Related Video and Audio

VIDEO 1 MINUTE 44 SECONDSVIDEO 1 MINUTE 44 SECONDS1:44

Play video በሐማስ ጥቃት የሞቱ ወታደሮችን አስከሬን ለማግኘት እስራኤል እንዴት የንስር ወፍን ተጠቀመች? from BBCበሐማስ ጥቃት የሞቱ ወታደሮችን አስከሬን ለማግኘት እስራኤል እንዴት የንስር ወፍን ተጠቀመች?

Play video በሐማስ ጥቃት የሞቱ ወታደሮችን አስከሬን ለማግኘት እስራኤል እንዴት የንስር ወፍን ተጠቀመች? from BBC

VIDEO 1 MINUTE 18 SECONDSVIDEO 1 MINUTE 18 SECONDS1:18

Play video ሕይወት በጋዛ፡ “ጦርነቱ መቶ ዓመታትን ወደኋላ መልሶናል” from BBCሕይወት በጋዛ፡ “ጦርነቱ መቶ ዓመታትን ወደኋላ መልሶናል”

Play video ሕይወት በጋዛ፡ “ጦርነቱ መቶ ዓመታትን ወደኋላ መልሶናል” from BBC

VIDEO 2 MINUTES 31 SECONDSVIDEO 2 MINUTES 31 SECONDS2:31

Play video ‘ቢያንስ ሆስፒታሉ ጥቃት አይደርስበትም ብለን አስበን ነበር’፡ ከሆስፒታል የሸሹ የጋዛ ነዋሪዎች from BBC‘ቢያንስ ሆስፒታሉ ጥቃት አይደርስበትም ብለን አስበን ነበር’፡ ከሆስፒታል የሸሹ የጋዛ ነዋሪዎች

Play video ‘ቢያንስ ሆስፒታሉ ጥቃት አይደርስበትም ብለን አስበን ነበር’፡ ከሆስፒታል የሸሹ የጋዛ ነዋሪዎች from BBC

VIDEO 2 MINUTESVIDEO 2 MINUTES2:00

Play video ጋዛን የጎበኘው ቢቢሲ የዓለም አቀፍ ኤዲተር ጄረሚ ቦውን እይታ from BBCጋዛን የጎበኘው ቢቢሲ የዓለም አቀፍ ኤዲተር ጄረሚ ቦውን እይታ

Play video ጋዛን የጎበኘው ቢቢሲ የዓለም አቀፍ ኤዲተር ጄረሚ ቦውን እይታ from BBC

VIDEO 1 MINUTE 30 SECONDSVIDEO 1 MINUTE 30 SECONDS1:30

Play video አሜሪካ ከ60 በላይ አውሮፕላን ተሸካሚ ሁለተኛ መርከቧን ወደ እስራኤል አስጠጋች from BBCአሜሪካ ከ60 በላይ አውሮፕላን ተሸካሚ ሁለተኛ መርከቧን ወደ እስራኤል አስጠጋች

Play video አሜሪካ ከ60 በላይ አውሮፕላን ተሸካሚ ሁለተኛ መርከቧን ወደ እስራኤል አስጠጋች from BBC

VIDEO 1 MINUTE 48 SECONDSVIDEO 1 MINUTE 48 SECONDS1:48

Play video ሐማስ ጋዛ ውስጥ የገነባቸው ወደ እስራኤል የሚያሻግሩት ዋሻዎች from BBCሐማስ ጋዛ ውስጥ የገነባቸው ወደ እስራኤል የሚያሻግሩት ዋሻዎች

Play video ሐማስ ጋዛ ውስጥ የገነባቸው ወደ እስራኤል የሚያሻግሩት ዋሻዎች from BBC

VIDEO 3 MINUTES 27 SECONDSVIDEO 3 MINUTES 27 SECONDS3:27

Play video ሕይወት በጋዛ፡ ከቤታቸው ወጥተው መጠለያ ፍለጋ መንከራተት from BBCሕይወት በጋዛ፡ ከቤታቸው ወጥተው መጠለያ ፍለጋ መንከራተት

