በደላንታ ወገል ጤና ከተማ ትላንት የድሮን ጥቃት ተፈጽሟል፡፡ የምስራቅ አማራ ፋኖ ዋና መሰረቱ ደላንታ፣ አምባሰል፣ ሀብሩ ወረዳዎች ናቸው፡፡ እነዚህን 3 ወረዳዎች ወታደራዊ መሰረት አድርጎ የምስራቅ አማራ ፋኖ በሰሜን እና ደቡብ ወሎ የተለያዩ ኦፕሬሽኖችን እያደረገ ይገኛል፡፡
ነበልባሎቹ በውጫሌ፣ በኩታበር፣ በደላንታ፣ በወረባቦ፣ በሃብሩ ወረዳ መርሳ እና ወልዲያ የአገዛዙን ጦር እና ሆዳደሩን ሚሊሻ አጭደው ሲከምሩት ሰንብተዋል፡፡

በኩታበር ወረዳ ወርቃሪያ ብቻ 113 በደቡብ ወሎ ከሚገኙ ሁሉም ወረዳዎች የተውጣጣ ሚሊሻ ወደ አፈርነት ቀይረውታል፡፡ በተሁለደሪ ወረዳ 27 የሚሊሻ አባላት ተገድለዋል፡፡ በአምባሰል ወረዳ 148 የሚሊሻ አባላት ወደ ግዳጅ የገቡ ሲሆን ከዚህ ውስጥ ግማሹ ተገድሎ፣ ግማሹ ጠፍቶ አሁን የቀሩት 18 ብቻ ናቸው፡፡
ከሳምንት በፊት በውጫሌ-ሃይቅ በነበረው ውጊያ ከ200 በላይ የአገዛዙ ወታደሮች ተገድለዋል፡፡
በደንካ ሚካኤል ብቻ በአንድ ጉድጓድ 8 የአገዛዙ ሰራዊት መቀበራቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል፡፡
በሰሜን ወሎ ሲሪንቃ፣ በአምባሰል ወረዳ ድብል፣ በተንታ ወረዳ ጫጫ መስቀል፣ በጃማ፣ በአማራ ሳይንት የቀባሪ ያለህ፣ የአገዛዙ ሰራዊት በዘመቻ ተቀብሯል፡፡
በዚህ የተበሳጨው ብልጽግና ንጹሃን ዜጎችን፣ ወጣቶችን በገበያ ስፍራ፣ በቤተ-ክርስትያን፣ በመነሃሪያ፣ በሆቴል እና ሬስቶራንቶች እየገደለ ይገኛል፡፡
በአማራ ክልል በፋኖ እና በመከላከያ ሰራዊቱ መካከል ጦርነቱ ከተጀመረ በኋላ ትላንት በደላንታ ወረዳ ወገል ጤና የተጣለውን ጨምሮ 61 የድሮን ጥቃት ደርሷል፡፡
በዚህም በርካታ አርሶ አደሮች፣ ተማሪዎች፣ የቤተ-ክርስትያን አገልጋዮች ተገድለዋል፡፡ ብልጽግና የፋኖን ጦር ማሸነፍ አልቻለም፡፡ ከሰሞኑ አዲስ ስትራቴጂ ነድፏል፡፡ ከላይ በድሮን ከታች በከባድ መሳሪያ ህዝብን ማሸበር የሚል እቅድ አንዱ ነው፡፡ ሌላው በዋና ዋና የፋኖ አመራሮች ላይ የድሮን ጥቃት ማድረስ ነው፡፡
በሰሜን ጎንደር ዞን ቆላ ድባ የሰለጠኑ የኮማንዶ አባላት አርበኛ መሳፍንት ተስፉን ለመግደል ተሰማርተው አፈር በልተው ቀርተዋል፡፡
ትላንት በደላንታ ወረዳ ወገል ጤና ከተማ በተቃጣ የድሮን ጥቃት ከ20 በላይ ንጹሃን አማራዎች እንደ ቅጠል ረግፈዋል፡፡
ነገር ግን በድሮን ድብደባ የሚመጣ ለውጥ፣ የሚሸነፍ ሰራዊት ፋኖ የለውም፡፡ በድሮን እና በመሳሪያ ብዛት በጦር ሜዳ ላይ ለውጥ እንደማመጣ ከታሪክ ስንመለከት የአሜሪካ እና የታሊባን ጦርነት በአፍጋኒስታ የነበረውን መመልከት እንችላለን፡፡
በ2008 ዓ.ም የመስከረም አንዱ ጥቃት በአሜሪካ በአልቃሂዳ ቡድን ከተፈጸመ በኋላ በወቅቱ በፕሬዝዳንት ጆርጅ ደብሊው ቡሽ የምትመራው አሜሪካ በአፍጋኒስታን የሚንቀሳቀሰውን ኢስላዋሚ ታጣቂ ቡድን መሪ ኦስማን ቢን ላደንን ለመግደል እና ታሊባንን አጠፋለሁ ብላ እጅግ ዘመናዊ የረቀቁ እና አለኝ ያለቻቸውን መሳሪያዎች ይዛ ሰተት ብላ አፍጋኒስታን ውስጥ ገባች፡፡
አለኝ ያለቻቸውን ድቶኖች፣ ዘመናዊ የስለላ መሳሪያዎች፣ ሲአይኤን ጨምሮ ሙሉ የስለላ ተቋማቷን አሰማርታ መጨረሻዋ ወታደሮቿን አስበልታ በአለም መድረክ ተዋርዳ አፍጋኒስታን ለታሊባን አስረክባ መውጧን እናስታውሳለን፡፡
በአንጻሩ የፋኖ ጦር እየተከተለው ያለው “የጉሬላ ውጊያ” “guerrilla fighting” ambushes, sabotage, and hit-and-run attacks የጦርነት ስልት በፈረንጆቹ ከ1804-1814 ስፔን እና ፖርቹጋል የፈረንሳዩን ጦር ያሸነፉበት የፔንሱላ ጦርነት አንዱ ነው፡፡
ሌላው የቨትናም ጦርነት ነው፡፡ በፈረንጆቹ 1955-1975 ቪት ኮንጎ እና የደቡብ ቨትናም ጦር ትልቂ የጦር መሳሪያ የታጠቀውን የአሜሪካን ጦር ያሸነፉበት የጉሬላ ውጊያ ሁለተኛው በታሪክ የሚነገር ነው፡፡
በቅርቡም በኩባ፣ በአፍጋኒስታን፣ ኢራቅ እና ሶሪያ ተሞክሮ ተግባራዊ የሆነ የጦርነት ስትራቴጂ ሲሆን በዘመናዊ የጦር መሳሪያ እና በሰለጠነ ወታደር እጃቸውን ያስገቡ ታላላቂ አገራት ተሸንፈው የወጡበት የጦርነት ስልት ነው፡፡
መሰባሰብ አስወግዱ፣ ተፈጥሮን ጋር ተመሳሰሉ የድሮን ጥቃትን ለመከላከል ሁነኛ መፍትሄ ናቸው፡፡
ድል ለፋኖ!! አሻራ ሚዲያ
