December 7, 2023 – Zemedkun Bekele
Zemedkun Bekele (ዘመዴ),
• አዲስ አበባ ቴሌግራም እንዳይሠራ መደረጉን እየሰማሁ ነው። አሁንም በቪፒኤን እንደሚጠቀሙም እየነገሩኝ ነው። ከእኔ ከዘመዴ በቀር በቴሌግራም የሚጠቀም አክቲቪስትም ጋዜጠኛም የለም። እናም ቴሌግራም በአዲስ አበባም ሆነ በኢትዮጵያ እንዳይሠራ የሚደረግ ከሆነ እኔ ደግሞ ቀን በቀን ማታ ማታ በመረጃ ቲቪ በቀጥታ ስርጭት እመጣለሁ ማለት ነው። ሃላስ…
“…በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ከቀኑ 9:00 ጀምሮ ፒያሳ በሚገኘው በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የመሰብቢያ አዳራሽ ኮሚሽነር ጌቱ አርጋው የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር እና የፌዴራል ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነር መላኩ ፈንታ ፎሊስ ነፍሴ ጉዳዩ ይመለከተዋል የተባለን ሁሉ ሰብስበው ነበር። ይሄን ስብሰባ በተመለከተና በቀጣይ ፖሊስ ሊወስድ ስላቀደው እርምጃም በቀደም ዕለት በዕለተ ማክሰኞው የቲክቶክ መርሀ ግብሬ ላይ በስሱ እንደነገርኳችሁም ይታወሳል። የስብሰባው ዓላማም ህዳር 30/2016 ዓም በኢህአፓ መሪነት፣ ከኢዜማና ከባልደራስ በሥነ ምግባር በተባረሩ አባላት አማካኝነት ተዘጋጅቶ በአዲስ አበባ ይካሄዳል ስለተባለው “ጦርነት ይብቃ፣ ሰላም ይስፈን” በሚል መሪ ቃል ሊደረግ ስለታቀደው የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ ነበር። ሰብሳቢዎቹ ሰልፋን አስመልክተው ለፖሊስ አባላቱ ስብሰባውን የመሩት ግን ከዚህ በፊት ባልታየና ባልተለመደ በተደናገጠ እና ፍራቻ በተሞላበት አንደበት ነበር። ከዚህ ቀደም እንደነበረው ማስፈራራት እና ዛቻ ምናምን አልነበረም። ፋኖን መሳደብም አልነበረም። ቅዝቅዝ ባለ ሁኔታ ነበር ስብሰባውን የመሩት።
“…ሰብሳቢዎቹ በዚያው ሙትት ባለ ስሜት ውስጥ ሆነው ለፖሊስ አባላቱ ያስተላለፉት መልእክየት “የእሁዱ ሰላማዊ ሰልፍ በፌደራል መንግሥቱም፣ በከተማ አስተዳደሩም ዕውቅና የሌለውና የተከለከለ መሆኑን፣ ከዚህ ጋር ተያይዞም ከመከላከያ፣ ከፌዴራል ፖሊስ፣ ከአዲስ አበባ ፖሊስ ጋር በመሆን በተቀናጀ እና በተጠና መንገድ፦
