በእስራኤል እና በሐማስ መካከል በተደረሰው ስምምነት መሠረት ለአራተ ቀናት የሚቆየው የተኩሰ አቁም ዛሬ ሐሙስ ረፋድ አራት ሰዓት ላይ እንደሚጀምር ሐማስ አስታወቀ።

Related Video and Audio

VIDEO 1 MINUTE 44 SECONDSVIDEO 1 MINUTE 44 SECONDS1:44

Play video በሐማስ ጥቃት የሞቱ ወታደሮችን አስከሬን ለማግኘት እስራኤል እንዴት የንስር ወፍን ተጠቀመች? from BBCበሐማስ ጥቃት የሞቱ ወታደሮችን አስከሬን ለማግኘት እስራኤል እንዴት የንስር ወፍን ተጠቀመች?

Play video በሐማስ ጥቃት የሞቱ ወታደሮችን አስከሬን ለማግኘት እስራኤል እንዴት የንስር ወፍን ተጠቀመች? from BBC

VIDEO 1 MINUTE 18 SECONDSVIDEO 1 MINUTE 18 SECONDS1:18

Play video ሕይወት በጋዛ፡ “ጦርነቱ መቶ ዓመታትን ወደኋላ መልሶናል” from BBCሕይወት በጋዛ፡ “ጦርነቱ መቶ ዓመታትን ወደኋላ መልሶናል”

Play video ሕይወት በጋዛ፡ “ጦርነቱ መቶ ዓመታትን ወደኋላ መልሶናል” from BBC

VIDEO 2 MINUTES 31 SECONDSVIDEO 2 MINUTES 31 SECONDS2:31

Play video ‘ቢያንስ ሆስፒታሉ ጥቃት አይደርስበትም ብለን አስበን ነበር’፡ ከሆስፒታል የሸሹ የጋዛ ነዋሪዎች from BBC‘ቢያንስ ሆስፒታሉ ጥቃት አይደርስበትም ብለን አስበን ነበር’፡ ከሆስፒታል የሸሹ የጋዛ ነዋሪዎች

Play video ‘ቢያንስ ሆስፒታሉ ጥቃት አይደርስበትም ብለን አስበን ነበር’፡ ከሆስፒታል የሸሹ የጋዛ ነዋሪዎች from BBC

VIDEO 2 MINUTESVIDEO 2 MINUTES2:00

Play video ጋዛን የጎበኘው ቢቢሲ የዓለም አቀፍ ኤዲተር ጄረሚ ቦውን እይታ from BBCጋዛን የጎበኘው ቢቢሲ የዓለም አቀፍ ኤዲተር ጄረሚ ቦውን እይታ

Play video ጋዛን የጎበኘው ቢቢሲ የዓለም አቀፍ ኤዲተር ጄረሚ ቦውን እይታ from BBC

VIDEO 1 MINUTE 30 SECONDSVIDEO 1 MINUTE 30 SECONDS1:30

Play video አሜሪካ ከ60 በላይ አውሮፕላን ተሸካሚ ሁለተኛ መርከቧን ወደ እስራኤል አስጠጋች from BBCአሜሪካ ከ60 በላይ አውሮፕላን ተሸካሚ ሁለተኛ መርከቧን ወደ እስራኤል አስጠጋች

Play video አሜሪካ ከ60 በላይ አውሮፕላን ተሸካሚ ሁለተኛ መርከቧን ወደ እስራኤል አስጠጋች from BBC

VIDEO 1 MINUTE 48 SECONDSVIDEO 1 MINUTE 48 SECONDS1:48

Play video ሐማስ ጋዛ ውስጥ የገነባቸው ወደ እስራኤል የሚያሻግሩት ዋሻዎች from BBCሐማስ ጋዛ ውስጥ የገነባቸው ወደ እስራኤል የሚያሻግሩት ዋሻዎች

Play video ሐማስ ጋዛ ውስጥ የገነባቸው ወደ እስራኤል የሚያሻግሩት ዋሻዎች from BBC

VIDEO 3 MINUTES 27 SECONDSVIDEO 3 MINUTES 27 SECONDS3:27

Play video ሕይወት በጋዛ፡ ከቤታቸው ወጥተው መጠለያ ፍለጋ መንከራተት from BBCሕይወት በጋዛ፡ ከቤታቸው ወጥተው መጠለያ ፍለጋ መንከራተት

