Related Video and Audio

VIDEO 1 MINUTE 44 SECONDSVIDEO 1 MINUTE 44 SECONDS1:44
Play video በሐማስ ጥቃት የሞቱ ወታደሮችን አስከሬን ለማግኘት እስራኤል እንዴት የንስር ወፍን ተጠቀመች? from BBCበሐማስ ጥቃት የሞቱ ወታደሮችን አስከሬን ለማግኘት እስራኤል እንዴት የንስር ወፍን ተጠቀመች?
- BBC
Play video በሐማስ ጥቃት የሞቱ ወታደሮችን አስከሬን ለማግኘት እስራኤል እንዴት የንስር ወፍን ተጠቀመች? from BBC

VIDEO 1 MINUTE 18 SECONDSVIDEO 1 MINUTE 18 SECONDS1:18
Play video ሕይወት በጋዛ፡ “ጦርነቱ መቶ ዓመታትን ወደኋላ መልሶናል” from BBCሕይወት በጋዛ፡ “ጦርነቱ መቶ ዓመታትን ወደኋላ መልሶናል”
- BBC
Play video ሕይወት በጋዛ፡ “ጦርነቱ መቶ ዓመታትን ወደኋላ መልሶናል” from BBC

VIDEO 2 MINUTES 31 SECONDSVIDEO 2 MINUTES 31 SECONDS2:31
Play video ‘ቢያንስ ሆስፒታሉ ጥቃት አይደርስበትም ብለን አስበን ነበር’፡ ከሆስፒታል የሸሹ የጋዛ ነዋሪዎች from BBC‘ቢያንስ ሆስፒታሉ ጥቃት አይደርስበትም ብለን አስበን ነበር’፡ ከሆስፒታል የሸሹ የጋዛ ነዋሪዎች
- BBC
Play video ‘ቢያንስ ሆስፒታሉ ጥቃት አይደርስበትም ብለን አስበን ነበር’፡ ከሆስፒታል የሸሹ የጋዛ ነዋሪዎች from BBC

VIDEO 2 MINUTESVIDEO 2 MINUTES2:00
Play video ጋዛን የጎበኘው ቢቢሲ የዓለም አቀፍ ኤዲተር ጄረሚ ቦውን እይታ from BBCጋዛን የጎበኘው ቢቢሲ የዓለም አቀፍ ኤዲተር ጄረሚ ቦውን እይታ
- BBC
Play video ጋዛን የጎበኘው ቢቢሲ የዓለም አቀፍ ኤዲተር ጄረሚ ቦውን እይታ from BBC

VIDEO 1 MINUTE 30 SECONDSVIDEO 1 MINUTE 30 SECONDS1:30
Play video አሜሪካ ከ60 በላይ አውሮፕላን ተሸካሚ ሁለተኛ መርከቧን ወደ እስራኤል አስጠጋች from BBCአሜሪካ ከ60 በላይ አውሮፕላን ተሸካሚ ሁለተኛ መርከቧን ወደ እስራኤል አስጠጋች
- BBC
Play video አሜሪካ ከ60 በላይ አውሮፕላን ተሸካሚ ሁለተኛ መርከቧን ወደ እስራኤል አስጠጋች from BBC

VIDEO 1 MINUTE 48 SECONDSVIDEO 1 MINUTE 48 SECONDS1:48
Play video ሐማስ ጋዛ ውስጥ የገነባቸው ወደ እስራኤል የሚያሻግሩት ዋሻዎች from BBCሐማስ ጋዛ ውስጥ የገነባቸው ወደ እስራኤል የሚያሻግሩት ዋሻዎች
- BBC
Play video ሐማስ ጋዛ ውስጥ የገነባቸው ወደ እስራኤል የሚያሻግሩት ዋሻዎች from BBC

VIDEO 3 MINUTES 27 SECONDSVIDEO 3 MINUTES 27 SECONDS3:27
Play video ሕይወት በጋዛ፡ ከቤታቸው ወጥተው መጠለያ ፍለጋ መንከራተት from BBCሕይወት በጋዛ፡ ከቤታቸው ወጥተው መጠለያ ፍለጋ መንከራተት
- BBC
Play video ሕይወት በጋዛ፡ ከቤታቸው ወጥተው መጠለያ ፍለጋ መንከራተት from BBC
ጭምቅ ሃሳብ
- እስራኤል በጋዛ ላይ የመትፈጽመውን ጥቃት አጠናክራ ቀጥላለች
- የእስራኤል ጦር ጋዛ ውስጥ ከ400 በላይ ዒላማዎችን መምታቱን ገለጸ
- ከሁለት ወር ባነሰ ጊዜ 100 ሺህ ሕንፃዎች የወደሙባት የፍርስራሽ ክምሯ ጋዛ በሳተላይት ዕይታ
- አንድ ግለሰብ አሜሪካ ውስጥ በሚገኝ የእስራኤል ቆንስላ በር ላይ እራሱን በእሳት አቃጠለ
- ሐማስ እና እስራኤል የተኩስ አቁም ፋታ ስምምነቱን በመጣስ እየተወነጃጀሉ ነው
- በእየሩሳሌም በተከፈተ ተኩስ ሶስት ሰዎች ተገደሉ
- ሩስያ ታጋቾችን በመልቀቁ ሐማስን አመሰገነች
- እስራኤል በዌስት ባንክ ባደረሰችው ጥቃት ሁለት ፍልስጤማውያን ልጆች ተገደሉ
- በሐማስ ታግተው የነበሩ 12 ሰዎች ሲለቀቁ 30 ፍልስጤማውያን ከእስር ነጻ ወጡ
- ከእስራኤል እስር ነጻ የወጣት ታዳጊ “ድብደባ ተፈጽሞብኛል” አለ
- እስራኤል የተኩስ አቁም ስምምነት ተጥሶ ጥቃት እንደተፈጸመባት አስታወቀች
- የሞሳድ እና የሲአይኤ ኃላፊዎች ኳታር ይገኛሉ
- በጋዛ ከቦምብ ይልቅ ሕክምና ሳያገኙ የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር ሊበልጥ ይችላል ተባለ
- ሐማስ ሁሉም ታጋቾች በቁጥጥሩ ስር እንደማይገኙ አስታወቀ
- በእስራኤል ጥቃት የተገደሉት ከ14ሺህ በላይ መሆኑ ተገለጸ
- ኳታር ደመኞቹን አስራኤልን እና ሐማስን እንዴት ከስምምነት እንዲደርሱ አስቻለች?