፩ኛ፦ በዚህ ጉዳይ ቅስቀሳ የሚያደርጉ እና ተፅዕኖ ሊፈጥሩ ይችላሉ ወይንም ከሰልፉ ጀርባ ሊኖሩ ይችላሉ ተብለው የሚጠረጠሩ ሰዎችን መኖሪያ ቤት፣ ቢሮ ወዘተ የተጠናከረ ፍተሻ በማድረግ ሰዎቹንም ማፈንና መሰወር እንዳለባቸው ትእዛዝ መውረዱን አስረግጠው ተናግረዋል።
፪ኛ፦ በመቀጠልም ከዚህ በተጨማሪ ሕጋዊ ሆነው የሚንቀሳቀሱ ስፖርት ቤቶችና ጂም ቤቶች ውስጥ ስኳርና ውፍረት ደም ግፊትም ለመቀነስ ሳይሆን ለጦርነት ዝግጁ የሚያደርግ ወታደራዊ ሥልጠና የሚመስል የአካል ብቃት ሥልጠና እየሰጡ ነውና በእነሱም ውስጥ የሚገኙ ሰልጣኞችና አሰልጣኞች ላይ ክትትል ተደርጎ የተጠናከረ አፈሳ እንዲደረግ ታዟል።
፫ኛ፦ በዚህ የአፈሳ ኢላማ ውስጥ ግሮሰሪዎች፣ ጫት ቤቶች፣ ሺሻና የኳስ ማሳያ እና አሬቄና ጠላ ቤቶችም የአፈሳው በረከት እንዲደርሳቸውም ተነግሯል።
፬ኛ፦ ይህን ታሳቢ በማድረግ የህወሓት ኃይሎችም በበቀል ስሜት ሊሳተፉበት ስለሚችሉም በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ ኤርትራውያን ላይ ሰፊ የማሰር፣ የማዋከብ፣ የመሰወር ዘመቻም እንዲጀመር ታዟል። ይኸም ከትናንት ጀምሮ በኮንደሚንየም በሚኖሩ ኤርትራውያን ላይ በግልጽ ተግባራዊ መደረግ ጀምሯል። ከኤርትራውያኑም ጋር ጎን ለጎን አንዳንድ የትግራይ ተወላጆችም እንዲሁ ታሳቢ ተደርገዋል።
፭ኛ፦ ከወታደሩና ከፖሊስ አባላትም በቲክቶክና በዩቲዩብ የሚተላለፉ መርሀ ግብሮችን እንደሚከታተሉ የሚጠረጠሩም አባላት ይሄ የመታሰርና የመታፈን ዕጣ እንዲደርሳቸው ይደረጋልም ተብሏል። በአጠቃላይ የፋኖ ሁናቴ እና አካሄድ የሀገሪቱን ፖለቲካ በ6 ወር ውስጥ ከሥር መሠረቱ መነቅነቁም ነው የታየው።
“…ዐማራው እንደ በግ ሲታረድ የትም ያልነበሩት፣ ድምጻቸው ያልተሰማው፣ እንዲያውም ከኦሮሙማው እኩል ዐማራን በሊቀ መንበራቸው በዶር ብርሃኑ ነጋ አማካኝነት “ሰፋሪና መጤ” እያለ ለአራጆቹ ካራ ሲያቀብል የነበረው ኢዜማ ግንቦት 7ም አሁን ደግሞ ከኢህአፓ ጋር ተመሳጥሮ ዐማራን ለማስመታት፣ የአዲስ አበባንም ቅስም ለመስበር ባለቀ ሰዓት ካርድ ስቦ መነሣቱ ሊታወቅ ይገባል። “አብረን ትግል ከጀመርናቸው ፓርቲዎች መካከል ደርግም በጉልበት፣ ወያኔም በትጥቅ፣ ኦነግም በብልጠት በኢትዮጵያ መንበረ ሥልጣን ይዘዋል። የቀረሁት እኔ ኢህአፓ ብቻ ነኝ የምትለዋ ኢህአፓ በዚህ አጋጣሚ ለአንድ ቀንም ቢሆን በሚል ለሥልጣን ማሰፍሰፏ ነው የሚነገረው።
