November 29, 2023 – Konjit Sitotaw 

“ጦርነት ይቁም! ሠላም ይስፈን በሚል መሪ ቃል!!!

መከላከያ ባስቸኳይ ወደካምፑ ይመለስ

በአዲስ አበባ የሰላማዊ ሰልፍ ጥሪ

ቀን ሕዳር 30/2016

ሰአት 4 ከጠዋቱ፤ መነሻ አራት ኪሎ የድል ሐውልት

======. ======. =======

በዛሬው እለት ህዳር 19 ቀን 2016 ዓ.ም. በሰላማዊ ሰልፉ አስተባባሪዎች በተፈረመ ደብዳቤ፣ ጦርነት እንዲቆም፣ መከላከያ ሠራዊቱ ከዘመተባቸው ክልሎች ወጥቶ ወደ ጦር ካምፑ እንዲመለስና ፖለቲካዊ ውይይቶች እንዲከፈቱ የሚጠይቅ ህዝባዊ የአደባባይ ሠልፍ እንደሚካሄድ ተገልጿል።

አስተባባሪዎቹ ዛሬ ለአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ጽ/ቤት፣ የማሣወቂያ ደብዳቤ አስገብተዋል። ህዝባዊ ሠልፉ መነሻውን አራት ኪሎ የድላችን ኃውልት አድርጎ በተለያዩ ጎዳናዎችንና አደባባዮችን በማለፍ መዳረሻውን መስቀል አደባባይ አድርጎ የዕለቱን መልዕክት በማስተላለፍ ይጠናቀቃል። መላው ሠላም ወዳድ ኢትዮጵያዊያን በሙሉ በሠልፉ በነቂስ እንዲታደሙና አገር የማዳን የዜግነት ግዴታቸውን እንዲወጡ አስተባባሪዎቹ ጥሪ አስተላልፈዋል።

በሚቀጥሉት ጥቂት ቀናትም በፕሬስ ኮንፍረንስ ዝርዝሩን እንደሚገልጹም አስተባባሪዎቹ አሣውቀዋል።