ቀጥታ

ሐማስ 24 ታጋቾችን ሲለቅ አስራኤል 39 እስረኞችን ፈታች

Related Video and Audio

VIDEO 1 MINUTE 44 SECONDSVIDEO 1 MINUTE 44 SECONDS1:44

Play video በሐማስ ጥቃት የሞቱ ወታደሮችን አስከሬን ለማግኘት እስራኤል እንዴት የንስር ወፍን ተጠቀመች? from BBCበሐማስ ጥቃት የሞቱ ወታደሮችን አስከሬን ለማግኘት እስራኤል እንዴት የንስር ወፍን ተጠቀመች?

Play video በሐማስ ጥቃት የሞቱ ወታደሮችን አስከሬን ለማግኘት እስራኤል እንዴት የንስር ወፍን ተጠቀመች? from BBC

VIDEO 1 MINUTE 18 SECONDSVIDEO 1 MINUTE 18 SECONDS1:18

Play video ሕይወት በጋዛ፡ “ጦርነቱ መቶ ዓመታትን ወደኋላ መልሶናል” from BBCሕይወት በጋዛ፡ “ጦርነቱ መቶ ዓመታትን ወደኋላ መልሶናል”

Play video ሕይወት በጋዛ፡ “ጦርነቱ መቶ ዓመታትን ወደኋላ መልሶናል” from BBC

VIDEO 2 MINUTES 31 SECONDSVIDEO 2 MINUTES 31 SECONDS2:31

Play video ‘ቢያንስ ሆስፒታሉ ጥቃት አይደርስበትም ብለን አስበን ነበር’፡ ከሆስፒታል የሸሹ የጋዛ ነዋሪዎች from BBC‘ቢያንስ ሆስፒታሉ ጥቃት አይደርስበትም ብለን አስበን ነበር’፡ ከሆስፒታል የሸሹ የጋዛ ነዋሪዎች

Play video ‘ቢያንስ ሆስፒታሉ ጥቃት አይደርስበትም ብለን አስበን ነበር’፡ ከሆስፒታል የሸሹ የጋዛ ነዋሪዎች from BBC

VIDEO 2 MINUTESVIDEO 2 MINUTES2:00

Play video ጋዛን የጎበኘው ቢቢሲ የዓለም አቀፍ ኤዲተር ጄረሚ ቦውን እይታ from BBCጋዛን የጎበኘው ቢቢሲ የዓለም አቀፍ ኤዲተር ጄረሚ ቦውን እይታ

Play video ጋዛን የጎበኘው ቢቢሲ የዓለም አቀፍ ኤዲተር ጄረሚ ቦውን እይታ from BBC

VIDEO 1 MINUTE 30 SECONDSVIDEO 1 MINUTE 30 SECONDS1:30

Play video አሜሪካ ከ60 በላይ አውሮፕላን ተሸካሚ ሁለተኛ መርከቧን ወደ እስራኤል አስጠጋች from BBCአሜሪካ ከ60 በላይ አውሮፕላን ተሸካሚ ሁለተኛ መርከቧን ወደ እስራኤል አስጠጋች

Play video አሜሪካ ከ60 በላይ አውሮፕላን ተሸካሚ ሁለተኛ መርከቧን ወደ እስራኤል አስጠጋች from BBC

VIDEO 1 MINUTE 48 SECONDSVIDEO 1 MINUTE 48 SECONDS1:48

Play video ሐማስ ጋዛ ውስጥ የገነባቸው ወደ እስራኤል የሚያሻግሩት ዋሻዎች from BBCሐማስ ጋዛ ውስጥ የገነባቸው ወደ እስራኤል የሚያሻግሩት ዋሻዎች

Play video ሐማስ ጋዛ ውስጥ የገነባቸው ወደ እስራኤል የሚያሻግሩት ዋሻዎች from BBC

VIDEO 3 MINUTES 27 SECONDSVIDEO 3 MINUTES 27 SECONDS3:27

Play video ሕይወት በጋዛ፡ ከቤታቸው ወጥተው መጠለያ ፍለጋ መንከራተት from BBCሕይወት በጋዛ፡ ከቤታቸው ወጥተው መጠለያ ፍለጋ መንከራተት

