November 26, 2023 – ምንሊክ ሳልሳዊ 

ስርዐት አልበኝነትን ያነገሰው የወሮበሎች አገዛዝ (ምንሊክ ሳልሳዊ)

ስለ አብይ አገዛ ባለፉት አመታት በርካታ ጉዳዮች ተነስተዋል። የአብይ አገዛዝ በውሸቱና በማጭበርበር
ፖለቲካው አፍዝዟቸው የሰገዱለት የተወሰዱት ሲነቁበት የተወሰኑት ደሞ እየሰገዱለት ሲሆን የተወሰኑት
ደሞ ለስለላ በውጪ ሃገር አሰማርቷቸው የለውጥ ሃዋርያ ሆነው ለመነበብ ከመሞከራቸውም አልፎ
የተለያዩ ቴክኖሎጂዎችን በመተቀን አቅጣጫ በመተቆም የአማራን ሕዝብ እያስደበደቡት ነው
በኢትዮጵያ የተንሰራፋው እና የዘር ፖለቲካን በተረንነት እየተጠቀመበት በሃገር እና በሕዝብ ላይ ከፍተኛ
ሰቆቃና ኪሳራ እየፈጸመ ያለው የከሰረ መንግስት በዋነኛነት ስርዐት አልበኝነትን የሃገሪቱ መመሪያ አድርጎ
ከመንቀሳቀሱም በላይ ባለስልታኖቹ የሕግ የበላይነትን በመደፍጠጥ ከፍተኛ የሆነ ወንጀል በሕዝብ ላይ
እንዲሁም በአለም አቀፍ ዲፕሎማቶች ላይ በመፈጸም የሃገራችንን መልካም ገፅታዎችን እያበላሹ
ቀጥለዋል።

ስርዓት አልበኝነት የሕግ የበላይነትን ውጦታል። ጠንካራ መንግስታዊ መዋቅር ባለመኖሩ ስርአት አልበኝነት
በሀገሪቱ ነግሷል። ህግና ስርዓት መከበር አለበት የሚሉ ዜጎች ወደ እስር ቤት እየተወረወሩ ይገኛሉ። ዜጎች
በዘፈቀደ ከሕግ ውጪ ስለሚጋዙ በኢትዮጵያ መንግስታዊ ስርዐት አልበኝነት ከመስፋፋትም አልፎ መደበኛ
የመንግስት ስራ ሆኗል። በአለም አቀፍ ደረጃ በመንግስትነት ስልጣን ላይ ተቀምጦ በህግ አልመራም እና
አሻፈረኝ ያለው የአብይ አገዛዝ ብቻ ነው። ነገሮች ሁሉ ከመስመር ወተዋል። መንግስት ነኝ የሚለው አካል
ሁሉም ነገር ከቁጥጥሩ ውጪ ነው። በህግ አምላክ ሀገር በህግ ትመራ ያሉት በሙሉ በሚባልበት ሁኔታ
በወሕኒ ቤት ናቸው። ሃገርን እያመሱ እየዘረፉ እየገደሉ ያሉ ስርዐት አልበኛ ቡድኖች አገሪቷን እየመሩ
በሕግ አምላክ የሚሉትን እያሳደዱ እያሰሩ ይገኛሉ። በሕገመንግስት እና በዲሞክራሲ ሽፋን ሕዝብን
እያንገላቱ ያሉ የመንግስት ባለስልታናት ሃይ የሚላቸው ስለጠፋ ስርዐት አልበኝነቱ ሃገሪቷን ወደ ገደል
ወስዷታል ሰላሟን እንድታታ አድርጓል። ይህ ከባድ አደጋ የሕግ የበላነትን ደፍጥጦ ሃገር በግለሰቦች ተራና
በማሃይማን ውሳኔ እንድትመራ በሩን ከፍቱ ስርዐት አልበኝነትን አንግሷል።

