November 27, 2023 – Konjit Sitotaw 

የወራሪ ቡድኑ ሰራዊት በደብረታቦር መስጊድ ላይ ጉዳት ማድረሱ ተገለፀ።

1. የህግና የሞራል ተጠያቂነትን አሽቀንጥሮ የጣለው ወራሪ ሰራዊት ዛሬ በደብረታቦር ከተማ ውስጥ በሚገኝ መስጊድ ላይ ከባድ መሳሪያዎችን በመተኮስ ጉዳት እንዳደረሰ ታውቋል። በትላንትናው ዕለትም በተመሳሳይ በዚሁ የደብረታቦር የአቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ ቤተክርስቲያንን በከባድ መሳሪያ መደብደቡና ጉዳት ማድረሱ ይታወሳል።

2. በሌላ መረጃ ደግሞ ይህ ሰውበላ ሰራዊት በቢቸና ደብር (ከቢቸና ከተማ 3ኪሜ ርቀት) ዛሬ የአካባቢውን የገበሬ ማህበርን መጋዘን በመስበር ሽንብራና የተለያዩ እህሎችን መዝረፉን የአካባቢው ምንጮች አስታውቀዋል። ሰራዊቱ ከመጋዝኑ ከዘረፈው ውስጥ 164 ኩንታል ለምርጥ ዘር የመጣ ሽምብራ ይገኝበታል።