“…ኢህአፓ ከኦሮሞዎቹ በኩል ለሚነሣ ጥያቄም መልስ ለመስጠት መዘጋጀቷ ነው የተነገረው። ኦሮሞዎቹን ለማቀዝቀዝ “ዐማራ በምንሊክ ጊዜ ለደረሰው በደል፣ እንደ የባርያ ንግድ ለመሰሳሉት በይፋ ኦሮሞን ይቅርታ ይጠይቃል። ለዚህ ደግሞ ይሄን እንዲፈጽም ያዘጋጀነው የእኛ ፋኖ አለ። እናም ኦሮሞዎቹን ለመያዝ እምብዛም አያስቸግርም። ትግሬን ኮርነር በማድረግ እንደ ጥሬ እህል እየበተኑ ማቆየት ነው። ዐማራ ሰላም አርሶ ሰላም ውሎ ከገባ አይረብሽም፣ በሰላም ለመገዛትም አያስቸግርም። እሱን በማባበል መያዝ ብቻ ነው። ሥልጣን ላይ ማንም ወጣ አልወጣ ደንታው አይደለም ባዮች ናቸው አሉ። አሁን ካለው ሁኔታ ተነሥተን ስንመለከት አሜሪካኖቹ በአብይ አሕመድ አገዛዝ ተስፋ መቁረጣቸውንና እሱን በማስወገድ ከነርሱ ጋር ስምም ሁነው የሚሠሩ ሰዎችን ወደ መጫወቻ ሜዳው ለማስገባት ተፍተፍ እያሉ ነው የሚመስለው። ለአሜሪካ ታማኝ በመምሰል ራሳቸውን ለሽያጭ ያቀረቡ ሁሉ ደግሞ በዐማራው ሕዝብ ቅቡል አልሆን ብለው ነው የተገኙት። በአሜሪካ የዐማራ ማኅበራት፣ ጋዜጠኞች፣ የከሰሩ የፖለቲካ ሰዎች ሁሉ ቆዳ እየቀየሩ ዐማራ፣ ዐማራ የሚል ነጠላ ዜማ እየቋጩ ቢመጡም ወፍ የለም ነው የሆነባቸው። ብአዴንም ዐማራ ዐማራ የሚዘፍኑ አዝማሪ ፖለቲከኞችን ወደ ዋሽንግተን በስደተኛ መልክ ብትልክም ወፍ የለም ነው የሆነው።
“…ለዚህ ነው የፊታችን ሕዳር 30/2016 ይደረጋል ተብሎ የሚጠበቀው የእሁዱ ሰልፍ በኢህአፓ በኩል የተዘጋጀው። ይሄ ሰልፍ ትናንት መቅረቱ ከተዘገበ በኋላ ቆይቶ “በፍጹም አይቀርም በማለት ሰልፉ እንደማይቀር ኢህአፓና ኢዜማ ግንቦት 7ቶች በድጋሚ መግለጻቸውም ነው የተሰማው። ሰልፉ ገና ሳይጀመር ዐማራው በገፍ እየታሰረ ሲሆን ሰልፉ በግድ ቢደረግ እንኳ የሰልፉም ዕለት፣ ከሰልፉም በኋላም ቢሆን በግልጽ ዐማራውን ለማስመታትና አብይን ለማስወገድ ለሚፈለገው ጉዞ ፊሽካ በመንፋት ማስጀመሪያ በማድረግ አሜሪካኖቹ ቀልባቸው ያረፈበትን ብርሃኑ ነጋን ወደ ጠቅላይነ ሚንስትርነት በማምጣት ሥልጣን ላይ ለማውጣት የሚደረግ ሥራ ነው የሚሉም አሉ። ለብልፅግና ያደረው ናትናኤል መኮንንም የእሁዱን ሰልፍ በተመለከተ ኡሉታዊ ዜና በገፁ ከለጠፈ በኋላ ያነሣውም የእርሱ የቅርብ አለቃ ብርሃኑ ነጋ ቀጣይ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ይሆናል በሚል ቀቢጸ ተስፋ እንደሆነ ተነግሯል።