Play video ሕይወት በጋዛ፡ ከቤታቸው ወጥተው መጠለያ ፍለጋ መንከራተት from BBC

ጭምቅ ሃሳብ

  1. ኳታር ደመኞቹን አስራኤልን እና ሐማስን እንዴት ከስምምነት እንዲደርሱ አስቻለች?
  2. የእስራኤል እና ሐማስ የተኩስ አቁም ፋታ ምንን ይዟል?
  3. የእስራኤል መከላከያ ‘ጦርነቱ አላከተመም’ ሲል አስጠነቀቀ
  4. እስራኤል ልታጠፋው ቀን ከሌት የምትፈልገው በጋዛ የሐማስ መሪ ያህያ ሲንዋር ማን ነው?
  5. የጋዛ ትልቁ ሆስፒታል አልሺፋ ዳይሬክተር በእስራኤል መከላከያ በቁጥጥር ስር ዋሉ
  6. የጋዛ ጊዜያዊ የተኩስ አቁም ስምምነት የዘገየው ከታጋቾች ዝርዝር ጋር በተያያዘ ነው ተባለ
  7. እስራኤል በጃባሊያ የስደተኞች መጠለያ በፈጸመችው ጥቃት የአንድ ቤተሰብ 52 አባላት ተገደሉ
  8. የጋዛው ጊዜያዊ የተኩስ አቁም ስምምነት እንደሚዘገይ ተገለጸ
  9. ይህ ጦርነት ሳይሆን ሽብርተኝነት ነው፡ ፖፕ ፍራንሲስ
  10. ዶ/ር ቴድሮስ ባልደረባቸው ከአራት ቤተሰቧ ጋር መገደሏን አስታወቁ
  11. ደቡብ አፍሪካ የእስራኤል ኤምባሲ እንዲዘጋ እና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቷ እንዲቋረጥ ወሰነች
  12. የእስራኤል ካቢኔ የታገቱትን ነጻ ለማውጣት የተደረሰውን ስምምነት አፀደቀ
  13. ሐማስ እና እስራኤል ‘ጊዜያዊ የተኩስ አቁም’ ለማድረግ ወደ ስምምነት ተቃርበዋል ተባለ
  14. ዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት ኔታንያሁ ላይ የእስር ትዕዛዝ እንዲያወጣ ደቡብ አፍሪካ ጠየቀች
  15. በጋዛ የተገደሉ ፍልስጤማውያን ቁጥር 13 ሺህ ደረሰ- የጋዛ ጤና ሚኒስቴር
  16. የኳታር ጠቅላይ ሚኒስትር ታጋቾችን የማስለቀቅ ስምምነት ላይ ‘መተማመን መጨመሩን’ ተናገሩ
  17. የጃፓን ዕቃ ጫኝ መርከብ ቀይ ባሕር ላይ በየመን ሁቲ አማጺያን ታገተ
  18. እስራኤል ተመድ ባቋቋመው የትምህርት ቤት መጠለያ ባደረሰችው ጥቃት በርካቶች መገደላቸው ተነገረ

