ሐማስ 11 ተጨማሪ ታጋቾችን ሲለቅ እስራኤል 30 ህጻናትን ጨምሮ 33 እስረኞችን ፈታችRelated Video and Audio
የዓለም ጤና ድርጅት በጋዛ በጥቃቶች ከሚገደሉ ሰዎች በላይ ሕክምና ሳያገኙ ሕይወታቸውን ሊያጡ የሚችሉ ሰዎች ቁጥር ሊጨምር ይችላል አለ።ድርጅቱ ይህን ማስጠንቀቂያ የሰጠው በጋዛ በሚገኙ መጠለያ ጣቢያዎች በልጆች እና ጨቅላዎች ላይ የተቅማጥ በሽታ እና የመተንፈኛ ኢንፌክሽን መበራከቱን ተከትሎ ነው።በእነዚህ በሽታዎች እየተጠቁ ላሉት ምንም አይነት የሕክምና እርዳታ እየተሰጠ አለመሆኑን ድርጅቱ ገልጾ የካንሰር፣ የልብ ወይም የስኳር ህመምተኞችም ምንም አይነት የጤና ድጋፍ እያገኙ አለመሆኑንን ገልጿል።የተመድ የሕጻናት አድን ድርጅት (ዩኒሴፍ) በበኩሉ በጦርነቱ ምክንያት በከፍተኛ ደረጃ የቆሰሉ ሕጻናት በመኪና ማቆሚያ ቦታዎች እና ሜዳዎች ላይ ወድቀው ይገኛሉ ብሏል።ሰብዓዊ እርዳታ አቅራቢ ድርጅቶች ጦርነቱን ዳግም መጀመር ጨርሶ መታሰብ የለበትም የሚሉ ሲሆን፣ ዘላቂ የሆነ የተኩስ አቁም ስምምነት በሁለቱ ተዋጊዎች መካከል እንዲደረግም ጠይቀዋል።
ሐማስ እና እስራኤል ለጦርነቱ ፋታ ለመስጠት የደረሱትን ስምምነት ቢያራዝሙም በጋዛ ሰማይ ላይ ትልቅ ጭስ ታይቷል።አንዳንድ ሪፖርቶች እንደሚጠቁሙት ከሆነ የተኩስ አቁም ስምምነቱ መራዘሙን ያላወቁ ፍልስጤማውያን ቡድኖች በእስራኤል ወታደሮች ላይ ተኩስ ሳይከፍቱ አልቀሩም።በኳታር አደራዳሪነት ሐማስ እና እስራኤል ለአራት ቀናት ተኩስ ለማቆም የደረሱት ስምምነት ሰኞ ዕለት ለሁለት ተጫማሪ ቀናት መራዘሙ ይታወሳል።ለተጨማሪ 48 ሰዓታት ተኩስ ለማቆም በተደረሰው ስምምነት ወቅት ሦስት ፍልስጤማውያን በአንድ እስራኤላዊ ለመለወጥ ሐማስ እና እስራኤል ተስማምተዋል።
ሐማስ በመስከረም 26ቱ ጥቃት የታገቱት ሰዎች በሙሉ በቁጥጥሩ ስር እንደማይገኙ አስታወቀ።በኳታር የሚገኙ አንድ ከፍተኛ የሐማስ መሪ ቁጥራቸው በውል የማይታወቁ ታጋቾች በሌሎች ሚሊሻ ቡድኖች እጅ እንደሚገኙ ገልጸዋል።ለምሳሌ በመስከረም 26ቱ ጥቃት ተሳታፊ ከነበሩት ቡድኖች መካከል አንዱ የሆነው የፍልስጤም እስላማዊ ጂሃድ 20 ታጋቾችን ይዞ ይገኛል። ከእነዚህ መካከል አስሩ ዛሬ የሚለቀቁ ሲሆን፣ ቀሪዎቹ ደግሞ ነገ ረቡዕ ይለቀቃሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ሐማስ ታጋቾችን እየለቀቀ ለጦርነቱ ፋታ የሚሰጥበት ቀን እንዲራዘም ፍላጎት ቢኖረውም፣ እስራኤል ግን የተኩስ አቁም ስምምነቱ ዕለታዊ ግምገማ እየተካሄደበት በየዕለቱ እንዲራዘም ፍላጎት አላት።ሐማስ መረጃ ለመሰብሰብ እና የታጋቾች መገኛ ቦታን ለማወቅ ረዘም ያለ ጊዜ ያስፈልገኛል እያለ ነው።በጋዛ የቴሌኮም መሠረተ ልማቶች መውደማቸው እና የነዳጅ አቅርቦት ውስንነት ይህን የፍለጋ ተግባር ከባድ እንደሚያደርገው ይገመታል።
