Related Video and Audio

VIDEO 1 MINUTE 44 SECONDSVIDEO 1 MINUTE 44 SECONDS1:44

Play video በሐማስ ጥቃት የሞቱ ወታደሮችን አስከሬን ለማግኘት እስራኤል እንዴት የንስር ወፍን ተጠቀመች? from BBCበሐማስ ጥቃት የሞቱ ወታደሮችን አስከሬን ለማግኘት እስራኤል እንዴት የንስር ወፍን ተጠቀመች?

Play video በሐማስ ጥቃት የሞቱ ወታደሮችን አስከሬን ለማግኘት እስራኤል እንዴት የንስር ወፍን ተጠቀመች? from BBC

VIDEO 1 MINUTE 18 SECONDSVIDEO 1 MINUTE 18 SECONDS1:18

Play video ሕይወት በጋዛ፡ “ጦርነቱ መቶ ዓመታትን ወደኋላ መልሶናል” from BBCሕይወት በጋዛ፡ “ጦርነቱ መቶ ዓመታትን ወደኋላ መልሶናል”

Play video ሕይወት በጋዛ፡ “ጦርነቱ መቶ ዓመታትን ወደኋላ መልሶናል” from BBC

VIDEO 2 MINUTES 31 SECONDSVIDEO 2 MINUTES 31 SECONDS2:31

Play video ‘ቢያንስ ሆስፒታሉ ጥቃት አይደርስበትም ብለን አስበን ነበር’፡ ከሆስፒታል የሸሹ የጋዛ ነዋሪዎች from BBC‘ቢያንስ ሆስፒታሉ ጥቃት አይደርስበትም ብለን አስበን ነበር’፡ ከሆስፒታል የሸሹ የጋዛ ነዋሪዎች

Play video ‘ቢያንስ ሆስፒታሉ ጥቃት አይደርስበትም ብለን አስበን ነበር’፡ ከሆስፒታል የሸሹ የጋዛ ነዋሪዎች from BBC

VIDEO 2 MINUTESVIDEO 2 MINUTES2:00

Play video ጋዛን የጎበኘው ቢቢሲ የዓለም አቀፍ ኤዲተር ጄረሚ ቦውን እይታ from BBCጋዛን የጎበኘው ቢቢሲ የዓለም አቀፍ ኤዲተር ጄረሚ ቦውን እይታ

Play video ጋዛን የጎበኘው ቢቢሲ የዓለም አቀፍ ኤዲተር ጄረሚ ቦውን እይታ from BBC

VIDEO 1 MINUTE 30 SECONDSVIDEO 1 MINUTE 30 SECONDS1:30

Play video አሜሪካ ከ60 በላይ አውሮፕላን ተሸካሚ ሁለተኛ መርከቧን ወደ እስራኤል አስጠጋች from BBCአሜሪካ ከ60 በላይ አውሮፕላን ተሸካሚ ሁለተኛ መርከቧን ወደ እስራኤል አስጠጋች

Play video አሜሪካ ከ60 በላይ አውሮፕላን ተሸካሚ ሁለተኛ መርከቧን ወደ እስራኤል አስጠጋች from BBC

VIDEO 1 MINUTE 48 SECONDSVIDEO 1 MINUTE 48 SECONDS1:48

Play video ሐማስ ጋዛ ውስጥ የገነባቸው ወደ እስራኤል የሚያሻግሩት ዋሻዎች from BBCሐማስ ጋዛ ውስጥ የገነባቸው ወደ እስራኤል የሚያሻግሩት ዋሻዎች

Play video ሐማስ ጋዛ ውስጥ የገነባቸው ወደ እስራኤል የሚያሻግሩት ዋሻዎች from BBC

VIDEO 3 MINUTES 27 SECONDSVIDEO 3 MINUTES 27 SECONDS3:27

Play video ሕይወት በጋዛ፡ ከቤታቸው ወጥተው መጠለያ ፍለጋ መንከራተት from BBCሕይወት በጋዛ፡ ከቤታቸው ወጥተው መጠለያ ፍለጋ መንከራተት

Play video ሕይወት በጋዛ፡ ከቤታቸው ወጥተው መጠለያ ፍለጋ መንከራተት from BBC

ጭምቅ ሃሳብ

  1. በሐማስ ታግተው የነበሩ 12 ሰዎች ሲለቀቁ 30 ፍልስጤማውያን ከእስር ነጻ ወጡ
  2. ከእስራኤል እስር ነጻ የወጣት ታዳጊ “ድብደባ ተፈጽሞብኛል” አለ
  3. እስራኤል የተኩስ አቁም ስምምነት ተጥሶ ጥቃት እንደተፈጸመባት አስታወቀች
  4. የሞሳድ እና የሲአይኤ ኃላፊዎች ኳታር ይገኛሉ
  5. በጋዛ ከቦምብ ይልቅ ሕክምና ሳያገኙ የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር ሊበልጥ ይችላል ተባለ
  6. ሐማስ ሁሉም ታጋቾች በቁጥጥሩ ስር እንደማይገኙ አስታወቀ
  7. በእስራኤል ጥቃት የተገደሉት ከ14ሺህ በላይ መሆኑ ተገለጸ
  8. ኳታር ደመኞቹን አስራኤልን እና ሐማስን እንዴት ከስምምነት እንዲደርሱ አስቻለች?
  9. ሐማስ 41 ታጋቾችን ሲለቅ እስራኤል 78 ፍልስጤማውያንን ፈታች
  10. የእስራኤል እና ሐማስ የተኩስ አቁም ፋታ ምንን ይዟል?
  11. የእስራኤል መከላከያ ‘ጦርነቱ አላከተመም’ ሲል አስጠነቀቀ
  12. እስራኤል ልታጠፋው ቀን ከሌት የምትፈልገው በጋዛ የሐማስ መሪ ያህያ ሲንዋር ማን ነው?
  13. የጋዛ ትልቁ ሆስፒታል አልሺፋ ዳይሬክተር በእስራኤል መከላከያ በቁጥጥር ስር ዋሉ
  14. የጋዛ ጊዜያዊ የተኩስ አቁም ስምምነት የዘገየው ከታጋቾች ዝርዝር ጋር በተያያዘ ነው ተባለ
  15. እስራኤል በጃባሊያ የስደተኞች መጠለያ በፈጸመችው ጥቃት የአንድ ቤተሰብ 52 አባላት ተገደሉ

