November 25, 2023

1. ቡሬ ከተማ ትላንት በነበረ ውጊያ ህዝብ ሲረብሹና ለብልፅግና ያደሩ በቁጥር 31 ያህል የአድማ ብተና እና ሚሊሺያ አባላት ተወግደዋል።

2. በእንጅባራ ከተማ የተሰራው የምሽት ኦፕሬሽን በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል። ኦፕሬሽኑ የብልፅግና ሰራዊትን ሎጅስቲክ ኢላማ ያደረገ እንደነበር የፋኖ የዘመቻ መምሪያ አስታውቋል። በዚህም በርካታ የነፍስ ወከፍ መሳሪያዎች ተማርከዋል።

3. ዱር ቤቴ ዛሬ ሌሊት በተደረገ ውጊያ የብልጽግና ሰራዊት ሙትና ቁስለኛ ሆኗል። የተረፈው ወደ መርዓዊ አቅጣጫ ፈርጥጧል።

4. አዲስ ዘመን ከተማ ሌሊት ላይ በፋኖ ተይዛለች። አዲስ ዘመን ከባህርዳር ወደ እብናት እና ጎንደር፣ እንዲሁም ከጎንደር ወደ ደብረ ታቦርና ባህርዳር የሚወስደው መንገድ ላይ ያለች ስትራቴጂካዊ ቦታ ነች።

5. የጠላት ሃይል መንገድ ሲመሩ የነበሩ የምዕራብ ጎጃም የፖሊስ መምሪያ ሃላፊዎች ተወግደዋል።

6. ሸዋሮቢት ከተማ ዙሪያ ከትናንት ወዲያ የተጀመረው ውጊያ በብልፅግና ሰራዊት ላይ ከፍተኛ ኪሳራ አድርሷል።  ( ashara Media )