Play video ሕይወት በጋዛ፡ ከቤታቸው ወጥተው መጠለያ ፍለጋ መንከራተት from BBC

ጭምቅ ሃሳብ

  1. እስራኤል በጋዛ ላይ የመትፈጽመውን ጥቃት አጠናክራ ቀጥላለች
  2. የእስራኤል ጦር ጋዛ ውስጥ ከ400 በላይ ዒላማዎችን መምታቱን ገለጸ
  3. ከሁለት ወር ባነሰ ጊዜ 100 ሺህ ሕንፃዎች የወደሙባት የፍርስራሽ ክምሯ ጋዛ በሳተላይት ዕይታ
  4. አንድ ግለሰብ አሜሪካ ውስጥ በሚገኝ የእስራኤል ቆንስላ በር ላይ እራሱን በእሳት አቃጠለ
  5. ሐማስ እና እስራኤል የተኩስ አቁም ፋታ ስምምነቱን በመጣስ እየተወነጃጀሉ ነው
  6. በእየሩሳሌም በተከፈተ ተኩስ ሶስት ሰዎች ተገደሉ
  7. ሩስያ ታጋቾችን በመልቀቁ ሐማስን አመሰገነች
  8. እስራኤል በዌስት ባንክ ባደረሰችው ጥቃት ሁለት ፍልስጤማውያን ልጆች ተገደሉ
  9. በሐማስ ታግተው የነበሩ 12 ሰዎች ሲለቀቁ 30 ፍልስጤማውያን ከእስር ነጻ ወጡ
  10. ከእስራኤል እስር ነጻ የወጣት ታዳጊ “ድብደባ ተፈጽሞብኛል” አለ
  11. እስራኤል የተኩስ አቁም ስምምነት ተጥሶ ጥቃት እንደተፈጸመባት አስታወቀች
  12. የሞሳድ እና የሲአይኤ ኃላፊዎች ኳታር ይገኛሉ
  13. በጋዛ ከቦምብ ይልቅ ሕክምና ሳያገኙ የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር ሊበልጥ ይችላል ተባለ
  14. ሐማስ ሁሉም ታጋቾች በቁጥጥሩ ስር እንደማይገኙ አስታወቀ
  15. በእስራኤል ጥቃት የተገደሉት ከ14ሺህ በላይ መሆኑ ተገለጸ
  16. ኳታር ደመኞቹን አስራኤልን እና ሐማስን እንዴት ከስምምነት እንዲደርሱ አስቻለች?
  17. ሐማስ 41 ታጋቾችን ሲለቅ እስራኤል 78 ፍልስጤማውያንን ፈታች
  18. የእስራኤል እና ሐማስ የተኩስ አቁም ፋታ ምንን ይዟል?
  19. የእስራኤል መከላከያ ‘ጦርነቱ አላከተመም’ ሲል አስጠነቀቀ
  20. እስራኤል ልታጠፋው ቀን ከሌት የምትፈልገው በጋዛ የሐማስ መሪ ያህያ ሲንዋር ማን ነው?
  21. የጋዛ ትልቁ ሆስፒታል አልሺፋ ዳይሬክተር በእስራኤል መከላከያ በቁጥጥር ስር ዋሉ
  22. የጋዛ ጊዜያዊ የተኩስ አቁም ስምምነት የዘገየው ከታጋቾች ዝርዝር ጋር በተያያዘ ነው ተባለ
  23. እስራኤል በጃባሊያ የስደተኞች መጠለያ በፈጸመችው ጥቃት የአንድ ቤተሰብ 52 አባላት ተገደሉ

