Related Video and Audio

VIDEO 1 MINUTE 44 SECONDSVIDEO 1 MINUTE 44 SECONDS1:44

Play video በሐማስ ጥቃት የሞቱ ወታደሮችን አስከሬን ለማግኘት እስራኤል እንዴት የንስር ወፍን ተጠቀመች? from BBCበሐማስ ጥቃት የሞቱ ወታደሮችን አስከሬን ለማግኘት እስራኤል እንዴት የንስር ወፍን ተጠቀመች?

Play video በሐማስ ጥቃት የሞቱ ወታደሮችን አስከሬን ለማግኘት እስራኤል እንዴት የንስር ወፍን ተጠቀመች? from BBC

VIDEO 1 MINUTE 18 SECONDSVIDEO 1 MINUTE 18 SECONDS1:18

Play video ሕይወት በጋዛ፡ “ጦርነቱ መቶ ዓመታትን ወደኋላ መልሶናል” from BBCሕይወት በጋዛ፡ “ጦርነቱ መቶ ዓመታትን ወደኋላ መልሶናል”

Play video ሕይወት በጋዛ፡ “ጦርነቱ መቶ ዓመታትን ወደኋላ መልሶናል” from BBC

VIDEO 2 MINUTES 31 SECONDSVIDEO 2 MINUTES 31 SECONDS2:31

Play video ‘ቢያንስ ሆስፒታሉ ጥቃት አይደርስበትም ብለን አስበን ነበር’፡ ከሆስፒታል የሸሹ የጋዛ ነዋሪዎች from BBC‘ቢያንስ ሆስፒታሉ ጥቃት አይደርስበትም ብለን አስበን ነበር’፡ ከሆስፒታል የሸሹ የጋዛ ነዋሪዎች

Play video ‘ቢያንስ ሆስፒታሉ ጥቃት አይደርስበትም ብለን አስበን ነበር’፡ ከሆስፒታል የሸሹ የጋዛ ነዋሪዎች from BBC

VIDEO 2 MINUTESVIDEO 2 MINUTES2:00

Play video ጋዛን የጎበኘው ቢቢሲ የዓለም አቀፍ ኤዲተር ጄረሚ ቦውን እይታ from BBCጋዛን የጎበኘው ቢቢሲ የዓለም አቀፍ ኤዲተር ጄረሚ ቦውን እይታ

Play video ጋዛን የጎበኘው ቢቢሲ የዓለም አቀፍ ኤዲተር ጄረሚ ቦውን እይታ from BBC

VIDEO 1 MINUTE 30 SECONDSVIDEO 1 MINUTE 30 SECONDS1:30

Play video አሜሪካ ከ60 በላይ አውሮፕላን ተሸካሚ ሁለተኛ መርከቧን ወደ እስራኤል አስጠጋች from BBCአሜሪካ ከ60 በላይ አውሮፕላን ተሸካሚ ሁለተኛ መርከቧን ወደ እስራኤል አስጠጋች

Play video አሜሪካ ከ60 በላይ አውሮፕላን ተሸካሚ ሁለተኛ መርከቧን ወደ እስራኤል አስጠጋች from BBC

VIDEO 1 MINUTE 48 SECONDSVIDEO 1 MINUTE 48 SECONDS1:48

Play video ሐማስ ጋዛ ውስጥ የገነባቸው ወደ እስራኤል የሚያሻግሩት ዋሻዎች from BBCሐማስ ጋዛ ውስጥ የገነባቸው ወደ እስራኤል የሚያሻግሩት ዋሻዎች

Play video ሐማስ ጋዛ ውስጥ የገነባቸው ወደ እስራኤል የሚያሻግሩት ዋሻዎች from BBC

VIDEO 3 MINUTES 27 SECONDSVIDEO 3 MINUTES 27 SECONDS3:27

Play video ሕይወት በጋዛ፡ ከቤታቸው ወጥተው መጠለያ ፍለጋ መንከራተት from BBCሕይወት በጋዛ፡ ከቤታቸው ወጥተው መጠለያ ፍለጋ መንከራተት