ቀጥታ ዘገባ

  1. የታተመዉ 4:344:3442 ፍልስጤማውያን ነጻ እንደሚወጡ ተገለጸትናንት ከሐማስ እገታ ነጻ የወጡት እስራኤላውያን እናት እና ልጅFamily handoutCopyright: Family handoutትናንት ከሐማስ እገታ ነጻ የወጡት እስራኤላውያን እናት እና ልጅImage caption: ትናንት ከሐማስ እገታ ነጻ የወጡት እስራኤላውያን እናት እና ልጅበሁለተኛው ቀን የታጋቾች እና እስረኞች ልውውጥ 42 ፍልስጤማውያን ከእስራኤል እስር ቤት እንደሚለቀቁ የተገለጸ ሲሆን ሐማስ ደግሞ 14 እስራኤላውያንን ከእገታ ነጻ ያወጣል ተብሏል።የፍልስጤም የታራማዊች ማኅበር ዛሬ ነጻ ይወጣሉ የተባሉ የ42 ፍልስጤማውያን ዝርዝር ከእስራኤል መንግሥት እንደደረሰው አስታውቋል።ማኅበሩ ከእነዚህ መካከል 18ቱ ሴቶች ሲሆኑ 24ቱ ደግሞ ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች ናቸው ብሏል።ፍልስጤማውያኑ እና እስራኤላውያኑ የሚለቀቁበት ሰዓት አልተገለጸም።Article share tools
  2. የታተመዉ 4:114:11ከእገታ ነጻ የወጡ ሰዎች ጤና ‘ጥሩ’ መሆኑን ያከማቸው ሆስፒታል አስታወቀትናንት ከሐማስ እገታ ነጻ ከወጣቱ 13 እስራኤላውያን መካከል ለ8ቱ የሕክምና አገልግሎት የሰጠው ሆስፒታል የታካሚዎቹ ጤና ‘ጥሩ’ የሚባል መሆኑን ገለጸ።በቴል አቪቭ የሚገኘው ሽናይደር ሆስፒታል የተቀበልኳቸው 4 ሕጻናት እና 4 ሴቶች ጤና ጥሩ ነው ብሏል።ሆስፒታሉ ጨምሮም ከእገታ ነጻ የወጡት ሰዎች ከቤተሰቦቻቸው ጋር ሆነው ለእነርሱ ተብሎ በተዘጋጀ የሆስፒታሉ ክፍል ውስጥ በጤና ባለሙያዎች የቅርብ ክትትል እየደረገላቸው እንደሆነ ገልጿል።ትናንት ሐማስ ለ7 ሳምንታት ያክል አግቶ ያቆያቸውን 13 እስራኤላውያንን፣ 10 የታይላንድ እና 1 የፊሊፒንስ ዜጋ መልቀቁ ይታወሳል።Article share tools
  3. የታተመዉ 3:223:22ዛሬ ተጨማሪ ታጋቾች ይለቀቃሉ ተብሎ ይጠበቃለእስራኤላውያን ቤተሰቦችArielCopyright: Arielእስራኤል ዛሬ ተጨማሪ 13 ታጋቾች ይለቀቃሉ ብዬ እጠብቃለሁ አለች።በአንጻሩ እስራኤል ቁጥራቸው ከፍ ያሉ ፍልስጤማውያንን ከእስር ቤት እንደምትለቅ ይጠበቃል።ከዚህ በተጨማሪ በርካታ የሰብዓዊ እርዳታ ቁሳ ቁስ የጫኑ ከባድ የደረቅ ጭንት መኪኖች ወደ ጋዛ ለመግባት ግብጽ ድንበር ላይ እየተጠባበቁ ይገኛሉ።ምንም እንኳ በኳታር አደራዳሪነት በሐማስ እና እስራኤል መካከል ለጦርነቱ ፋታ ለመስጠት ከስምምነት ቢደረስም በጋዛ ከፍተኛ የሰብዓዊ ቀውስ እንዳለ እየተገለጸ ነው።ነዳጅ፣ ምግብ፣ ውሃ እና የሕክምና መሳሪያዎች ከፍተኛ እጥረት አለ።ትናንት አርብ ወደ 200 የሚጠጉ ከባድ ተሸከርካሪዎች ጋዛ ደርሰው ነበር ይህም ከመስከረም 26 በኋላ ትልቁ ቁጥር ሆኖ ተመዝግቧል።Article share tools
  4. የታተመዉ 3:203:20እስራኤል የምትለቃቸው ፍልስጤማውያን እስረኞች እነማን ናቸው? ለምንስ ታስረው ቆዩ?እስራኤል ሊፈቱ የሚችሉ 300 ፍልስጤማውያንን ስም ዝርዝር አሳውቃለች። አብዛኞቹ ዕድሜያቸው 17 ወይም 18 ናቸው። አጠቃላይ ግን ዕድሜያቸው ከ14 እስከ 59 ይደርሳል። 274 ያህሉ ደግሞ ወንዶች ናቸው።ተጨማሪ ያንብቡArticle share tools