ቀጥታ ዘገባ

  1. የታተመዉ 5:575:57ከሁለት ወር ባነሰ ጊዜ 100 ሺህ ሕንፃዎች የወደሙባት የፍርስራሽ ክምሯ ጋዛ በሳተላይት ዕይታበእስራኤል እና በሐማስ መካከል የተደረሰው የተኩስ አቁም ፋታ ከመጀመሩ በፊት ቢቢሲ ያገኛቸው አዳዲስ የሳተላይት ምስሎች በሰሜን ጋዛ የደረሰውን ከፍተኛ የውድመት መጠን የሚያሳዩ ናቸው።ተጨማሪ ያንብቡArticle share tools
  2. የታተመዉ 4:334:33ተመድ በሐማስ ተፈጽመዋል የተባሉ ፆታዊ ጥቃቶች አሳሳቢ ናቸው አለUN WomenUN WomenCopyright: UN Womenየተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሴቶች ጉዳይ ተቋም መስከረም 26/2016 ዓ.ም. በሐማስ ጥቃት ወቅት ተፈጽመዋል የተባሉ ፆታን መሠረት ያደረጉ ጥቃቶች አሳሳቢ ናቸው አለ።ሐማስ ጥቃቱን ሲያደርስ በእስራኤል ማኅብረሰብ አባላት ላይ ተፈጽመዋል የተባሉ ፆታን መሠረት ያደረጉ ጥቃቶች ምርመራ እንዲደረግባቸው እና ጥፋተኞች በሕግ እንዲጠየቁ ተቋሙ ጠይቋል።ሐማስ ተዋጊዎቹ ጾታን መሠረት ያደረጉ ጥቃቶችን አልፈጸሙም በማለት ሲያስተባብል ቆይቷል።Article share tools
  3. የታተመዉ 4:314:31በምሥል፡ ከተኩስ አቁም ፋታ በኋላ በቀጠለው ጦርነት በጋዛ የደረሰ ውድመትበጋዛ የደረሰ ውድመትReutersCopyright: Reutersየተኩስ አቁም ፋታ ካበቃ በኋላ እስራኤል ድብደባዋን ቀጥላበታለች።የአገሪቱ ጦር እስካሁን ከ400 ያላሱ የሐማስ መገኛዎችን መትቻለሁ ብሏል።በጥቃቱ ቤተሰቦቻቸውን እና ንብረታቸውን ያጡ ፍልስጤማውያን ሲያነቡ ተይተዋል።በሁለተኛው ዙር ጥቃት በእስራኤል ዒላማ ውስጥ የገባው እና ከባድ ጉዳት የደረሰበት በደቡብ ጋዛ የሚገኘው ኻን ዩኒስ ነው።ከፍርስራሽ ስር የሟቾች አስክሬንን ለማውጣት የሚጣጣሩ ፍልስጤማውያንGetty ImagesCopyright: Getty Imagesከፍርስራሽ ስር የሟቾችን አስክሬን ለማውጣት የሚጣጣሩ ፍልስጤማውያንImage caption: ከፍርስራሽ ስር የሟቾችን አስክሬን ለማውጣት የሚጣጣሩ ፍልስጤማውያንበደቡባዊ ጋዛ በአየር ጥቃት የተገደሉ ሰዎች አስክሬን ሲወጣ የቤተሰብ አባላት ሲያለቅሱ ታይተዋል።Getty ImagesCopyright: Getty Imagesበደቡባዊ ጋዛ በአየር ጥቃት የተገደሉ ሰዎች አስክሬን ሲወጣ የቤተሰብ አባላት ሲያለቅሱImage caption: በደቡባዊ ጋዛ በአየር ጥቃት የተገደሉ ሰዎች አስክሬን ሲወጣ የቤተሰብ አባላት ሲያለቅሱArticle share tools
  4. የታተመዉ 3:573:57የእስራኤል ጦር ጋዛ ውስጥ ከ400 በላይ ዒላማዎችን መምታቱን ገለጸበእስራኤል ጥቃት የፈረሰ ሕንጻGetty ImagesCopyright: Getty Imagesለቀናት የቆየው ጊዜያዊ የተኩስ አቁም ትናንት አርብ አብቅቶ እስራኤል ማለዳ በጋዛ ላይ ጥቃቷን መልሳ ከጀመረች በኋላ እስከ ዛሬ ቅዳሜ ጠዋት ድረስ ከ400 በላይ ዒላማዎችን ማጥቃቷን ጦር ሠራዊቷ አስታወቀ።የእስራኤል መከላከያ ኃይል (አይዲኤፍ) እንዳለው የአገሪቱ የአየር፣ የባሕር እና የምድር ኃይል ደቡባዊ የጋዛ ሰርጥን ጨምሮ መላዋን ጋዛን ዒላማ ያደረጉ ጥቃቶችን መፈጸማቸውን አመልክቷል።ጨምሮም “ተዋጊ ጄቶች በኻን ዩኒስ አካባቢ ባሉ ከ50 በሚልቁ ዒላማዎች ላይ መጠነ ሰፊ ጥቃት ፈጽመዋል” ብሏል።ጦር ኃይሉ የፍልስጤማ እስላማዊ ጂሃድ የተባለው ቡድን እንደ ማዘዣ ማዕከል ይጠቀምበታል ያለውን በሰሜናዊ ጋዛ የሚገኝ አንድ መስጂድን በአየር ጥቃት መምታቱን ገልጿል። ቢቢሲ ይህንን የእስራኤል ሠራዊት ክስ ከገለልተኛ ወገን ማረጋገጥ አልቻለም።እስራኤል የሰሜናዊ ጋዛ ነዋሪዎች አካባቢያቸውን ለቀው ወደ ደቡብ እንዲሄዱ ካዘዘች በኋላ፣ በመቶ ሺዎቸ የሚቆጠሩ የጋዛ ነዋሪዎች በደቡባዊ የሰረጡ ክፍል ውስጥ በምትገኘው የኻን ዩኒስ ከተማ በአብዛኛው በጊዜያዊ የድንኳን መጠለያ ውስጥ ይገኛሉ።Article share tools