ቀጥታ ዘገባ

  1. የታተመዉ 5:095:09ሳምንታትን በፍርሃት፣ በእንግልት እና በረሃብ ያሳለፉት የሐማስ ታጋቾች ታሪክባዶ አግዳሚ ወንበሮች እንደ አልጋ ያገለግላሉ። “የታፈኑ” አየር የሌላቸው ክፍሎች ውስጥ ይታጎራሉ። ከትንሽ አንዳንዴም ምንም ምግብ አይቀርብላቸውም። በሐማስ የታገተው ታዳጊ የመስከረም 26ቱን ጥቃት ያደረሰውን ጉዳት የሚያሳይ ቪዲዮ ቪዲዮን እንዲመለከት ተደርጓል።ተጨማሪ ያንብቡArticle share tools
  2. የታተመዉ 3:133:13የጊዜያዊ ተኩስ አቁም ስምምነቱ የሚራዘምበት ዕድል ሰፊ ነውለሁለት ቀናት የተራዘመው የተኩስ አቁም ፋታ ማክሰኞ ጀምሯል።በሁለቱ ወገኖች ስምምነት ሌላ የ48 ሰዓታት የተኩስ አቁም ፋታ የመራዘም ጥሩ ዕድል እንዳለ እየተነገረ ነው።አነሰም በዛም በዕቅዱ መሠረት እየተጓዘ የሚገኘውን ስምምነት ሁለቱም ወገኖች የሚፈልጉት እንደሆነ ግልጽ ነው።የሚካሄዱት ድርድሮች የደረሱበትን ሁኔታ ማወቅ ባይቻልም ድርድሩ እየተካሄደ ይገኛል። ስምምነቱ እንዲቀጥል የሚደረገው ጥረት ጠንካራ ሆኗል።ይህ ሂደት ሲጠናቀቅ የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ወታደሮቻቸው በጋዛ ውስጥ “ሙሉ ኃይል” እንዲጠቀሙ ማቀዳቸውን ስለመናገራቸው መዘንጋት የለብንም።በእስራኤል ጋዛ ድንበር የሚገኝ ታንክ ላይ የሚራመድ የእስራኤል ወታደርReutersCopyright: ReutersArticle share tools
  3. የታተመዉ 23:57 28 ህዳር 202323:57 28 ህዳር 2023ከእስራኤል እስር ነጻ የወጣት ታዳጊ “ድብደባ ተፈጽሞብኛል” አለከእስራኤል እስር ቤቶች ነጻ ከወጣቱ መካከል አንዱ የሆነው የ14 ዓመት ታዳጊ፤ በእስር ላይ ሳለ ድብደባ ይፈጸምበት እንደነበረ ተናገረ።አሕመድ ናዋፍ ሳላኢማ የተባለው ታዳጊ ለአል ጃዚራ ሲናገር “በመጀመሪያው ቀን ጦርነት ብዙ ድብደባዎች ነበሩ፤ ሴት ታሳሪዎች ሲደበደቡ ነበር” ብሏል።ታዳጊው ከእስር ከተለቀቀ በኋላ በቤቱ እንዲቀመጠ እና ነጻ መውጣቱን በማስመልከት ደስታውን በአደባባይ እንዳይገልጽ ማስጠንቀቂያ ጭምር እንደተሰጠው ተናግሯል።“ደስታ መግለጽ እንደማይቻል ተነግሮኛል፤ ከቤት መውጣት አልችልም። ይህን ሕግ ከጣስኩ ተመልሼ እታሰራለሁ” ብሏል።ቢቢሲ የዚህን ሪፖርት ትክክለኛነት ከገለልተኛ ወገን ማጣራት አልቻለም። እስራኤል የታሳሪዎችን መብት እጠብቃለሁ ትላለች።Article share tools
  4. የታተመዉ 23:44 28 ህዳር 202323:44 28 ህዳር 2023ሐማስ ከእስራኤል አፍንጫ ስር ወታደራዊ ልምምድ በማድረግ እንዴት ኃይሉን መገንባት ቻለ?አምስት ፍልስጤማውያን ቡድኖች ሐማስ መስከረም 26 በእስራኤል ላይ ጥቃት ሲፈጽም ተሳታፊ ነበሩ። ለዚህም ላለፉት ሦስት ዓመታት ከእስራኤል አፍንጫ ስር በጋራ ወታደራዊ ልምምድ ሲያደርጉ መቆየታቸውን የሚያመለክቱ መረጃዎች እየወጡ ነው።ተጨማሪ ያንብቡArticle share tools
  5. የታተመዉ 23:44 28 ህዳር 202323:44 28 ህዳር 2023በእስራኤል ጥቃት የተገደሉት ከ14ሺህ በላይ መሆኑ ተገለጸጋዛGetty ImagesCopyright: Getty Imagesበሐማስ የሚተዳደረው ጤና ሚንስቴር በእስራኤል የአየር፣ የምድር እና የባሕር ጥቃቶች የተገደሉት ሰዎች ቁጥር ከ14ሺህ 500 በላይ መሆኑን አስታወቁ።የጋዛ ባለስልጣናት መሞታቸው ከተረጋገጡ ሰዎች በተጨማሪ እስካሁን ድረስ 1ሺህ 500 የሚሆኑ ሰዎች አድራሻ መጥፋቱን አስታውቀዋል።መስከረም 26/2016 ዓ.ም. ማለዳ ላይ ሐማስ ወደ እስራኤል ድንበር ተሻግሮ ድንገተኛ ጥቃት ከከፈተ በኋላ እስራኤል ጠንካራ የአጸፋ እርምጃ መውሰድ መጀመሯ ይታወሳል።ሐማስ እስራኤላ ላይ ባደረሰው ጥቃት ከ1ሺህ 200 ሰዎች በላይ ገድሎ ወደ 240 የሚጠጉ ሰዎችን አግቶ ወስዶ ነበር።Article share tools