Play video ሕይወት በጋዛ፡ ከቤታቸው ወጥተው መጠለያ ፍለጋ መንከራተት from BBC

ጭምቅ ሃሳብ

  1. ለአራት ቀናት የሚቆየው ተኩስ አቁም ነገ ሐሙስ ረፋድ አራት ሰዓት ይጀምራል
  2. ይህ ጦርነት ሳይሆን ሽብርተኝነት ነው፡ ፖፕ ፍራንሲስ
  3. ዶ/ር ቴድሮስ ባልደረባቸው ከአራት ቤተሰቧ ጋር መገደሏን አስታወቁ
  4. ደቡብ አፍሪካ የእስራኤል ኤምባሲ እንዲዘጋ እና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቷ እንዲቋረጥ ወሰነች
  5. የእስራኤል ካቢኔ የታገቱትን ነጻ ለማውጣት የተደረሰውን ስምምነት አፀደቀ
  6. ሐማስ እና እስራኤል ‘ጊዜያዊ የተኩስ አቁም’ ለማድረግ ወደ ስምምነት ተቃርበዋል ተባለ
  7. ዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት ኔታንያሁ ላይ የእስር ትዕዛዝ እንዲያወጣ ደቡብ አፍሪካ ጠየቀች
  8. በጋዛ የተገደሉ ፍልስጤማውያን ቁጥር 13 ሺህ ደረሰ- የጋዛ ጤና ሚኒስቴር
  9. የኳታር ጠቅላይ ሚኒስትር ታጋቾችን የማስለቀቅ ስምምነት ላይ ‘መተማመን መጨመሩን’ ተናገሩ
  10. የጃፓን ዕቃ ጫኝ መርከብ ቀይ ባሕር ላይ በየመን ሁቲ አማጺያን ታገተ
  11. እስራኤል ተመድ ባቋቋመው የትምህርት ቤት መጠለያ ባደረሰችው ጥቃት በርካቶች መገደላቸው ተነገረ

