December 5, 2023 – Konjit Sitotaw
የኢትዮጵያ ፕ*ሮ*ቴ*ስ*ታን*ቲዝም፦ ከተቅለስላሸነት ወደ ተናካሽነት
++++
(ቀሲስ ኤፍሬም እሸቴ)
U/ ዘመነ ተቅለስላሸነት ….
በቀድሞው ዘመን የነበረው የሀገራችን ፕ*ሮ*ቴ*ስ*ታን*ቲዝም ተቅለስላሽ እና አንገት ደፊ ነበር። ግራህን ቢመቱህ ቀኝህን ስጠው የሚል፣ ቢያንስ ቀርበው የማያውቁትን ሰዎች ለማሳሳት አቅም የነበረው ነበር። አንዳንድ ወላጆች ልጆቻቸው “ሲበላሹ” ወይ ጴ*ጤ በሆነና ከዚህ መጥፎ ተግባሩ በተመለሰ እስከማለት ይደርሱ ነበር።
ያ የድሮው *ንጤ ከመጠጥ የተጣላ፣ ከኃጢአት የራቀ የሚመስል የቀበሮ ባህታዊ ነበር። በውስጥ የሚያደርገውን፣ የልቡን ሸፍጠኝነት ለተረዳ ግን ከፈሪሳዊ በላይ ፈሪሳዊ መሆኑን ይገነዘባል፡፡
ያ የድሮው *ንጤ ቢያንስ መጽሐፍ እየጠቀሰ ሊከራክርህ ይሞክራል። በርግጥ የሚናገረውን ተናግሮ መልስ መስጠት ስትጀምር አይሰማህም። ቀጥሎ ስለሚናገረው ነው የሚያስበው። አንዳንዴ ሕሊናውን አንዳች ሌላ ኃይል ሲዘጋው ይታይሃል:: ይናገራል እንጂ አይሰማም። ከድሮው *ንጤ ጋራ የምንከራከረው እሱን ለማሳመን ሳይሆን ትምህርቱ የተሳሳተ መሆኑን ለሌሎች ቀራቢዎቹ ለማሳየትና ራሳቸውን እንዲጠብቁ ለማድረግ ነበር። ጌታ በማርቆስ ወንጌል ምዕራፍ 9 ቁጥር 29 ላይ እንዳለው ያንን የድሮውን *ንጤ የተጠናወተው ጸላዒ “በጸሎትና በጦም ካልሆነ በምንም ሊወጣ አይችልም” የተባለው ዓይነት ነው።
እውነቱን ለመናገር ያንን የድሮ *ንጤ ትምህርቱን ለማምከን ተችሎ ነበር። በእግዚአብሔር ቸርነት። ያቺ ይዟት የመጣትን የጥቅስ ዝናር አራግሮ መከራከሪያ እስኪያጣ ድረስ ጭራውን ቆልሮ ተመልሶ ነበር። ኋላ ግን የኛኑ ሰዎች እኛው መካከል አመሳስሎ በመላክ (ተሐድሶነት) ጥሩ ውጤት አግኝቷል። ብዙዎችን ከተቀደሰ መንገዳቸው ማስወጣትም ችሏል። ያ ቅልስልስነቱ ግእዝ በሚጠቅሱ ሰዎች ተለውጦ ብዙዎችን ለማታለል ሞክሯል። ያም ቢሆን ግን እግር በእግር እየተከታተሉ መልስ በሚሰጡት መምህራን ጥረት አደብ መግዛት ችሏል።
ለ/ ከተቅለስላሽነት ወደ ተናካሽነት
++++
ባለፉት 10+ ዓመታት የሀገራችን ፕ*ሮ*ቴ*ስ*ታን*ቲዝም ከተቅለስላሽነት ወደ ተናካሽነት ተሸጋግሯል። ምክንያቱ ደግሞ በቁጥር ከሕዳጥነት ወደ ብዙኀነት በመሸጋገሩ አለመሆኑ የታወቀ ነገር ነው። በርግጥ በጥቂት ጊዜያት ከፍተኛ የሆነ ዕድገት በማሳየት ላይ ይገኛል። ዕድገት ማሳየቱ ግን ከተቅለስላሽነት ወደ ተናካሽነት ለመሸጋገሩ አንድ ምክንያት ቢሆን እንጂ ዋነኛው ምክንያቱ አይደለም። ዋነኛው ምክንያቱ የፖለቲካ ሥልጣንን ለመቆጣጠር መቻሉ ነው።