  6. የታተመዉ 23:36 28 ህዳር 202323:36 28 ህዳር 2023በሐማስ ታግተው የነበሩ 12 ሰዎች ሲለቀቁ 30 ፍልስጤማውያን ከእስር ነጻ ወጡከእገታ የተለቀቁReutersCopyright: Reutersእስራኤል በመስከረም 26ቱ ጥቃት ታግተው ከነበሩት ሰዎች መካከል 12 ሰዎች ነጻ መውጣታቸውን አስታወቀች።10 እስራኤላውያን እና 2 የታይላንድ ዜጎች ከሐማስ እገታ ነጻ ወጥተው እስራኤል ድንበር መግባታቸውን የአገሪቱ ጦር አስታውቋል።እስካሁን በጋዛ ታግተው የነበሩ እና ነጻ የወጡ ሰዎች ቁጥር 81 የደረሰ ሲሆን ከእነዚህ መካከል 61 እስራኤላውያን ናቸው።እስራኤል በበኩሏ 30 ፍልስጤማውያንን ከእስር የለቀቀች ሲሆን ይህም አጠቃላይ ቁጥሩን ወደ 180 ከፍ አድርጎታል።እስካሁን ድረስ ከእስራኤል እስር ቤቶች ነጻ የወጣቱ አብዛኛዎቹ ሴቶች እና ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ወንዶች ናቸው።Article share tools
  7. የታተመዉ 9:47 28 ህዳር 20239:47 28 ህዳር 2023እስራኤል የተኩስ አቁም ስምምነት ተጥሶ ጥቃት እንደተፈጸመባት አስታወቀችጋዛGetty ImagesCopyright: Getty Imagesየእስራኤል መከላከያ ሠራዊት የተኩስ አቁም ስምምነቱ ተጥሶ አባላቱ አቅራቢያ ሦስት ፍንዳታዎች ማጋጠማቸውን አስታወቀ።ጦሩ ዛሬ ማክሰኞ ረፋድ ላይ በሰሜን ጋዛ ባጋጠመው ፍንዳታ በርካታ የሠራዊቱ አባላት ቀላል ጉዳት እንደደረሰባቸው አስታውቋል።ሐማስ በበኩሉ ፍንዳታው ያጋጠው የእስራኤል ጦር የተኩስ አቁም ስምምነቱን በመጣሱ ነው ብሏል።የሐማስ የጦር ክንፍ አል-ቃስም ብርጌድ ቃል አቀባይ፣ ሐማስ ለስምምነቱ ተገዢ መሆኑን ጠቅሰው አደራዳሪዎች ግን እስራኤል በምድር እና በአየር ተኩስ እንድታቆም ጫና ማሳደር አለባቸው ብለዋል።ዛሬ ረፋድ ላይ በሰሜን ጋዛ ሰማይ ላይ ትልቅ ጭስ ታይቶ የነበረ ሲሆን፣ ይህ ጭስም በምን ምክንያት እንደተፈጠረ እስካሁን ድረስ ግልጽ አይለም።ቀደም ስል ሲወጡ የነበሩ ሪፖርቶች የተኩስ አቁም ስምምነቱ መራዘሙን ያላወቁ ፍልስጤማውያን ቡድኖች በእስራኤል ወታደሮች ላይ ተኩስ ከፍተዋል ብለው ነበር።Article share tools
  8. የታተመዉ 9:41 28 ህዳር 20239:41 28 ህዳር 2023የሞሳድ እና የሲአይኤ ኃላፊዎች ኳታር ይገኛሉየእስራኤል እና የአሜሪካ የስለላ ተቋማት ኃላፊዎች በቀጣይ ሊደረግ ስለሚችል የተኩስ አቁም ስምምነት ለመወያየት ኳታር ይእንደሚገኙ ተነገረ።ሮይተርስ እና የፈረንሳይ የዜና ወኪል፣ አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ እንደዘገቡት የእስራኤሉ ሞሳድ እና የአሜሪካ ሲአይኤ የስለላ ተቋማት ኃላፊዎች ከኳታር ጠቅላይ ሚኒስትር ጋር ይገናኛሉ።በኳታር አደራዳሪነት ሐማስ እና እስራኤል ለአራት ቀናት ተኩስ ለማቆም የደረሱት ስምምነት ሰኞ ዕለት ለሁለት ተጨማሪ ቀናት ተራዝሟል።በዚህ አዎንታዊ ለውጥ ላይ ለተጨማሪ ቀናት ለጦርነቱ ፋታ ለመስጠት ውይይት ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል።በዚህ ውይይት ላይ የግብፅ ባለሥልጣናትም ተሳታፊ ስለመሆናቸው ተመላክቷል።Article share tools
