
የአማራ ሕዝብ እያነቁት ያሉትን እነ ሽመልስን እያመሰገነ የሕልውና ትግሉን አጠናክሮ መቀጠል አለበት ።
አቶ ሽመልስ አብዲሳ ማክሰኞ አዳማ በነበረው የምክክር ጉባዬ ለኦሮሞ ምሁራን ያስተላለፈው መልዕክት በአማራ ሕዝብ ላይ ቀጥታ ጂኖሳይድ አውጇል። ይህ ግለሰብ በአማራ ሕዝብ ላይ ጂኖሳይድ ሲያውጅ የመጀመሪያው ባይሆንም የኦሕዴድ አገዛዝ በአማራ ሕዝብ ላይ ያለውን አቋም እና ወደፊት ያቀደውን ያሳያል። ሕወሓት አማራውን በወረርሽኝ እና በክትባት ለማጥፋት ብዙ ሰርቶ አልተሳካለትም።
የአማራ ክልል አመራሮች ይህንን እየሰሙና እያዩ ለአማራ ሕዝብ ከመቆርቆር ይልቅ የገዢው አጋር በመሆን አማራውን እያስደፈሩት ይገኛሉ። ይህ አደገኛ አካሄድ ለማስቆም ከደመቀ መኮንን ጀምሮ እስከ ታች አመራሮች ድረስ አንዳችም ስራ ሲሰሩ አልታየም። ለአማራ ቆመናል ብለው በአማራው ላይ የቆሙ ስለሆን ሕዝቡ ለነፃነቱ እና ለመብቱ ለሕልውናው ማድረግ የጀመረውን ትግል አጠናክሮ መቀጠል አለበት፤ አማራው እንዲታገል የሚያደርጉትን እንደ ሽመልስ አብዲሳ ያሉትን ሰዎች እያመሰገነ ለሕልውናው ትግል ካለመታከት ሊሰራ ይገባዋል።
ይህንን ከታች ያለውን በጥሞና ያዳምጡት