Play video ሕይወት በጋዛ፡ ከቤታቸው ወጥተው መጠለያ ፍለጋ መንከራተት from BBC

ጭምቅ ሃሳብ

  1. ኳታር ደመኞቹን አስራኤልን እና ሐማስን እንዴት ከስምምነት እንዲደርሱ አስቻለች?
  2. የእስራኤል እና ሐማስ የተኩስ አቁም ፋታ ምንን ይዟል?
  3. የእስራኤል መከላከያ ‘ጦርነቱ አላከተመም’ ሲል አስጠነቀቀ
  4. እስራኤል ልታጠፋው ቀን ከሌት የምትፈልገው በጋዛ የሐማስ መሪ ያህያ ሲንዋር ማን ነው?
  5. የጋዛ ትልቁ ሆስፒታል አልሺፋ ዳይሬክተር በእስራኤል መከላከያ በቁጥጥር ስር ዋሉ
  6. የጋዛ ጊዜያዊ የተኩስ አቁም ስምምነት የዘገየው ከታጋቾች ዝርዝር ጋር በተያያዘ ነው ተባለ
  7. እስራኤል በጃባሊያ የስደተኞች መጠለያ በፈጸመችው ጥቃት የአንድ ቤተሰብ 52 አባላት ተገደሉ
  8. የጋዛው ጊዜያዊ የተኩስ አቁም ስምምነት እንደሚዘገይ ተገለጸ
  9. ይህ ጦርነት ሳይሆን ሽብርተኝነት ነው፡ ፖፕ ፍራንሲስ
  10. ዶ/ር ቴድሮስ ባልደረባቸው ከአራት ቤተሰቧ ጋር መገደሏን አስታወቁ
  11. ደቡብ አፍሪካ የእስራኤል ኤምባሲ እንዲዘጋ እና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቷ እንዲቋረጥ ወሰነች
  12. የእስራኤል ካቢኔ የታገቱትን ነጻ ለማውጣት የተደረሰውን ስምምነት አፀደቀ
  13. ሐማስ እና እስራኤል ‘ጊዜያዊ የተኩስ አቁም’ ለማድረግ ወደ ስምምነት ተቃርበዋል ተባለ
  14. ዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት ኔታንያሁ ላይ የእስር ትዕዛዝ እንዲያወጣ ደቡብ አፍሪካ ጠየቀች
  15. በጋዛ የተገደሉ ፍልስጤማውያን ቁጥር 13 ሺህ ደረሰ- የጋዛ ጤና ሚኒስቴር
  16. የኳታር ጠቅላይ ሚኒስትር ታጋቾችን የማስለቀቅ ስምምነት ላይ ‘መተማመን መጨመሩን’ ተናገሩ
  17. የጃፓን ዕቃ ጫኝ መርከብ ቀይ ባሕር ላይ በየመን ሁቲ አማጺያን ታገተ
  18. እስራኤል ተመድ ባቋቋመው የትምህርት ቤት መጠለያ ባደረሰችው ጥቃት በርካቶች መገደላቸው ተነገረ