ለአንድ ሃገር በቅድሚያና በዋነኝነት የሕግ የበላይነት ግዴታ እና ሊቀድም የሚገባው ጥብቅ ጉዳይ ነው።
መንግስታት የማይደራደሩበት ጉዳይ ቢኖር የሕገ የበላይነትን ማስፈን ነው። የሕግ የበላይነት ተብሎ
ተደጋግሞ ሲነገር የምንሰማው በሰለጠኑት ሃገሮች የሚታየው የዲሞክራሲ መሰረት ነው። የሌብነቱና
የዝርፊያው መጧጧፍ፣ ብሔርተኝነት ላይ ተሰንቅሮ አገራዊ ራዕይ ማጣት መበራከት፣ የሰብዓዊና
የዴሞክራሲያዊ መብቶች ጥሰት መበራከት፣ በመንግሥታዊ ተቋማት ውስጥ የብልሹ አሠራሮች ቅጥ
ማጣት፣ የመንግሥት ባለሥልጣናትና የባለሀብቶች በጥቅም የተሳሰረ አደገኛ ጉድኝት፣ የፍትሕ ሥርዓቱ
የዜጎችን ዕንባ መፍሰስ አለማቆም፣ የሕገወጦችና የሥርዓተ አልበኞች መንሰራፋት፣ ከቦታ ወደ ቦታ
በሰላም ተንቀሳቅሶ ጉዳይን ማከናወን አለመቻል፣ በጠራራ ፀሐይ ዜጎችን እያገቱ በሚሊዮኖች የሚቆጠር
ገንዘብ የሚጠይቁ ወረበሎች ከልካይ ማጣትና በርካታ ችግሮች የመንግሥት ያለህ የሚያሰኙ የዘመናችን
አደገኛ ክስተቶች ናቸው፡፡ የመንግሥት ተቀዳሚ ኃላፊነት ደግሞ የሕግ የበላይነት፣ የዜጎችን ሰላምና
ደኅንነት ማረጋገጥ ነው፡፡ ትላንትም ዛሬም ነገም የሕግ የበላይነት ይረጋገጥ ነው ለዚህ ደሞ ሕዝባዊ
መንግስት አስፈላጊና ዋነናው ነው። ብልፅግና የሚባለው የለብለብ ፓርቲ የሕግ የበላይነትን ማስፈን
አይደለም ሃገርን በወጉ ማስተዳደር አልቻለም።

በፖለቲካው በኢኮኖሚውና በማሕበረሰቡ መስክ የሚፈፀመው ደባ እጅግ አደገና ነው፤ የሃገርን እና
የሕዝብን ሃብት ከማውደምና ከመዝረፍ ጀምሮ በጦርነት ከጥቅም ውጪ የሚደረጉና ሆን ተብለው
በተፈጠሩ ጥላቻዎች የሚካሂደት የተንኮል መርሃግብሮች ሰርቶ መኖር የሚፈልገውን ሕዝብ ዋጋ
እያስከፈሉት ከመሆኑም ባሻገር በስልጣን ለመቆየት ብቻ ሲባል የሚከናወኑ መንግስታዊ ሽብሮችና
ስርዐት አልበኝነቶች እጅግ አደገኛ አደጋዎችን እንድንጋፈጥ አድርጎናል። ይህ ደሞ ስልታን የያዘው አካል
የፈተረው ችግር ሲሆን በስልጣን ለመቆየት የሚደረገው አካል ነው። ለምሳሌ ኢኮኖሚውን ብንወስድ
የኢትዮጵያ የንግድ ስርዓት በሌቦች፣ በኮትሮባንዲስቶችና በሽፍቶች የተተበተበና ስርዓት አልበኝነት
የሰፈነበት ነው ። ኹሉም የአገሪቱ የንግድ ስርዓት በሙሉ ተበላሽቷል በሚባልበት ደርጃ ላይ መሆኑን ራሱ
ለስልጣኑ የሚታገለው ስርዐት አልበኝነትን ያነገሰው አካል ያመነው ጉዳይ ነው። የሲሚንቶ፣ የጤፍ፣
የምግብ ዘይት፣ የስንዴ፣ የወርቅ፣ የማዳበሪያ፣ እና የሌሎች ፍጆታዎች የንግድ ስርዓት ህግን ባልተከተለ
አሰራር የሚመራና ህገወጥ ደላሎች የበዙብት በመሆኑ እጅግ የተበላሸ ሲሆን በአብይ አገዛዝ ባለስልጣናት
በተለይ በኦሮሚያ ክልል ባለስልጣናትና ቤተሰቦቻቸው የተያዘና የሃገሪቱን እድገት ቆልፎ ያስቀመጠ አደገና
የኢኮኖሚ ወሮበላት እየተካሄደ መሆኑ ይታወቃል።