  5. የታተመዉ 3:543:54አንድ ግለሰብ አሜሪካ ውስጥ በሚገኝ የእስራኤል ቆንስላ በር ላይ እራሱን በእሳት አቃጠለበአሜሪካዋ ጆርጂያ ግዛት አትላንታ ከተማ ውስጥ ከሚገኝ የእሰራኤል ቆንስላ ጽህፈት ቤት በር ላይ ተቃውሞውን ለመግለጽ እራሱን በእሳት በማቃጠሉ ከባድ ጉዳት እንደደረሰበት ፖሊስ አስታወቀ።ተጨማሪ ያንብቡArticle share tools
  6. የታተመዉ 8:41 1 ታህሳስ 20238:41 1 ታህሳስ 2023ኳታር ለግጭቱ ዳግም ፋታ ለመስጠጥ ንግግር እየተካሄደ ነው አለችለ7 ቀናት ጋብ ብሎ የነበረው ግጭት ዳግም ተጀምሯል።ReutersCopyright: Reutersለ7 ቀናት ጋብ ብሎ የነበረው ግጭት ዳግም ተጀምሯል።Image caption: ለ7 ቀናት ጋብ ብሎ የነበረው ግጭት ዳግም ተጀምሯል።የኳታር መንግሥት እስራኤል እና ሐማስ ዳግም ለጦርነቱ ፋታ ለመስጠት ድርድር እያደረጉ እንደሆነ ገለጸ።የኳታር መንግሥት ሁለቱን ኃይሎች አደራድሮ ባለፉት 7 ቀናት ጦርነቱ ጋብ ብሎ የእስረኞች እና የታጋቾች ልውውጥ ከመደረጉ በተጨማሪ ሰብዓዊ እርዳታ ጋዛ ሲደርስ ነበር።ይሁን እንጂ ሐማስ እና እስራኤል የደረሱት ስምምነት በማብቃቱ ከዛሬ ማለዳ ጀምሮ ሁለቱ ኃይሎች ዳግም ወደ ጦርነት ተመልሰዋል።የኳታር የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እስራኤል ዳግም በጋዛ ሰርጥ ወታደራዊ ዘመቻ መጀመሯ አሳዛኝ ነው ብሏል።ይሁን እንጂ የኳታር መንግሥት ከሌሎች አጋሮች ጋር በመሆን “ለሰብዓዊነት ሲባል ግጭት እንዲቆም ስምምነት እንዲደረስ” ጥረት ማድረጉን እንደሚቀጥል አስታውቋል።Article share tools
  7. የታተመዉ 8:37 1 ታህሳስ 20238:37 1 ታህሳስ 2023የተመድ ዋና ፀሐፊ ግጭት መጀመሩ “እጅግ አሳዛኝ ነው” አሉአንቶኒዮ ገተሬዝGetty ImagesCopyright: Getty Imagesአንቶኒዮ ገተሬዝImage caption: አንቶኒዮ ገተሬዝየተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ በጋዛ ግጭት መጀመሩ “በጣም አሳዛኝ ነው” አሉ።ዋና ፀሐፊው በማኅበራዊ ገጻቸው በኩል ባሰፈሩት መልዕክtእ ባለፉት ቀናት ተግባራዊ ተደርጎ የነበረው ስምምነትን ማስቀጠል ይቻላል የሚል ተስፋ እነeዳላቸው ገልጸዋል።ባለፉት ሰባት ቀናት እስራኤል እና ሐማስ ለጦርነቱ ፋታ ለመስጠት ተስማምተው ታጋቾች እና እስረኞችን ሲለዋወጡ ቆይተዋል።ከመስከረም 26ቱ ድንገተኛ ጥቃት በኋላ በጋዛ ሰርጥ 6ሺህ ሕጻናትን ጨምሮ 14ሺህ 800 ሰዎች መገደላቸውን በሐማስ የሚተዳደረው ጤና ሚንስቴር አስታውቋል።በእስራኤል ደግሞ ከ1200 የማያንሱ ሰዎች ተገድለዋል።Article share tools
  8. የታተመዉ 8:35 1 ታህሳስ 20238:35 1 ታህሳስ 2023በምስል፡ ሮኬቶች እና የአየር ጥቃቶችከሰባት ቀናት የጦርነት ፋታ በኋላ የእስራኤል እና ሐማስ ውጊያ ተጀምሯል።ከዛሬ አርብ ንጋት ጀምሮ ሮኬቶች ከጋዛ እና ወደ ጋዛ ሲወነጨፉ ታይተዋል።የእስራኤል ጦር “ዘመቻ ጀምሬያለሁ” ያለ ሲሆን በጋዛ ሰርጥ የአየር ድብደባዎችን እያደረገ ይገኛል።በጋዛ ሰማይ ላይ ትልቅ ጭስ ታይቷልReutersCopyright: Reutersዛሬ ረፋድ በጋዛ ሰማይ ላይ ትልቅ ጭስ ታይቷልImage caption: ዛሬ ረፋድ በጋዛ ሰማይ ላይ ትልቅ ጭስ ታይቷልበደቡባዊ ጋዛ የወደመ መኖሪያ ቤትReutersCopyright: Reutersበደቡባዊ ጋዛ የወደመ መኖሪያ ቤትImage caption: በደቡባዊ ጋዛ የወደመ መኖሪያ ቤትጦርነት ዳግም መቀስቀሱን ተከትሎ ፍልስጤማውያን መኖሪያቸውን ጥለው ለመሸሽ ተገደዋልReutersCopyright: Reutersጦርነት ዳግም መቀስቀሱን ተከትሎ ፍልስጤማውያን መኖሪያቸውን ጥለው ለመሸሽ ተገደዋልImage caption: ጦርነት ዳግም መቀስቀሱን ተከትሎ ፍልስጤማውያን መኖሪያቸውን ጥለው ለመሸሽ ተገደዋልሮኬቶች ከጋዛ ሰርጥ ወደ እስራኤል ሲወነጨፉ ታይተዋልReutersCopyright: Reutersሮኬቶች ከጋዛ ሰርጥ ወደ እስራኤል ሲወነጨፉ ታይተዋልImage caption: ሮኬቶች ከጋዛ ሰርጥ ወደ እስራኤል ሲወነጨፉ ታይተዋልArticle share tools