- ሐማስ 41 ታጋቾችን ሲለቅ እስራኤል 78 ፍልስጤማውያንን ፈታች
- የእስራኤል እና ሐማስ የተኩስ አቁም ፋታ ምንን ይዟል?
- የእስራኤል መከላከያ ‘ጦርነቱ አላከተመም’ ሲል አስጠነቀቀ
- እስራኤል ልታጠፋው ቀን ከሌት የምትፈልገው በጋዛ የሐማስ መሪ ያህያ ሲንዋር ማን ነው?
- የጋዛ ትልቁ ሆስፒታል አልሺፋ ዳይሬክተር በእስራኤል መከላከያ በቁጥጥር ስር ዋሉ
- የጋዛ ጊዜያዊ የተኩስ አቁም ስምምነት የዘገየው ከታጋቾች ዝርዝር ጋር በተያያዘ ነው ተባለ
- እስራኤል በጃባሊያ የስደተኞች መጠለያ በፈጸመችው ጥቃት የአንድ ቤተሰብ 52 አባላት ተገደሉ
ቀጥታ ዘገባ
- የታተመዉ 4:38 3 ታህሳስ 20234:38 3 ታህሳስ 2023የተኩስ አቁም ፋታው ካበቃ በኋላ ስለእስራኤል እና ሐማስ ጦርነት የምናውቀው ምንድን ነው?
AFPCopyright: AFPበጥቃቱ ከፈራረሱት ሕንጻዎች በቅርብ ርቀት ላይ ተቀምጠው ከቤታቸው የተረፈውን የሚያዩ ነዋሪዎችImage caption: በጥቃቱ ከፈራረሱት ሕንጻዎች በቅርብ ርቀት ላይ ተቀምጠው ከቤታቸው የተረፈውን የሚያዩ ነዋሪዎች
- ለአንድ ሳምንት የዘለቀው የተኩስ አቁም ፋታ ስምምነት ዐርብ ዕለት ከተጠናቀቀ በኋላ እስራኤልበጋዛ ላይ የማያባራ የአየር ጥቃት እየፈጸመች ትገኛለች።
- እስራኤል ጦርነቱ ከጀመረ አንስቶ የከፋ የአየር ጥቃት በደቡባዊ ጋዛ ከተማ ኻን ዩኒስ ላይ መፈፀሟን ነዋሪዎች ተናግረዋል።
- ከኻን ዩኒስ ከተማ ምሥራቃዊ አካባቢ የሚኖሩ ነዋሪዎችም ወደ ደቡብ እንዲሄዱ ቀደም ብሎ በእስራኤል ጦር ተነግሯቸዋል።
- የተኩስ አቁም ፋታው ዐርብ እለት ካበቃ በኋላ የእስራኤል ጦር ከ400 በላይ የሐማስ ኢላማዎችን መትቻለሁ ብሏል።
- በጋዛ በሐማስ የሚተዳደረው ጤና ሚኒስቴር እስራኤል አዲስ እየፈፀመች ባለችው ጥቃት ወደ 200 የሚጠጉ ሰዎች መገደላቸውን ገልጿል።
- ሚኒስቴሩ ጦርነቱ ከጀመረ አንስቶ በጋዛ የተገደሉ ሰዎች ቁጥር ከ15 ሺህ 200 በላይ መድረሱን አስታውቆ፣ከእነዚህም ውስጥ 6 ሺህ ያህሉ ሕጻናት ናቸው ብሏል።
- የተኩስ አቁም ፋታውን ለማስቀጠል በኳታር ሲካሄድ የነበረው ድርድር አልተሳካም።እስራኤልም ተደራዳሪዎቿ ዶሃን ለቀው እንዲወጡ ትዕዛዝ ሰጥታለች።
- እንደ ፍልስጤም ቀይ ጨረቃ ከሆነ ወደ 100 የሚደርሱ ሰብዓዊ እርዳታ የጫኑ ተሽከርካሪዎች በግብፅ በኩል ወደ ጋዛ ገብተዋል።
- ሆኖም የእርዳታ ድርጅቶች የገባው እርዳታ በቂ አለመሆኑን ገልጸው፣እስራኤል በሙሉ ከበባ ውስጥ ባስገባቻት ጋዛ ያለው የሰብዓዊ ሁኔታ አሳሳቢ እንደሆነ አስጠንቅቀዋል።
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- የታተመዉ 4:27 3 ታህሳስ 20234:27 3 ታህሳስ 2023ካማላ ሐሪስ እስራኤል ዓለም አቀፍ እና ሰብዓዊ ሕጎችን ማክበር አለባት አሉ
ReutersCopyright: Reutersየአሜሪካ ምክትል ፕሬዚደንት ካማላ ሐሪስ እስራኤል ዓለም አቀፍ እና የሰብዓዊ መብት ሕጎችን ልታከብር ይገባል አሉ።ምክትል ፕሬዚደንቷ አገራቸው ፍልስጤማውያን በአስገዳጅ መፈናቀላቸውን እንደማትፈቅድም ተናግረዋል።ካማላ ሐሪስ ይህን ያሉት በኮፕ28 የአየር ንብረት ጉባኤ ወቅት ከግብጹ ፕሬዚደንት አብደል ፈታህ አል ሲሲ ጋር ባደረጉት ውይይት ወቅት ነው።ምክትል ፕሬዚደንቷ ይህን ከተናገሩ ከሰዓታት በኋላም እስራኤል ከሐማስ እራሷን የመከላከል መብት አላት፤ ነገርግን ዓለም አቀፍ እና ሰብዓዊ ሕጎችን ማክበር አለባት ሲሉ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል።