November 28, 2023 

የአሜሪካ የታችኛው ሕግ አውጭ ምክር ቤት በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ ለመምከር ለቀጣዩ ሐሙስ ስብሰባ ጠርቷል።

የምክር ቤቱ የውጭ ጉዳይ ኮሚቴ የአፍሪካ ጉዳዮች ንዑስ ኮሚቴ፣ “በኢትዮጵያ፣ ተስፋ ወይስ የበረታ ስጋት፤ የአሜሪካ ፖሊሲ ኹኔታ’’ በሚል ርዕሰ ጉዳይ ላይ በጠራው ምክክር ጉዳዩ ላይ በቀጥታ ይመለከታቸዋል የተባሉ የአሜሪካ ባለስልጣናትን ምስክርነት እንደሚያዳምጥና ሰፋ ያለ ምክክር እንደሚያደርግ አስታውቋል።

በምክር ቤቱ ንዑስ ኮሚቴ ምክክር ላይ ምስክርነታቸውን በቀጥታ በሚተላለፈው ምክክር ላይ ያሰማሉ ተብለው ስማቸው የተገለጸው የአሜሪካ ባለስልጣናት፣ በአፍሪካ ቀንድ የአሜሪካ ልዩ ልዑክ ማይክ ሐመር እና በአሜሪካ ዓለማቀፍ ተራድዖ ድርጅት (ዩኤስአይዲ) የአፍሪካ ቢሮ ረዳት ሃላፊ ቴለር ቤከልማን ናቸው።

ከኹለቱ ባለስልጣናት በተጨማሪ፣ ሌሎች ምስክሮች ሊጋበዙ እንደሚችሉም ምክር ቤት ባወጣው አጭር መግለጫ ጠቅሷል።