“…ደርጉ አቢይ አሕመድን በኢህአፓ ግንቦት 7 ኢዜማ ለመተካት ምዕራባውያኑ ተፍተፍ እያሉ ይገኛሉ። ይሄ ነገር ቀድሞ የሸከካቸው የኦሮሞ ምሁራን፣ ቦለጢቀኞች፣ አክቲቪስቶች በሙሉ ኦህዴድና ኦነግ በአስቸኳይ ታርቀው አንድ ላይ ይቁሙ። ይታረቁ። ከ150 ዓመት በኋላ በእጃችን የገባውን ወርቃማ ዕድል በኦህዴድ ስግብግብነትና በኦነግ ግትርነት ማጣት የለብንም እያሉ በመወትወት ላይም ይገኛሉ። ኦኤምኤን እና ኦቢኤን ራሱ አንድ ጣቢያ እስኪመስሉ ድረስ ነው እየወተወቱ ያሉት። የሰላም ሚንስትር ዴኤታው ኦነጉ አቶ ታዬ ደንደአም ኦነግና ገዢው ፓርቲ በፍጥነት ይስማሙ ዘንድ በግልጽ ወጥቶ የሚለፍፈውም ወዶ አይምሰላችሁ። የኦነግ አክቲቪስቶችም ከአሁኑ ብርሃኑ ነጋንና … ከታች ይቀጥላል…
ከላይኛው… የቀጠለ…
…ብርሃኑ ወጣበት የሚባለውን የጉራጌ ማኅበረሰብ በሰፊው በመክሰስ ተጠምደዋል። አዳነች አበቤ በየቦታው እየዞረች ፎቶ ከመነሣት ውጪ ፋብሪካና ቢዝነሱ በሙሉ በብርሃኑ ነጋ ዘመዶች የተያዘ ነው ብለውም ዋይ ዋይ እያሉ ያሉትም የጠረጠሩትን ጠርጥረው ስለጠረጠሩም ነው።
♥ የሚደንቀው ነገር ሰሞኑን 5 ሰዓት የፈጀና ከጠቅላይ ሚንስትሩ ጋር ወደ 7 የሚጠጉ ሰብሳቢዎች በቁጥር እስከ 20 የሚደርሱ ተሰብሳቢዎች ያደረጉት እጅግ አደገኛ ውይይት ደርሶኛል። በድምጽ ቀረጻው ላይ የተጠቀሱት ስሞች ዶ/ር አብይ አህመድ፣ ኦቦ ሽመልስ አብዲሳ፣ ዶ/ር ፍቃዱ ቢቂላ፣ ኮሎኔል አበበ ገርሱ፣ ዶ/ር ቀንአ ያደታ፣ አቶ ኢብራሂም እና ሌሎች ጥቂት ሰዎች ስማቸው ያልተጠቀሰ ነገር ግን እርስዎ ተብለው እዚያው በሊቀመንበሩ የተጠሩ ሰዎች ያደረጉት አደገኛ ስብሰባ ደርሶኛል። በሰፊው እመጣበታለሁ። ሰሞኑን እሱን ነው ርዕሰ አንቀጼ አድርጌ የማቀርብላችሁ። ጠብቁኝ። ጉድ ትሰማላችሁ።
“…በሌላ በኩል ህወሓትን አማሪካ ከመቃብር ብታወጣትም እንደሚጠበቀው መግነዟን ፈትታ መንቀሳቀስ አልጀመረችላትምም። የህወሓት ኮምፓሷ ተሰብሯል። ወገቧ ተቆርጧል ስለዚህ በድሮ በሬ እያረሰች መላወስ ባትችልም ልጆቿ ግን ተስፋ ሳይቆርጡ በረከቱ እንዳያመልጠን በቶሎ እንፍጠን እያሉም ነው። ህወሓት ወደ ማእከላዊ ኢትዮጵያ የፖለቲካ ምህዳር ለመመለስ ብትፈልግም መሪዎቿ ተቸካይ፣ አሮጌ አቁማዳ፣ አዲስ አስተሳሰብ የሌላቸው፣ ከልጅነት እስከ መጃጀት መስመርና ኃይልና ብለው መስመር ላይ ተተክለው የቀሩ፣ በዳይፐር እየሄዱ ወጣት ተተኪ የማያስጠጉ ሸታታዎች፣ በድዳቸው እየበሉ፣ በከዘራ እየተንፏቀቁ፣ አይናቸው ማየት አቅቶትም የሥልጣን ጥመኞች ሆነው በመወገማቸው የዳግም ሥልጣን መጨበጫ ዕድል የላቸውም። ህወሓት ከትግሬ ሕዝብም አንጀት ስለወጣች ወደ ትግሬ አንጀት ለመመለስ የግድ ወልቃይትና ራያን ማስመለስ ኤርትራን በመውጋት መበቀል አለባት። አሜሪካኖቹ አለን የሚሉትን ኃይል እናጉልበት እንዲሁም ጥበብ ሁሉ ተጠቅመው ባለ በሌለ ፈረንካም፣ ዲፕሎማሲም እየረዷቸው ነው። የአውሮጳና የአሜሪካ ፖለቲከኞች፣ አምባሳደሮች ጭምር መዋያ ማደሪያቸው መቀሌ ከሆነ ሰነባብቷል። ሆኖም ግን ጠብ ያለ ነገር የለም። ወደፊትም ጠብ የሚል ነገር በትግሬ ነፃ አውጪዋ በኩል አይኖርም።