ቀጥታ ዘገባ

  1. የታተመዉ 4:094:09ታጋቾች በግብጽ በኩል ወደ እስራኤል እንደሚወሰዱ ተገለጸታጋቾችGetty ImagesCopyright: Getty Imagesበእስራኤልና በሐማስ መከካል የተደረሰው የተኩስ አቁም ፋታ ከተጀመረ ጥቂት ሰዓታትን አስቆጥሯል።ለአራት ቀናት የሚቆየውንም የተኩስ አቁም ፋታ ተከትሎ እርዳታ ወደ ጋዛ ሰርጥ መግባት መጀመሩ ተገልጿል።በስምምነቱ መሰረት ዛሬ ከሰዓት በኋላ 13 ታጋቾች ለአለም አቀፉ ቀይ መስቀል ድርጅት ይሰጣሉ። በግብጽ ራፋህ የድንበር ማቋረጫ በኩልም የሚወጡ ይሆናል።በግብጽ ድንበር በኩልም የእስራኤል የጸጥታ ኃይሎች ተቀብለው አስፈላጊውን የማንነት ማረጋገጫ ያደርጋሉ።በመቀጠልም የህክምና ምርመራዎችን ለማድረግ ወደ ሆስፒታሎች ከተወሰዱም በኋላ ከቤተሰቦቻቸው ጋር የሚገናኙ ይሆናል።ከሰዓታትም በኋላ እስራኤል በእስር ቤት ውስጥ ካስገባቻቸው በሺዎች ከሚቆጠሩ ፍልስጤማውያንም የተወሰኑት የሚለቀቁ ይሆናል።Article share tools
  2. የታተመዉ 3:063:06ኳታር ደመኞቹን እስራኤልን እና ሐማስን እንዴት ከስምምነት እንዲደርሱ አስቻለች?ኳታር ትንሽ አገር ናት። ልቧ ግን ትልቅ ነው። ኳታር ድሃ አገር ነበረች። አሁን ታሪክ ተቀይሯል። ኳታር የምዕራቡ ዓለም ወዳጅ ናት። አሸባሪ የሚባሉ ቡድኖችም አለኝታችን ይሏታል። መጠጊያችን ይሏታል።ተጨማሪ ያንብቡArticle share tools
  3. የታተመዉ 2:292:29የእስራኤል እና ሐማስ የተኩስ አቁም ፋታ ምንን ይዟል?የጋዛ ጥቃትReutersCopyright: Reutersውጊያ ማቆም፦ በእስራኤል እና በሐማስ መካከል የተደረሰው ውጊያ የማቆም ስምምነት ጊዜያዊ ሲሆን ለአራት ቀናት እንደሚቆይም ተገልጿል። በደቡብ እስራኤል የምትገኘው የቢቢሲ ዘጋቢ የእስራኤል ጦር የተኩስ አቁም ፋታ እስከተጀመረበት የመጨረሻዋ ሰዓት ድረስ በጥቃቱ እንደቀጠለ ታዝባለች።የታጋቾች እና እስረኞች መለቀቅ፦ በሐማስ የተወሰዱ 13 ህጻናት እና ሴቶች ዛሬ ከሰዓት የሚለቀቁ ሲሆን በአራቱ ቀናትም 50 ታጋቾች ይለቀቃሉ። በልውውጡም እስራኤል በተለያዩ እስር ቤቶቿ ከሳረቻቸው በሺዎች ከሚቆጠሩ ውስጥ 150 ፍልስጤማውያን የሚለቀቁ ይሆናል።የተኩስ አቁም ፋታ የመራዘም ሁኔታ፦ ከሚለቀቁት ታጋቾች በተጨማሪ በየ10 ታጋቾች አንድ ቀን የውጊያ ፋታ ሊኖር እንደሚችልም ተጠቁሟል።እርዳታ እና ነዳጅ፦ 200 እርዳታ የጫኑ መኪናዎች፣ አራት ነዳጅ የጫኑ ተሽከርካሪዎች እና እንዲሁም አራት የምግብ ማብሰያ የጫኑ መኪናዎች በግብጽ የድንበር ማቋረጫ በኩል ወደ ጋዛ እንዲገቡ ይፈቀድላቸዋል። ግብጽ በየቀኑ 13 ሺህ ሊትር ናፍጣ ወደ ጋዛ እንዲገባ እንደሚፈቀድም አስታውቃለች።Article share tools
  4. የታተመዉ 1:541:54የእስራኤል መከላከያ ‘ጦርነቱ አላከተመም’ ሲል አስጠነቀቀየጋዛ ጥቃትAFPCopyright: AFPለአራት ቀናት የሚቆየው የተኩስ አቁም ፋታ ከመጀመሩ ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት ባወጣው መግለጫ የእስራኤል መከላከያ “ጦርነቱ አላበቃም ” ሲል በጋዛ ለሚኖሩ ፍልስጤማውያን አስጠንቅቋል።”የሰብዓዊ የተኩስ አቁም ፋታው ጊዜያዊ” ነው ሲሉም የእስራኤል መከላከያ ኃይል ቃለ አቀባይ አቪቻይ አድራይ በአረብኛ ቋንቋ ተናግረዋል።”ሰሜናዊ የጋዛ ሰርጥ አደገኛ የጦር ቀጠና ነው እናም ወደ ሰሜናዊ ጋዛ መንቀሳቀስ የተከለከለ ነው። ለደህንነታቸው ስትሉ በደቡባዊ ጋዛ ባለው የሰብዓዊ ዞን ውስጥ መቆየት አለባችሁ” ሲሉ ለጋዛውያን ተናግረዋል።እስራኤል ደህንነቱ የተጠበቀ ነው ያለችው ደቡባዊ ጋዛንም የማያባራ የአየር ጥቃት ስትፈጽምበት መቆየቱ ይታወሳል።Article share tools