  9. የታተመዉ 7:49 28 ህዳር 20237:49 28 ህዳር 2023በጋዛ ከቦምብ ይልቅ ሕክምና ሳያገኙ የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር ሊበልጥ ይችላል ተባለበጋዛ ያሉ ሕጻናትReutersCopyright: Reutersበጋዛ ያሉ ሕጻናትImage caption: በጋዛ ያሉ ሕጻናትየዓለም ጤና ድርጅት በጋዛ በጥቃቶች ከሚገደሉ ሰዎች በላይ ሕክምና ሳያገኙ ሕይወታቸውን ሊያጡ የሚችሉ ሰዎች ቁጥር ሊጨምር ይችላል አለ።ድርጅቱ ይህን ማስጠንቀቂያ የሰጠው በጋዛ በሚገኙ መጠለያ ጣቢያዎች በልጆች እና ጨቅላዎች ላይ የተቅማጥ በሽታ እና የመተንፈኛ ኢንፌክሽን መበራከቱን ተከትሎ ነው።በእነዚህ በሽታዎች እየተጠቁ ላሉት ምንም አይነት የሕክምና እርዳታ እየተሰጠ አለመሆኑን ድርጅቱ ገልጾ የካንሰር፣ የልብ ወይም የስኳር ህመምተኞችም ምንም አይነት የጤና ድጋፍ እያገኙ አለመሆኑንን ገልጿል።የተመድ የሕጻናት አድን ድርጅት (ዩኒሴፍ) በበኩሉ በጦርነቱ ምክንያት በከፍተኛ ደረጃ የቆሰሉ ሕጻናት በመኪና ማቆሚያ ቦታዎች እና ሜዳዎች ላይ ወድቀው ይገኛሉ ብሏል።ሰብዓዊ እርዳታ አቅራቢ ድርጅቶች ጦርነቱን ዳግም መጀመር ጨርሶ መታሰብ የለበትም የሚሉ ሲሆን፣ ዘላቂ የሆነ የተኩስ አቁም ስምምነት በሁለቱ ተዋጊዎች መካከል እንዲደረግም ጠይቀዋል።Article share tools
  10. የታተመዉ 7:38 28 ህዳር 20237:38 28 ህዳር 2023ለጦርነት ፋታ ለመስጠት ስምምነት ቢኖርም በጋዛ ሰማይ ላይ ጭስ ታየጋዛAFP TVCopyright: AFP TVሐማስ እና እስራኤል ለጦርነቱ ፋታ ለመስጠት የደረሱትን ስምምነት ቢያራዝሙም በጋዛ ሰማይ ላይ ትልቅ ጭስ ታይቷል።አንዳንድ ሪፖርቶች እንደሚጠቁሙት ከሆነ የተኩስ አቁም ስምምነቱ መራዘሙን ያላወቁ ፍልስጤማውያን ቡድኖች በእስራኤል ወታደሮች ላይ ተኩስ ሳይከፍቱ አልቀሩም።በኳታር አደራዳሪነት ሐማስ እና እስራኤል ለአራት ቀናት ተኩስ ለማቆም የደረሱት ስምምነት ሰኞ ዕለት ለሁለት ተጫማሪ ቀናት መራዘሙ ይታወሳል።ለተጨማሪ 48 ሰዓታት ተኩስ ለማቆም በተደረሰው ስምምነት ወቅት ሦስት ፍልስጤማውያን በአንድ እስራኤላዊ ለመለወጥ ሐማስ እና እስራኤል ተስማምተዋል።Article share tools
  11. የታተመዉ 7:29 28 ህዳር 20237:29 28 ህዳር 2023ሐማስ ሁሉም ታጋቾች በቁጥጥሩ ስር እንደማይገኙ አስታወቀበቅርቡ ከእገታ ነጻ የወጣ ታዳጊReutersCopyright: Reutersበቅርቡ ከእገታ ነጻ የወጣ ታዳጊImage caption: በቅርቡ ከእገታ ነጻ የወጣ ታዳጊሐማስ በመስከረም 26ቱ ጥቃት የታገቱት ሰዎች በሙሉ በቁጥጥሩ ስር እንደማይገኙ አስታወቀ።በኳታር የሚገኙ አንድ ከፍተኛ የሐማስ መሪ ቁጥራቸው በውል የማይታወቁ ታጋቾች በሌሎች ሚሊሻ ቡድኖች እጅ እንደሚገኙ ገልጸዋል።ለምሳሌ በመስከረም 26ቱ ጥቃት ተሳታፊ ከነበሩት ቡድኖች መካከል አንዱ የሆነው የፍልስጤም እስላማዊ ጂሃድ 20 ታጋቾችን ይዞ ይገኛል። ከእነዚህ መካከል አስሩ ዛሬ የሚለቀቁ ሲሆን፣ ቀሪዎቹ ደግሞ ነገ ረቡዕ ይለቀቃሉ ተብሎ ይጠበቃል።በመስከረም 26ቱ ጥቃት ተሳታፊ ከሆኑ ቡድኖች መካከል አንዱ የፍልስጤም እላማዊ ጂሃድ ነውBBCCopyright: BBCበመስከረም 26ቱ ጥቃት ተሳታፊ ከሆኑ ቡድኖች መካከል አንዱ የፍልስጤም እላማዊ ጂሃድ ነውImage caption: በመስከረም 26ቱ ጥቃት ተሳታፊ ከሆኑ ቡድኖች መካከል አንዱ የፍልስጤም እላማዊ ጂሃድ ነውሐማስ ታጋቾችን እየለቀቀ ለጦርነቱ ፋታ የሚሰጥበት ቀን እንዲራዘም ፍላጎት ቢኖረውም፣ እስራኤል ግን የተኩስ አቁም ስምምነቱ ዕለታዊ ግምገማ እየተካሄደበት በየዕለቱ እንዲራዘም ፍላጎት አላት።ሐማስ መረጃ ለመሰብሰብ እና የታጋቾች መገኛ ቦታን ለማወቅ ረዘም ያለ ጊዜ ያስፈልገኛል እያለ ነው።በጋዛ የቴሌኮም መሠረተ ልማቶች መውደማቸው እና የነዳጅ አቅርቦት ውስንነት ይህን የፍለጋ ተግባር ከባድ እንደሚያደርገው ይገመታል።Article share tools