ሐሪስ በርካታ ፍልስጤማውያን ተገድለዋል ሲሉም እስራኤል ሰላማዊ ሰዎችን ለመጠበቅ ብዙ ማድረግ አለባት ብለዋል።“ሁላችንም ይህ ጦርነት በተቻለ ፍጥነት እንዲቆምና የእስራኤል እና የፍልስጤማውያን ደኅንነት መጠበቁን ማረጋገጥ እንፈልጋለን፤ በመሆኑም ዘላቂ ሰላምን ለመፍጠር ጥረቶቻችንን ማፍጠን አለብን” ብለዋል።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 7:38 2 ታህሳስ 20237:38 2 ታህሳስ 2023ተኩስ አቁሙ ካበቃበት ከአርብ ጀምሮ በጋዛ 193 ሰዎች ተገድለዋል፡ የጤና ሚኒስቴር
Getty ImagesCopyright: Getty Imagesሐዘንተኞች በጋዛ ናስር ሆስፒታልImage caption: ሐዘንተኞች በጋዛ ናስር ሆስፒታልለአንድ ሳምንት ያህል የቆየው የእስራኤል እና የሐማስ ጊዜያዊ ተኩስ አቁም አብቅቶ እስራኤል በጋዛ ላይ ጥቃት ከጀመረችበት ከትናንት አርብ አንስቶ ወደ 200 የሚጠጉ ሰዎች መገደላቸው ተነገረ።በሐማስ የሚመራው የጋዛ ሰርጥ ጤና ሚስኒቴር ዛሬ ቅዳሜ ከሰዓት በኋላ እንዳስታወቀው፣ ከአርብ ጀምሮ እስራኤል እያካሄደችው ባለው ጥቃት 193 ሰዎች ተገድለዋል።ለሰባት ቀናት የዘለቀው ጊዜያዊ ተኩስ አቁም ካበቃ በኋላ እስራኤል በጀመረችው ጥቃት ከተገደሉት ፍልስጤማውያን በተጨማሪም 652 ሰዎች የመቁሰል ጉዳት እንደደረሰባቸው ሚኒስቴሩ አሳውቋል።ከመስከረም 26ቱ የሐማስ ጥቃት በኋላ እስራኤል በጋዛ ሰርጥ በከፈተችው ጥቃት የተገደሉ ሰዎች አጠቃላይ ቁጥር ደግሞ ከ15,000 ማለፉን እንዲሁም ከ40,000 በላይ ሰዎች እንደቆሰሉ ሚኒስቴሩ አመልክቷል።አክሎም በጥቃቱ ሰለባ ከሆኑት መካከል 70 በመቶ የሚሆኑት ሴቶች እና ሕጻናት መሆናቸውም ተገልጿል።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 5:57 2 ታህሳስ 20235:57 2 ታህሳስ 2023ከሁለት ወር ባነሰ ጊዜ 100 ሺህ ሕንፃዎች የወደሙባት የፍርስራሽ ክምሯ ጋዛ በሳተላይት ዕይታበእስራኤል እና በሐማስ መካከል የተደረሰው የተኩስ አቁም ፋታ ከመጀመሩ በፊት ቢቢሲ ያገኛቸው አዳዲስ የሳተላይት ምስሎች በሰሜን ጋዛ የደረሰውን ከፍተኛ የውድመት መጠን የሚያሳዩ ናቸው።ተጨማሪ ያንብቡArticle share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 4:33 2 ታህሳስ 20234:33 2 ታህሳስ 2023ተመድ በሐማስ ተፈጽመዋል የተባሉ ፆታዊ ጥቃቶች አሳሳቢ ናቸው አለ
UN WomenCopyright: UN Womenየተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሴቶች ጉዳይ ተቋም መስከረም 26/2016 ዓ.ም. በሐማስ ጥቃት ወቅት ተፈጽመዋል የተባሉ ፆታን መሠረት ያደረጉ ጥቃቶች አሳሳቢ ናቸው አለ።ሐማስ ጥቃቱን ሲያደርስ በእስራኤል ማኅብረሰብ አባላት ላይ ተፈጽመዋል የተባሉ ፆታን መሠረት ያደረጉ ጥቃቶች ምርመራ እንዲደረግባቸው እና ጥፋተኞች በሕግ እንዲጠየቁ ተቋሙ ጠይቋል።ሐማስ ተዋጊዎቹ ጾታን መሠረት ያደረጉ ጥቃቶችን አልፈጸሙም በማለት ሲያስተባብል ቆይቷል።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 4:31 2 ታህሳስ 20234:31 2 ታህሳስ 2023በምሥል፡ ከተኩስ አቁም ፋታ በኋላ በቀጠለው ጦርነት በጋዛ የደረሰ ውድመት