ቀጥታ ዘገባ

  1. የታተመዉ 5:215:21የጋዛ ትልቁ ሆስፒታል አልሺፋ ዳይሬክተር በእስራኤል መከላከያ በቁጥጥር ስር ዋሉየአልሺፋ ሆስፒታልReutersCopyright: Reutersየጋዛ ትልቁ ሆስፒታል አልሺፋ ዳይሬክተር በእስራኤል መከላከያ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የሆስፒታሉ የህክምና ባለሙያ ተናገሩ። ዳይሬክተሩ አቡ ሳላሚያ ከሆስፒታሉ የሚወጡ ህመምተኞችን አጅበው ባሉበት ሰዓት በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የአልሺፋ የአጥንት ህክምና ክፍል ኃላፊ ዶክተር አድናን አል ቡርሽ ገልጸዋል።የእስራኤል መከላከያ በጉዳዩ ላይ የሰጠው አስተያየት የለም።እስራኤል የሐማስ እዝ በሆስፒታሉ ስር አለ በሚል በአልሺፋ ላይ ወረራ በመፈጸም ተቆጣጥራው ትገኛለች።ሐማስም ሆነ የሆስፒታሉ የህክምና ባለሙያዎች ይህንን ክስ አይቀበሉትም። የእስራኤል ጦር ባለፈው ሳምንት ሆስፒታሉን ከተቆጣጠረ በኋላ የሐማስ ዋሻ ነው ያለውን እና 55 ሜትር እርዝማኔ አለው ያለውቪዲዮ አሳይቷል።ህሙማንን ጨምሮ በመቶዎች የሚቆጠሩ ፍልስጤማውያን ሆስፒታሉን ለቀው እንዲወጡ በእስራኤል ትዕዛዝ ተሰጥቶናል በሚል በእግራቸው ሸሽተዋል። እስራኤል ትዕዛዝ አልሰጠሁም ስትል አስተባብላለች።Article share tools
  2. የታተመዉ 4:534:53እስራኤል በራፋህ ያደረሰቻቸው የአየር ጥቃቶች በምስልእስራኤል በግብጽ እና ጋዛ የድንበር ማቋረጫ ራፋህ የአየር ጥቃቶችን ፈጽማለች።በኻን ዩኒስ አቅራቢያ የምትገኘው ራፋህ እስራኤል በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ፍልስጤማውያን ሰሜናዊ ጋዛን ለቀው እንዲሸሹባት ከተመረጡት ከተሞች አንዷ ናት።የእስራኤል መከላከያ በበኩሉ ባለፉት 24 ሰዓታት በፈጸመው ጥቃቶች 300 የሐማስ ኢላማዎችን መትቻለሁ ብሏል።የራፋህ የአየር ጥቃትGetty ImagesCopyright: Getty Imagesየራፋህ የአየር ጥቃትGetty ImagesCopyright: Getty Imagesየራፋህ የአየር ጥቃትGetty ImagesCopyright: Getty ImagesArticle share tools
  3. የታተመዉ 4:454:45የጋዛ ጊዜያዊ የተኩስ አቁም ስምምነት የዘገየው ከታጋቾች ዝርዝር ጋር በተያያዘ ነው ተባለየጋዛ ጥቃትGetty ImagesCopyright: Getty Imagesዛሬ፣ ሐሙስ ረፋድ ላይ ተግባራዊ እንዲሆን ሲጠበቅ የነበረው ጊዜያዊ የተኩስ አቁም ለመዘግየቱ ከታጋቾች ዝርዝር ጋር በተያያዘ መሆኑን የፍልስጤም ባለስልጣናት ገለጹ።የዘገየውም በመጨረሻዋ ሰዓት መሆኑንም ለአጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ተናግረዋል።የትኞቹ ታጋቾች ይለቀቁ? እንዴት? በሚለውም ዝርዝር ምክንያትም መራዘሙ ተነግሯል። ጊዜያዊ የተኩስ አቁሙም አርብ ተግባራዊ ሊሆን እንደሚችልም የእስራኤል መንግሥት ምንጭ ለቢቢሲ ተናግረዋል።የቀረውም ጉዳይ የሎጂስቲክ እንደሆነም ነው የተናገሩት።ኳታር በበኩሏ የተኩስ አቁም ስምምነቱ መቼ እንደሚጀምር በቀጣዩ ሰዓታት እንደሚገለጽ አስታውቃለች።የኳታር መንግሥት ቃለ አቀባይ እንደተናገሩት ከእስራኤል እና ሐማስ ጋር የተደረገው ስምምነት የተያያዘው ውይይት ቀጥሏል ብለዋል። በነዚህም ውይይቶች ላይ ግብጽ እና አሜሪካ የሚሳተፉ ሲሆን “ጦርነቱ ጋብ የሚልባቸውን ቀናት ፈጠን ብሎ የማስጀመር እንዲሁም ሁለቱ ወገኖች ስምምነቱ እንዲያከብሩ የሚያስፈልጉ ጉዳዮችም ውይይቱ ቀጥሏል” ተብሏል።Article share tools