  9. የታተመዉ 3:54 1 ታህሳስ 20233:54 1 ታህሳስ 2023እስራኤል በ3 ሰዓታት ውስጥ በፈጸመቻቸው የአየር ጥቃት 32 ፍልስጤማውያን መገደላቸው ተገለጸየጋዛ ጥቃትGetty ImagesCopyright: Getty Imagesእስራኤል የተኩስ አቁም ፋታው ማብቃቱን ተከትሎ ባሉ ሶስት ሰዓታት በፈጸመቻቸው የአየር ጥቃቶች 32 ፍልስጤማውያን መገደላቸውን የጋዛ የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።በሐማስ አስተዳደር ስር የሚገኘው የጤና ሚኒስቴር እስራኤል በበርካታ የጋዛ ስፍራዎች የአየር ጥቃት እየፈጸመች ነው ብሏል።ለሰባት ቀናት የዘለቀውን የተኩስ አቁም ፋታ ተከትሎ የተከተለው ጥቃትም አስደንጋጭ ነው ተብሏል።የተባበሩት መንግሥታት የህጻናት መርጃ ድርጅት፣ ዩኒሴፍ ለቢቢሲ እንደተናገረው በደቡባዊ ጋዛ ያለው ሁኔታ “አስፈሪ ነው” ብለዋል።”ያለው ሁኔታ ለነዋሪዎች አሰቃቂ ነው። በፊታቸው ላይም ፍርሃት ይነበባል” ሲሉ የዩኒሴፍ ባልደረባ ጄምስ ኤልደር ለቢቢሲ ተናግረዋል።በአሁኑ ወቀድት በደቡባዊ ጋዛ በሚገኝ ሆስፒታል ውስጥ እንደሚገኙ የተናገሩት ጄምስ ከተቋሙ በ50-100 ሜትር ርቀትም ላይ የአየር ጥቃት ተፈጽሟል ብለዋል።የተኩስ አቁም ፋታው ማብቃቱንም “ሁሉም ሰው የሚፈራው ቅዠት” ደርሷል ሲሉ ገልጸው ሰብዓዊ ቀውሱም ለበርካቶች ሞት እንደሚሆንም አስጠንቅቀዋል።Article share tools
  10. የታተመዉ 2:48 1 ታህሳስ 20232:48 1 ታህሳስ 2023ሐማስ እና እስራኤል የተኩስ አቁም ፋታ ስምምነቱን በመጣስ እየተወነጃጀሉ ነውየጋዛ ጥቃትGetty ImagesCopyright: Getty Imagesሐማስ እና እስራኤል ለሰባት ቀናት የቆየው የተኩስ አቁም ፋታ ስምምነትን በመጣስ እየተወነጃጀሉ ነው።ሐማስ የስምምነቱ አካል የሆነው በሰሜናዊ ጋዛ ሰርጥ ነዳጅ እንዲገባ መፈቀድ ቢኖርበትም እስራኤል በመከልከሏ ስምምነቱን ጥሳለች እንዳለ ለድርድሩ ቅርብ የሆኑ ምንጭ ለቢቢሲ ተናግረዋል።እስራኤል በበኩሏ ሐማስ ተጨማሪ ታጋቾችን ለመልቀቅ ፈቃደኛ ባለመሆኑ ስምምነቱ ተጥሷል ብላለች።ለድርድሩ ቅርብ የሆኑት እኚሁ ምንጭ በበኩላቸው ሐማስ በጋዛ የተወሰዱ ወንዶች ታጋቾችን፤ ሴቶችን እና ህጻናቶችን በለቀቀው መልኩ ለመልቀቅ ፈቃደኛ አይደለም ብለዋል።የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ በበኩላቸው በስምምነቱ መሰረት ሐማስ ሁሉንም ሴቶች ታጋቾች እንዳልለቀቀ እና በእስራኤልም ላይ ሮኬት አስወንጭፏል ብለዋል።” እስራኤል ታጋቾችን ለማስለቀቅ፣ ሐማስን ለማጥፋት እና ጋዛ በእስራኤል ነዋሪዎች ላይ ስጋት እንዳትፈጥር የጀመረችውንም ወታደራዊ ዘመቻ ከግብ ለማድረስ ትቀጥላለች” ብለዋል።Article share tools
  11. የታተመዉ 1:52 1 ታህሳስ 20231:52 1 ታህሳስ 2023እስራኤል በራፋህ በፈጸመችው የአየር ጥቃት ስድስት ፍልስጤማውያን ተገደሉለሰባት ቀናት የዘለቀው የተኩስ አቁም ፋታ ማብቃቱን ያወጀው የእስራኤል ጦር በደቡባዊ ጋዛ ራፋህ ከተማ በፈጸመው የአየር ጥቃት ስድስት ፍልስጤማውያን ተገደሉ።ጥቃቱ ዛሬ ማለዳ መፈጸሙንም በሐማስ አስተዳደር ስር የሚገኘው የጤና ሚኒስቴር ቃለ አቀባይ ለአጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ተናግረዋል።የተኩስ አቁም ፋታው ዛሬ ማለዳ ያቆመ ሲሆን እስራኤልም ሐማስ ሮኬት አስወንጭፏል በማለት ስምምነቱን ጥሷል ስትል ከሳለች።