  12. የታተመዉ 4:56 28 ህዳር 20234:56 28 ህዳር 2023ከ6 ሺህ በላይ ፍልስጤማውያን እስረኞች በእስራኤል ሲገኙ ከ2ሺህ በላይ የሚሆኑት ክስ አልተመሰረተባቸውምፍልስጤማውያን እስረኞች ሲፈቱ የነበረው ደስታReutersCopyright: Reutersየተኩስ አቁም ፋታውን ተከትሎ በእስራኤል እስር ቤት የሚገኙ 150 የሚሆኑ ታዳጊዎች እና ሴቶች ፍልስጤማውያን እስረኞች ተለቀዋል።በአራተኛው ዙር 30 ህጻናትን ጨምሮ 33 ፍልስጤማውያን እስረኞች ተፈትተዋል። በእስራኤል እስር ቤቶች 6 ሺህ 704 ፍልስጤማውያን ታስረው እንደሚገኙ የመብት ተቋማት ያስታወቁ ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ 2 ሺህ ሰባ የሚሆኑት ፍርድ ቤት አልቀረቡም ወይም ክስ አልተመሰረተባቸውም።አስተዳደራዊ እስራት ተብሎ በሚጠራውም ሁኔታ በእስራኤል እስር ቤቶች እንደሚገኙ ሃሞኬድ የተባለው የእስራኤል የመብት ድርጅት አስታውቋል።የሐማስ እና የእስራኤል የተኩስ አቁም ፋታ ተከትሎም በአራት ዙሮች 150 ፍልስጤማውያን ተፈትተዋል።በትናንትናውም ዕለት 33 ህጻናት እና ሴቶች ፍልስጤማውያን እስረኞች ሲፈቱም በርካቶች ደስታቸውን ሲገልጹም ታይተዋል።እስራኤል በወረራ በያዘቻት ዌስት ባንክ አቅራቢያ በሚገኘው ራማላህ የፍተሻ ኬላም ሲደርሱም ፍልስጤማውያን ተቀብለዋቸዋል።እስረኞቹ ድንጋይ መወርወርን ጨምሮ በግድያ ሙከራ እንደተጠረጠሩ ቢገለጽም በርካቶቹም ክስም ሳይመስረትባቸው በእስር ቤቶች ቆይተዋል።በዌስት ባንክ የሚኖሩ ፍልስጤማውያን ቤተሰቦች ቢያንስ አንድ የቤተሰብ አባላቸው በእስራኤል እስር ቤቶች ውስጥ ታስረው እንደሚገኙ ይታሰባል።ፍልስጤማውያኑ በእስራኤል ውስጥ በመታሰራቸውም ዘመዶቻቸው ወደ እስራኤል ሄደው መጎብኘት አይችሉም።መስከረም መጨረሻ የደረሰውንም ጥቃት ተከትሎ በእስራኤል እስር ቤቶች ያለ ፍርድ የታሰሩ ፍልስጤማውያን ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩንም የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች አስታውቀዋል።ፍልስጤማውያን እስረኞች ሲፈቱ የነበረው ደስታReutersCopyright: Reutersፍልስጤማውያን እስረኞች ሲፈቱ የነበረው ደስታReutersCopyright: Reutersፍልስጤማውያን እስረኞች ሲፈቱ የነበረው ደስታReutersCopyright: ReutersArticle share tools
  13. የታተመዉ 2:18 28 ህዳር 20232:18 28 ህዳር 2023የታይላንድ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር የተለቀቁ ታይላንዳውያን ታጋቾችን ለመውሰድ ወደ እስራኤል አቀኑየታይላንድ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ፓርንፕሬይ ባሂድድሃ ኑካራEPACopyright: EPAየታይላንድ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ፓርንፕሬይ ባሂድድሃ ኑካራ የተኩስ አቁም ፋታውን ተከትሎ የተለቀቁ 17 ታይላንዳውያን ታጋቾችን ወደ አገራቸው ለመውሰድ ወደ እስራኤል አቀኑ።ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ፓርንፐሬይ በጥቂት ሰዓታት ውስጥ እስራኤል ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል።ከተለቀቁትም መካከል ሐማስ መስከረም መጨረሻ ባደረሰው ጥቃት የተጎዱ ሶስት የታይላንድ ዜጎችም በሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸው ሲሆን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩም ይጎበኟቸዋል ተብሏል።ባለስልጣኑ በእስራኤል ውስጥ ተቀጥረው ከሚገኙ የታይላንድ ሰራተኞችም ጋር እንደሚገናኙ የታይላንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።የተለቀቁት ታጋቾችም ሐሙስ እለት ወደ ባንኮክ እንደሚመለሱም ይጠበቃል። ተጨማሪ 15 የታይላንድ ዜጎች በሐማስ ታግተው እንደሚገኙም የታይላንድ ባለስልጣናት አስታውቀዋል።Article share tools
  14. የታተመዉ 23:59 27 ህዳር 202323:59 27 ህዳር 2023ከተለቀቁት ታጋቾች መካከል የሶስት ዓመት መንትያ እህትማማቾች እና እናታቸው ተካተውበታልየሶስት ዓመት መንትያ እህትማማቾች እና እናታቸውHandoutCopyright: Handoutበአራተኛ ዙር ከተለቀቁት ታጋቾች መካከል የሶስት ዓመት ዕድሜ ያላቸው መንትያ እህትማማቾች እና እናታቸው እንደተካተቱበት ተገለጸ።ሻሮን አሎን ኩኒያ እና መንትያ ልጆቿ ኤማ እና ዩሊ ቢለቀቁም ባለቤቷ እና ወንድሙ አሁንም ታግተው እንዳሉ ይታመናል።ሐማስ መስከረም መጨረሻ ላይ ጥቃት በከፈተበት ወቅት ቤሰተቡ በአንድ ቤት ውስጥ ተጠልለው ነበር ተብሏል። ሐማስ ቤቱን በእሳት ሲያቀጥለው እና ቤተሰቡ ሊያመልጥ ሲሞክርም ተይዘው መታገታቸውም ተነሯል።የሻሮን እህት ዳንኤል አሎኒ እና ልጇም ታግተው የነበሩ ሲሆን ሁለቱም አርብ እለት ከእገታ ተለቀዋል። የታገቾች እና የጠፉ ቤተሰቦች ኮሚቴም መንትያዎቹ እህትማማቾን አስመልክቶ መግለጫ አውጥቷል።ኤማ “በጣም አስደናቂ እና በፍቅር የተሞላች ህጻን ናት። ከአሻንጉሊት ይልቅ የጭነት መኪናዎችን የምትመርጥ እውነተኛ የኪቡዝ ተወላጅ ናት። እህቷ ዩሊ ዓይናፋር ስትሆም ከመታገቷ በነበሩት ሳምንታት የበለጠ ተጫዋች እየሆነች ነበር” የሚል መግለጫም አውጥቷል።ሻሮን እና ባለቤቷ ዴቪድ የተገናኙት እሱ በሚተውንበት ፊልም ላይ የህዝብ ግንኙነት ትሰራ በነበረበት ወቅት መሆኑም ተገልጿል።Article share tools
  15. የታተመዉ 23:57 27 ህዳር 202323:57 27 ህዳር 2023የአሜሪካ ባሕር ኃይል የእስራኤላዊያንን መርከብ አግተው የነበሩ ታጣቂዎችን በቁጥጥር ሥር አዋለየአሜሪካ ባሕር ኃይል እሑድ ዕለት የመን ድንበር አቅራቢያ ከእሥራኤል ጋር ግንኙነት ያለውን የጭነት መርከብ አግተው የነበሩ ታጣቂዎችን በቁጥጥር ሥር እንዳዋሉ የአሜሪካ ባለሥልጣናት ገለጹ።ተጨማሪ ያንብቡArticle share tools
  16. የታተመዉ 23:31 27 ህዳር 202323:31 27 ህዳር 2023ሐማስ 11 ተጨማሪ ታጋቾችን ሲለቅ እስራኤል 30 ህጻናትን ጨምሮ 33 እስረኞችን ፈታችከእስር የተፈታ ፍልስጤማዊ ህጻንGetty ImagesCopyright: Getty Imagesበተኩስ አቁም ፋታው አራተኛ ቀን ሐማስ 11 ተጨማሪ እስራኤላውያን ታጋቾችን ሲለቅ እስራኤል 30 ህጻናትን ጨምሮ 33 ፍልስጤማውያን እስረኞችን ፈታለች።ሐማስ ከለቀቃቸው ታጋቾች መካከል የሶስት ዓመት መንትያ ህጻናት እንደሚገኙበትም ተገልጿል።በኳታር አሸማጋይነት የተደረሰውን የተኩስ አቁም ፋታን ተከትሎ እስካሁን ድረስ 69 ታጋቾችን በሶስት ዙሮች ለቋል። እስራኤል በበኩሏ 150 ህጻናት እና ሴቶች ፍልስጤማውያን እስረኞችን ፈታለች።ለአራት ቀናት ይቆያል ተብሎ የነበረው የተኩስ አቁም ፋታ ለተጨማሪ ሁለት ቀናት የተራዘመ ሲሆን በዚህም ጊዜ ተጨማሪ ህጻናት እና ሴቶች በአብዛኛው የተካተቱበት የታጋቾች እና የእስረኞች ልውውጥ እንደሚደረግ ይጠበቃል።Article share tools