ReutersCopyright: Reutersየተኩስ አቁም ፋታ ካበቃ በኋላ እስራኤል ድብደባዋን ቀጥላበታለች።የአገሪቱ ጦር እስካሁን ከ400 ያላሱ የሐማስ መገኛዎችን መትቻለሁ ብሏል።በጥቃቱ ቤተሰቦቻቸውን እና ንብረታቸውን ያጡ ፍልስጤማውያን ሲያነቡ ተይተዋል።በሁለተኛው ዙር ጥቃት በእስራኤል ዒላማ ውስጥ የገባው እና ከባድ ጉዳት የደረሰበት በደቡብ ጋዛ የሚገኘው ኻን ዩኒስ ነው።
Getty ImagesCopyright: Getty Imagesከፍርስራሽ ስር የሟቾችን አስክሬን ለማውጣት የሚጣጣሩ ፍልስጤማውያንImage caption: ከፍርስራሽ ስር የሟቾችን አስክሬን ለማውጣት የሚጣጣሩ ፍልስጤማውያን
Getty ImagesCopyright: Getty Imagesበደቡባዊ ጋዛ በአየር ጥቃት የተገደሉ ሰዎች አስክሬን ሲወጣ የቤተሰብ አባላት ሲያለቅሱImage caption: በደቡባዊ ጋዛ በአየር ጥቃት የተገደሉ ሰዎች አስክሬን ሲወጣ የቤተሰብ አባላት ሲያለቅሱArticle share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 3:57 2 ታህሳስ 20233:57 2 ታህሳስ 2023የእስራኤል ጦር ጋዛ ውስጥ ከ400 በላይ ዒላማዎችን መምታቱን ገለጸ
Getty ImagesCopyright: Getty Imagesለቀናት የቆየው ጊዜያዊ የተኩስ አቁም ትናንት አርብ አብቅቶ እስራኤል ማለዳ በጋዛ ላይ ጥቃቷን መልሳ ከጀመረች በኋላ እስከ ዛሬ ቅዳሜ ጠዋት ድረስ ከ400 በላይ ዒላማዎችን ማጥቃቷን ጦር ሠራዊቷ አስታወቀ።የእስራኤል መከላከያ ኃይል (አይዲኤፍ) እንዳለው የአገሪቱ የአየር፣ የባሕር እና የምድር ኃይል ደቡባዊ የጋዛ ሰርጥን ጨምሮ መላዋን ጋዛን ዒላማ ያደረጉ ጥቃቶችን መፈጸማቸውን አመልክቷል።ጨምሮም “ተዋጊ ጄቶች በኻን ዩኒስ አካባቢ ባሉ ከ50 በሚልቁ ዒላማዎች ላይ መጠነ ሰፊ ጥቃት ፈጽመዋል” ብሏል።ጦር ኃይሉ የፍልስጤማ እስላማዊ ጂሃድ የተባለው ቡድን እንደ ማዘዣ ማዕከል ይጠቀምበታል ያለውን በሰሜናዊ ጋዛ የሚገኝ አንድ መስጂድን በአየር ጥቃት መምታቱን ገልጿል። ቢቢሲ ይህንን የእስራኤል ሠራዊት ክስ ከገለልተኛ ወገን ማረጋገጥ አልቻለም።እስራኤል የሰሜናዊ ጋዛ ነዋሪዎች አካባቢያቸውን ለቀው ወደ ደቡብ እንዲሄዱ ካዘዘች በኋላ፣ በመቶ ሺዎቸ የሚቆጠሩ የጋዛ ነዋሪዎች በደቡባዊ የሰረጡ ክፍል ውስጥ በምትገኘው የኻን ዩኒስ ከተማ በአብዛኛው በጊዜያዊ የድንኳን መጠለያ ውስጥ ይገኛሉ።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 3:54 2 ታህሳስ 20233:54 2 ታህሳስ 2023አንድ ግለሰብ አሜሪካ ውስጥ በሚገኝ የእስራኤል ቆንስላ በር ላይ እራሱን በእሳት አቃጠለበአሜሪካዋ ጆርጂያ ግዛት አትላንታ ከተማ ውስጥ ከሚገኝ የእሰራኤል ቆንስላ ጽህፈት ቤት በር ላይ ተቃውሞውን ለመግለጽ እራሱን በእሳት በማቃጠሉ ከባድ ጉዳት እንደደረሰበት ፖሊስ አስታወቀ።ተጨማሪ ያንብቡArticle share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 8:41 1 ታህሳስ 20238:41 1 ታህሳስ 2023ኳታር ለግጭቱ ዳግም ፋታ ለመስጠጥ ንግግር እየተካሄደ ነው አለች