የተኩስ አቁም ፋታውን ተከትሎ በእስራኤል እስር ቤት የሚገኙ 150 የሚሆኑ ታዳጊዎች እና ሴቶች ፍልስጤማውያን እስረኞች ተለቀዋል።በአራተኛው ዙር 30 ህጻናትን ጨምሮ 33 ፍልስጤማውያን እስረኞች ተፈትተዋል። በእስራኤል እስር ቤቶች 6 ሺህ 704 ፍልስጤማውያን ታስረው እንደሚገኙ የመብት ተቋማት ያስታወቁ ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ 2 ሺህ ሰባ የሚሆኑት ፍርድ ቤት አልቀረቡም ወይም ክስ አልተመሰረተባቸውም።አስተዳደራዊ እስራት ተብሎ በሚጠራውም ሁኔታ በእስራኤል እስር ቤቶች እንደሚገኙ ሃሞኬድ የተባለው የእስራኤል የመብት ድርጅት አስታውቋል።የሐማስ እና የእስራኤል የተኩስ አቁም ፋታ ተከትሎም በአራት ዙሮች 150 ፍልስጤማውያን ተፈትተዋል።በትናንትናውም ዕለት 33 ህጻናት እና ሴቶች ፍልስጤማውያን እስረኞች ሲፈቱም በርካቶች ደስታቸውን ሲገልጹም ታይተዋል።እስራኤል በወረራ በያዘቻት ዌስት ባንክ አቅራቢያ በሚገኘው ራማላህ የፍተሻ ኬላም ሲደርሱም ፍልስጤማውያን ተቀብለዋቸዋል።እስረኞቹ ድንጋይ መወርወርን ጨምሮ በግድያ ሙከራ እንደተጠረጠሩ ቢገለጽም በርካቶቹም ክስም ሳይመስረትባቸው በእስር ቤቶች ቆይተዋል።በዌስት ባንክ የሚኖሩ ፍልስጤማውያን ቤተሰቦች ቢያንስ አንድ የቤተሰብ አባላቸው በእስራኤል እስር ቤቶች ውስጥ ታስረው እንደሚገኙ ይታሰባል።ፍልስጤማውያኑ በእስራኤል ውስጥ በመታሰራቸውም ዘመዶቻቸው ወደ እስራኤል ሄደው መጎብኘት አይችሉም።መስከረም መጨረሻ የደረሰውንም ጥቃት ተከትሎ በእስራኤል እስር ቤቶች ያለ ፍርድ የታሰሩ ፍልስጤማውያን ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩንም የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች አስታውቀዋል።
የታይላንድ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ፓርንፕሬይ ባሂድድሃ ኑካራ የተኩስ አቁም ፋታውን ተከትሎ የተለቀቁ 17 ታይላንዳውያን ታጋቾችን ወደ አገራቸው ለመውሰድ ወደ እስራኤል አቀኑ።ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ፓርንፐሬይ በጥቂት ሰዓታት ውስጥ እስራኤል ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል።ከተለቀቁትም መካከል ሐማስ መስከረም መጨረሻ ባደረሰው ጥቃት የተጎዱ ሶስት የታይላንድ ዜጎችም በሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸው ሲሆን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩም ይጎበኟቸዋል ተብሏል።ባለስልጣኑ በእስራኤል ውስጥ ተቀጥረው ከሚገኙ የታይላንድ ሰራተኞችም ጋር እንደሚገናኙ የታይላንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።የተለቀቁት ታጋቾችም ሐሙስ እለት ወደ ባንኮክ እንደሚመለሱም ይጠበቃል። ተጨማሪ 15 የታይላንድ ዜጎች በሐማስ ታግተው እንደሚገኙም የታይላንድ ባለስልጣናት አስታውቀዋል።