ከዚህ በተጨማሪም እስራኤል በሰሜን ጋዛ በፈጸመችው የአየር ጥቃት ሁለት ልጆች መገደላቸውን ኤኤፍፒ በአል አህሊ ሆስፒታል የህክምና ባለሙያ የሆኑትን ዶክተር ፋዴል ናይምን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል።በርካታ የጋዛ ሰርጥ አካባቢዎችም በእስራኤል የአየር ጥቃት እንደተፈጸመባቸው የጋዛ የሃገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።በኳታር አሸማጋይነት የተደረሰውን የተኩስ አቁም ፋታ ተከትሎ ሐማስ 110 ታጋቾችን ሲለቅ እስራኤል ደግሞ 240 ህጻናት እና ሴቶች ፍልስጤማውያን እስረኞችን ፈታለች።ጦርነቱ ዳግም መጀመር በከበባ ውስጥ ባለች የጋዛ ሰርጥ የከፋ ስብዓዊ ቀውስ ያስከትላልም ተብሏል።Article share tools
  12. የታተመዉ 1:15 1 ታህሳስ 20231:15 1 ታህሳስ 2023የጋዛ የተኩስ አቁም ፋታ ማብቃቱን እና ጦርነት መቀጠሉን እስራኤል አስታወቀችየእስራኤል መከላከያReutersCopyright: Reutersለሰባት ቀናት የዘለቀው የጋዛ የተኩስ አቁም ፋታ ማብቃቱን እና ጦርነት መቀጠሉን እስራኤል አስታወቀች።የእስራኤል ጦር ሐማስ ስምምነቱን ጥሷል ሲል ከሷል። “ሐማስ ሰብዓዊ የተኩስ አቁም ፋታውን በመጣስ ሮኬት ወደ እስራኤል አስወንጭፏል።የእስራኤል መከላከያ ኃይል በጋዛ ሰርጥ ከሐማስ ጋር የሚያደርገውን ጦርነት ቀጥሏል” ሲልም የእስራኤል መከላከያ መግለጫ አውጥቷል። እስራኤል ይህንን ማወጇን ተከትሎ እስራኤል በጋዛ ሰርጥ የአየር ጥቃቶች እየፈጸመች ስለመሆኑ ሪፖርቶች ወጥተዋል።የእስራኤል መከላከያ በበኩሉ ” የሐማስ ኢላማዎችን እያጠቃሁ” ነው ብሏል። በኳታር አሸማጋይነት የተደረሰውን የተኩስ አቁም ፋታ ተከትሎ ሐማስ 110 ታጋቾችን ሲለቅ እስራኤል ደግሞ 240 ህጻናት እና ሴቶች ፍልስጤማውያን እስረኞችን ፈታለች።Article share tools
  13. የታተመዉ 1:14 1 ታህሳስ 20231:14 1 ታህሳስ 2023ብሊንከን ከእስካሁኑ ጠንከር ባለ መልዕክታቸው እስራኤል ሲቪሎችን እንድትታደግ ጠየቁየአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን እስራኤል በጋዛ ከሐማስ ጋር በምታደርገው ጦርነት ለሲቪሎች ጥበቃ የምታደርግበትን መለኪያዎችን በግልጽ አስቀምጠዋል። ከእስካሁኑ በጣም ጠንካራ በተባለው የአሜሪካ አስተያየት፤ የእስራኤል መንግሥት ተጨማሪ ፍልስጤማውያንን ማፈናቀል እንዲያቆም፣ እንደ ሆስፒታሎች፣ የኃይል አቅርቦትን ጨምሮ እና የውሃ ተቋማት ባሉ ወሳኝ መሠረተ ልማቶች ላይ ጉዳት እንዳያደርስ ብሊንከን መናገራቸው ታውቋል።ተጨማሪ ያንብቡArticle share tools
  14. የታተመዉ 5:05 30 ህዳር 20235:05 30 ህዳር 2023ሩስያ ታጋቾችን በመልቀቁ ሐማስን አመሰገነችየሩሲያ ሰንደቅ ዓላማAFPCopyright: AFPሐማስ ሁለት ሩሲያዊ ታጋቾችን በትናንትናው ዕለት መልቀቁን ተከትሎ የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ምስጋናውን ለሐማስ አቅርቧል።ሩሲያ እንዳሳወቀችው ታጋቾቹ የተለቀቁት በእስራኤል እና ሐማስ ከተደረገው ስምምነት ጋር የተያያዘ አይደለም ብላለች።”ወገኖቻችን በትናንትናው ዕለት የተለቀቁት ከሐማስ አመራሮች ጋር ባደረግነው ስምምነት መስረት” ነው ብሏል።”ለጥያቄቻችን አዎንታዊ ምላሽ ለሰጡን የሐማስ አመራሮች ምስጋናችንን እናቀርባለን። በጋዛ ሰርጥ የተያዙ ሌሎች ሩሲያውያን እንዲለቀቁም ጥረታችንን እንቀጥላለን” በማለት ባወጣው መግለጫ አትቷል።Article share tools