ReutersCopyright: Reutersለ7 ቀናት ጋብ ብሎ የነበረው ግጭት ዳግም ተጀምሯል።Image caption: ለ7 ቀናት ጋብ ብሎ የነበረው ግጭት ዳግም ተጀምሯል።የኳታር መንግሥት እስራኤል እና ሐማስ ዳግም ለጦርነቱ ፋታ ለመስጠት ድርድር እያደረጉ እንደሆነ ገለጸ።የኳታር መንግሥት ሁለቱን ኃይሎች አደራድሮ ባለፉት 7 ቀናት ጦርነቱ ጋብ ብሎ የእስረኞች እና የታጋቾች ልውውጥ ከመደረጉ በተጨማሪ ሰብዓዊ እርዳታ ጋዛ ሲደርስ ነበር።ይሁን እንጂ ሐማስ እና እስራኤል የደረሱት ስምምነት በማብቃቱ ከዛሬ ማለዳ ጀምሮ ሁለቱ ኃይሎች ዳግም ወደ ጦርነት ተመልሰዋል።የኳታር የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እስራኤል ዳግም በጋዛ ሰርጥ ወታደራዊ ዘመቻ መጀመሯ አሳዛኝ ነው ብሏል።ይሁን እንጂ የኳታር መንግሥት ከሌሎች አጋሮች ጋር በመሆን “ለሰብዓዊነት ሲባል ግጭት እንዲቆም ስምምነት እንዲደረስ” ጥረት ማድረጉን እንደሚቀጥል አስታውቋል።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 8:37 1 ታህሳስ 20238:37 1 ታህሳስ 2023የተመድ ዋና ፀሐፊ ግጭት መጀመሩ “እጅግ አሳዛኝ ነው” አሉ
Getty ImagesCopyright: Getty Imagesአንቶኒዮ ገተሬዝImage caption: አንቶኒዮ ገተሬዝየተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ በጋዛ ግጭት መጀመሩ “በጣም አሳዛኝ ነው” አሉ።ዋና ፀሐፊው በማኅበራዊ ገጻቸው በኩል ባሰፈሩት መልዕክtእ ባለፉት ቀናት ተግባራዊ ተደርጎ የነበረው ስምምነትን ማስቀጠል ይቻላል የሚል ተስፋ እነeዳላቸው ገልጸዋል።ባለፉት ሰባት ቀናት እስራኤል እና ሐማስ ለጦርነቱ ፋታ ለመስጠት ተስማምተው ታጋቾች እና እስረኞችን ሲለዋወጡ ቆይተዋል።ከመስከረም 26ቱ ድንገተኛ ጥቃት በኋላ በጋዛ ሰርጥ 6ሺህ ሕጻናትን ጨምሮ 14ሺህ 800 ሰዎች መገደላቸውን በሐማስ የሚተዳደረው ጤና ሚንስቴር አስታውቋል።በእስራኤል ደግሞ ከ1200 የማያንሱ ሰዎች ተገድለዋል።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 8:35 1 ታህሳስ 20238:35 1 ታህሳስ 2023በምስል፡ ሮኬቶች እና የአየር ጥቃቶችከሰባት ቀናት የጦርነት ፋታ በኋላ የእስራኤል እና ሐማስ ውጊያ ተጀምሯል።ከዛሬ አርብ ንጋት ጀምሮ ሮኬቶች ከጋዛ እና ወደ ጋዛ ሲወነጨፉ ታይተዋል።የእስራኤል ጦር “ዘመቻ ጀምሬያለሁ” ያለ ሲሆን በጋዛ ሰርጥ የአየር ድብደባዎችን እያደረገ ይገኛል።
ReutersCopyright: Reutersዛሬ ረፋድ በጋዛ ሰማይ ላይ ትልቅ ጭስ ታይቷልImage caption: ዛሬ ረፋድ በጋዛ ሰማይ ላይ ትልቅ ጭስ ታይቷል
ReutersCopyright: Reutersበደቡባዊ ጋዛ የወደመ መኖሪያ ቤትImage caption: በደቡባዊ ጋዛ የወደመ መኖሪያ ቤት
ReutersCopyright: Reutersጦርነት ዳግም መቀስቀሱን ተከትሎ ፍልስጤማውያን መኖሪያቸውን ጥለው ለመሸሽ ተገደዋልImage caption: ጦርነት ዳግም መቀስቀሱን ተከትሎ ፍልስጤማውያን መኖሪያቸውን ጥለው ለመሸሽ ተገደዋል
ReutersCopyright: Reutersሮኬቶች ከጋዛ ሰርጥ ወደ እስራኤል ሲወነጨፉ ታይተዋልImage caption: ሮኬቶች ከጋዛ ሰርጥ ወደ እስራኤል ሲወነጨፉ ታይተዋልArticle share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 3:54 1 ታህሳስ 20233:54 1 ታህሳስ 2023እስራኤል በ3 ሰዓታት ውስጥ በፈጸመቻቸው የአየር ጥቃት 32 ፍልስጤማውያን መገደላቸው ተገለጸ
