December 2, 2023 – VOA Amharic
እስራኤል እና ሐማስ ከሰባት ቀናት እፎይታ በኋላ ዛሬ ማለዳ እንደገና ውጊያ ቀጥለዋል። የእስራኤል መከላከያ ኃይል እንደሚለው፣ ውጊያው የቀጠለው ሐማስ የተኩስ ማቆም ስምምነቱን በመጣስ ሮኬት መተኮሱን ተከትሎ ነው።
ከጋዛ የተወነጨፈውን ሮኬት ኃይሉ ማክሸፉን በ X ማኅበራዊ መድረክ ላይ አስታውቋል።
በሐማስ የሚተዳደረው እና በጋዛ የሚገኘው የጤና ሚኒስቴር፣ በዛሬ ማለዳው ጥቃት ቢያንስ 32 ሰ…