  4. የታተመዉ 3:033:03እስራኤል በጃባሊያ የስደተኞች መጠለያ በፈጸመችው ጥቃት የአንድ ቤተሰብ 52 አባላት ተገደሉየጋዛ ጥቃትAFPCopyright: AFPእስራኤል ረቡዕ በጃባሊያ የስደተኞች መጠለያ በፈጸመችው ጥቃት የአንድ ቤተሰብ አምሳ ሁለት አባላት መገደላቸውን የፍልስጤም ባለስልጣናት አስታውቀዋል።እስራኤል በጋዛ ላይ እየፈጸመችው ያለው የማያባራ የአየር ጥቃት ዛሬ ረፋድ ተግባራዊ ይሆናል ተብሎ በነበረው ጊዜያዊ የተኩስ አቁም ስምምነት ጋብ እንደሚል ተጠብቆ ነበር። ነገር ግን የተኩስ አቁም ስምምነት ተግባራዊ አልሆነም፤ መቼ እንደሚጀምርም ግልጽ አልሆነም።የፍልስጤም አስተዳደር የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ሪያድ አል ማሊኪ በስደተኞቹ መጠለያ በተፈጸመው ጥቃት የተገደሉት 52 ሰዎች የአንድ ቤተሰብ አባላት መሆናቸውንም ገልጸዋል።“ዛሬ ጥዋት ብቻ በጃባሊያ የስደተኞች መጠለያ የኳድራ ቤተሰብ 52 አባላት ለዘር እንዳይተርፉ ሆነው ተፈጅተዋል” ብለዋል።ቢቢሲ ይህንን በገለልተኝነት ማረጋገጥ አልቻለም። የፍልስጤም አስተዳደር መቀመጫውን እስራኤል በኃይል በያዘቻት ዌስት ባንክ ያደረገ ነው።Article share tools
  5. የታተመዉ 2:142:14የጋዛው ጊዜያዊ የተኩስ አቁም ስምምነት እንደሚዘገይ ተገለጸየጋዛ ጥቃትReutersCopyright: Reutersየጋዛው ጦርነት ጊዜያዊ የተኩስ አቁም ስምምነት ዛሬ ረፋድ ላይ ተግባራዊ እንዲደረግ በእስራኤል እና በሐማስ መካከል ስምምነት ላይ ቢደረስም ቢቢሲ እንደሚዘገይ ከእስራኤል መንግሥት ምንጭ መረጃ ሰምቷል።በጋዛ የታገቱት ከአርብ በፊት እንደማይለቀቁ የእስራኤል ከፍተኛ ባለስልጣን ተናግረዋል።በእስራኤል እና በሐማስ መካከል በተደረገው ስምምነት ላይ ንግግሮች መቀጠላቸውን የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ብሔራዊ የጸጥታ አማካሪ ትዛኪ ዘኔግቢ ባወጡት መግለጫ አስታውቀዋል። ቀደም ብሎ የእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ የመጀመሪያዎቹ ታጋቾች ሐሙስ እንደሚለቀቁ አስታውቆ ነበር።በስምምነቱ መሰረትም በሐማስ የተወሰዱ 50 ታጋቾች የሚለቀቁ ሲሆን በልውውጡም እስራኤል ካሰረቻቸው ፍልስጤማውያን ውስጥ 150 ሴቶች እና ህጻናት የሚለቀቁ ይሆናል።ሰባተኛ ሳምንቱን በያዘው የጋዛው ጦርነት ከ13 ሺህ በላይ ፍልስጤማውያን ሲገደሉ ከነዚህም በርካቶቹ ህጻናት መሆናቸውን የጋዛ ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል። ከእስራኤል በኩል ደግሞ 1 ሺህ 200 ተገድለዋል።Article share tools
  6. የታተመዉ 2:132:13የሆሊውዷ ተዋናይት እስራኤልን ‘በማውገዟ’ ከስክሪም ተከታታይ ፊልም ተባረረችየሆሊውዷ ተዋናይት ሜሊሳ ባሬራ ፍልስጤምን በመደገፍ ማህበራዊ ሚዲያ ያሰፈረቻቸው ጽሑፎች ጸረ ሴማዊ ናቸው በማለት ከምትሠራበት ፊልም እንድተባረረ ተደረገ። ተዋናይቷ በጋዛ እየተካሄደ ስላለው ጦርነት የሚገልጹ ጽሁፎችን በማህበራዊ ሚዲያዋ ገጿ አጋርታለች። ከነዚህም ጽሁፎችን አንዱ እስራኤልን “በዘር ማጥፋት እና ዘር ማጽዳት’ የሚከሰው አንዱ ነው።ተጨማሪ ያንብቡArticle share tools
  7. የታተመዉ 2:132:13‘ የፍልስጤማውያንን ህጻናት ግድያ የደገፉት’ የኦባማ የቀድሞ ረዳት በቁጥጥር ስር ዋሉበቀድሞ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ የስልጣን ዘመን የውጪ ጉዳይ ረዳት የነበሩት ባለስልጣን በጋዛ የደረሰውን የፍልስጤማውያንን ግድያ በመደገፍ እና የእስልምና እምነትን በማንቋሸሸቻው በቁጥጥር ስር ዋሉ።ተጨማሪ ያንብቡArticle share tools
  8. የታተመዉ 2:132:13እስራኤል ልታጠፋው ቀን ከሌት የምትፈልገው በጋዛ የሐማስ መሪ ያህያ ሲንዋር ማን ነው?ያህያ ሲንዋር ደብዛው ጠፍቷል። ለነገሩ በሺዎች የሚቆጠሩት የእስራኤል ወታደሮች በሰላዮች እና ድሮኖች ታግዘው ያለበትን ለማወቅ በሚያነፈንፉበት ወቅት አድራሻውን ማጥፋቱ አይገርምም።ተጨማሪ ያንብቡArticle share tools
