በኤርትራ የተለያዮ ግንባሮች ወታደራዊ ዝግጅት እንዲደረግ ትእዛዝ መሰጠቱ ተሰማ::
የኤርትራ ወታደራዊ አመራሮች ከሁመራ እስክ አሰብ ግንባር ያለውን ሀይል የሚመሩት ከፍተኛ ወታደራዊ ጀነራሎች ባደረጉት ግምገማ የፋኖ ታጣቂዎች የአብይ አህመድ መከላከያን እያሸነፉት ይገኛሉ ይህን የፋኖ ሀይል ብልፅግና መቋቋም አቅቶታል ሲሉ በግምገማቸው ላይ አስቀምጠዋል::
እንዲህ ሀገር ውስጥ ያለውን ሀይል መቋቋም የማይችል ብልፅግና ባህር ቢል ወደብ ቢል ህልም ከመሆን ውጭ ፍሬ አልባ ምኞት ነው ሲሉ አጣጥለውታል::
ሆኖም አብይ አህመድ ከጦርነት ወደ ጦርነት የመሸጋገር አባዜ ያለበት ስለሆነ የኤርትራ መንግስት አስፈላጊውን ዝግጅት ጨርሷል ብለዋል::
ምንጭ : ኢትዮ ፎረም