Getty ImagesCopyright: Getty Imagesእስራኤል የተኩስ አቁም ፋታው ማብቃቱን ተከትሎ ባሉ ሶስት ሰዓታት በፈጸመቻቸው የአየር ጥቃቶች 32 ፍልስጤማውያን መገደላቸውን የጋዛ የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።በሐማስ አስተዳደር ስር የሚገኘው የጤና ሚኒስቴር እስራኤል በበርካታ የጋዛ ስፍራዎች የአየር ጥቃት እየፈጸመች ነው ብሏል።ለሰባት ቀናት የዘለቀውን የተኩስ አቁም ፋታ ተከትሎ የተከተለው ጥቃትም አስደንጋጭ ነው ተብሏል።የተባበሩት መንግሥታት የህጻናት መርጃ ድርጅት፣ ዩኒሴፍ ለቢቢሲ እንደተናገረው በደቡባዊ ጋዛ ያለው ሁኔታ “አስፈሪ ነው” ብለዋል።”ያለው ሁኔታ ለነዋሪዎች አሰቃቂ ነው። በፊታቸው ላይም ፍርሃት ይነበባል” ሲሉ የዩኒሴፍ ባልደረባ ጄምስ ኤልደር ለቢቢሲ ተናግረዋል።በአሁኑ ወቀድት በደቡባዊ ጋዛ በሚገኝ ሆስፒታል ውስጥ እንደሚገኙ የተናገሩት ጄምስ ከተቋሙ በ50-100 ሜትር ርቀትም ላይ የአየር ጥቃት ተፈጽሟል ብለዋል።የተኩስ አቁም ፋታው ማብቃቱንም “ሁሉም ሰው የሚፈራው ቅዠት” ደርሷል ሲሉ ገልጸው ሰብዓዊ ቀውሱም ለበርካቶች ሞት እንደሚሆንም አስጠንቅቀዋል።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 2:48 1 ታህሳስ 20232:48 1 ታህሳስ 2023ሐማስ እና እስራኤል የተኩስ አቁም ፋታ ስምምነቱን በመጣስ እየተወነጃጀሉ ነው
Getty ImagesCopyright: Getty Imagesሐማስ እና እስራኤል ለሰባት ቀናት የቆየው የተኩስ አቁም ፋታ ስምምነትን በመጣስ እየተወነጃጀሉ ነው።ሐማስ የስምምነቱ አካል የሆነው በሰሜናዊ ጋዛ ሰርጥ ነዳጅ እንዲገባ መፈቀድ ቢኖርበትም እስራኤል በመከልከሏ ስምምነቱን ጥሳለች እንዳለ ለድርድሩ ቅርብ የሆኑ ምንጭ ለቢቢሲ ተናግረዋል።እስራኤል በበኩሏ ሐማስ ተጨማሪ ታጋቾችን ለመልቀቅ ፈቃደኛ ባለመሆኑ ስምምነቱ ተጥሷል ብላለች።ለድርድሩ ቅርብ የሆኑት እኚሁ ምንጭ በበኩላቸው ሐማስ በጋዛ የተወሰዱ ወንዶች ታጋቾችን፤ ሴቶችን እና ህጻናቶችን በለቀቀው መልኩ ለመልቀቅ ፈቃደኛ አይደለም ብለዋል።የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ በበኩላቸው በስምምነቱ መሰረት ሐማስ ሁሉንም ሴቶች ታጋቾች እንዳልለቀቀ እና በእስራኤልም ላይ ሮኬት አስወንጭፏል ብለዋል።” እስራኤል ታጋቾችን ለማስለቀቅ፣ ሐማስን ለማጥፋት እና ጋዛ በእስራኤል ነዋሪዎች ላይ ስጋት እንዳትፈጥር የጀመረችውንም ወታደራዊ ዘመቻ ከግብ ለማድረስ ትቀጥላለች” ብለዋል።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 1:52 1 ታህሳስ 20231:52 1 ታህሳስ 2023እስራኤል በራፋህ በፈጸመችው የአየር ጥቃት ስድስት ፍልስጤማውያን ተገደሉለሰባት ቀናት የዘለቀው የተኩስ አቁም ፋታ ማብቃቱን ያወጀው የእስራኤል ጦር በደቡባዊ ጋዛ ራፋህ ከተማ በፈጸመው የአየር ጥቃት ስድስት ፍልስጤማውያን ተገደሉ።ጥቃቱ ዛሬ ማለዳ መፈጸሙንም በሐማስ አስተዳደር ስር የሚገኘው የጤና ሚኒስቴር ቃለ አቀባይ ለአጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ተናግረዋል።የተኩስ አቁም ፋታው ዛሬ ማለዳ ያቆመ ሲሆን እስራኤልም ሐማስ ሮኬት አስወንጭፏል በማለት ስምምነቱን ጥሷል ስትል ከሳለች።