  9. የታተመዉ 9:20 22 ህዳር 20239:20 22 ህዳር 2023ለአራት ቀናት የሚቆየው ተኩስ አቁም ዛሬ ሐሙስ ረፋድ አራት ሰዓት ይጀምራልራፋህ ውስጥ ከተፈጸመ የአየር ጥቃት በኋላ ከፍርስራሽ ስር በሕይወት ያሉ ሰዎችን ለመፈለግ የሚጥሩ ሰዎችAFPCopyright: AFPራፋህ ውስጥ ከተፈጸመ የአየር ጥቃት በኋላ ከፍርስራሽ ስር በሕይወት ያሉ ሰዎችን ለመፈለግ የሚጥሩ ሰዎችImage caption: ራፋህ ውስጥ ከተፈጸመ የአየር ጥቃት በኋላ ከፍርስራሽ ስር በሕይወት ያሉ ሰዎችን ለመፈለግ የሚጥሩ ሰዎችበእስራኤል እና በሐማስ መካከል በተደረሰው ስምምነት መሠረት ለአራተ ቀናት የሚቆየው የተኩሰ አቁም ዛሬ ሐሙስ ረፋድ አራት ሰዓት ላይ እንደሚጀምር ሐማስ አስታወቀ።ቢቢሲ ከምንጮቹ ማረጋገጥ እንደቻለው ከአንድ ወር በላይ እየተካሄደ ያለውን ውጊያ ለአራት ቀናት ጋብ ለማድረግ የተደረሰው ስምምነት ሐሙስ ተግባራዊ መሆን ይጀምራል።የተኩስ አቁሙ እውን ከሆነ ከሰዓታት በኋላ ደግሞ በሐማስ እጅ ከሚገኙት ታጋቾች የመጀመሪያዎቹ ከሰዓት በኋላ ይለቀቃሉ ተብሎ ይጠበቃል።የሐማስ ፖለቲካ ቢሮ ኃላፊ ሙሳ አቡ ማርዙክ ለአል-ጃዚራ ቴሌቪዥን እንደተናገሩት ለቀናት የሚዘልቀው ውጊያ ጋብ የማድረግ ስምምነት የመጀመሪያዎቹ ታጋቾች ከመለቀቃቸው ከሰዓታት በፊት ተግባራዊ እንደሚሆን አረጋግጠዋል።የግብፅ የደኅንነት ምንጮች ለሮይተርስ ዜና ወኪል ተኩስ ማቆሙ ሐሙስ ረፋድ አራት ሰዓት ላይ ተግባራዊ እንዲሆን አደራዳሪዎች መፈለጋቸውን ተናግረዋል።ለዚህም ምክንያቱ ታጋቾቹን ከመልቀቁ በፊት ሐማስ “ጥቂት ሰዓታት” እንደሚያስፈልገው በመግለጹ መሆኑነ ተናግረዋል።የእስራኤል የመከላከያ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ውጊያው ጋብ ማለት የሚጀምረው “ሐሙስ በሆነ ሰዓት ላይ” እንደሆነ ለሮይተርስ ገልጸዋል።በተጨማሪም የዜና ወኪሉ የአስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኤሊ ኮኽን ምንም እንኳን ትክክለኛውን ሰዓት ከመግለጽ ቢቆጠቡም እስራኤል የመጀመሪያዎቹን ነጻ የሚወጡ ታጋቾች ሐሙስ ዕለት እንደሚቀበሉ መናገራቸውን ዘግቧል።Article share tools
  10. የታተመዉ 6:10 22 ህዳር 20236:10 22 ህዳር 2023ይህ ጦርነት ሳይሆን ሽብርተኝነት ነው፡ ፖፕ ፍራንሲስፖፕ ፍራንሲስReutersCopyright: Reutersፖፕ ፍራንሲስImage caption: ፖፕ ፍራንሲስየካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ጳጳስ የሆኑት ፖፕ ፍራንሲስ በእስራኤል እና በሐማስ መካከል እየተካሄደ ያለው ግጭት ጦርነት ሳይሆን “ሽብርተኝነት” ነው አሉ።ጳጳሱ ይህንን የተናገሩት በሐማስ የታገቱ ሰዎች ቤተሰቦችን እና በጋዛ ውስጥ የሚኖሩ ዘመዶች ያሏቸውን ሰዎች በተናጠል አግኝተው ባነጋገሩበት ወቅት ነው።ፖፕ ፍራንሲስ አስካሁን እየተካሄደ ያለው የእስራኤል-ሐማስ ግጭት ከጦርነት በላይ በመሆን “የሽብር ድርጊት” እየሆነ ነው ብለዋል።በዚህም ሁለቱም ፍልስጤማውያን እና እስራኤላውያን “እየተሰቃዩ ነው” ሲሉ ጦርነቱ በሕዝቡ ላይ ያስከተለውን ጉዳት በጥብቅ አውግዘዋል።ቫቲካን ውስጥ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ በሚገኘው መኖሪያቸው በርካታ ሰዎችን በየሳምንቱ ከሚያገኙበት ሥነ ሥርዓት በኋላ ጳጳሱ ባደረጉት ንግግር “ሁለቱም ወገኖች እንደተሰቃዩ ሰምቻለሁ፣ በጣም ተሰቃይተዋል” ብለዋል።ጨምረውም “ሰላም እንዲሰፍን ወደፊት እንጓዝ. . . ሁላችሁም ተባረኩ” ሲሉ ለሰላም ጥሪ አቅርበዋል።Article share tools