“…እስከ ታህሳስ 19/2016 ዓም ድረስ አቢይ አህመድን በዚህም በዚያም፣ በኩዴታም በመተትም፣ በመርዝም፣ በጋርድም ብቻ በተገኘው መንገድ ለማስወገድ ወያኔም፣ ኦነግም እየሠሩ እንደሆነ ኦሮሞዎቹና ህወሓቶቹ በውስጥ መስመር ሲያጉረመርሙ ይደመጣሉ። አቢይ አሕመድን ይታደገዋል ተብሎ ይጠበቅ የነበረው የጎንደር እና የጎጃም ዐማራም ከአቢይ ከራሱ ደም ስለተቃባ አቢይ አሁን ደቡቦች ላይ ብቻ ተንጠላጥሎ ይገኛል። የደቡብ ጴንጤና የኦሮሞ እስላም ለአቢይ ለጊዜው መሸሸጊያ ሆነው ተገኝተዋል። አቢይ አህመድ እንደምንም ብሎ ከኤርትራ ጋር ጦርነት በመጀመር በኢትዮጵያውያን መሪዎች የታሪክ መዝገብ ውስጥ ስሙን “የአሰብን፣ ወደብ፣ ቀይ ባሕርንም ያስመለሰ መሪ” ተብሎ ለአንድም ቀን ቢሆን መጻፍን በመፈለጉ ጦርነት ከኤርትራ ጋር ማድረግን እንደ አማራጭ ወስዶ ይዟል። ኦሮሞ ቀይ ባሕር ለአዲሲቷ ኦሮሚያ ነው ብሎ እንዲታገል፣ ትግሬ ኤርትራን መበቀያ ነው ብሎ ከጎኑ እንዲቆም፣ ዐማራው ቢያኮርፍም ኢትዮጵያኒስቱ ግን ለኢትዮጵያ ነው ብሎ እንዲደግፈው በማደረግ ለቀይ ባህር ውጊያ መዘጋጀቱ ነው ነው የሚነገረው። በኢሳያስ ከሩሲያ ጋር መግጠም የበሰጩት አማሪካኖች ከጀርባው ቢኖሩም ታሳቢ ያደረገውም በዋናነት ቀይ ባህርን ለምትፈልገው ለተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ሲሆን ድጋፉም ከእርሷ ይገኛል በሚል እንደሆነ ነው የሚነገረው። ነገር ግን የሰሞኑ የሩሲያው መሪ የፑቲን የኤምሬትስ ጉብኝትና በአቢይ አህመድ ወዳጅ የተደረገላቸው አቀባበል ነገሮችን ለአቢይ መልካም የሚያደርግለት አይመስልም የሚሉም አሉ። ሩሲያ የኤርትራ ወዳጅ ናት። ኤርትራ ደግሞ የኤምሬት ፀበኛ፣ የሳዑዲም ወዳጅ ናት። ሳዑዲና ኤምሬትስ ደግሞ ባላንጣ ናቸው። ሳዑዲ ሰሞኑን ብቻ 25 ተዋጊ ጀቶችን በአሰብ ወደብ ማሳረፏም ተነግሯል። ይታያችኋል ጦርነት በቀጠናው ሲጀመር ኤርትራ፣ ትግራይ፣ አፋር እና ዐማራ እንዴት እንደ የመን እንደሚወድሙ። ኦርቶዶክሳውያን ሴሞች በኩሻንኩሽ ሃም ተደርገው ድቅቅ ድብልቅልቅ ያለ ነገር ነው የሚታየው።