  17. የታተመዉ 11:33 27 ህዳር 202311:33 27 ህዳር 2023እስራኤል እና ሐማስ ጊዜያዊ ተኩስ አቁሙን ማራዘማቸውን ኳታር አስታወቀችተኩስ አቁምን በመጠቀም ፍልስጤማውያን ከሰሜናዊ ጋዛ እየወጡ ነውReutersCopyright: Reutersተኩስ አቁምን በመጠቀም ፍልስጤማውያን ከሰሜናዊ ጋዛ እየወጡ ነውImage caption: ተኩስ አቁምን በመጠቀም ፍልስጤማውያን ከሰሜናዊ ጋዛ እየወጡ ነውበእስራኤል እና በሐማስ መካከል የተደረሰው እና ለአራት ቀናት የቆየው ጊዜያዊ የተኩስ አቁም ለተጨማሪ ሁለት ቀናት እንዲራዘም ከስምምነት መደረሱን ኳታር አስታወቀች።ባለፈው አርብ ጀምሮ እስከ ዛሬ ሰኞ ሌሊት ድረስ ታጋቾችን እና እስረኞችን ለመልቀቅ እንዲሁም ሰብዓዊ እርዳታዎች ወደ ጋዛ እንዲደርሱ ለማስቻል የተደረሰው ጦርነት የመግታት ስምምነት ሰኞ ሌሊት ያበቃል ተብሎ ነበር።ባለፉት አራት ቀናት ሐማስ ከእስራኤል ታጋቾች የተወሰኑትን የለቀቀ ሲሆን፣ እስራኤል ደግሞ ፍልስጤማውያን እስረኞችን ለቃለች።በተጨማሪም በችግር ላይ ለሚገኙት የጋዛ ነዋሪዎች ምግብ፣ ውሃ፣ መድኃኒት እና ነዳጅ እንዲገባ ተደርጓል።በእስራኤል እና በሐማስ መካከል ግጭቱን በጊዜያዊነት እንዲያቆሙ ለማስቻል ኳታር ቁልፍ ሚና የተጫወተች ሲሆን፣ ግብፅ፣ አሜሪካ እና ሌሎች ወገኖች ተሳታፊ ናቸው።Article share tools
  18. የታተመዉ 9:40 27 ህዳር 20239:40 27 ህዳር 2023የጋዛ ጊዜያዊ ተኩስ አቁም ሊያበቃ ቢቃረብም ለማራዘም ጥረት እየተደረገ ነውየተኩስ አቁሙን የጋዛ ነዋሪዎች ምግብ እና መድኃኒት ለማግኘት እየተጠቀሙበት ነውReutersCopyright: Reutersየተኩስ አቁሙን የጋዛ ነዋሪዎች ምግብ እና መድኃኒት ለማግኘት እየተጠቀሙበት ነውImage caption: የተኩስ አቁሙን የጋዛ ነዋሪዎች ምግብ እና መድኃኒት ለማግኘት እየተጠቀሙበት ነውዛሬ ሰኞ በእስራኤል እና በሐማስ መካከል ለአራት ቀናት የተደረሰው ጦርነት ጋብ የማድረግ ስምምነት የሚያበቃበት ዕለት ቢሆንም ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ተኩስ አቁሙ እንዲራዘም ግፊት እያደረገ ነው።ባለፉት ሦስት ቀናት ሐማስ ከእስራኤል አግቶ ከወሰዳቸው ሰዎች መካከል የለቀቀ ሲሆን እስራኤል ደግሞ በእስር ቤቶቿ ውስጥ የነበሩ በርካታ ፍልስጤማውያንን ፈትታለች።ከዚህም ባሻገር ለሳምንታት በእስራኤል ጥቃት ምክንያት በመሠረታዊ አቅርቦቶች እጦት ሲሰቃዩ ለቆዩት የጋዛ ነዋሪዎች ሰብዓዊ እርዳታ እና ነዳጅ መግባት ችሏል።ይህ ለቀናት የቆየው ጊዜያዊ ተኩስ አቁም ዛሬ ሌሊት ከማብቃቱ በፊት እንዲራዘም ጥረት እየተደረገ ነው። የኔቶው ዋና ፀሐፊ የንስ ስቶልተንበርግ እና የአውሮፓ ኅብረት የውጭ ፖሊሲ ኃላፊ ጆሴፍ ቦሬል ጥሪ ካቀረቡት መካከል ናቸው።የመጀመሪያው ስምምነት እንዲደረስ ወሳኝ ሚና የነበራት ኳታር፣ ግብፅ፣ አሜሪካ፣ የአውሮፓ ኅብረት እና ስፔን፤ እስራኤል እና ሐማስ ጋዛ ውስጥ የደረሱት ጊዜያዊ ተኩስ አቁሙ እንዲራዘም ጥረት እያደረጉ መሆናቸውን የፍልስጤም ብሔራዊ ባለሥልጣን ሪያድ አል-ማሊኪ ተናግረዋል።የግብፅ የደኅንነት ምንጮች ለሮይተርስ ዜና ወኪል እንደተናገሩት ጦርነት የቆመበት ፋታ በቀናት ለማራዘም የሚደረገው ጥረት ወደ ስምምነት እየተጠጋ መሆኑን አመልክተዋል።