  5. የታተመዉ 23:50 24 ህዳር 202323:50 24 ህዳር 202339 ፍልስጤማውያን ከእስራኤል እስር ቤት ተለቀቁከእስር የወጣ ፍልስጤማዊReutersCopyright: Reutersበእስራኤል እና በሐማስ መካከል በተደረሰው ስምምነት መሠረት 39 ፍልስጤማውያን አርብ ምሽት ከእስራኤል እስር ቤት ተለቀቁ።አብዛኛዎቹ ከእስራኤል እስር ቤት የተለቀቁት በዕድሜ ወጣት የሆኑ እና ድንጋይ ከመወርወር እስከ የግድያ ሙከራ በሚሉ ክሶች የታሰሩ ነበሩ።24 ሴቶች እና 15 ወንዶች ከእስር ተለቀው ዌስት ባንክ ሲደርሱ በርካታ ደጋፊዎች የፍልስጤም ሰንደቅ ዓላማን እያውለበለቡ በደስታ ተቀብለዋቸዋል።አርብ ከእስር ከተለቀቁት ፍልስጤማውያን መካከል አንዷ ማራህ ባኬር ስትሆን፣ በእስራኤል ፖሊስ አባል ላይ በስለት ጥቃት ፈጽማለች በሚል ከስምንት ዓመት በፊት የ16 ዓመት ታዳጊ ሳለች ነበር የታሰረችው።ማራህ “መፈታቴ አስደንቆኛል” ያለች ሲሆን፣ ከእስር የወጣችው በርካታ ፍልስጤማውያን በእስራኤል ጥቃት የተገደሉበት ወቅት በመሆኑ ሙሉ ደስታ አይሰጠኝም ብላለች።Article share tools
  6. የታተመዉ 23:47 24 ህዳር 202323:47 24 ህዳር 2023እስራኤል 13 ዜጎቿ ነጻ መውጣታቸውን ይፋ አደረገችጠቅላይ ሚንስትር ቤኒያሚን ኔታኒያሁReutersCopyright: Reutersጠቅላይ ሚንስትር ቤኒያሚን ኔታኒያሁImage caption: ጠቅላይ ሚንስትር ቤኒያሚን ኔታኒያሁየእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታኒያሁ በሐማስ ከታገቱ ዜጎቻቸው መካከል 13ቱን መረከባቸውን ይፋ አደረጉ።“የመጀመሪያዎቹን ታጋቾች ተቀብለናል። ሕጻናት፣ እናቶቻቸው እና ሌሎች ሴቶችን። እያንዳንዳቸው ለእኛ ትልቅ ትርጉም አላቸው” ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ።“አንድ ነገር ላይ ትኩረት እንድታደርጉ – ለቤተሰብ አባላት – ለእስራኤል ዜጎች፡ ሁሉንም ታጋቾች ለመመለስ ቁርጠኞች ነን” ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጨምረው ተናግረዋል።በቀጣይ አራት ቀናት 50 እስራኤላውያን ታጋቾች እና 150 ፍልስጤማውያን ከእገታ እና ከእስር ነጻ ይወጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።Article share tools
  7. የታተመዉ 23:45 24 ህዳር 202323:45 24 ህዳር 2023ከሐማስ እገታ ነጻ የወጡ ሰዎች ቤተሰብ አባላት እፎይታታጋቾችBBCCopyright: BBCትናንት አርብ ሐማስ 13 እስራኤላውያን፣ 10 የታይላንድ እና 1 የፊሊፒንስ ዜጋን ከእገታ መልቀቁ ታውቋል።ሐማስ እና እስራኤል በደረሱት ስምምነት መሠረት ነጻ የወጡት 13 ሴቶች እና ሕጻናት እስራኤላውያን አገራቸው ደርሰዋል።በሌላ በኩሉ 39 ፍልስጤማውያን ከእስራኤል እስርቤት ተለቀው ወደ ዌስት ባንክ ተወስደዋል።ነጻ ከወጡት እስራኤላውያን መካከል አራቱ ዕድሜያቸው ሁለት፣ አራት፣ ስድስት እና 9 ሲሆን ከመካከላቸው የ85 ዓመት አዛውንት ሴትም ይገኙበታል።ዮኒ አሸር የተባሉት እስራኤላዊ የ34 ዓመቷ ባለቤቱ እና የ4 እና የ2 ዓመት ሴት ልጆቹ ታግተውበት ነበር።“ከደረሰብን ጉዳት እና አሳዛኝ መከረ ቤተሰቤን ለመታደግ ቆርጫለሁ። አሁን ላይ ደስታዬን አልገልጽም። ደስታዬን የምገልጸው ሁሉም ታጋቾች ሲለቀቁ ብቻ ነው” ብሏል።ኪታይ ከፍቅረኛዋ ዊቻኢ ካላፓት ጋርBBCCopyright: BBCኪታይ ከፍቅረኛዋ ዊቻኢ ካላፓት ጋርImage caption: ኪታይ ከፍቅረኛዋ ዊቻኢ ካላፓት ጋርየታይላንድ ዜጎች መለቀቅም በወዳጅ ዘመዶቻቸው በኩል የተለያየ ስሜትን ፈጥሯል። በተለይ ኪቲያ ቱኤንግሳኤንግ ከእገታው በኋላ በተደበላለቀ ስሜት ውስጥ አልፋላች።ኪታይ የ28 ዓመቱ ፍቅረኛዋ ዊቻኢ ካላፓት መስከረም 26 ላይ ከታገተ በኋላ መገደሉ በታይላንድ መንግሥት ተነግሯት ነበር። ቀጥሎ ደግሞ በጥቃቱ ተገድለዋል ከተባሉት የታይላንድ ዜጎች ዝርዝር ውስጥ የፍቅረኛዋ ስም አልነበረም።ከአምስት ቀናት በፊት የፍቅረኛዋን ስም በሐማስ ታግተው ከሚገኙ ሰዎች ስም ዝርዝር ውስጥ ከተመለከተች በኋላ አርብ ነጻ ወጥቷል።Article share tools