በአራተኛ ዙር ከተለቀቁት ታጋቾች መካከል የሶስት ዓመት ዕድሜ ያላቸው መንትያ እህትማማቾች እና እናታቸው እንደተካተቱበት ተገለጸ።ሻሮን አሎን ኩኒያ እና መንትያ ልጆቿ ኤማ እና ዩሊ ቢለቀቁም ባለቤቷ እና ወንድሙ አሁንም ታግተው እንዳሉ ይታመናል።ሐማስ መስከረም መጨረሻ ላይ ጥቃት በከፈተበት ወቅት ቤሰተቡ በአንድ ቤት ውስጥ ተጠልለው ነበር ተብሏል። ሐማስ ቤቱን በእሳት ሲያቀጥለው እና ቤተሰቡ ሊያመልጥ ሲሞክርም ተይዘው መታገታቸውም ተነሯል።የሻሮን እህት ዳንኤል አሎኒ እና ልጇም ታግተው የነበሩ ሲሆን ሁለቱም አርብ እለት ከእገታ ተለቀዋል። የታገቾች እና የጠፉ ቤተሰቦች ኮሚቴም መንትያዎቹ እህትማማቾን አስመልክቶ መግለጫ አውጥቷል።ኤማ “በጣም አስደናቂ እና በፍቅር የተሞላች ህጻን ናት። ከአሻንጉሊት ይልቅ የጭነት መኪናዎችን የምትመርጥ እውነተኛ የኪቡዝ ተወላጅ ናት። እህቷ ዩሊ ዓይናፋር ስትሆም ከመታገቷ በነበሩት ሳምንታት የበለጠ ተጫዋች እየሆነች ነበር” የሚል መግለጫም አውጥቷል።ሻሮን እና ባለቤቷ ዴቪድ የተገናኙት እሱ በሚተውንበት ፊልም ላይ የህዝብ ግንኙነት ትሰራ በነበረበት ወቅት መሆኑም ተገልጿል።
በተኩስ አቁም ፋታው አራተኛ ቀን ሐማስ 11 ተጨማሪ እስራኤላውያን ታጋቾችን ሲለቅ እስራኤል 30 ህጻናትን ጨምሮ 33 ፍልስጤማውያን እስረኞችን ፈታለች።ሐማስ ከለቀቃቸው ታጋቾች መካከል የሶስት ዓመት መንትያ ህጻናት እንደሚገኙበትም ተገልጿል።በኳታር አሸማጋይነት የተደረሰውን የተኩስ አቁም ፋታን ተከትሎ እስካሁን ድረስ 69 ታጋቾችን በሶስት ዙሮች ለቋል። እስራኤል በበኩሏ 150 ህጻናት እና ሴቶች ፍልስጤማውያን እስረኞችን ፈታለች።ለአራት ቀናት ይቆያል ተብሎ የነበረው የተኩስ አቁም ፋታ ለተጨማሪ ሁለት ቀናት የተራዘመ ሲሆን በዚህም ጊዜ ተጨማሪ ህጻናት እና ሴቶች በአብዛኛው የተካተቱበት የታጋቾች እና የእስረኞች ልውውጥ እንደሚደረግ ይጠበቃል።
በእስራኤል እና በሐማስ መካከል የተደረሰው እና ለአራት ቀናት የቆየው ጊዜያዊ የተኩስ አቁም ለተጨማሪ ሁለት ቀናት እንዲራዘም ከስምምነት መደረሱን ኳታር አስታወቀች።ባለፈው አርብ ጀምሮ እስከ ዛሬ ሰኞ ሌሊት ድረስ ታጋቾችን እና እስረኞችን ለመልቀቅ እንዲሁም ሰብዓዊ እርዳታዎች ወደ ጋዛ እንዲደርሱ ለማስቻል የተደረሰው ጦርነት የመግታት ስምምነት ሰኞ ሌሊት ያበቃል ተብሎ ነበር።ባለፉት አራት ቀናት ሐማስ ከእስራኤል ታጋቾች የተወሰኑትን የለቀቀ ሲሆን፣ እስራኤል ደግሞ ፍልስጤማውያን እስረኞችን ለቃለች።በተጨማሪም በችግር ላይ ለሚገኙት የጋዛ ነዋሪዎች ምግብ፣ ውሃ፣ መድኃኒት እና ነዳጅ እንዲገባ ተደርጓል።በእስራኤል እና በሐማስ መካከል ግጭቱን በጊዜያዊነት እንዲያቆሙ ለማስቻል ኳታር ቁልፍ ሚና የተጫወተች ሲሆን፣ ግብፅ፣ አሜሪካ እና ሌሎች ወገኖች ተሳታፊ ናቸው።