  5. የታተመዉ 1:231:23በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የእስራኤል- ሐማስ የተኩስ አቁም ፋታ ጀመረየጋዛ ጥቃትEPACopyright: EPAበጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የእስራኤል ሐማስ የተኩስ አቁም ፋታ ጀመረ።ለአራት ቀናት የሚዘልቀው የውጊያ ፋታ ከአንድ ሰዓት በፊት የጀመረ ሲሆን ለ15 ደቂቃ ያህል አልፎ አልፎ ፍንዳታዎች ተሰምተዋል።የተኩስ አቁም ፋታው ከመጀመሩ በፊት ባሉት 20 እና 30 ደቂቃዎችም የመጨረሻዎቹ የአየር ጥቃቶችም ተፈጽመዋል።ለሰባት ሳምንታት ያህል የማያባራ ጥቃት በጋዛ ላይ የፈጸመው የእስራኤል መከላከያም ፋታው እስኪጀመር እስከ መጨረሻዋ ሰዓትም ድረስ ጥቃቱን አላቆመም ነበር።ቢቢሲ የድሮኖች ድምጽ የሰማ ቢሆንም በባለፉት 20 ደቂቃዎች የአየር ጥቃቶች፣ የካበድ መሳሪያ ድምጾች ወይክ ከፍተኛ ፍንዳታዎች አልተሰሙም።በስምምነቱ መሰረት ሐማስ 50 ታጋቾችን እንዲሁም እስራኤል 150 የፍልስጤም እስረኞችን በአራት ቀናት የሚለቁ ይሆናል።Article share tools
  6. የታተመዉ 0:240:24እስራኤል በጋዛ የሚገኘው አል ሺፋ ሆስፒታል ዳይሬክተርን አሰረችየእስራኤል ጦር በጋዛ ከተማ የሚገኘው የአል ሺፋ ሆስፒታል ላይ ከከፈተው አወዛጋቢ ዘመቻ አንድ ሳምንት በኋላ ለጥያቄ በሚል የሆስፒታሉን ዳይሬክተር አስሯል። ዶክተር ሞሃመድ አቡ ሳልመያ በቁጥጥር ስር በዋሉበት ወቅት ህመምተኞችን ወደ ደቡባዊ የጋዛ ክፍል አጅበው በመውጣት እንደነበሩ ባልደረባቸው ለቢቢሲ ተናግረዋል። የእስራኤል ጦር ሆስፒታሉ “የሐማስ የዕዝና ቁጥጥር ማዕከል ሆኖ እንዳገለገለ ማስረጃ ከመኖሩ ጋር” በተያያዘ ለጥያቄ መታሰራቸውን ገልጿል። ሆኖም ኃላፊውም ሆነ ሃማስ ይህንን ክስ አይቀበሉትም።ተጨማሪ ያንብቡArticle share tools
  7. የታተመዉ 23:32 23 ህዳር 202323:32 23 ህዳር 2023የጋዛ ሰርጥ በባለፉት 24 ሰዓታትበእስራኤል እና በሐማስ የተደረሰው የተኩስ አቁም ፋታ ሊጀመር የቀረው ከአንድ ሰዓት ያነሰ ጊዜ ቢሆንም በጋዛ የአየር ጥቃቱ ቀጥሏል።የእስራኤል ጦር በጋዛ ላይ የሚፈጽመውን የአየር እና የድሮን ጥቃቶቹን እንደቀጠለ ነው።የጋዛ ጥቃትGetty ImagesCopyright: Getty Imagesየጋዛ ጥቃትGetty ImagesCopyright: Getty Imagesየጋዛ ጥቃትGetty ImagesCopyright: Getty Imagesየጋዛ ጥቃትGetty ImagesCopyright: Getty Imagesየጋዛ ጥቃትGetty ImagesCopyright: Getty ImagesArticle share tools
  8. የታተመዉ 10:10 23 ህዳር 202310:10 23 ህዳር 2023ከእገታ ቀድሞ ነጻ ማን ይውጣል የሚለው በሰብዓዊነት ላይ የተመሰረተ ነው ተባለየኳታር የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ መጂድ አል-አንሳሪReutersCopyright: Reutersየኳታር የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ መጂድ አል-አንሳሪImage caption: የኳታር የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ መጂድ አል-አንሳሪየኳታር የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ መጂድ አል-አንሳሪ ከሐማስ እገታ ቀድሞ ነጻ የሚወጣው የሚለየው በሰብዓዊነት ላይ በመመሥረት ይሆናሉ አሉ።