የኢትዮጵያ ፕ*ሮ*ቴ*ስ*ታን*ቲዝም ጠንካራ የፖለቲካ ርዕዮተ ዓለም የተጫነው ነው። በደቡብ እና በኦሮሚያ እንዲሁም በምዕራብ ኢትዮጵያ ፕ*ሮ*ቴ*ስ*ታን*ቲዝም የሕዝቡ ብቸኛ አማራጭ ተደርጎ ቀርቧል። ኦርቶዶክስን የመሳሰሉ እምነቶች የተወሰኑ ሕዝቦች ተደርገው በይፋ ይነገራሉ፡፡ መንግሥታዊ ቢሮክራሲው ለ*ንጤው ብቻ የተሰጠ እስኪመስል ድረስ ኦርቶዶክሱ ከመንግሥታዊ ኃላፊነቶች ተጠራርጎ ወጥቷል። የቀረውም ቢሆን በሥልጣን እርከን ላይ መውጣት ከፈለገ ኦርቶዶክስ እምነቱን መቀየር እንዳለበት የማያሻማ መልዕክት እንዲደርሰው ተደርጓል። ኦሮሚያን በመሳሰሉ ክልሎች የምናውቃቸው ብዙ ኦርቶዶክሳውያን በይፋ ማተባቸውን በጥሰው እምነታቸውን እየቀየሩ የፖለቲካ ማዕዱ ተሳታፊ ሆነዋል።
በዚህ ዓይን አውጣነት ፖለቲካውን መዘወር የቻለው የዘመናችን ፕ*ሮ*ቴ*ስ*ታን*ቲዝም አሁን ባንኩንም ታንኩንም ማዘዝ እንደቻለ አረጋግጧል:: ስለዚህ ከተቅለስላሸነቱ ወጥቶ ተናካሽ ሆኗል:: በቤተ እምነቱ አዳራሾች የሚሰጠው ትምህርት ዒላማው ኦርቶዶክስ ነው። የቴሌቪዥኑ ዝግጅት ዒላማ ኦርቶዶክስ ነው። የማኅበራዊ ሚዲያው ክርክር ዒላማ ኦርቶዶክስ ነው። የርሱ እምነት ትክክለኛነት ማሳያ የኦርቶዶክስን “ስሕተት” ማሳየት ነው። ግን ይህ አካሄድ ያዋጣዋል?
+++
ሐ/ ምሳሌዎች
ኮሜዲያን እሸቱ መለሰ ቤተ ክርስቲያን ለማሠራት ለ2 ሳምንታት ባደረገው የገንዘብ ማሰባሰቢያ ዝግጅት መጨረሻ ላይ ስለ በጎ ተግባሩ የቤተ ክርስቲያናችን ዘማርያን በመዝሙር ማመስገናቸውን ተከትሎ “ኦርቶዶክሶች ግለሰብ ያመልካሉ” የሚሉ ተናካሽ *ን*ጤ*ዎች ማኅበራዊ ሚዲያውን ሲያጥለቀልቁት ነገሩ ሌላ ሳይሆን የተናካሽነቱ አንዱ መገለጫ መሆኑ ገብቶኛል፡፡ ተቅለስላሹን የድሮ ጴ*ጤ ጥቅሱን በጥቅስ መመለስ ተችሏል፡፡ የአሁኑን ተናካሽ *ን*ጤ ግን በጥቅስ ብቻ መመለስ የሚቻል አይመስልም :: በሕግ አግባብ ሥርዓት ማስያዝ ይቻል ካልሆነ።
ነገር ግን ዳኛውም እርሱ፣ ፖሊሱም እርሱ፣ ሚኒስትሩም እርሱ ከሆነ በምን ሕግ ተው ይባላል? መቋሚያውን፣ ከበሮውን፣ ጸናጽሉን መቀለጃ ሲያደርገው፣ በቤተ ክርስቲያናችን መጻሕፍት ሲቀልድና ሲዘባበት፣ አንዳንድ ቦታዎች በጉልበት አማኞቻችንን ሲገዳደር ስትመለከት መፍትሔው ጥቅስ እንዳልሆነ ይገባሃል። (በነገራችን ላይ ላሊበላ የሰፈረው የመንግሥት ጦር ሕዝቡን “ድንጋይ ታመልካላችሁ” ይላቸው እንደነበር በአደባባይ ሚዲያ መዘገቡን እናስታውሳለን።)
የሀገራችን ተናካሽ ፕ*ሮ*ቴ*ስ*ታን*ቲዝም በራሱ መሪዎችና በጎ ሕሊና ባላቸው ብዙዎቹ አማኞቹ አማካይነት ቶሎ ይህንን ጦረኛ ጠባዩን መለወጥ ካልቻለ ሀገራችንን ወደ መካከለኛው ዘመን የአውሮፓ የእምነት ግጭት ታሪክ ይቀይራታል ብዬ እፈራለሁ። አውሮፓ በካቶሊኮችና ፕሮ*ቴስታ*ንቶች ጦርነት ብዙ ጉዳት ማስተናገዱን ታሪክ ይነግረናል። ይሰውረን።