ዛሬ ሰኞ በእስራኤል እና በሐማስ መካከል ለአራት ቀናት የተደረሰው ጦርነት ጋብ የማድረግ ስምምነት የሚያበቃበት ዕለት ቢሆንም ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ተኩስ አቁሙ እንዲራዘም ግፊት እያደረገ ነው።ባለፉት ሦስት ቀናት ሐማስ ከእስራኤል አግቶ ከወሰዳቸው ሰዎች መካከል የለቀቀ ሲሆን እስራኤል ደግሞ በእስር ቤቶቿ ውስጥ የነበሩ በርካታ ፍልስጤማውያንን ፈትታለች።ከዚህም ባሻገር ለሳምንታት በእስራኤል ጥቃት ምክንያት በመሠረታዊ አቅርቦቶች እጦት ሲሰቃዩ ለቆዩት የጋዛ ነዋሪዎች ሰብዓዊ እርዳታ እና ነዳጅ መግባት ችሏል።ይህ ለቀናት የቆየው ጊዜያዊ ተኩስ አቁም ዛሬ ሌሊት ከማብቃቱ በፊት እንዲራዘም ጥረት እየተደረገ ነው። የኔቶው ዋና ፀሐፊ የንስ ስቶልተንበርግ እና የአውሮፓ ኅብረት የውጭ ፖሊሲ ኃላፊ ጆሴፍ ቦሬል ጥሪ ካቀረቡት መካከል ናቸው።የመጀመሪያው ስምምነት እንዲደረስ ወሳኝ ሚና የነበራት ኳታር፣ ግብፅ፣ አሜሪካ፣ የአውሮፓ ኅብረት እና ስፔን፤ እስራኤል እና ሐማስ ጋዛ ውስጥ የደረሱት ጊዜያዊ ተኩስ አቁሙ እንዲራዘም ጥረት እያደረጉ መሆናቸውን የፍልስጤም ብሔራዊ ባለሥልጣን ሪያድ አል-ማሊኪ ተናግረዋል።የግብፅ የደኅንነት ምንጮች ለሮይተርስ ዜና ወኪል እንደተናገሩት ጦርነት የቆመበት ፋታ በቀናት ለማራዘም የሚደረገው ጥረት ወደ ስምምነት እየተጠጋ መሆኑን አመልክተዋል።ሐማስ የተኩስ አቁሙ እንዲራዘም እና ተጨማሪ ታጋቾችን ለመልቀቅ ፍላጎት እንዳለው ያሳወቀ ሲሆን፣ የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታኒያሁም ስምምነቱ እንዲራዘም የማድረግ ዕድል እንዳለ ገልጸው፣ ነገር ግን ከስምምነቱ ማብቃት በኋላ በጋዛ ውስጥ ሠራዊታቸው የሚያካሂደው ዘመቻ በሙሉ ኃይል እንደሚጀመር ተናግረዋል።
በእስራኤል እና በሐማስ መካከል የተደረሰው የእስረኞች እና የታጋቾች ልውውጥ ስምምነት የውስብስብ እና ያላሰለሰ ዲፕሎማሲያዊ ጥረት ውጤት ነው።በድርድሩ በርካታ አካላት ታሳትፈዋል። በዚህም እስካሁን 58 ታጋቾች ነጻ የወጡ ሲሆን ከአርብ ዕለት ጀምሮ 117 ፍልስጥኤማውያን እስረኞች ተለቀዋል።ዛሬ ሰኞ እኩለ ሌሊት ላይ በሚያበቃው የእስራኤል እና የሐማስ ስምምነት መሠረት 50 እስራኤላውያን ታጋቾች የሚለቀቁ ሲሆን፣ በምላሹ 150 ፍልስጥኤማውያን ከእስር ይፈታሉ።ለመሆኑ ቁጥሮቹ ለምን ተለያዩ? ስለተለቀቁ ሰዎች ቁጥር እስካሁን የምናውቀው ምንድን ነው?
