
ከ 4 ሰአት በፊት
የሩስያ ወታደሮች ሁለት እጅ የሰጡ የዩክሬን ወታደሮችን ሲገድሉ የሚያሳይ ቪዲዮ መውጣቱን ተከትሎ ዩክሬን ምርመራ ከፈተች።
ቪዲዮው “የሩስያ ወታደራዊ መለዮ የለበሱ ግለሰቦች” ያልታጠቁ የዩክሬን ወታደሮች ላይ በቅርብ ርቀት ሲተኩሱባቸው እንደሚያሳይም የዩክሬን አቃብያነ ህግ ገልጸዋል።
የጦር እስረኞችን መግደል የጦር ህጎችን እንዲሁም ልምዶችን በከባድ መልኩ የጣሰ ነው ሲሉም ነው እነዚሁ አቃብያነ ህግ የተናገሩት።
ቪዲዮው በገለልተኛ አካል ያልጣራ ሲሆን ሩሲያም ይህንን አስመልክቶ የሰጠችው አስተያየት የለም።
ሩሲያ በዩክሬን ላይ የፈጸመችው ወረራን ተከትሎ ሁለቱ ወገኖች የጄኔቫ ኮንቬንሽኖችን በመጣስ ሲካሰሱ ይሰማል። የጄኔቫ ኮንቬሽን ጦርነቶች በምን አግባብ ሊካሄዱ ይገባል? እንዲሁም የጦር እስረኞችን አያያዝ ጨምሮ ሌሎች አለም አቀፍ ህጎችን በበላይነት ይቆጣጠራል።
“የጦር ህጎችን እና ልምዶችን በመጣስ እንዲሁም ሆን ብሎ እና አቅዶ ግድያ በመፈጸም” ምርመራዎችን እንደከፈተም የዩክሬን ጠቅላይ አቃቤ ህግ ቢሮ እሁድ ዕለት ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።
- በኒው ዮርክ ሁለት ልጆችን ጨምሮ አራት ግለሰቦች በስለት ተወግተው ተገደሉከ 5 ሰአት በፊት
- በኪሲንጀር ትዕዛዝ ከ2 ሚሊዮን ቶን በላይ ቦምብ የዘነበባት ካምቦዲያ እንዴት ታስታውሳቸዋለች?ከ 6 ሰአት በፊት
- የአሜሪካ ጦር መከርብ ቀይ ባሕር ላይ ከየመን የተተኮሱ ድሮኖችን መትቶ መጣሉን ገለጸከ 6 ሰአት በፊት
“የጦር እስረኞቹ ግድያ እንደ ከባድ የዓለም አቀፍ ወንጀል ለመቆጠር ብቁ” መሆኑንም ነው ቢሮው ያስታወቀው።
ቅድመ መረጃ እንደሚያመለክተው ጥቃቱ የተፈጸመው በዩክሬን ምስራቃዊ ዶኔትስክ ክልል ውስጥ በምትገኘው ስቴፖቭ መንደር አቅራቢያ መሆኑንም ገልጿል።
ቪዲዮው በማን እና መቼ እንደተቀረጸም ዝርዝር መረጃ ከመስጠት ተቆጥቧል።
ግድያው ተፈጽሞበታል የተባለው አካባቢ በሩሲያ እና ዩክሬን ኃይሎች መካከል ከባድ ውጊያን አስተናግዷል። ሩሲያ አቪዲቭካ አቅራቢያ የምትገኘውንም ግዛት ለመቆጣጠር ከፍተኛ ውጊያ እያደረገች ትገኛለች። ሩሲያ ከጠቀለለቻት ዶኔትስክ ግዛት መዲና የሆነችው አቪድቭካ አቅራቢያ የምትገኘው ይህች ግዛት የዪክሬን ዋነኛ ምሽግ መሆኗም እየተነገረ ነው።
የዩክሬን ጦር አሁድ እለት በሰጠው የተለየ መግለጫ “የዓለም ማህበረሰብ የሩሲያን ድርጊት በማውገዝ የወራሪውን ወታደራዊ አመራር ለፍርድ እንዲያቀርብም ነው” ያሳሰበው።
የሩሲያ ጦር በቀረበበት ክስ ላይ እስካሁን የሰጠው አስተያየት የለም።
