December 5, 2023 – Konjit Sitotaw

የአዲስ አበባ ስታዲዮም ሱቆች በቀጀላ መርዳሳ ውሳኔ ለባለጊዜዎች ሊታደል ሲሆን ፤ ነባር ተከራዮች እንዲባረሩ ተደርጓል። በአዲስ አበባ ስታዲዮም ዙሪያ ባለጊዜዎችን ለማስፈር በቀጀላ መርዳሳ በወጣው አዲስ መመሪያ መሰረት በስታዲዮሙ ሱቆች ውስጥ ተከራይተው ለረዥም አመታት የቆዩ ተከራዮች እንዲለቁ እና በዙሪያው ያሉ መኪና አለማማጆች እንዲባረሩ መደረጉ ታውቋል።
ይህ እርምጃ ተቃውሞ እንዳያስነሳ አዲስ አበባ እስታዲየም ለጊዜው እንዲታጠር የተደረገ ሲሆን በአጥሩ ጀርባ አስፈላጊ ስራዎች ከተሰሩና ባለጊዜዎች ሱቆቹን እና አከባቢውን ከተረከቡ በኃላ አጥሩ እንደሚፈርስ እና ከጅማ ከሃረር ከአዳማ እንዲሁም ከተለያዩ የኦሮሚያ አከባቢዎች በርካታ ባለጊዜዎች ተዘጋጅተው በአዲስ አበባ ስታዴም ዙሪያ ባሉ ሱቆችና አከባቢዎች ድልድል እንደተሰጣቸው ታውቋል።
በአዲስ አበባ ስታዲየም ዙሪያ የሚሰሩ የመኪና አከራዮች የተለያዩ ሱቆች በ15 ቀናት እንዲለቁ እና ዙሪያውም ሊታጠር መሆኑን ከቀናት በፊት ባስነበብናቹ መሠረት ከዛሬ ጀምሮ ተግባራዊ መሆን ጀምሯል። በአዲስ አዲስ አበባ ስታዲየም ዙሪያ በተለምዶ ትንሿ ስታዲየም መኪና አለማማጆች ዛሬ መነሳታቸው እና ባህልና ስፖርት ለኢትዮጵያ እግርኳስና ለኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌድሬሽን ተዕዛዞች በቀጣይም ተግባራዊ መሆናቸውን የሚቀጥሉ መሆኑ ተሰምቷል። እንደሚታወሰው የአዲስ አበባ ስታዲየም በዕድሳት ሰበብ አገልግሎት መስጠት ካቆመ አራት ዓመታትን ሊያስቆጥር ተቃርቧል።