ከዚህ በተጨማሪም እስራኤል በሰሜን ጋዛ በፈጸመችው የአየር ጥቃት ሁለት ልጆች መገደላቸውን ኤኤፍፒ በአል አህሊ ሆስፒታል የህክምና ባለሙያ የሆኑትን ዶክተር ፋዴል ናይምን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል።በርካታ የጋዛ ሰርጥ አካባቢዎችም በእስራኤል የአየር ጥቃት እንደተፈጸመባቸው የጋዛ የሃገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።በኳታር አሸማጋይነት የተደረሰውን የተኩስ አቁም ፋታ ተከትሎ ሐማስ 110 ታጋቾችን ሲለቅ እስራኤል ደግሞ 240 ህጻናት እና ሴቶች ፍልስጤማውያን እስረኞችን ፈታለች።ጦርነቱ ዳግም መጀመር በከበባ ውስጥ ባለች የጋዛ ሰርጥ የከፋ ስብዓዊ ቀውስ ያስከትላልም ተብሏል።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 1:15 1 ታህሳስ 20231:15 1 ታህሳስ 2023የጋዛ የተኩስ አቁም ፋታ ማብቃቱን እና ጦርነት መቀጠሉን እስራኤል አስታወቀች
ReutersCopyright: Reutersለሰባት ቀናት የዘለቀው የጋዛ የተኩስ አቁም ፋታ ማብቃቱን እና ጦርነት መቀጠሉን እስራኤል አስታወቀች።የእስራኤል ጦር ሐማስ ስምምነቱን ጥሷል ሲል ከሷል። “ሐማስ ሰብዓዊ የተኩስ አቁም ፋታውን በመጣስ ሮኬት ወደ እስራኤል አስወንጭፏል።የእስራኤል መከላከያ ኃይል በጋዛ ሰርጥ ከሐማስ ጋር የሚያደርገውን ጦርነት ቀጥሏል” ሲልም የእስራኤል መከላከያ መግለጫ አውጥቷል። እስራኤል ይህንን ማወጇን ተከትሎ እስራኤል በጋዛ ሰርጥ የአየር ጥቃቶች እየፈጸመች ስለመሆኑ ሪፖርቶች ወጥተዋል።የእስራኤል መከላከያ በበኩሉ ” የሐማስ ኢላማዎችን እያጠቃሁ” ነው ብሏል። በኳታር አሸማጋይነት የተደረሰውን የተኩስ አቁም ፋታ ተከትሎ ሐማስ 110 ታጋቾችን ሲለቅ እስራኤል ደግሞ 240 ህጻናት እና ሴቶች ፍልስጤማውያን እስረኞችን ፈታለች።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 1:14 1 ታህሳስ 20231:14 1 ታህሳስ 2023ብሊንከን ከእስካሁኑ ጠንከር ባለ መልዕክታቸው እስራኤል ሲቪሎችን እንድትታደግ ጠየቁየአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን እስራኤል በጋዛ ከሐማስ ጋር በምታደርገው ጦርነት ለሲቪሎች ጥበቃ የምታደርግበትን መለኪያዎችን በግልጽ አስቀምጠዋል። ከእስካሁኑ በጣም ጠንካራ በተባለው የአሜሪካ አስተያየት፤ የእስራኤል መንግሥት ተጨማሪ ፍልስጤማውያንን ማፈናቀል እንዲያቆም፣ እንደ ሆስፒታሎች፣ የኃይል አቅርቦትን ጨምሮ እና የውሃ ተቋማት ባሉ ወሳኝ መሠረተ ልማቶች ላይ ጉዳት እንዳያደርስ ብሊንከን መናገራቸው ታውቋል።ተጨማሪ ያንብቡArticle share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 5:05 30 ህዳር 20235:05 30 ህዳር 2023ሩስያ ታጋቾችን በመልቀቁ ሐማስን አመሰገነች
AFPCopyright: AFPሐማስ ሁለት ሩሲያዊ ታጋቾችን በትናንትናው ዕለት መልቀቁን ተከትሎ የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ምስጋናውን ለሐማስ አቅርቧል።ሩሲያ እንዳሳወቀችው ታጋቾቹ የተለቀቁት በእስራኤል እና ሐማስ ከተደረገው ስምምነት ጋር የተያያዘ አይደለም ብላለች።”ወገኖቻችን በትናንትናው ዕለት የተለቀቁት ከሐማስ አመራሮች ጋር ባደረግነው ስምምነት መስረት” ነው ብሏል።”ለጥያቄቻችን አዎንታዊ ምላሽ ለሰጡን የሐማስ አመራሮች ምስጋናችንን እናቀርባለን። በጋዛ ሰርጥ የተያዙ ሌሎች ሩሲያውያን እንዲለቀቁም ጥረታችንን እንቀጥላለን” በማለት ባወጣው መግለጫ አትቷል።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 3:55 30 ህዳር 20233:55 30 ህዳር 2023በእየሩሳሌም በተከፈተ ተኩስ ሶስት ሰዎች ተገደሉ
