November 26, 2023 – ምንሊክ ሳልሳዊ 

የደም ካሳ እንዳይዘረፍ ማን ዋስትና ይሰጣል ? ዘረፋውና የመሳሪያ ግዢው የፈጠረው የዶላር ማጣት በሽታ ……….. የሩዋንዳውን የደም ካሳ ሕወሓት በልቶታል፤ የሶማሊያው ላይ ኦሕዴድ አሰፍስፏል !

የሃገሪቱን የውጪ ምንዛሬ ሙጥጥ እያደረገ የሚዘርፈው የአብይ አገዛዝ፤ ለአፍሪካ ልማት ባንክ ሳይከፍል እንደተከፈለ አድርጎ በተዘዋዋሪ የዘረፈው የአብይ አገዛዝ፣ የውጪ ምንዛሬን ወደአገር እንዳይገባ የሚያደርጉና ዶላርን ከሃገር የሚያሸሸ ባለስልጣናትን የታቀፈው የአብይ አገዛዝ ከፍተኛ የውጪ ምንዛሬ እጥረት ሲገጥመው አበዳሪዎች ዶላሩን ሲከለክሉት አሁን ደግሞ በሶማሊያ የሞቱ የሰላም አስከባሪ ወታደሮችን የደም ካሳ እንዲከፈለው ጠይቋል። ይህ ሁሉ የዶላር ችግር የፈጠረው ውጥረት ነው። ዶላሩ ባይዘረፍ እና ለመሳሪያ ግዢ ባይውል ኖሮ ይህን ሰዓት የዶላር ችግር ባልኖረ ነበር ። በተጨማሪም ለሃገር ውስጥ የፖለቲካ ችግሮች ፖለታዊ መፍትሄ ቢሰጥና መንግስታዊ የሃይል ተግባራት ቢቆሙ የዶላሩ ችግር መፍትሄ ያገኝ ነበር።

የዶላር ችግር ያመጣው ጣጣ 8000 የፔፕሲ ሰራተኞች ስራ አጥ ሆነው ከነቤተሰባቸው ሜዳ ላይ ሊበተኑ መሆኑን የሰማነው ትላንት ነው። ባለፉት አምስት አመታት ሃገሪቷ ያገኘቻቸው ብድሮች፤ እርዳታዎች፤ ከተለያዩ መስኮች የተገኙ የውጪ ምንዛሬዎች የት ገቡ ብለው ብትጠይቅ አንድም ለሕዝብ ጥቅም አልዋሉም ። ካሁን ቀደም ወደ ሩዋንዳ ዘምቶ የነበረውን የሰላም አስከባሪ ሃይል የተከፈለውን ዶላር ሕወሓቶች ዘርፈውታል፤ አሁን ደሞ በተራው ኦሕዴድ ወደ ሶማሊያ የዘመተውን የሰላም አስከባሪ ሃይል የኢትዮጵያ ወታደሮችን የደም ካሳ ሊዘርፍ አሰፍስፏል። #MinilikSalsawi