የኢትዮጵያ ህዝብ በኑሮ ውድነትና በሕገወጥ ንግድ ተማሯል የመንግሥት አመራሮች፣ ደላሎችና
ባለሀብቶች ተቀናጅተው በፈጠሩት ብልሹ አሰራር ሕዝቡ እየተጎዳ ነው ። ትናንሽ ነጋዴዎች በትልልቅ
ነጋዴዎች ጉዳት ይደርስባቸዋል፣ ደላሎችን መቆጣጠር ባለመቻሉም ሕገወጥነት የበላይነትን ይዟል ፤ ይህ
የሚመራው በመንግስት ባለስልጣናት ነው ። የኢኮኖሚ አሻጥር ዋና ተዋኛን ራሳቸው ሆነው ስለ ሕኛ ስለ
ደንብ ስብሰባ ውይይት ወርክሾፕ በማዘጋጀት ሕብረተሰቡን በውሸት የሚዲያ ፍጆታ ይጫወቱበታል።
በዋነኝነት በየስብሰባውና ወርክሾፑ ንግግር የሚያደርጉት የአሻጥሩ መሪዎቹ የስርዐት አልበኝነቱ
አስተባባሪዎች መሆናቸውን ስታይ ያበሳቻል። አገር በምን አይነት ሆዳሞች እንደምትመራ ስትመለከተ
ትበኛለህ፤ እነዚህ ባለስልታናት በሃሰተና ንግግራቸው በመሰረታዊ ፍጆታዎች ላይ የተደራሽነት ፍትሃዊነት
እና የዋጋ ችግር መኖሩን ቢናገሩም ችግሩ አሁንም ተባብሶ እንደቀጠለ ነው ፤ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ
ሳይኖራቸው ሀብታም የሆኑና በንግድ ስርዓቱ ውስጥ የሚገኙ በርካታ ነጋዴዎች አሉ። እነዚሁ
ባለስልጣናት በፈጠሩት ስርዐት አልበኝነት አብዛኛው የንግድ ማህበረሰብ የንግድ ፈቃዱን እየዘጋ ወደ
ሕገወጥ ንግድ እየተቀላቀለ ነው፤ ለዚህ ሁሉ ኪሳራ ተተያቂዎቹ ራሳቸው የስልጣን ጥማት አስክሯቸው
አሻጥር የሚሰሩት አብይ እና ጄሌዎቹ ናቸው።

ብልጽግና የአለም አቀፍ ማጅራት መቺዎች ስብስብ ነው የምንለው ወደን አይደለም፤ የአብይ ሚኒስትሮች
ጠባቂዎቻቸውን እየላኩ ታላላቅ ዲፕሎማቶችን በማስደብደብ እና በመዝረፍ ስራ ላይ ተሰማርተዋል። ይህ
መንግስታዊ ሽብር ነው። ካሁን ቀደም የነበሩ መንግስታት የገነቡትን የሃገር መልካም ገፅታ እነ አብይ
አበላሽተውታል። የውሸታሞች፣ የግፈኞችና የሌቦች ስብስብ የሆነው ብልፅግና በሃገሪቱ ለውጥ ከማምጣት
ይልቅ ስርዐት አልበኝነትን አስፍኗል።

