ ውድቅ መደረጉንም ተከትሎ ፓርላማው በነሱ ላይ በሚያሳልፈው ውሳኔ አልተገኙም።
ጁሊየስ ማሌማ በአንድ ወቅት የኤኤንሲ ፓርቲ የወጣቶች ክንፍ መሪ ነበር።
ጃኮብ ዙማ ወደ ሥልጣን እንዲወጡ አስተዋፅዖ ቢያደርግም ሁለቱ ሰዎች ባለመስማማታቸው ማሌማ ከፓርቲው ተወገደ።
የኢኤፍኤፍ መሪ ሆኖ በለተይ የቀድሞው ፕሬዝደንት የመንግሥት ገንዘብ ተጠቅመው የግል መኖሪያቸውን አድሰዋል በሚል ከተከሰሱ በኋላ ፀረ-ዙማ ዘመቻ በማካሄድ ቀንደኛው ነበር።
ብዙዎቹ ማሌማ በፈረንጆቹ 2012 ከፓርቲው ሲወገድ የፖለቲካ ሕይወቱ አበቃለት ብለው ነበር።
