December 1, 2023 – Konjit Sitotaw
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ እርስቲያንን ጨምሮ ሌሎች የክርስቲያን ማኅበረሰብ አካላት የኢትዮጵያ አብያተክርስቲያናት ሕብረትን ለመመስረት ወሰኑ።

በኢትዮጵያ ስላለው የሰብአዊ ቀውስ እና የግጭት ሁኔታ በተደረገው የውይይት ዓውድ ፣ አብያተ ክርስቲያናት አንድነታቸውን ማጠናከር እንዳለባቸው ተገንዝበው ዛሬ ብሔራዊ የአብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት ለመመስረት ራሳቸውን አደራ ሰጥተዋል” ብለዋል። ሲል የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት በይፋዊ የፌስቡክ ገጹ አስታውቋል።
በጉባኤው የተገኘው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ልዑክ በቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ሊቀ ጳጳስ የተመራ ሲሆን ፤ የወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ዮናስ ይገዙ ዲቢሳ እና የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ ካርዲናል ብርሃነየሱስ ሱራፌል ልዑካን ቡድኖቻቸውን በመምራት ተሳትፈዋል።
የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት ባወጣው መግለጫ ሁነቱን ታሪካዊ የአንድነት ትዕይንት በኢትዮጵያ ሲል ገልጿል።