ቃል አቀባዩ ይህን ያሉት እስራኤል እና ሐማስ ሲያደርጉት የነበረው ድርድር ከነገ አርብ ጠዋት 1 ሰዓት ጀምሮ ተፈጻሚ እንደሚሆን ይፋ ባደረጉበት ወቅት ነው።እስራኤል ከጠዋቱ 1 ሰዓት ጀምሮ ለአራት ቀናት የሚዘልቅ ጦርነት የማቆም ፋታ የምትሰጥ ሲሆን፣ ሐማስ ደግሞ ከሰዓት 10 ሰዓት ላይ 13 ታጋቾችን ይለቃል ተብሎ ይጠበቃል።እስራኤልም እንዲሁም በእስር ቤት ይዛቸው የምትገኛቸውን ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ እስረኞችን ትለቃለች።የኳታር የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ በመግለጫቸው ቀድመን ትኩረት የምንሰጠው ሴቶች እና ሕጻናትን በተቻለ መጠን ከጉዳት መጠበቅ ነው ያሉ ሲሆን ነገ ነጻ የሚሆኑት ታጋቾች ማንነት ይፋ ባይሆንም ሁሉም ግን ሕጻናት እና ሴቶች መሆናቸውን ገልጸዋል።ሐማስ እስራኤል ላይ መስከረም 26 ድንገተኛ ጥቃት ከፍቶ 1200 በላይ ሰዎች ገድሎ ከ230 ያላሱ ሰዎችን አግቶ መውሰዱ ይታወሳል።ሐማስ ከሳምንታት በፊት በእስራኤል ተደጋጋሚ የአየር ድብደባ በጋዛ ተይዘው ከነበሩ ታጋቾች መካከል 50 የሚሆኑት ተገድዋል ማለቱ ይታወሳል።Article share tools
  9. የታተመዉ 9:51 23 ህዳር 20239:51 23 ህዳር 2023ኳታር የእስራኤል-ሐማስ ጦርነት ፋታ አርብ ጠዋት እንደሚጀምር አስታወቀችበሐማስ ታግተው ከሚገኙት መካከል የአንድ ቤተሰብ አባል የሆኑት ኤሬዝ እና ሳሃር ይገኙበታልIDO DANCopyright: IDO DANበሐማስ ታግተው ከሚገኙት መካከል የአንድ ቤተሰብ አባል የሆኑት ኤሬዝ እና ሳሃር ይገኙበታልImage caption: በሐማስ ታግተው ከሚገኙት መካከል የአንድ ቤተሰብ አባል የሆኑት ኤሬዝ እና ሳሃር ይገኙበታልእስራኤል እና ሐማስን ስታደራድር የቆየችው ኳታር በተደረሰው ስምምነት መሠረት ለቀናት የሚቆየው ጦርነት የማቆም ፋታ ነገ አርብ በጋዛ ሰዓት አቆጣጠር ከጠዋቱ 1 ሰዓት እንደሚጀምር አስታወቀች።ሐማስ ደግሞ በስምምነቱ መሠረት የመጀመሪያዎቹን 13 ታጋቾች አርብ ከሰዓት በኋላ 10 ሰዓት ላይ ይለቃል ብላለች።በሐማስ ታግተው ከነበሩት መካከል ቀድመው የሚለቀቁት ሴቶች እና ሕጻናት እንደሚሆኑ የኳታር የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ መጂድ አል-አንሳሪ ተናግረዋል።ቃል አቀባዩ ታጋቾቹን ነገ ከሰዓት ከሐማስ የሚረከበው ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ማኅበር መሆኑንም ጨምረው ተናግረዋል።Article share tools
  10. የታተመዉ 8:52 23 ህዳር 20238:52 23 ህዳር 2023የእስራኤል አየር ኃይል በአንድ ቀን 300 የሐማስ ዒላማዎችን መምታቱን ገለጸየእስራኤል አየር ኃይል በጋዛ ሰርጥ የሚገኙ 300 የሐማስ ዒላማዎችን በ24 ሰዓታት ውስጥ መደብደቡን ገለጸ።ጦሩ በኤክስ ገጹ (የቀድሞው ትዊተር) ላይ እንዳለው ከሆነ በአየር ኃይሉ የተደበደቡት የሐማስ “ማዘዣ ጣቢያዎች፣ ዋሻዎች፣ ጦር መሳሪያ ማከማቻ ሰፍራዎች፣ ጦር መሳሪያ ማምረቻዎች እና ፀረ-ታንክ ሚሳኤል መተኮሻ ቦታዎች” ናቸው።የእስራኤል ጦር መግለጫን ተከትሎ ሐማስ እስካሁን ያለው ነገር የለም።Article share tools