  15. የታተመዉ 3:55 30 ህዳር 20233:55 30 ህዳር 2023በእየሩሳሌም በተከፈተ ተኩስ ሶስት ሰዎች ተገደሉየእስራኤል ፖሊስGetty ImagesCopyright: Getty Imagesበእየሩሳሌም የአውቶብስ ጣቢያ በተከፈተ ተኩስ ሶስት ሰዎች ተገደሉ።ተኩሱ የተከፈተበት የስራ ሰዓት መግቢያ ላይ እንደሆነም ተነግሯል።ፖሊስ እንዳስታወቀው ማለዳ በስራ ሰዓት መግቢያ እና ሰዎች በሚበዙበት ወቅት ሁለት ታጣቂዎች ከእየሩሳሌም ወጣ ብሎ በሚገኘው የአውቶብስ ጣቢያ ላይ ተኩስ ከፍተዋል ብሏል።ፖሊስ ሪፖርቱ የደረሰው በአገሬው ሰዓት አቆጣጠር ከጥዋቱ 1 ሰዓት ከ40 መሆኑን አስታውቋል። በተኩሱም የ24 ዓመት ሴትን ጨምሮ ሶስት ሰዎች ሲገደሉ ስድስት ሰዎች ቆስለዋል።የእስራኤል ብሄራዊ ደህንነት ሚኒስትር ኢታማር ቤን ግቪር እንደተናገሩት ተኩሱን የከፈቱት ሁለት ግለሰቦች የሐማስ አባላት ናቸው ብለዋል።ግለሰቦቹም በምስራቅ እየሩሳሌም ነዋሪዎች መሆናቸውንም አክለዋል። “በግልጽ ሐማስ የፈጸማቸው ናቸው። በአንደኛው በኩል የተኩስ አቁም ይላሉ በሌላኛው የሽብር ተግባር ይፈጽማሉ” ሲሉ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል።የደረሰው ጥቃት በእስራኤል ውስጥ ላሉ ሰላማዊ ዜጎች የጦር መሳሪያ ማከፋፈል አስፈላጊነትን የሚያሳይ ነው ብለዋል።Article share tools
  16. የታተመዉ 0:53 30 ህዳር 20230:53 30 ህዳር 2023እስራኤል በዌስት ባንክ ባደረሰችው ጥቃት ሁለት ፍልስጤማውያን ልጆች ተገደሉእስራኤል በኃይል በያዘቻት ዌስት ባንክ የእስራኤል ወታደሮች በፈጸሙት ጥቃት ሁለት ህጻናትን ጨምሮ አራት ፍልስጤማውያን መገደላቸውን የፍልስጤም ባለስልጣናት ተናገሩ። የደህንነት ካሜራ ቪዲዮዎች የስምንት ዓመቱ አደም አል-ጉል እና የ14 ዓመቱ ባዝል አቡ አል-ዋፋ በጄኒን ከተማ በተመሳሳይ ሁኔታ በጥይት ሲመቱ አሳይተዋል።ተጨማሪ ያንብቡArticle share tools
  17. የታተመዉ 0:14 30 ህዳር 20230:14 30 ህዳር 2023የጋዛ የተኩስ አቁም ፋታ እንደሚቀጥል የእስራኤል ጦር አስታወቀየእስራኤል ጦርReutersCopyright: Reutersስድስተኛ ቀኑን የያዘው የተኩስ አቁም ፋታ እንደሚቀጥል የእስራኤል ጦር አስታውቋል።ሐማስ በበኩሉ የተኩስ አቁም ፋታው ለአንድ ቀን እንደተራዘመ አስታውቋል።ሐማስ ለሰባተኛ ቀን የተኩስ አቁም ፋታውን ለማራዘም ስምምነት ላይ መደረሱንም ሮይተርስ የዜና ወኪል ዘግቧል።የእስራኤል ጦር የተራዘመው የተኩስ አቁም ፋታ ለምን ያህል ጊዜ እንደሚቆይ አልገለጸም።ዛሬ ይጠናቀቃል የተባለው የተኩስ አቁም ፋታ ‘ ተጨማሪ ታጋቾችን የማስለቀቁን ሂደትም ለማስቀጠል አሸማጋዮቹ ካደረጉት ጥረት ጋር ተያይዞም ይቀጥላል” ተብሏል።በስምምነቱ መሰረት ሐማስ የወሰዳቸውን ታጋቾች የሚለቅ ሲሆን በልውውጡም እስራኤል የያዘቻቸውን ህጻናት እና ሴቶች ፍልስጤማዊ እስረኞችን ትፈታለች።Article share tools
  18. የታተመዉ 0:03 30 ህዳር 20230:03 30 ህዳር 2023ስድስተኛ ቀኑን በያዘው የተኩስ አቁም ፋታ የተከሰቱ ዋና ዋና ጉዳዮችሰንደቅ ዓላማ የሚያውለበልብ ፍልስጤማዊReutersCopyright: Reutersበሐማስ እና እስራኤል መካከል የተደረሰው የተኩስ አቁም ፋታ ስድስተኛ ቀኑን ይዟል። በባለፉት ስድስት ቀናት ሐማስ ወስዷቸው የነበሩ ታጋቾች ሲለቀቁ በልውውጡ እስራኤል ህጻናት እና ሴቶች ፍልስጤማውያን እስረኞችን ፈትታለች። ለሁለተኛ ጊዜ የተራዘመው የተኩስ አቁም ፋታ ዛሬ የሚጠናቀቅ ሲሆን ለማራዘምም ንግግሮች እየተደረጉ ይገኛሉ።በባለፉት ሰዓታት ከተከሰቱ ዋና ዋና ጉዳዮች መካከል፦ተጨማሪ ታጋቾች ተለቀው ወደ እስራኤል ተመልሰዋል
    • ሁለት እስራኤላዊ ሩሲያውያን ታጋቾች በትናንትናው ዕለት ተለቀው ወደ እስራኤል ተመልሰዋል።
    • በኋላም ሌሎች 10 እስራኤላውያን እንዲሁም አራት የታይላንድ ዜጎች ተፈትተው በዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ኮሚቴ አማካኝነት ወደ እስራኤል ተወስደዋል።
    • እስራኤል በልውውጡ 30 ፍልስጤማውያን እስረኞች መልቀቋን አስታውቃለች። ኳታር ቀደም ሲል የሚለቀቁት እስረኞች 16 ህጻናት እንዲሁም 14 ሴቶች መሆናቸውን አስታውቃለች።
