November 25, 2023 – Zemedkun Bekele

የፋኖ ውሎ በቡሬ…! ( ዘመድኩን በቀለ )

• በውስጥ መስመር የተላከ

“…ዛሬ እግር ጥሎኝ በቡሬ ከተማ ከትሜ ነበር። የቡሬ ሕዝብ ፈጣሪውን አመስግኖ ቤቱን በመጠራረግና ግድፍት የነካውን ዕቃ በማጽዳት ላይ ነበር። ልክ 3:21 ሲል ተኩስ ተጀመረ። እህ ቆንጆዎቹ ገቡ ማለት ነው ብሎ ሰዉ ወደ አጠባው ተመለሰ። ለተወሰነ ደቂቃ ከተተኳኮሱ በኋላ አለቀ። የሆነው እንዲህ ነው። የብአዴን ግልገል ካድሬዎች በመከላከያ ኦነግ እየታጀቡ ሲያናፉ እንዘጭ እንቦጭ ሲሉ ዋሉ። አደሩ። በማይክራፎን አስለፈፉ። ነገሥራ እንድትጀምሩ አሉ። ሚሊሻ ግባ ወደ እርሻ መባሉ ቀርቶ የመንግሥት ሠራተኛውን ነገ ሥራ እንድትጀምር እያሉ አደነቆሩት።

“…ፋኖ ሆየ አጠና፣ አደባ፣ አቀደ ቀን ቆጥሮ ግልገል ካድሬ በአጥቦ አይለብስ ሚሊሻና በእውር ድንብር በሚንጋጋ የአብይ ኦነግ ሠራዊት ታጅቦ ስብሰባ ጠራ። ካድሬ የስብሰባ አዳራሹ ገባ። ፋኖ አውሎነፍስ ሄሪኬን ሱናሚ ሆኖ ከተፍ። ምድረ ግልገል ካድሬ አላባቸው። ላብ ጨረሱ። መቅኔአቸውን በላብ መልክ ጨረሱ። ምድረ አጥቦ አይለብስ የእሳት አራት ሆኑ። በተነነ በቀለጠ መቅኔ ሲድህ ሲያንቧች የፋኖ ጥይት በጭንቅላታቸው ተቆጠረባቸው። የጢንዝዛ ቤት ሠሩባቸው።

“…ምልምል ግልገል ካድሬ የብልፅግና ጽ/ቤት ሓላፊ ተብሎ የተሾመ ይገርማል የሚባል (ዲያቆን) የጢንዝዛ ቤት ከተሠራባቸው አንዱ ነው። በህይውት አለ ፋኖ ማርኮ ወስዶታል የሚሉ አሉ። ከፖሊስ፣ ከአጥቦ አይለብስ ሚሊሻ፣ ከመከላከያ ኦነግ አያሌ ቁጥር ያላቸው ወደማይመለሱበት ተሸኙ። በንፁሀን ላይ በከባድ መሳሪያ ጉዳት ደርሷል። የቡሬ ጤና ጣቢያ የከባድ መሳሪያ ሰለባ ሆኗል። ባለሙያወችም ጉዳት እንደደረሰባቸው ይነገራል። ሙትና ቁስለኛ ሲያመላልስ የነበረ አንቡላንስ አንድ ባጃጅ ገጭቶ ሹፌሩ ትንሽ ጉዳት ደርሶበታል። አበቃሁ።

• ዲዲሞስ ቶማስ ነኝ ቡሬ ጎጃም።