ሐማስ የተኩስ አቁሙ እንዲራዘም እና ተጨማሪ ታጋቾችን ለመልቀቅ ፍላጎት እንዳለው ያሳወቀ ሲሆን፣ የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታኒያሁም ስምምነቱ እንዲራዘም የማድረግ ዕድል እንዳለ ገልጸው፣ ነገር ግን ከስምምነቱ ማብቃት በኋላ በጋዛ ውስጥ ሠራዊታቸው የሚያካሂደው ዘመቻ በሙሉ ኃይል እንደሚጀመር ተናግረዋል።በተኩስ አቁሙ ሚስቱ እና ሁለት ልጆቹ ከእገታ የተለቀቁለት እስራኤላዊው ዮኒ አሸርIsrael Defense ForcesCopyright: Israel Defense Forcesበተኩስ አቁሙ ሚስቱ እና ሁለት ልጆቹ ከእገታ የተለቀቁለት እስራኤላዊው ዮኒ አሸርImage caption: በተኩስ አቁሙ ሚስቱ እና ሁለት ልጆቹ ከእገታ የተለቀቁለት እስራኤላዊው ዮኒ አሸርArticle share tools
  19. የታተመዉ 7:35 27 ህዳር 20237:35 27 ህዳር 2023እስካሁን ስንት ታጋቾች እና እስረኞች ተለቀቁ?ከእስር የተለቀቀ ፍልስጥኤማዊ የሐማስን መለያ ሰንደቅ አላማን ጭንቅላቱ እና አንገቱ ላይ አስሮ ከእናቱ አቅፎ ሰላም ሲልGetty ImagesCopyright: Getty Imagesበእስራኤልና በሐማስ ስምምነት መሠረት ከእስር የተለቀቀ ፍልስጥኤማዊ ከእናቱ ጋር ሲገናኝImage caption: በእስራኤልና በሐማስ ስምምነት መሠረት ከእስር የተለቀቀ ፍልስጥኤማዊ ከእናቱ ጋር ሲገናኝበእስራኤል እና በሐማስ መካከል የተደረሰው የእስረኞች እና የታጋቾች ልውውጥ ስምምነት የውስብስብ እና ያላሰለሰ ዲፕሎማሲያዊ ጥረት ውጤት ነው።በድርድሩ በርካታ አካላት ታሳትፈዋል። በዚህም እስካሁን 58 ታጋቾች ነጻ የወጡ ሲሆን ከአርብ ዕለት ጀምሮ 117 ፍልስጥኤማውያን እስረኞች ተለቀዋል።ዛሬ ሰኞ እኩለ ሌሊት ላይ በሚያበቃው የእስራኤል እና የሐማስ ስምምነት መሠረት 50 እስራኤላውያን ታጋቾች የሚለቀቁ ሲሆን፣ በምላሹ 150 ፍልስጥኤማውያን ከእስር ይፈታሉ።ለመሆኑ ቁጥሮቹ ለምን ተለያዩ? ስለተለቀቁ ሰዎች ቁጥር እስካሁን የምናውቀው ምንድን ነው?
    • በእስራኤል እና በሐማስ ስምምነት መሠረት እስካሁን በጋዛ ታግተው የነበሩ 39 እስራኤላውያን ተለቀዋል።
    • በእስረኞች እና በታጋቾች ልውውጡ በእስራኤል እስር ቤት ታስረው የነበሩ 117 ፍልስጥኤማውያን ከእስር ተፈተዋል።
    • ሌላ ሮኒ ክሪቮይ የተባለ ሩሲያዊ-እስራኤላዊ ታጋችም እሑድ ዕለት በሐማስ ተለቋል። ሆኖም ታጋቹ የተለቀቀው በሦስት ፍልስጤማውያን እስረኞች ለውጥ አይደለም።
    • ከሐማስ ጋር በተደረገ ሌላ ድርድርም በተመሳሳይ ቀን በሐማስ ታግተው የነበሩ አንድ የፍሊፒንስ ዜጋ እና 17 የታይላንድ ዜጎች ተለቀዋል።
    ይህ ስምምነት አርብ ዕለት ተግባራዊ መሆን ከመጀመሩ በፊት ደግሞ ሦስት እስራኤላዊ ታጋቾች የተለቀቁ ሲሆን፣ አራተኛው በእስራኤል ጦር አማካኝነት ነጻ መውጣት ችሎ ነበር።መስከረም ወር መጨረሻ ላይ ሐማስ በእስራኤል ላይ የፈፀመውን ድንበር ዘለል ጥቃት ተከትሎ በአጠቃላይ ወደ 240 የሚጠጉ ሰዎች በጋዛ ታግተዋል ተብሎ ይታመናል።Article share tools
  20. የታተመዉ 6:49 27 ህዳር 20236:49 27 ህዳር 2023የእስራኤል ወታደርን ሕይወት የታደገው ኤርትራዊ ጥገኝነት ጠያቂ ቋሚ የመኖሪያ ፈቃድ ተሰጠውበሐማስ ጥቃት ወቅት ጉዳት የደረሰበትን የአንድ እስራኤላዊ ኮሎኔል ሕይወትን ያተረፈው ኤርትራዊ ለፈጸመው ተግባር በእስራኤል መንግሥት ቋሚ የመኖሪያ ፈቃድ ተሰጠው።ተጨማሪ ያንብቡArticle share tools