  8. የታተመዉ 23:42 24 ህዳር 202323:42 24 ህዳር 2023″አባቴ አሁንም እገታ ላይ ነው፤ ለሌሎች ቤተሰቦች ግን ደስተኛ ነኝ”ማያና ከወላጅ አባቷ ጋርFAMILY HANDOUTCopyright: FAMILY HANDOUTማያና ከወላጅ አባቷ ጋርImage caption: ማያና ከወላጅ አባቷ ጋርማያና ካፕሉን ኬይዳር ምንም እንኳ እርግጠኛ ባትሆንም አባቷ አሁንም በሐማስ እገታ ስር እንዳለ ታምናለች።ትናንት አርብ ነጻ ከሆኑት መካከል አባቷ አንዱ እንደማይሆን ቀድማ ብትገነዘብም፤ 13 እስራኤላውያን መለቀቃቸው ተስፋ ሰጪ እንደሆነ ትናገራለች።ሐማስ አባቷ ይኖርበት ወደ ነበረው መንደር ከገባ ከሰዓታት በኋላ ወላጅ አባቷ በሐማስ ታጣቂዎች ተይዞ ሲሄድ የሚያሳይ ምስል ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ መመልከቷን ታስታውሳለች።ሐማስ እና ታጋችSMCopyright: SMማያና አባቴ ነሁንም ጻ ባይሆንም “የቤተሰብ አባላታቸውን ለሚያገኙ ሰዎች ግን ደስተኛ ነኝ” ብላለች።በኳታር አደራዳሪነት እስራኤል እና ሐማስ በደረሱት ስምምነት መሠረት በቀጣይ 4 ቀናት 50 እስራኤላውያን ነጻ ይወጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።ማያናም ይህ ስምምነት ተፈጻሚ ሆኖ ብዙ ታጋቾችን ነጻ ማውጣት እንዲቻል ምኞቴ ነው ስትል ለቢቢሲ ተናግራለች።Article share tools
  9. የታተመዉ 12:15 24 ህዳር 202312:15 24 ህዳር 2023በሐማስ ከተለቀቁት ታጋቾች መካከል 13ቱ እስራኤላውያን ናቸውAl Qahera TVAl Qahera TVCopyright: Al Qahera TVበሐማስ እና እስራኤል መካከል በተደረሰው ስምምነት መሠረት ዛሬ አርብ ነጻ ከወጡት ታጋቾች መካከል 13ቱ እስራኤላውያን መሆናቸው ተገለጸ።የእስራኤል አምቡላንስ አገልግሎት ኃላፊ የቀይ መስቀል ምንጮችን ጠቅሰው እንደተናገሩት 13 የአገራቸው ዜጎች ነጻ መውጣታቸን ተናግረዋል።ቀደም ቀይ መስቀል ዛሬ በጠቅላለው 24 ሰዎች መለቀቃቸውን አስታውቋል።ኳታር ዛሬ ነጻ የወጡት 13ቱ እስራኤላውያን፣ 10 የታይላንድ ዜጎች እና 1 ሰው ደግሞ የፊሊፒንስ ዜጋ መሆኑን አስታውቃለች።Article share tools
  10. የታተመዉ 12:09 24 ህዳር 202312:09 24 ህዳር 2023ታጋቾቹ የጤና መጓደል አይታይባቸውም ተባለታጋቾችAl Qahera TVCopyright: Al Qahera TVየእስራኤል ጤና ኃላፊዎች ዛሬ ከሐማስ እገታ ነጻ የወጡት ታጋቾች የጤና መጓደል አይታይባቸውም አሉ።የእስራኤል አምቡላንስ አገልግሎት ኃላፊ አሊ ቢን ታጋቾቹ ምንም አይነት አካላዊ የጤና መጓደል አይታይባቸውም ስለማለታቸው የእስራኤል ጦር ራዲዮ ዘግቧል።አል ቃሄር የተባለ የግብፅ የቴሌቪዥን ጣቢያ ታጋቾች ከአምቡላንስ ሲወርዱ አሳይቷል።ታጋቾቹ ከሰባት ሳምንታት እገታ በኋላ ነው ዛሬ ነጻ የወጡት።ኃላፊው ጨምረውም ከቀይ መስቀል ተወካዮች ከተረከቧቸው ታጋቾች መካከል 13ቱ የእስራኤል ዜጎች መሆናቸውን እና 11ዱ ደግሞ የውጭ አገር ዜጎች መሆናቸውን ጨምረው ተናግረዋል።Article share tools