  11. የታተመዉ 3:56 22 ህዳር 20233:56 22 ህዳር 2023ዶ/ር ቴድሮስ ባልደረባቸው ከአራት ቤተሰቧ ጋር መገደሏን አስታወቁዲማ አለሃጅ ከስድስት ወር ልጇ፣ ከባለቤቷ እና ከሁለት ወንድሞቿ ጋር ትናንት ተገድላለች።Tedros Adhanom GhebreyesusCopyright: Tedros Adhanom Ghebreyesusዲማ አለሃጅ ከስድስት ወር ልጇ፣ ከባለቤቷ እና ከሁለት ወንድሞቿ ጋር ትናንት ተገድላለች።Image caption: ዲማ አለሃጅ ከስድስት ወር ልጇ፣ ከባለቤቷ እና ከሁለት ወንድሞቿ ጋር ትናንት ተገድላለች።የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ቴድሮስ አድሃኖም አንድ ባልደረባቸው ከአራት የቤተሰብ አባሎቿ ጋር ጋዛ ውስጥ መገደሏን አስታወቁ።ዲማ አልሃጅ የተባለችው የዓለም ጤና ድርጅት ባልደረባ ከስድስት ወር ልጇ፣ ከባለቤቷ እና ከሁለት ወንድሞቿ ጋር ትናንት ማክሰኞ መገደሏን ገልጸዋል።“ሐዘናችንን የምገልጽበት ቃላት የለኝም” ብለዋል ዋና ዳይሬክተሩ በኤክስ (ትዊተር) ገጻቸው ላይ።ዶ/ር ቴድሮስ ጨምረውም ከመስከረም 26 ወዲህ 108 የተባበሩት መንግሥታት ሠራተኞች በጋዛ መገደላቸውን ገልጸዋል።Article share tools
  12. የታተመዉ 3:18 22 ህዳር 20233:18 22 ህዳር 2023ደቡብ አፍሪካ የእስራኤል ኤምባሲ እንዲዘጋ እና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቷ እንዲቋረጥ ወሰነችየደቡብ አፍሪካ ምክር ቤት በፕሪቶሪያ የሚገኘው የእስራኤል ኤምባሲ እንዲዘጋ እና ከእስራኤል ጋር ያለ ሁሉም ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እንዲቋረጥ ወሰነ።ተጨማሪ ያንብቡArticle share tools
  13. የታተመዉ 2:20 22 ህዳር 20232:20 22 ህዳር 2023እስራኤል ከእስር የምትለቃቸውን ፍልስጤማውያንን ዝርዝር አወጣችየእስራኤል እስር ቤት (ፋይል ፎቶ)Getty ImagesCopyright: Getty Imagesየእስራኤል እስር ቤት (ፋይል ፎቶ)Image caption: የእስራኤል እስር ቤት (ፋይል ፎቶ)እስራኤል ከሐማስ ጋር በተደረሰው ስምምነት መሠረት ከእስር የምትለቃቸውን 300 ፍልስጤማውያንን ዝርዝር ይፋ አደረገች።በእስራኤል የፍትሕ ሚኒስቴር ገጽ ላይ የወጣው ዝርዝር የታሳሪዎችን ስም፣ እድሜ እና ለእስር ተዳርገውበታል የተባለው የሕግ ጥሰትን ዘርዝሯል።አብዛኞቹ ታሳሪዎች ከ14 እስከ 18 የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ሲሆን፤ ድንጋይ መወርወር፣ ከሐማስ ጋር ግንኙነት መፍጠር ወይም የሐማስን ጥቃት ማወደስ ከሚሉ ክሶች አንስቶ ቦምብ መወርወር እንዲሁም የግድያ ሙከራ መፈጸም የሚሉ ክሶች የቀረቡባቸው ናቸው።እስራኤል 300 ፍልስጤማውያንን እለቃለሁ ብትልም በስምምነቱ መሠረት በመጀመሪያው ዙር የሚለቀቁት እስረኞች 150 ሰዎች ናቸው።ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብቶች ተከራካሪ ድርጅት ሂዩማን ራይትስ ዋች ከ7ሺህ ያላነሱ ፍልስጤማውያን በእስራኤል እስር ቤቶች ውስጥ እንደሚገኙ የገለጸ ሲሆን፣ ከእነዚህ መካከል 200 ሴቶች እና 60 ልጆች ይገኙባቸዋል።የሂዩማን ራይትስ ዋች ዳይሬክተር ሳሪ ባሺ የፍልስጤማውያን ታዳጊዎች ጉዳይ በእስራኤል ወታደራዊ ሕግ እንዲታይ በመደረጉ ወላጆች ወይም ጠበቆች በሌሉበት እንዲመረመሩ እና ለተራ ጥፋቶች ለረዥም ሰዓት በእስር እንዲቆዩ ይደረጋሉ ብለዋል።Article share tools
  14. የታተመዉ 0:09 22 ህዳር 20230:09 22 ህዳር 2023ኳታር የሐማስ እና እስራኤል የደረሱት ስምምነት መቼ ተግባራዊ እንደሚደረግ ይፋ ይደረጋል አለችበጋዛ ያሉ ስደተኞችGetty ImagesCopyright: Getty Imagesበእስራኤል እና በሐማስ መካከል ስምምነት እንዲደርስ ያስቻለችው ኳታር ሐማስ እና እስራኤል የደረሱት ስምምነት መቼ ተግባራዊ እንደሚደረግ ይፋ አድርጋለች።በዚህም የባሕረ ሰላጤዋ አገር “የተኩስ አቁም የሚጀምርበት ጊዜ በሚቀጥሉት 24 ሰዓታት ውስጥ ይፋ ይሆናል” ብላለች።የተኩስ አቁሙ ለአራት ቀናት ይቆያል ከማለት ባለፈ “ሊራዘም ይችላል” ስትል አስታውቃለች።Article share tools
