Minilik Salsawi = አማራ ክልልን ለሁለት ለሶስት መከፋፈል የሚሉት ሃሳብ አዲስ አይደለም ! አብይ አሕመድ ጠረጴዛ ላይ የነበረ አሁንም ያለ ነው። ብልጽግና በሚያመቸው መልኩ እንጂ በሕዝብ ፍላጎት ላይ የተመሰረተ ስራ ሲሰራ አይተን ሰምተን አናውቅም። እነጃልመሮ እና ሌሎችም ኦሮሚያ በውስጡ ያሉ እንደ ወለጋ እና ባሌ ተነጥለው ክልል እንዲሆኑ ጠይቀዋል ሸዋም እንዲሁ ፤ እነ ጀዋር የአማራ ክልል ትልቅ ነው መከፋፈል አለበት ብለው ከነገሩን አራት ዓመት ሆኖታል ። ለምን በዚህ ጉዳይ ላይ ውሳኔ አይሰጥም ? የሚለው አካል ፋይሉን አንስቶ የመበጣጠስ ሕልሙን ሊያሳካ ተግባራዊ እንቅስቃሴ ጀምሯል።
አማራ ክልል ካልከፋፈልነው ሕዝቡ አይገዛልንም በሚል መነሾ እንደ ደቡብ ክልል ሊበጣጥሱት ካሰቡ አመታት ሆኗቸዋል። ለዚሁም ይሆናቸው ዘንድ የተለያዩ ቡድኖችን ለወሎ፤ ለጎንደር፤ ለአገው እና ሌሎች አከባቢዎች ቀደም ብለው አዘጋጅተው ፕሮፓጋንዳ ሲሰራባቸው ታዝበናል። ለዚህም ጉዳይ ተዘጋጅተው በምርጫ ቦርድ እውቅና ያገኙ የክልልነት ጥያቄ የሚያቀርቡ የፖለቲካ ፓርቲዎች በብልፅግና ተዘጋጅተዋል። ዛሬ ላይ ኮማንድ ፖስቱ ያቀረበው እና ተመስገን ጥሩነህ እንደተናገረ አድርገው ያቅርቡት እንጂ ይህ የቆየ የአብይ አሕመድ ሃሳብ እና እቅድ ነው። ፋኖ እየከረከመ ልክ ሲያስገባቸው በጭንቀት የተወጠሩት ብልጽግናዎች እቅዱን ቶሎ ወደ ተግባር ለማምጣት እየተጉ ነው።
የአማራን ሕዝብ ለማንበርከክ የሚኬድበትን መንገድ የአብይን አገዛዝ ዋጋ እንዳያስከፍለው ያሰጋል። አንድ ሆኖ የኖረን ሕዝብ አንድ አይደለህም መከፋፈል አለብህ የሚል የራሳቸውን በብሄርና በቋንቋ ያደራጁትን ሕገመንግስት የሚጥስ አሰራር እያሳዩን ነው። ይህ የለመዱትና ሕገመንግስት መናድ የሚሉት ተቃዋሚዎችን ለመክሰስ ብቻ የሚጠቀሙበት ሕገ መንግስታቸውን ራሳቸው ሊንዱት እያሟሟቁ ነው። ሕገመንግስታችን የሚሉትን በደቡብ ክልል ላይ ንደውታል። የአማራ ክልል ላይም ንደውታል። ሕገመንግስቱ እነሱ ሲንዱት ፅድቅ ሌሎች ሕገመንግስታዊ ጥያቄ ሲያነሱ ወንጀል የሚሆንበትም ለዚሁ ነው። ራሳቸው እናመልከዋለን የሚሉት ሕገመንግስት ለውሸት ትርክታቸውና ተቃዋሚዎቻቸውን ለማጥቃት ይጠቀሙበታል። የሕግ የበላይነት በሌለበት አገር ስለ ሕግ ማንሳት ስለ ሚናገሩለት ሕገ መንግስት ማውራት ስለ ራሳቸው ዳኝነት መናገር ቅንጦት ነው። #MinilikSalsawi