  11. የታተመዉ 11:35 24 ህዳር 202311:35 24 ህዳር 2023ቀይ መስቀል ዛሬ የተለቀቁት ታጋቾች 24 መሆናቸውን ገለጸቀይ መስቀልReutersCopyright: Reutersዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ማኅበር ዛሬ አርብ ሐማስ የለቀቃቸው ታጋቾች ቁጥር 24 መሆኑን አስታወቀ።ቀደም ሲል 12 የታይላንድ ዜጎች ነጻ መውጣታቸውን የታይላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ገልጸው ነበር።የእስራኤል ጦር ደግሞ 13 ታጋቾችን ከቀይ መስቀል መረከቡን ገልጿል።በጠቅላላው በዛሬው ዕለት 25 ታጋቾች ተለቀዋል የተባለ ቢሆንም፣ ቀይ መስቀል የተለቀቁት ሰዎች ቁጥር 24 ናቸች በማለቱ የቁጥር ልዩነቱ እንዴት እንደመጣ ግልጽ አይደለም።Article share tools
  12. የታተመዉ 11:15 24 ህዳር 202311:15 24 ህዳር 2023የእስራኤል ጤና ማዕከላት ለታጋቾች ሕክምና ለመስጠት እየተጠባበቀ ነውአምቡላንስIsraeli Government Press OfficeCopyright: Israeli Government Press Officeበሐማስ ታግተው ለነበሩ ሰዎች የመጀመሪያ ደረጃ ሕክምና ለመስጠት የተቋቋሙት ማዕከላት ታጋቾችን እየተጠባበቁ ነው።ቀደም ሲል የእስራኤል ጦር ሐማስ የለቀቃቸውን 13 ታጋቾች መረከቡ ተገልጿል።ዛሬ አርብ ሐማስ የለቀቃቸው ሴቶች እና ሕጻናት ለሰባት ሳምንታት ያህል በጦርነት ቀጠና ውስጥ ይዞ አቆይቷቸዋል።እስራኤልReutersCopyright: ReutersቤተሰብReutersCopyright: ReutersArticle share tools
  13. የታተመዉ 11:03 24 ህዳር 202311:03 24 ህዳር 2023የእስራኤል ጦር 13 ታጋቾችን ከቀይ መስቀል ተረከበየእስራኤል ጦር ሐማስ የለቀቃቸውን 13 ታጋቾች መረከቡ ተዘገበ።የፈረንሳይ ዜና ወኪል የሆነው አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ የእስራኤል የደኅንነት ምንጮችን ጠቅሶ እንደዘገበው ጦሩ ታግተው የነበሩ ሰዎችን ከቀይ መስቀል ተረክቧል።ቀደም ሲሉ ከሐማስ እገታ ነጻ ይወጣሉ የተባሉት 13 ታጋቾች ለቀይ መስቀል ተላልፈው መሰጠታቸው ተገልጾ ነበር።ታጋቾቹ በጋዛ እና ግብፅ መካከል በሚገኘው የራፋህ የድንበር በር አልፈው ወደ ግብፅ ተሻግረው ነበር።ይህን ሂደት ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታኒያሁ ከከፍተኛ የአገሪቱ ጦር መኮንኖች ጋር በመሆን በቅርበት ሲከታተሉት ቆይተዋል።በእስራኤል እና በሐማስ መካከል በተደረሰው ስምምነት መሠረት ዛሬ ጠዋት የጀመረው እና ለቀናት የሚቆየው ጦርነት ጋብ የማድረግ አካል የሆነው የታጋቾች መለቀቅ በቀጣይ ቀናትም እንደሚቀጥል ይጠበቃል።Article share tools