  15. የታተመዉ 0:03 22 ህዳር 20230:03 22 ህዳር 2023ሐማስ 150 ፍልስጤማውያን ከእስራኤል እስር ነጻ ይወጣሉ አለሐማስ ከእስራኤል ጋር በደረሰው ስምምነት መሠረት 150 ፍልስጤማውያን ከእስራኤል እስር ቤት ይወጣሉ አለ።ሐማስ ከእስራኤል አግቶ ከያዛቸው መካከል 50 ሰዎችን ለመልቀቅ መስማማቱ ይታወሳል። 50ዎቹ ታጋቾች በእስራኤል እስር ቤቶች ውስጥ ባሉ 150 ፍልስጤማውያን ሴቶች እና ህጻናት ምትክ እንደሚለቀቁ ገልጿል።በስምምነቱ መሠረት በመቶዎች የሚቆጠሩ የሰብዓዊ እርዳታ፣ የህክምና ቁሳቁስ እና ነዳጅ የጫኑ የጭነት መኪናዎች ወደ ጋዛ እንዲገቡ ያስችላል ሲል ሐማስ ገልጿል።እስራኤል ለጦርነቱ ፋታ በምትሰጥበት ወቅት በጋዛ ማንንም እንደማታጠቃ እና እንደማታሰር መግለጿን መግለጫው አክሏል።በአራቱ ቀናት በደቡባዊ ጋዛ የአየር ትራፊክ ሙሉ በሙሉ ይቆማል። በሰሜን ጋዛ ደግሞ ለስድስት ሰዓታት እንደሚቆም ተናግሯል።ዩናይትድ ኪንግደም እና አሜሪካን ጨምሮ በበርካታ አገራት አሸባሪ ተብሎ የተፈረጀው ሐማስ መስከረም 26 አሰቃቂ ጥቃት ከመፈጸም ባለፈ ወደ 230 የሚጠጉ ሰዎችን አፍኖ ወስዷል።Article share tools
  16. የታተመዉ 23:46 21 ህዳር 202323:46 21 ህዳር 2023ባይደን ታጋቾችን ለማስለቀቅ የተደረሰውን ስምምነት አወደሱባይደን እና ኔታኒያሁEPACopyright: EPAጆ ባይደን “ለሳምንታት በእስር እና በቃላት ሊገለጽ የማይችል መከራ” ሲያሳልፉ ከነበሩ ታጋቾች መካከል አንዳንዶቹ ከቤተሰቦቻቸው ጋር ሊቀላቀሉ መሆኑ “በጣም አስደስቶኛል” ብለዋል።የአሜሪካው ፕሬዝዳንት የኳታር እና የግብጽ መሪዎች ስምምነቱ እንዲደረስ ላሳዩት “ወሳኝ አመራር እና አጋርነት” አመስግነዋቸዋል።የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ለጦርነቱ ፋታ ለመስጠት ላሳዩት “ቁርጠኝነት” አድናቆታቸውን ችረዋቸዋል።”የዚህ ስምምነት ሃሳቦች ሙሉ በሙሉ መተግበራቸው አስፈላጊ ነው” ሲል አጽንኦት ሰጥተዋል።በስምምነቱ መሠረት በርካታ ሰብዓዊ ድጋፍ ወደ ጋዛ እንዲገባ በማገዛቸውም ኔታንያሁን አመስግነዋቸዋል።“ይህም በጋዛ የሚገኙ ንጹሐን ፍልስጤማውያን ቤተሰቦችን ያግዛል” ብለዋል።በመቶዎች የሚቆጠሩ መድኃኒት እና ነዳጅ የጫኑ ተሽከርካሪዎች በስምምነቱ መሠረት ጋዛ እንዲገቡ ይፈቀድላቸዋል።Article share tools
  17. የታተመዉ 23:36 21 ህዳር 202323:36 21 ህዳር 2023የእስራኤል ካቢኔ የታገቱትን ነጻ ለማውጣት የተደረሰውን ስምምነት አፀደቀየታጋች ቤተሰብGetty ImagesCopyright: Getty Imagesየእስራኤል ካቢኔ በሐማስ ታግተው የሚገኙ 50 ሰዎችን ነጻ ለማውጣት የተደረሰውን ስምምነት አጸደቀ።የእስራኤል ጠቅላይ ሚንስትር ጽህፈት ቤት 50 ታጋቾች በአራት ቀናት ውስጥ እንደሚለቀቁ አስታውቋል።በምላሹ እስራኤል የተኩስ አቁም ለማድረግ ተስማምታለች።በስምምነቱ መሠረት በመጀመሪያዎቹ አራት ቀናት ከሚለቀቁ 50 ታጋቾች በተጨማሪ “10 ታጋቾች በተለቀቁ ቁጥር አንድ ተጨማሪ የተኩስ አቁም ቀን ይኖራል” ተብሏል።ሐማስ መስከረም 26 በእስራኤል ላይ ድንገተኛ ጥቃት ፈጽሞ ከ230 ያላነሱ ሰዎችን አግቶ መውሰዱ ይታወሳል።ሐማስ እና እስራኤል በደረሱት ስምምነት መሠረት በቅድሚያ ታግተው የሚገኙ ሴቶች እና ሕጻናት ነጻ ይወጣሉ ተብሏል።Article share tools