- በእስራኤል እና በሐማስ ስምምነት መሠረት እስካሁን በጋዛ ታግተው የነበሩ 39 እስራኤላውያን ተለቀዋል።በእስረኞች እና በታጋቾች ልውውጡ በእስራኤል እስር ቤት ታስረው የነበሩ 117 ፍልስጥኤማውያን ከእስር ተፈተዋል።ሌላ ሮኒ ክሪቮይ የተባለ ሩሲያዊ-እስራኤላዊ ታጋችም እሑድ ዕለት በሐማስ ተለቋል። ሆኖም ታጋቹ የተለቀቀው በሦስት ፍልስጤማውያን እስረኞች ለውጥ አይደለም።ከሐማስ ጋር በተደረገ ሌላ ድርድርም በተመሳሳይ ቀን በሐማስ ታግተው የነበሩ አንድ የፍሊፒንስ ዜጋ እና 17 የታይላንድ ዜጎች ተለቀዋል።
ይህ ስምምነት አርብ ዕለት ተግባራዊ መሆን ከመጀመሩ በፊት ደግሞ ሦስት እስራኤላዊ ታጋቾች የተለቀቁ ሲሆን፣ አራተኛው በእስራኤል ጦር አማካኝነት ነጻ መውጣት ችሎ ነበር።መስከረም ወር መጨረሻ ላይ ሐማስ በእስራኤል ላይ የፈፀመውን ድንበር ዘለል ጥቃት ተከትሎ በአጠቃላይ ወደ 240 የሚጠጉ ሰዎች በጋዛ ታግተዋል ተብሎ ይታመናል።
ሐማስ በዛሬው ዕለት ይጠናቀቃል የተባለው የአራት ቀናት የተኩስ አቁም ፋታው መራዘሙን እንደሚሻ አስታውቋል።በኳታር አሸማጋይነት የተደረሰው የተኩስ አቁም ፋታ በዛሬው ዕለት የሚጠናቀቅ ሲሆን ስለመራዘሙ የተባለ ነገር የለም።በነዚህም ቀናት ሐማስ በሶስት ዙሮች 58 ታጋቾችን የለቀቀ ሲሆን እስራኤል በበኩሏ 117 ህጻናት እና ሴቶች ፍልስጤማውያን እስረኞችን ለቃለች። ሐማስ ባወጣው መግለጫ “የአራት ቀናት የተኩስ አቁም ፋታው እንዲራዘም እንፈልጋን። በሰብዓዊ የተኩሱ አቁሙ መሰረትም የሚለቀቁ ታጋቾችም ቁጥርም ይጨምራል” ብሏል።በኳታር እየተካሄደ ያለውን ድርድር በቅርበት እየተከታተሉ የፍልስጤም ከፍተኛ ባለስልጣን በበኩላቸው ሐማስ የተኩስ አቁም ፋታውን ከ2 እስከ 4 ቀናት ለማራዘም ፍላጎት እንዳለው ለአሸማጋዮቹ ማስታወቁን ለቢቢሲ ተናግረዋል።በነዚህም ቀናት ከ20-40 እስራኤውያን እስረኞች ሊፈቱ እንደሚችሉም ተጠቁሟል።በአራቱ ቀናት የተኩስ አቁም ፋታው ሐማስ 50 ታጋቾችን ለመልቀቅ እንዲሁም እስራኤል 150 ህጻናት እና ሴቶች ፍልስጤማውያን እስረኞችን ለመፍታት ስምምነት ላይ ተደርሷል።የእስራኤል መንግሥት የሐማስን መግለጫ አስመልክቶ ያለው ነገር የለም።ሆኖም ከዚህ ቀደም እስራኤል በየዕለቱ 10 እስራኤላዊ ታጋቾች የሚለቀቁ ከሆነ ፋታው በአንድ ቀን እንደሚራዘም አስታውቃለች። ሆኖም የተኩስ አቁም ፋታው ጊዜያዊ እንደሆነ እና ጦርነቱም ሐማስ ከምድረ ገጽ እስኪጠፋ ድረስ ይቀጥላል ብላለች።
በእስራኤል እና በሐማስ መካከል የተደረሰውን የአራት ቀናት የተኩስ አቁም ፋታ ተከትሎ ሐማስ 58 ታጋቾችን በሶስት ዙሮች ለቋል። እስራኤል በበኩሏ 117 ህጻናት እና ሴቶች ፍልስጤማውያን እስረኞችን ፈታለች።በትናንትናው ዕለት ሐማስ 14 እስራኤላውያን እና ሶስት የውጭ አገር ዜግነት ያላቸውን ታጋቾችን የለቀቀ ሲሆን እስራኤል ደግሞ 39 እስረኞችን ፈታለች።በአራቱ ቀናት የተኩስ አቁም ፋታው ሐማስ 50 ታጋቾችን ለመልቀቅ እንዲሁም እስራኤል 150 ህጻናት እና ሴቶች ፍልስጤማውያን እስረኞችን ለመፈታት ስምምነት ላይ ተደርሷል።በኳታር አሸማጋይነት የተደረሰው የተኩስ አቁም ፋታው በዛሬው ዕለት የሚጠናቀቅ ሲሆን ስለመራዘሙ የተባለ ነገር የለም።ሐማስ መስከረም መጨረሻ ላይ በደቡብ እስራኤል የፈጸመውን ጥቃት ተከትሎ 1 200 ሰዎች ሲገደሉ ከ200 በላይ ሰዎች ታግተዋል። እስራኤል በበኩሏ በጋዛ ሰርጥ ላይ በፈጸመችው የማያባራ የአየር ጥቃት ከ14 ሺህ 500 በላይ ፍልስጤማውያን ሲገደሉ ከነዚህም ውስጥ አብዛኛዎቹ ህጻናት መሆናቸውን በሐማስ አስተዳደር ስር ካለው የጋዛ ጤና ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያስረዳል።
Related Video and Audio