  14. የታተመዉ 10:19 24 ህዳር 202310:19 24 ህዳር 202313 ታጋቾች ለቀይ መስቀል ተላልፈው ተሰጡራፋ የድንበር በር የሰዎች እንቅስቃሴ ጨምሮ ታይቷል።ReutersCopyright: Reutersራፋ የድንበር በር የሰዎች እንቅስቃሴ ጨምሮ ታይቷል።Image caption: ራፋ የድንበር በር የሰዎች እንቅስቃሴ ጨምሮ ታይቷል።ዛሬ ከሐማስ እገታ ነጻ ይወጣሉ የተባሉት 13 ታጋቾች ለቀይ መስቀል ተላልፈው መሰጠታቸው ተዘገበ።ቻናል 12 የተባለ የእስራኤል ቴሌቪዥን ጣቢያ ቀይ መስቀል 13ቱን ታጋቾች ከሐማስ ተረክቦ በአሁኑ ሰዓት ወደ ግብፅ እያጓጓዛቸው እንደሆነ ዘግቧል።ታጋቾቹ በጋዛ እና ግብፅ መካከል በሚገኘው የራፋህ የድንበር በር የሚያልፉ ሲሆን፣ በአካባቢው የሰዎች እንቅስቃሴ ጨምሮ ታይቷል።ቀይ መስቀል ከሐማስ የተረከባቸውን 13ቱን ታጋቾች ወደ ግብፅ አሻግሮ ለእስራኤል ጦር የሚያስረክብ ይሆናል።ይህን ሂደትም የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታኒያሁ እና የእስራኤል ጦር አዛዥ ከቴል አቪቭ ሆነው በቅርበት እየተከታተሉት ነው ተብሏል።Article share tools
  15. የታተመዉ 9:23 24 ህዳር 20239:23 24 ህዳር 2023በሐማስ ታግተው የነበሩ 12 የታይላንድ ዜጎች ተለቀቁ12 የታይላንድ ዜጎች ከሐማስ እገታ ነጻ መውጣታቸውን የታይላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር አስታወቁ።ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኤምባሲ ኃላፊዎች “ታጋቾቹን ሊወስዱ እያመሩ ነው” ያሉ ሲሆን፣ ታጋቾቹን ከየት እና መቼ እንደሚቀበሉ ግን ያሉት ነገር የለም።ቀደም ሲል ግብፅ ከከፍተኛ ጥረት በኋላ 12 የታይላንድ ዜጎች እንዲለቀቁ አድርጊያለሁ ብላ ነበር።የታይላንድ ዜጎች መለቀቅን በተመለከተ እስካሁን በሐማስ በኩል የተባለ ነገር የለም።የታይላንድ ዜጎች መለቀቅ የተሰማው እስራኤል ሴቶች እና ሕጻናት የሆኑ 13 ታጋቾችን በቀይ መስቀል በኩል ከሐማስ እገታ ነጻ ይወጣሉ ብላ እየተጠባበቀች ባለበት ሰዓት ነው።ሐማስ መስከረም 26 በእስራኤል ላይ ድንገተኛ ጥቃት ፈጽሞ 230 ያላሱ ሰዎችን አግቶ ወደ ጋዛ ሰርጥ መውሰዱ ይታወሳል።Article share tools
  16. የታተመዉ 8:43 24 ህዳር 20238:43 24 ህዳር 2023ታጋቾችን ከሐማስ የመረከቡ ሥራ ቀላል አይሆንም ተባለዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ማኅበር ከሐማስ እገታ ነጻ የሚሆኑ ሰዎችን ለመረከብ ጋዛ ቀድሞ ቢገኝም ሂደቱ ግን ቀላል እንደማይሆን ተገምቷል።ቀይ መስቀል ታጋቾቹን ጋዛ ውስጥ የት እና ስንት ሰዓት እንደሚቀበል ይነገረዋል። ሁሉንም ታጋቾች ከአንድ ቦታ ወይም ከተለያዩ ቦታዎች ሊረከብ ይችላል።ቀይ መስቀል 13ቱን ታጋቾች ከሐማስ ተቀብሎ ደግሞ ወደ ግብፅ አሻግሮ ለእስራኤል ጦር ማስረከብ ይኖርበታል።ቀይ መስቀል ከዚህ በተጨማሪም ከእስራኤል እስር ቤቶች የሚለቀቁ ፍልስጤማውያንን ተቀብሎ ወደ መኖሪያቸው መሄድ የሚሹ ከሆነ ወደ ዌስት ባንክ ይወስዳል።Article share tools
  17. የታተመዉ 7:17 24 ህዳር 20237:17 24 ህዳር 2023የእስራኤል ጦር ነጻ የሚወጡ ታጋቾችን ለመቀበል መዘጋጀቱን ገለጸመጫወቻ ሰፍራIsrael Defense ForcesCopyright: Israel Defense Forcesየእስራኤል መከላከያ ኃይል አርብ [ዛሬ] ከሰዓት በኋላ ከሐማስ እገታ ነጻ ይወጣሉ ተብለው የሚጠበቁ ሰዎችን ለመቀበል ዝግጅት መጨረሱን አስታወቀ።ጦሩ በማኅበራዊ ሚዲያ ገጹ ለታጋቾች የሕክምና አገልግሎት የሚሰጡ እና የሚቆዩባቸው በርካታ ቦታዎች ዝግጁ ሆነዋል ብሏል።የእስራኤል ጦር በቀይ መስቀል በኩል ታጋቾቹን ከሐማስ ከተቀበለ በኋላ የመጀመሪያ የሕክምና እርዳታ ሰጥቶ ታጋቾች ከቤተሰብ አባላት ጋር በመላው እስራኤል በሚገኙ ሆስፒታሎች እንዲቀላቀሉ አደርጋለሁ ብሏል።