  11. የታተመዉ 8:52 23 ህዳር 20238:52 23 ህዳር 2023በእስራኤል-ሊባኖስ ድንበር አቅራቢያ ውጊያ መቀጠሉ ተገለጸየእስራኤል ወታደሮች በጋዛReutersCopyright: Reutersየእስራኤል ወታደሮች በጋዛImage caption: የእስራኤል ወታደሮች በጋዛእስራኤል እና ሊባኖስ በሚዋሰኑበት ድንበር አቅራቢያ በእስራኤል ጦር እና በሄዝቦላህ መካከል የሚደረገው ውጊያ መቀጠሉ ተገለጸ።የእስራኤል መከላከያ ኃይል ቃል አቀባይ ዳንኤል ሃጋሪ ጦራቸው ፀረ-ታንክ ቡድን ላይ እርምጃ መውሰዱን ገልጸዋል።ቀደም ሲል ከምድር ወደ ሰማይ የሚወነጨፍ ሚሳኤል በሌባኖስ የአየር ክልል ውስጥ እየበረረ የነበረ የእስራኤል የጦር አውሮፕላን ላይ ተተኩሶ የነበረ ቢሆንም፣ የእስራኤል ፀረ-ሚሳኤል ሥርዓት ጥቃቱን ማክሸፉ ተመላክቷል።ይህን ተከትሎ በርካታ ቁጥር ያላቸው የእስራኤል የጦር አውሮፕላኖች በደቡባዊ ሊባኖስ በሚገኙ የሄዝቦላሀ ዒላማዎችን መደብደባቸው ተገልጿል።ሄዝቦላህ በበኩሉ ተዋጊዎቹ አል-ማርጅ በተሰኘ አካባቢ በአንድ ቦታ ተሰባስበው የነበሩ የእስራኤል ወታደሮች ላይ ጥቃት ማድረሳቸውን አስታውቋል።Article share tools
  12. የታተመዉ 5:21 23 ህዳር 20235:21 23 ህዳር 2023የጋዛ ትልቁ ሆስፒታል አልሺፋ ዳይሬክተር በእስራኤል መከላከያ በቁጥጥር ስር ዋሉየአልሺፋ ሆስፒታልReutersCopyright: Reutersየጋዛ ትልቁ ሆስፒታል አልሺፋ ዳይሬክተር በእስራኤል መከላከያ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የሆስፒታሉ የህክምና ባለሙያ ተናገሩ። ዳይሬክተሩ አቡ ሳላሚያ ከሆስፒታሉ የሚወጡ ህመምተኞችን አጅበው ባሉበት ሰዓት በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የአልሺፋ የአጥንት ህክምና ክፍል ኃላፊ ዶክተር አድናን አል ቡርሽ ገልጸዋል።የእስራኤል መከላከያ በጉዳዩ ላይ የሰጠው አስተያየት የለም።እስራኤል የሐማስ እዝ በሆስፒታሉ ስር አለ በሚል በአልሺፋ ላይ ወረራ በመፈጸም ተቆጣጥራው ትገኛለች።ሐማስም ሆነ የሆስፒታሉ የህክምና ባለሙያዎች ይህንን ክስ አይቀበሉትም። የእስራኤል ጦር ባለፈው ሳምንት ሆስፒታሉን ከተቆጣጠረ በኋላ የሐማስ ዋሻ ነው ያለውን እና 55 ሜትር እርዝማኔ አለው ያለውቪዲዮ አሳይቷል።ህሙማንን ጨምሮ በመቶዎች የሚቆጠሩ ፍልስጤማውያን ሆስፒታሉን ለቀው እንዲወጡ በእስራኤል ትዕዛዝ ተሰጥቶናል በሚል በእግራቸው ሸሽተዋል። እስራኤል ትዕዛዝ አልሰጠሁም ስትል አስተባብላለች።Article share tools
  13. የታተመዉ 4:53 23 ህዳር 20234:53 23 ህዳር 2023እስራኤል በራፋህ ያደረሰቻቸው የአየር ጥቃቶች በምስልእስራኤል በግብጽ እና ጋዛ የድንበር ማቋረጫ ራፋህ የአየር ጥቃቶችን ፈጽማለች።በኻን ዩኒስ አቅራቢያ የምትገኘው ራፋህ እስራኤል በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ፍልስጤማውያን ሰሜናዊ ጋዛን ለቀው እንዲሸሹባት ከተመረጡት ከተሞች አንዷ ናት።የእስራኤል መከላከያ በበኩሉ ባለፉት 24 ሰዓታት በፈጸመው ጥቃቶች 300 የሐማስ ኢላማዎችን መትቻለሁ ብሏል።የራፋህ የአየር ጥቃትGetty ImagesCopyright: Getty Imagesየራፋህ የአየር ጥቃትGetty ImagesCopyright: Getty Imagesየራፋህ የአየር ጥቃትGetty ImagesCopyright: Getty ImagesArticle share tools
  14. የታተመዉ 4:45 23 ህዳር 20234:45 23 ህዳር 2023የጋዛ ጊዜያዊ የተኩስ አቁም ስምምነት የዘገየው ከታጋቾች ዝርዝር ጋር በተያያዘ ነው ተባለየጋዛ ጥቃትGetty ImagesCopyright: Getty Imagesዛሬ፣ ሐሙስ ረፋድ ላይ ተግባራዊ እንዲሆን ሲጠበቅ የነበረው ጊዜያዊ የተኩስ አቁም ለመዘግየቱ ከታጋቾች ዝርዝር ጋር በተያያዘ መሆኑን የፍልስጤም ባለስልጣናት ገለጹ።የዘገየውም በመጨረሻዋ ሰዓት መሆኑንም ለአጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ተናግረዋል።