  18. የታተመዉ 9:10 21 ህዳር 20239:10 21 ህዳር 2023ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታኒያሁ “ታጋቾች ነጻ ይወጣሉ ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ” አሉየእስራኤል ጠቅላይ ሚንስትር ቤኒያሚን ኔታኒያሁReutersCopyright: Reutersየእስራኤል ጠቅላይ ሚንስትር ቤኒያሚን ኔታኒያሁImage caption: የእስራኤል ጠቅላይ ሚንስትር ቤኒያሚን ኔታኒያሁየእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታኒያሁ ታጋቾችን ለማስለቀቅ በሚደረገው ጥረት በቅርቡ መልካም ዜና እጠብቃለሁ አሉ።ሮይተርስ የዜና ወኪል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጋዛ የሚገኙ ታጋቾችን በተመለከተ “መልካም ዜና ይኖራል ብዬ ተስፋ አድርጋለሁ” ስለማለታቸው ዘግቧል።ሐማስ መስከረም 26/2016 ዓ.ም. በእስራኤል ላይ ድንገተኛ ጥቃት አድርሶ ከ240 ያላሱ ሰዎች አግቶ ወደ ጋዛ መውሰዱን እስራኤል አሳውቃለች።ሐማስ እነዚህ ታጋቾች እንዲለቅ፣ እስራኤልም በበኩሏ የተኩስ አቁም እንድታደርግ የባሕረ ሰላጤዋ አገር ኳታር ስታደራድር ቆይታለች።ከዚህ ድርድር መልካም ውጤት እንደሚጠብቁ የኳታር የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ገልጸው ነበር።የሐማስ መሪም እንዲሁ ከእስራኤል ጋር ጊዜያዊ የተኩስ አቁም ለማድረግ ወደ ስምምነት ተቃርበናል ብለዋል።Article share tools
  19. የታተመዉ 8:40 21 ህዳር 20238:40 21 ህዳር 2023በሐማስ የታገቱትን ነጻ የማውጣት ድርድር ከጫፍ ድርሷል – የኳታር አደራዳሪኳታርAFPCopyright: AFPሐማስ በእስራኤል ላይ ድንገተኛ ጥቃት አድርሶ ያገታቸውን ሰዎች ለማስለቀቅ እየተደረገ ያለው ድርድር በስምምነት ሊቋጭ ከጫፍ መድረሱን የኳታር አደራዳሪ ገለጹ።የኳታር የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማጂድ አል-አንሳሪ ከስምምነት ለመድረስ ከጫፍ ደርሰናል ብለዋል።ኳታር ሐማስ የያዛቸውን ታጋቾች እንዲለቅ፤ እስራኤልም እየተጠየቀች ላለችው የተኩስ አቁም ስምምነት አዎንታዊ ምላሽ እንድትሰጥ እስራኤል እና ሐማስን ስታደራድር ቆይታለች።ቃል አቀባዩ “. . . ስምምነት ላይ ለመድረስ ተቃርበናል” ያሉ ሲሆን ድርድሩ አሁን ያለበትን ድረጃ “ወሳኝ እና የመጨረሻው” ላይ ነው ሲሉ ገልጸውታል።ኳታር በጠላትንት የሚተያዩት የእስራኤል እና የሐማስ ‘ወዳጅ’ እንዲሁም በሁለቱ ወገኖች እምነት የሚጣልባት አገር ሆና ብቅ ብላለች።ለመሆኑ ኳታር ምዕራባውያን አሸባሪ ያሉትን ሐማስ ለምን አስጠለለች? ማደራደሩስ ይሳካላታል? ዝርዝሩን እዚህ ያንብቡ ኳታር ምዕራባውያን አሸባሪ ያሉትን ሐማስ ለምን አስጠለለች? ማደራደሩስ ይሳካላታል?Article share tools
  20. የታተመዉ 8:22 21 ህዳር 20238:22 21 ህዳር 2023ሐማስ የእስራኤል የአየር ጥቃት መቆም የስምምነት አካል እንዲሆን ፍላጎት አለው ተባለሰው አልባ አውሮፕላንReutersCopyright: Reutersየእስራኤል መገናኛ ብዙኃን በእስራኤል እና በሐማስ መካከል እየተደረገ ባለው ተኩስ የማቆም ንግግር ውስጥ እስራኤል በጋዛ የአየር ክልል ላይ መብረሯን እንድታቆም ሐማስ መጠየቁን ዘገቡ።ዋላ የተሰኘ መገናኛ ብዙኃን በጋዛ የሚገኙት የሐማስ መሪ ያህያ ሲንዋር እስራኤል በጋዛ የአየር ክልል ላይ ሙሉ በሙሉ በረራዋን እንድታቆም ጠይቀዋል ያለ ሲሆን፣ ያኔት የተባለ የዜና ድረ-ገጽ ደግሞ እስራኤል በሰሜን ጋዛ ላይ ብቻ በቀን ለስድስት ሰዓታት ለመብረር እንድትስማማ ሐማስ ጥረት እያደረገ ነው ሲል ዘግቧል።እስራኤል በጋዛ ላይ በምድር፣ በአየር እና በባሕር ጥቃቶች እየፈጸመች ሁለት ወራት ሊሞላት የተቃረበች ሲሆን፣ አስካሁን ጋዛ ውስጥ ከፍተኛ ውድመት እያደረሰ ያለው የአገሪቱ አየር ኃይል ጥቃት ነው።እስራኤል ከተዋጊ አውሮፕላኖች በተጨማሪ በውል የማይታቁ የስለላ እና ጥቃት አድራሽ ሰው አልባ አውሮፕላኖችን (ድሮኖች) በጋዛ አሰማርታ ቆይታለች።