በኢትዮጵያ ሰላም መጥፋት እና የሕግ የባላይነት እንዳይኖር ከፍተኛው እንቅፋት እየሆኑ ያሉት የብልጽግና
ባለስልጣናት መሆናቸው በተደጋጋሚ እያየን ነው። በሃገር ውስጥ በዜጎች ላይ ከሚፈፅሙት ወንጀል አልበቃ
ያላቸው አለም አቀፍ ማጅራት መችነታቸውን በተግባር አሳይተዋል። የአለም ባንክ የኢትዮጵያ ዳይሬክተር
የሆኑትን ዲፕሎማት የአሕመድ ሸዴ ጠባቂዎች እንደደበደባቸውና ይህን ተከትሎ የአፍሪካ ልማት ባንክ
ሰራተኞቼ የደሕንነት ስጋት አለባቸው ብሎ ድርጅቱን እንደዘጋ ባለፉት ሁለት ቀናት ከሰማናቸው መረጃዎች
እና ከባንኩ ቢረጋገጥም አሁንም የአብይ አሕመድ መንግስት በይፋ ጥፋቱን አምኖ ይቅርታ መጠየቅ
ሲገባው ለማድበስበስ የሚሄድበት መንገድ አሳፋሪ መሆኑን የባንኩ ሰዎች ይናገራሉ። ኢትዮጵያ በአለም
መድረክ እያዋረዱ የሚገኙት የአብይ ባለስልጣናት ሃገሪቷን እና ዜጎቿን በጦርነት መግደላቸው ሳያንሳቸው
አለም አቀፍ ወንጀል መፈፀማቸው ለአፍሪካ የነፃነት ቀንዲል የሆነችዋን አገራችንን በአለም አደብባባይ
አዋርደዋታል። የሕግ የበላይነት አለመኖሩ ሕዝቡ ሰላሙን እንዲያጣ አብይና ባለስልጣናቱ በሕዝብ ላይ
እንዲቀልዱ ሆኗል።

አብይ አሕመድ እና ባለስልታናቱ በአማራ ክልል የከፈቱት ጦርነት ለስልታን ጥማት ካላቸው መነሾነት
መሆኑ ይታወቃል። ይህ የአማራ ክልሉ ጦርነት ከትግራይ ክልል በላይ ከፍተና ውድመት በክልሉ ላይ
እንዲደርስ አድርጓል። የሕወሓት ወታደሮች በትግራዩ ጦርነት እስከ ደብረሲና ዘልቀው ገብተው አማራ
ክልልን ማውደማቸው የሚታወስ ሲሆን ጎንደርና ጎጃም ለመግባት ባለመቻላቸው ባለማውደማቸው
ሲቆጭ የነበረው የአብይ አገዛዝ ራሱ ድሮኖችን አሰማርቶ አለም አቀፍ የጦር ሕግጋትን በመጣስ ሕዝብን
በመጨፍጨፍ፣ ሴቶን በመድፈር የሃይማኖት ተቁማታን በማቃጠል፣ ባንኮችን በመዝረፍ የገበሬውን
ሰብል በማቃጠል ፤ ንብረትን በማውደም የአማራ ክልልን ወደኋላ 40 አመት እንዲመለስ አድርጎታል።
በፋኖ ትግል እየተመከተ ያለው የአብይ ስርዐት አልበና አገዛዝ ሕኛ አስተዳደር በአማራ ክልል እንዳይኖር
ለማድረግ በየጊዜው የተለያዩ ሰንካላ ስራዎችን ቢሰራም የፋኖ ታጣቂዎች በተቆታተሩበት ቦታ ሕኛ ስርዐት
እንዲኖር በማድረግ ሕዝቡ በራሱ ሹመኞች እንዲተዳደር እያደረጉት መሆናቸውን ከየአከባቢው የሚወጡ
ዘገባዎች ያሳያሉ። የአብይ ስርዐት አልበና አገዛዝ ተቀባይነት ያሌላቸውን ምክን ያቶች በመደርደር ሕዝብን
እያንገላታና እየገደለ ሰላማዊ ዜጎች ሰርተውና አርሰው እንዳይኖሩ በማድረግ ላይ ይገናል። ይህንን ስርዐት
አልበንነት አስወግዶ በሕግ ለመመራት ፋኖ ትግሉን ቀጥሏል። ይህ የፋኖ ትግል በአራቱም አቅጣጫ
የተለያዩ ድሎችን በመቀናጀት ከሕዝብ ጋር ሆኖ እየገሰገሰ ይገናል።
ምንሊክ ሳልሳዊ