የትኞቹ ታጋቾች ይለቀቁ? እንዴት? በሚለውም ዝርዝር ምክንያትም መራዘሙ ተነግሯል። ጊዜያዊ የተኩስ አቁሙም አርብ ተግባራዊ ሊሆን እንደሚችልም የእስራኤል መንግሥት ምንጭ ለቢቢሲ ተናግረዋል።የቀረውም ጉዳይ የሎጂስቲክ እንደሆነም ነው የተናገሩት።ኳታር በበኩሏ የተኩስ አቁም ስምምነቱ መቼ እንደሚጀምር በቀጣዩ ሰዓታት እንደሚገለጽ አስታውቃለች።የኳታር መንግሥት ቃለ አቀባይ እንደተናገሩት ከእስራኤል እና ሐማስ ጋር የተደረገው ስምምነት የተያያዘው ውይይት ቀጥሏል ብለዋል። በነዚህም ውይይቶች ላይ ግብጽ እና አሜሪካ የሚሳተፉ ሲሆን “ጦርነቱ ጋብ የሚልባቸውን ቀናት ፈጠን ብሎ የማስጀመር እንዲሁም ሁለቱ ወገኖች ስምምነቱ እንዲያከብሩ የሚያስፈልጉ ጉዳዮችም ውይይቱ ቀጥሏል” ተብሏል።Article share tools
  15. የታተመዉ 3:03 23 ህዳር 20233:03 23 ህዳር 2023እስራኤል በጃባሊያ የስደተኞች መጠለያ በፈጸመችው ጥቃት የአንድ ቤተሰብ 52 አባላት ተገደሉየጋዛ ጥቃትAFPCopyright: AFPእስራኤል ረቡዕ በጃባሊያ የስደተኞች መጠለያ በፈጸመችው ጥቃት የአንድ ቤተሰብ አምሳ ሁለት አባላት መገደላቸውን የፍልስጤም ባለስልጣናት አስታውቀዋል።እስራኤል በጋዛ ላይ እየፈጸመችው ያለው የማያባራ የአየር ጥቃት ዛሬ ረፋድ ተግባራዊ ይሆናል ተብሎ በነበረው ጊዜያዊ የተኩስ አቁም ስምምነት ጋብ እንደሚል ተጠብቆ ነበር። ነገር ግን የተኩስ አቁም ስምምነት ተግባራዊ አልሆነም፤ መቼ እንደሚጀምርም ግልጽ አልሆነም።የፍልስጤም አስተዳደር የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ሪያድ አል ማሊኪ በስደተኞቹ መጠለያ በተፈጸመው ጥቃት የተገደሉት 52 ሰዎች የአንድ ቤተሰብ አባላት መሆናቸውንም ገልጸዋል።“ዛሬ ጥዋት ብቻ በጃባሊያ የስደተኞች መጠለያ የኳድራ ቤተሰብ 52 አባላት ለዘር እንዳይተርፉ ሆነው ተፈጅተዋል” ብለዋል።ቢቢሲ ይህንን በገለልተኝነት ማረጋገጥ አልቻለም። የፍልስጤም አስተዳደር መቀመጫውን እስራኤል በኃይል በያዘቻት ዌስት ባንክ ያደረገ ነው።Article share tools
  16. የታተመዉ 2:14 23 ህዳር 20232:14 23 ህዳር 2023የጋዛው ጊዜያዊ የተኩስ አቁም ስምምነት እንደሚዘገይ ተገለጸየጋዛ ጥቃትReutersCopyright: Reutersየጋዛው ጦርነት ጊዜያዊ የተኩስ አቁም ስምምነት ዛሬ ረፋድ ላይ ተግባራዊ እንዲደረግ በእስራኤል እና በሐማስ መካከል ስምምነት ላይ ቢደረስም ቢቢሲ እንደሚዘገይ ከእስራኤል መንግሥት ምንጭ መረጃ ሰምቷል።በጋዛ የታገቱት ከአርብ በፊት እንደማይለቀቁ የእስራኤል ከፍተኛ ባለስልጣን ተናግረዋል።በእስራኤል እና በሐማስ መካከል በተደረገው ስምምነት ላይ ንግግሮች መቀጠላቸውን የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ብሔራዊ የጸጥታ አማካሪ ትዛኪ ዘኔግቢ ባወጡት መግለጫ አስታውቀዋል። ቀደም ብሎ የእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ የመጀመሪያዎቹ ታጋቾች ሐሙስ እንደሚለቀቁ አስታውቆ ነበር።በስምምነቱ መሰረትም በሐማስ የተወሰዱ 50 ታጋቾች የሚለቀቁ ሲሆን በልውውጡም እስራኤል ካሰረቻቸው ፍልስጤማውያን ውስጥ 150 ሴቶች እና ህጻናት የሚለቀቁ ይሆናል።ሰባተኛ ሳምንቱን በያዘው የጋዛው ጦርነት ከ13 ሺህ በላይ ፍልስጤማውያን ሲገደሉ ከነዚህም በርካቶቹ ህጻናት መሆናቸውን የጋዛ ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል። ከእስራኤል በኩል ደግሞ 1 ሺህ 200 ተገድለዋል።Article share tools