“…በዚህ መሃል አቶ ጌታቸው ረዳ ከአሜሪካኖቹ ጋር በመቀሌ ከተወያየ በኋላ ወልቃይትና ራያ በእጄ ሳይገቡ ሕዝበ ውሳኔ ብሎ ነገር የለም በማለት እቅጩን ተናግሮ የአቢይ አሕመድን ካምፕ አስደንግጧል። ዐማራ ለንግግሩ አይሞቀው አይበርደው። የትግሬ ልዩ ኃይል፣ ሚሊሻው፣ ቲዲኤፍ የሚባለው የትግሬ ጦርም ሥልጠናውን በሃላል አጧጡፎታል። ወያኔ አሮጌ መሳሪያ አሳይታ ከባድ መሳሪያዋን ሳታወርድ፣ ሥልጠናም ሳታቋርጥ የመጨረሻም ባይሆን አንድ ግማሽ ሚልዮን የትግሬ ወጣት ለማስገበር ተፍተፍ እያለች ትገኛለች። አዲስ አበባ በትግሬ ለማኞች፣ የእኔ ቢጤዎች ተሞልቷል። ከወለጋ የተፈናቀሉ ዐማሮችም እንደዚሁ። ኦህዴድ አደህይቶ ለመግዛት የመረጠው ስልት በዚህ በኩል እየሠራለት ይመስላል። ፍጻሜው ባያምርም። የሚገርመው ኦሮሙማውም የመሣሪያና የአልባሳት ርዳታ ለህወሓት እያቀረበ ነው የሚሉም አሉ። መጀመሪያ በረሃብ የተጎዱ ሰዎች በትግራይ እንዲታዩ ይደረግና ቀጥሎ አሜሪካም በሰማንታ ፓወር በኩል እርዳታ በሚል ስንቅና ትጥቅ ለቲዲኤፍ እንደምታቀርብም ይጠበቃልም ነው የሚባለው። ኦሮሞዎቹ “ትግሬና ዐማራ በወልቃይትና በራያ ይፈሳፈሱ እኛ ለትግሬ ወዳጅ ሆነን ለምን ዐማራውን በትግሬ በኩል አናስወጋውም፣ ቢሞቱም ከሁለቱ ወገን ነው የሚሞቱት፣ ድቀት ቢመጣም ሁለቱ ናቸው የሚደቁት፣ ከዐማራው ይልቅ ከምን ለፌደራሊስቷ ወያኔ ድጋፋችንን እንደ መንግሥት አንሠጥም” የሚሉ ያሉ ሲሆን የበለፀገው የአቢይ አህመድ ኦሮሙማ ደግሞ ወያኔን አታውቋትም። ወያኔ ወልቃይትን ብትወስድ እኛ ጉዳያችን አልነበረም። ለዐማራ አግዘንም አይደለም በወልቃይት ጉዳይ ለዘብተኛ የሆነውና ለዐማራ ያደላን የምንመስለው። ነገር ግን ወልቃይትን ወያኔ ከወሰደች ከዚያ በኋላ ከሱዳን ጋር ገጥማ፣ የወደብ አክሰስም አድርጋ ለእኛም ታሰጋናለች። የሚሻለው ወያኔን በተስፋ እየሞላን ስትናደድ፣ የትግሬ ደጋፊ ግፊት ሲበዛባት፣ ሄጵ ብላ ጦርነት እየገጠመች ቀጥቅጣም ተቀጥቅጣም እየደቀቀች እያደቀቀችም እንድትመለስ ማድረግ ብቻ ነው። ከኤርትራ ጋር ውጊያ ብንገጥም ዐማራው በርግጠኝነት አያግዘንም፣ ትግሬ ግን ለበቀል ስለምትፈልግ ታግዘናለች፣ ስለዚህ ትግሬን ለፈንጅ ማብረጃ እየተጠቀምን በተስፋም እየሞላን በረጅም ቀጠሮ ማጀዘብ ነው ያለብን ነው የሚሉት። ለዚህ ደግሞ መከላከያው ግልጽ የመሞቻ ፈንጂ በገፍ እያቀበላት መቀጠል አለበት ነው የሚለው። ራያና ወልቃይት እንደ ካሽሚር መሆኑ ነው። እናም በቅርቡ ወያኔ በአቢይ ብራኑ ጁላ፣ በአሜሪካ ታግዛ በዐማራ ላይ መጠነ ሰፊ ጦርነት ትከፍታለች ተብሎም ይጠበቃል።