Getty ImagesCopyright: Getty Imagesበእየሩሳሌም የአውቶብስ ጣቢያ በተከፈተ ተኩስ ሶስት ሰዎች ተገደሉ።ተኩሱ የተከፈተበት የስራ ሰዓት መግቢያ ላይ እንደሆነም ተነግሯል።ፖሊስ እንዳስታወቀው ማለዳ በስራ ሰዓት መግቢያ እና ሰዎች በሚበዙበት ወቅት ሁለት ታጣቂዎች ከእየሩሳሌም ወጣ ብሎ በሚገኘው የአውቶብስ ጣቢያ ላይ ተኩስ ከፍተዋል ብሏል።ፖሊስ ሪፖርቱ የደረሰው በአገሬው ሰዓት አቆጣጠር ከጥዋቱ 1 ሰዓት ከ40 መሆኑን አስታውቋል። በተኩሱም የ24 ዓመት ሴትን ጨምሮ ሶስት ሰዎች ሲገደሉ ስድስት ሰዎች ቆስለዋል።የእስራኤል ብሄራዊ ደህንነት ሚኒስትር ኢታማር ቤን ግቪር እንደተናገሩት ተኩሱን የከፈቱት ሁለት ግለሰቦች የሐማስ አባላት ናቸው ብለዋል።ግለሰቦቹም በምስራቅ እየሩሳሌም ነዋሪዎች መሆናቸውንም አክለዋል። “በግልጽ ሐማስ የፈጸማቸው ናቸው። በአንደኛው በኩል የተኩስ አቁም ይላሉ በሌላኛው የሽብር ተግባር ይፈጽማሉ” ሲሉ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል።የደረሰው ጥቃት በእስራኤል ውስጥ ላሉ ሰላማዊ ዜጎች የጦር መሳሪያ ማከፋፈል አስፈላጊነትን የሚያሳይ ነው ብለዋል።Article share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 0:53 30 ህዳር 20230:53 30 ህዳር 2023እስራኤል በዌስት ባንክ ባደረሰችው ጥቃት ሁለት ፍልስጤማውያን ልጆች ተገደሉእስራኤል በኃይል በያዘቻት ዌስት ባንክ የእስራኤል ወታደሮች በፈጸሙት ጥቃት ሁለት ህጻናትን ጨምሮ አራት ፍልስጤማውያን መገደላቸውን የፍልስጤም ባለስልጣናት ተናገሩ። የደህንነት ካሜራ ቪዲዮዎች የስምንት ዓመቱ አደም አል-ጉል እና የ14 ዓመቱ ባዝል አቡ አል-ዋፋ በጄኒን ከተማ በተመሳሳይ ሁኔታ በጥይት ሲመቱ አሳይተዋል።ተጨማሪ ያንብቡArticle share tools
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- ይህንን ማስፈንጠሪያ ይውሰዱ
- ያጋሩView more share optionsይህንን ለሰው አጋራ
- የታተመዉ 0:14 30 ህዳር 20230:14 30 ህዳር 2023የጋዛ የተኩስ አቁም ፋታ እንደሚቀጥል የእስራኤል ጦር አስታወቀ
ReutersCopyright: Reutersስድስተኛ ቀኑን የያዘው የተኩስ አቁም ፋታ እንደሚቀጥል የእስራኤል ጦር አስታውቋል።ሐማስ በበኩሉ የተኩስ አቁም ፋታው ለአንድ ቀን እንደተራዘመ አስታውቋል።ሐማስ ለሰባተኛ ቀን የተኩስ አቁም ፋታውን ለማራዘም ስምምነት ላይ መደረሱንም ሮይተርስ የዜና ወኪል ዘግቧል።የእስራኤል ጦር የተራዘመው የተኩስ አቁም ፋታ ለምን ያህል ጊዜ እንደሚቆይ አልገለጸም።ዛሬ ይጠናቀቃል የተባለው የተኩስ አቁም ፋታ ‘ ተጨማሪ ታጋቾችን የማስለቀቁን ሂደትም ለማስቀጠል አሸማጋዮቹ ካደረጉት ጥረት ጋር ተያይዞም ይቀጥላል” ተብሏል።በስምምነቱ መሰረት ሐማስ የወሰዳቸውን ታጋቾች የሚለቅ ሲሆን በልውውጡም እስራኤል የያዘቻቸውን ህጻናት እና ሴቶች ፍልስጤማዊ እስረኞችን ትፈታለች።