እግዚአብሔር ይርዳኝ ለመሰቀል ዝግጁ ነኝ!!

“ጥቅል የንግግሬን ሃሳብ የወሰደልኝ ማንም የለም፣ ሁሉም መስማት የሚፈልገውን ብቻ መርጦ ነው የሚሰማው። መንግስትም በሚዲያው ቆራርጦ የሚመቸውን ወስዶ በሚዲያው አሰራጨ፣ ሌላውም የሚመቸውን ወሰደና ሁሉ አብጠለጠለኝ። ሁሉም ስቀለው ስቅለው አሉኝ። እግዚአብሔር ይርዳኝ ለመሰቀል ዝግጁ ነኝ። በዚህ ዘመን ምን እንድል ነበር የተፈለገው? እኔ ሸሽቼ ደኅንነቱ የተጠበቀ ቦታ ላይ ኾኜ ሳይሆን ፣ ከእናንተ ጋር መከራው ውስጥ ካላችሁት ጋር መሐል ኾኜ መታሰርንም መሰደብንም እያመንኩ ነው እየተናገርኩ ያለኹት።”

ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