November 29, 2023 – Konjit Sitotaw 

የአቶ ብናልፍ አንዷለም ተቋም አስቂኝ መግለጫ ሰጥቷል።

ሰላም በሌላት ሀገር የተቋቋመው ሰላም ሚኒስቴር በህዝብ የሚደርሱ በደሎችን እና የመከራ ጊዜያትን ዝም ብሎ በማለፍ ለመንግስት አጋዥነቱን የሚያሳየዉ ፣ ሀገር በጦርነት ተወጥራ በምትታመስበት ጊዜ  አንድም ቀን የመንግስትን ህዝብ የመጨፍጨፍ ተግባር  በመግለጫ ያልዎቀሰ ተቋም ዛሬ ደርሶ የሰላም ዘብ ነኝ ሊለን እየሞከረ ነው።

ትናንት በአዲስ አበባ በተዘጋጀዉ የሰላም ምክር ቤት ገባኤ የብልፅግና አሸርጋጅ የሆነዉ ብናልፍ አንዷለም ማንኛዉም ጥያቄ ያለዉ አካል ካለ በሰላማዊ መንገድ ቁጭ ብሎ በመነጋገር መፍትሔ ማምጣት ይቻላል። ያለ ሲሆን ነገር ግን አማራ ትናንት ሰላማዊ በሆነ መንገድ የጠየቀዉን ማንኛዉንም ጥያቄ በመሳሪያ ዝም ለማስባል ብዙ ተሞክሮ አልፏል ።በደል ፣እንግልት፣ ፣መሳደድ እና መከራ የቀሰቀሰዉ የአማራ ህዝብ ከልጁ ፋኖ ጋር በመሆን የገዳዩን መንግስት ጦር ድባቅ እየመታዉ ይገኛል።

የሠላም ሚኒስቴር ከመንግስት የወረደለትን ትዛዝ ከመቀበል ዉጪ የዜጎች ሰላም እጦት እና መሳደድ እንደማያሳስበዉ ከብልፅግና ሽንፈት ማግስት ስለሰላም መስበኩ  የአገዛዙን መንግስት በስልጣን ለማቆየት የተጠቀመዉ ብልሀት ነዉ  ።
ሀገርን እና ህዝብን የሚወክል ተቋም ንፁሀን ህዝብ በድሮን ሲደበደብ ሰብል ሲቃጠል ሴት ስትደፈር የህዝብ ድምፅ ለመሆን ይታገላል እንጅ በህዝብ ሞት ላይ አይሳለቅም የሠላም ሚኒስትር አማራን አይወክልም።
በዚህ መንግስትን ለማዳን  በተጠመዱ የተቋማት ሴራ ማንኛዉም የእምነት አባትም ሆነ የሀገር ሽማግሌ ተሳታፊ ቢሆን በአማራ ሞት እና መሳደድ ብሎም በጅምላ ለሚደረግበት የዘር ፍጅት ተባባሪ ይሆናል።