    በዌስት ባንክ ሁለት ልጆች ተገደሉ
    • እስራኤል በወረራ በያዘቻት ዌስት ባንክ ጄኒን ከተማ ሁለት ፍልስጤማውያን ህጻናት ተገድለዋል። አዳም አል ጉል የስምንት ዓመት ልጅ ሲሆን ባሴል አቡልዋፋ 14 ዓመቱ ነበር።
    • የፍልስጤም ባለስልጣናት እንደገለጹት ህጻናቱ የተገደሉት በእስራኤል ወታደሮች ነው። እስራኤል በበኩሏ ጦሯ ፈንጂ ወርውረዋል ተብለው በተጠረጠሩ ግለሰቦች ላይ እንደተኮሰና ሁለት “ከፍተኛ የሽብር አቀናባሪዎችን” ገድያለሁ ብላለች። የህጻናቱን ግድያ በተመለከተ የሰጠችው አስተያየት የለም።
    በእገታ ላይ የነበረው ጨቅላ እጣ ፈንታ
    • ሐማስ በእገታ ላይ የነበረው የ10 ወር ጨቅላ እስራኤል በፈጸመችው የጋዛ የአየር ጥቃት መገደሉን አስታውቋል። ከጨቅላው በተጨማሪ ታላቅ ወንድሙ እና እናቱም ተገድለዋል ብሏል።
    • እስራኤል በበኩሏ ይህንን እያጣራሁ ነው ብላለች። ማክሰኞ ዕለት ሐማስ ሁለት ሌሎች ትንንሽ ልጆች ለሌላ “እስላማዊ አንጃ ቡድን” እንደሰጣቸው አስታውቋል።
    Article share tools
  19. የታተመዉ 7:54 29 ህዳር 20237:54 29 ህዳር 2023የሰሜናዊ ጋዛ አካባቢዎች ለመኖሪያነት ከማይሆኑበት ደረጃ ላይ ደርሰዋል፡ የመንግሥታቱ ድርጅትየፈራረሱ ሕንጻዎችReutersCopyright: Reutersባለፉት ሳምንታት በእስራኤል ያልተቋረጠ ጥቃት ምክንያት ከባድ ውድመት በደረሰባት በጋዛ ሰሜናዊ ክፍል ውስጥ ያሉ ከፊል አካባቢዎች በአሁኑ ጊዜ ለመኖሪያነት እንደማይሆኑ የመንግሥታቱ ድርጅት ገለጸ።በጋዛ የድርጅቱ የስደተኞች ጉዳይ ዳይሬክተር የሆኑት ቶማስ ዋይት ይህንን ያሉት በሰሜናዊ የጋዛ ክፍል እና በጋዛ ከተማ ዙሪያ ያሉ አካባቢዎችን ከጉብኙ በኋላ ነው።እስራኤል የእግረኛ ሠራዊት ዘመቻ በጋዛ ላይ በጀመረችበት ጊዜ በሰሜናዊ ጋዛ የሚገኙ ሲቪሎች ከአካባቢው ለቀው እንዲወጡ ካዘዘች በኋላ በምድር እና በአየር ከባድ ጥቃቶችን ስትፈጽም መቆየቷ ይታወቃል።ዳይሬክተሩ ለቢቢሲ ራዲዮ 4 እንደተናገሩት “በደህናው ጊዜ ሞቅ ያለ የሕዝብ እንቅስቃሴ የሚካሄድባት ከተማ፣ ዛሬ መንገዶቿ በፍርስራሾች ተሸፍነዋል” ብለዋል።ጨምረውም በከተማዋ ዳርቻዎች በሚገኙ አካባቢዎች ያሉ ሁሉም ሕንጻዎች ፈራርሰው በመንገዶች ላይም የሚንቀሳቀስ ሰው እንደማይታይ ተናግረዋል።ቶማስ ዋይት በጋዛ ውስጥ በተመለከቷቸው እና ውስን ጉዳት በደረሰባቸው አካባቢዎች “ጥቂት ሰዎች ከሱቆች በር ላይ እና ከቤታቸው ደጅ ተቀምጠው” በማየታቸው የሕይወት ምልክቶች ቢመለከቱም ከተማዋ “ጸጥ ረጭ” እንዳለች ገልጸዋል።የመንግሥታቱ ድርጅት ቡድን በሰሜናዊ ጋዛ ወደሚገኘው ጃባሊያ የእርዳታ አቅርቦት ለማድረስ የተጓዘ ሲሆን፣ “በመጨረሻም አንዳች አይነት ድጋፍ በማግኘታቸው ነዋሪዎች ታላቅ እፎይታ ተሰምቷቸዋል” ብለዋል ዳይሬክተሩ።በሰሜናዊ ጋዛ ባደረጉት ጉብኝትም “ከፍተኛ መጠን ያለው ውድመት የደረሰባቸው” የተወሰኑ አካባቢዎች ለሰዎች መኖሪያ መሆን ከማይችሉበት ደረጃ ላይ እንደደረሱ አመልክተዋል።በአንጻራዊነት ደግሞ በጥቃቶቹ “ያልተነኩ የሚመስሉ” ሌሎች አካባቢዎች ቢኖሩም፣ የኤሌክትሪክ ኃይል እና ውስን የውሃ አቅርቦት ብቻ ስላላቸው ችግር ውስጥ መሆናቸውን ተናግረዋል።በተጨማሪም “ሁሉም መደበኛ አገልግሎቶች እና እንቅስቃሴዎች…ጋዛ ውስጥ የሉም” ብለዋል የመንግሥታቱ ድርጅት ባለሥልጣን።Article share tools
  20. የታተመዉ 5:09 29 ህዳር 20235:09 29 ህዳር 2023ሳምንታትን በፍርሃት፣ በእንግልት እና በረሃብ ያሳለፉት የሐማስ ታጋቾች ታሪክባዶ አግዳሚ ወንበሮች እንደ አልጋ ያገለግላሉ። “የታፈኑ” አየር የሌላቸው ክፍሎች ውስጥ ይታጎራሉ። ከትንሽ አንዳንዴም ምንም ምግብ አይቀርብላቸውም። በሐማስ የታገተው ታዳጊ የመስከረም 26ቱን ጥቃት ያደረሰውን ጉዳት የሚያሳይ ቪዲዮ ቪዲዮን እንዲመለከት ተደርጓል።ተጨማሪ ያንብቡArticle share tools