ሄሊኮፍተርIsrael Defense ForcesCopyright: Israel Defense Forcesጦሩ ታጋቾቹን ለመቀበል ያደረገውን ዝግጅት የሚያሳይ ምስል ያወጣ ሲሆን፣ በምስሎቹ ላይ የሕጻናት መጫወቻ እና ማረፊያ ቦታ እንዲሁም ታጋቾች ይጓጓዙበታል የተባለ የጦር ሄሊኮፕተር ይታያሉ።እስራኤል እና ሐማስን ስታደራድር የቆየችው ኳታር የመጀመሪያዎቹን 13 ታጋቾች አርብ ከሰዓት በኋላ 10 ሰዓት ላይ እንደሚለቀቁ ማስታወቋ ይታወሳል።ዛሬ ከሰዓት ነጻ የሚወጡት ታጋቾች በሙሉ ሴቶች እና ሕጻናትን ናቸው።Article share tools
  18. የታተመዉ 6:59 24 ህዳር 20236:59 24 ህዳር 2023ወደ ጋዛ የሚገባው የሰብዓዊ እርዳታ መጠን ጨመረእርዳታ የጫኑ መኪኖች ጋዛ ሲገቡGetty ImagesCopyright: Getty Imagesእርዳታ የጫኑ መኪኖች ጋዛ ሲገቡImage caption: እርዳታ የጫኑ መኪኖች ጋዛ ሲገቡእስራኤል እና ሐማስ ለሚካሄደው ጦርነት ፋታ ለመስጠት እና ታጋቾችን ለመልቀቅ ከስምምነት መድረሳቸውን ተከትሎ ወደ ጋዛ የሚገባው የሰብዓዊ እርዳታ መጠን ጨመረ።ስምምነቱ ተፈጻሚ ከሆነበት ከዛሬ አርብ ሰዓት አንስቶ ቢያንስ 60 መኪኖች ከግብፅ ተነስተው ወደ ጋዛ መግባታቸው ተገልጿል።ግብፅ በየቀኑ 130 ሺህ ሊትር ነዳጅ ወደ ጋዛ ይገባል ብላለች። የዓለም ምግብ ፕሮግራም ደግሞ 100 መኪኖች እርዳታ ለማድረስ ዝግጁ ናቸው ብሏል።ይሁን እንጂ ከጋዛ ሕዝብ ቁጥር አንጻር አሁንም ወደ ጋዛ ሰርጥ የሚላከው ምግብ እና ነዳጅ መጠን በቂ አይደለም እየተባለ ነው።የኦክስፋም ባልደረባ የሆኑት ላይላ ባርሁም ለቢቢሲ ሲናገሩ ወደ 200 የሚጠጉ ሰብዓዊ እርዳታ የጫኑ መኪኖች በቀጣይ አራት ቀናት ጋዛ እንደሚደርሱ ቢገለጽም፣ ሁለት ሚሊዮን ሕዝብ እርዳታ ጠባቂ ለሆነባት ጋዛ አቅርቦቱ በቂ አይደለም ብለዋል።Article share tools
  19. የታተመዉ 4:09 24 ህዳር 20234:09 24 ህዳር 2023ታጋቾች በግብፅ በኩል ወደ እስራኤል እንደሚወሰዱ ተገለጸታጋቾችGetty ImagesCopyright: Getty Imagesበእስራኤል እና በሐማስ መከካል የተደረሰው የተኩስ አቁም ፋታ ከተጀመረ ሰዓታትን አስቆጥሯል።ለአራት ቀናት የሚቆየውንም የተኩስ አቁም ፋታ ተከትሎ እርዳታ ወደ ጋዛ ሰርጥ መግባት መጀመሩ ተገልጿል።በስምምነቱ መሠረት ዛሬ ከሰዓት በኋላ 13 ታጋቾች ለዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ድርጅት ይሰጣሉ። በግብፅ ራፋህ የድንበር ማቋረጫ በኩልም የሚወጡ ይሆናል።በግብፅ ድንበር በኩልም የእስራኤል የፀጥታ ኃይሎች ተቀብለው አስፈላጊውን የማንነት ማረጋገጫ ያደርጋሉ።በመቀጠልም የሕክምና ምርመራዎችን ለማድረግ ወደ ሆስፒታሎች ከተወሰዱም በኋላ ከቤተሰቦቻቸው ጋር የሚገናኙ ይሆናል።ከሰዓታት በኋላም እስራኤል በእስር ከያዘቻቸው ውስጥ በሺዎች ከሚቆጠሩ ፍልስጤማውያንም የተወሰኑት የሚለቀቁ ይሆናል።Article share tools
  20. የታተመዉ 3:06 24 ህዳር 20233:06 24 ህዳር 2023ኳታር ደመኞቹን እስራኤልን እና ሐማስን እንዴት ከስምምነት እንዲደርሱ አስቻለች?ኳታር ትንሽ አገር ናት። ልቧ ግን ትልቅ ነው። ኳታር ድሃ አገር ነበረች። አሁን ታሪክ ተቀይሯል። ኳታር የምዕራቡ ዓለም ወዳጅ ናት። አሸባሪ የሚባሉ ቡድኖችም አለኝታችን ይሏታል። መጠጊያችን ይሏታል።ተጨማሪ ያንብቡArticle share tools