“…ሌላው በዐማራው በኩል የድርድር ጉዳይ በጥድፊያ መምጣት አለበት። በእነ ዶክተር ወንደሰን ፋይል የተከሰሱት የክስ ዶሴያቸው ቆሞ ወደ ድርድር መምጣት አለብን፣ የዐማራን ሕዝብ በመጨፍጨፍ በራሳችን ላይ መታነቂያ ገመድ አስገብተን ሸምቀቆውን እያጠበቅን ነው የምንገኘው። በፋኖ አመራሮች አመራሮች መካከል ሊከናውን የታቀደውን ሴራ በቶሎ መተግበር ያስፈልጋል። የሴራው ዋነኛ ዓላማም ፋኖዎቹን እርስ በእርስ …ከታች ይቀጥላል…
ከላይኛው የቀጠለ…
…ማጫረስ፣ ወይም አንዱ የፋኖ መሪ በሌላው የፋኖ መሪ ላይ እንዲቃረን፣ ያለመተማመን በመካከላቸው እንዲኖር እና እንዲወጋጉ ማድረግ። ይሄንንም ለማከናወን ጥቂት እውነታዎችን መሰረት በማድረግ ለምሳሌ የሚመሯቸውን የአባላት ቁጥር፣ ለአንዱ የፋኖ መሪ እውቅና እንዲሰጠው በማድረግ፣ ሌላውን በማግለል፣ ይሄንንም በተለያዩ የማኅበራዊ ሚዲያዎች እና በተለያዩ አካላት በኩል አንዱን የፋኖ መሪ ብቻ የማጀግን፣ የማሞካሸት፣ የማወደስ ሥራ በመሥራት ማበጣበጥ ያስፈልጋል። የብአዴን ፋኖዎችን በማስረግ ማስገደል፣ ጠቀም ያለ ገንዘብ በመስጠት ማማለል፣ በዐድማ ብተናና በሚሊሻ በማስወጋት እርስ በእርስ ማጨራረስ፣ በውጭ የተሰበሰበው ገንዘብ ቁጥሩን ከፍ በማድረግ በመጥራት ገንዘቡ ለማይደርሳቸው ነገር ግን ለመከላከያው ፈተና ለሆኑት በመንገር ማቃቃር። የፋኖ ገንዘብ ያዥ የሆኑትን ማባበል፣ ማስከዳት። ኢንተርኔቱን ቀስበቀስ በመክፈት የፋኖ አካላት የሚያደርጉትን የመረጃ ልውውጥ በማጥናት በድሮን የታገዘ መጠነ ሰፊ እርምጃ በመውሰድ ማኮላሸት ያስፈልጋል የሚልም ዕቅድ ይዘው እንቅስቃሴም ጀምረዋል።
“…የፊታችን ታህሳስ መጀመሪያ በደብረ ዘይት ከተማ የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ እና ኢትዮጵያ የጋራ የጦር ልምምድም ያደርጋሉ። የአቢይ አማካሪው ዳንኤል ክብረት እና የዳንኤል ታዛዥ ሻንጣው ነው ዳንኤል የሰጠውን መግለጫ ነው የሚያነበው የሚባለው ለገሰ ቱሉም ቀደም ብለው ሄደው ከአየር ኃይሉ አዛዦች ጋር ስለ ዝግጅቱ ግቢውን ተዘዋውረው መመለሳቸውን ወፎቼ በፎቶ አስደግፈው ልከውልኛል። ቼክ ሪፐብሊክም የለገሰችው የአየር መለማመጃ ሲሙዩሌተርም ተተክሎ ሥራ ጀምሯል። ተደብቆ የከረመው ደመቀ መኮንንም ዛሬ ብቅ ብሎ ለሕዝብ እንዲታይ ተደርጓል። ትናንት ማታም ባህርዳር በቆንጆዎቹ የተሠራው ኦፕሬሽን አስደማሚ ሆኖ ውሏል።
• ወፎቼ ክበሩልኝ…!
• ድል ለዐማራ ፋኖ…!
• ድል ለተገፋው ለዐማራ ሕዝብ…!
• ድርጅቱ ዘመዴ ነኝ አሸበርቲው…!