  17. የታተመዉ 2:13 23 ህዳር 20232:13 23 ህዳር 2023የሆሊውዷ ተዋናይት እስራኤልን ‘በማውገዟ’ ከስክሪም ተከታታይ ፊልም ተባረረችየሆሊውዷ ተዋናይት ሜሊሳ ባሬራ ፍልስጤምን በመደገፍ ማህበራዊ ሚዲያ ያሰፈረቻቸው ጽሑፎች ጸረ ሴማዊ ናቸው በማለት ከምትሠራበት ፊልም እንድተባረረ ተደረገ። ተዋናይቷ በጋዛ እየተካሄደ ስላለው ጦርነት የሚገልጹ ጽሁፎችን በማህበራዊ ሚዲያዋ ገጿ አጋርታለች። ከነዚህም ጽሁፎችን አንዱ እስራኤልን “በዘር ማጥፋት እና ዘር ማጽዳት’ የሚከሰው አንዱ ነው።ተጨማሪ ያንብቡArticle share tools
  18. የታተመዉ 2:13 23 ህዳር 20232:13 23 ህዳር 2023‘የፍልስጤማውያንን ሕጻናት ግድያን የደገፉት’ የኦባማ የቀድሞ ረዳት በቁጥጥር ስር ዋሉበቀድሞ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ የሥልጣን ዘመን የውጭ ጉዳይ ረዳት የነበሩት ባለሥልጣን በጋዛ የደረሰውን የፍልስጤማውያንን ግድያ በመደገፍ እና የእስልምና እምነትን በማንቋሸሻቸው በቁጥጥር ስር ዋሉ።ተጨማሪ ያንብቡArticle share tools
  19. የታተመዉ 2:13 23 ህዳር 20232:13 23 ህዳር 2023እስራኤል ልታጠፋው ቀን ከሌት የምትፈልገው በጋዛ የሐማስ መሪ ያህያ ሲንዋር ማን ነው?ያህያ ሲንዋር ደብዛው ጠፍቷል። ለነገሩ በሺዎች የሚቆጠሩት የእስራኤል ወታደሮች በሰላዮች እና ድሮኖች ታግዘው ያለበትን ለማወቅ በሚያነፈንፉበት ወቅት አድራሻውን ማጥፋቱ አይገርምም።ተጨማሪ ያንብቡArticle share tools
  20. የታተመዉ 9:20 22 ህዳር 20239:20 22 ህዳር 2023ለአራት ቀናት የሚቆየው ተኩስ አቁም ዛሬ ሐሙስ ረፋድ አራት ሰዓት ይጀምራልራፋህ ውስጥ ከተፈጸመ የአየር ጥቃት በኋላ ከፍርስራሽ ስር በሕይወት ያሉ ሰዎችን ለመፈለግ የሚጥሩ ሰዎችAFPCopyright: AFPራፋህ ውስጥ ከተፈጸመ የአየር ጥቃት በኋላ ከፍርስራሽ ስር በሕይወት ያሉ ሰዎችን ለመፈለግ የሚጥሩ ሰዎችImage caption: ራፋህ ውስጥ ከተፈጸመ የአየር ጥቃት በኋላ ከፍርስራሽ ስር በሕይወት ያሉ ሰዎችን ለመፈለግ የሚጥሩ ሰዎችበእስራኤል እና በሐማስ መካከል በተደረሰው ስምምነት መሠረት ለአራተ ቀናት የሚቆየው የተኩሰ አቁም ዛሬ ሐሙስ ረፋድ አራት ሰዓት ላይ እንደሚጀምር ሐማስ አስታወቀ።ቢቢሲ ከምንጮቹ ማረጋገጥ እንደቻለው ከአንድ ወር በላይ እየተካሄደ ያለውን ውጊያ ለአራት ቀናት ጋብ ለማድረግ የተደረሰው ስምምነት ሐሙስ ተግባራዊ መሆን ይጀምራል።የተኩስ አቁሙ እውን ከሆነ ከሰዓታት በኋላ ደግሞ በሐማስ እጅ ከሚገኙት ታጋቾች የመጀመሪያዎቹ ከሰዓት በኋላ ይለቀቃሉ ተብሎ ይጠበቃል።የሐማስ ፖለቲካ ቢሮ ኃላፊ ሙሳ አቡ ማርዙክ ለአል-ጃዚራ ቴሌቪዥን እንደተናገሩት ለቀናት የሚዘልቀው ውጊያ ጋብ የማድረግ ስምምነት የመጀመሪያዎቹ ታጋቾች ከመለቀቃቸው ከሰዓታት በፊት ተግባራዊ እንደሚሆን አረጋግጠዋል።የግብፅ የደኅንነት ምንጮች ለሮይተርስ ዜና ወኪል ተኩስ ማቆሙ ሐሙስ ረፋድ አራት ሰዓት ላይ ተግባራዊ እንዲሆን አደራዳሪዎች መፈለጋቸውን ተናግረዋል።ለዚህም ምክንያቱ ታጋቾቹን ከመልቀቁ በፊት ሐማስ “ጥቂት ሰዓታት” እንደሚያስፈልገው በመግለጹ መሆኑነ ተናግረዋል።የእስራኤል የመከላከያ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ውጊያው ጋብ ማለት የሚጀምረው “ሐሙስ በሆነ ሰዓት ላይ” እንደሆነ ለሮይተርስ ገልጸዋል።በተጨማሪም የዜና ወኪሉ የአስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኤሊ ኮኽን ምንም እንኳን ትክክለኛውን ሰዓት ከመግለጽ ቢቆጠቡም እስራኤል የመጀመሪያዎቹን ነጻ የሚወጡ ታጋቾች ሐሙስ ዕለት እንደሚቀበሉ መናገራቸውን ዘግቧል።