December 9, 2023 – Konjit Sitotaw 

ኢትዮጵያ በ1 ቢሊዮን ዶላር ቦንድ አከፋፈል ላይ ከአበዳሪዎቿ ጋር ያደረገችው ድርድር ትናንት ያለ ውጤት እንደተጠናቀቀ ሮይተርስ ዘግቧል።

ኢትዮጵያ በቀጣዩ ሰኞ በተቀመጠው ቀነ ገደብ የ33 ሚሊዮን ዶላር የቦንድ ወለድ መክፈል እንደማትችል ለአበዳሪዎቿ ማሳወቋን ዘገባው ጠቅሷል።

ድርድሩ ያለ ውጤት መጠናቀቁ፣ ኢትዮጵያ የውጭ ዕዳዋን መክፈል የማትችልበት ደረጃ ላይ መድረሷን ሊያሳይ እንደሚችል ዘገባው አመልክቷል።

ኢትዮጵያ በዓለማቀፍ ገበያ በኅዳር 2007 ዓ፣ም የሸጠችው የ1 ቢሊዮን ዶላር ቦንድ መክፈያ ጊዜ የሚያበቃው በቀጣዩ ዓመት ታኅሳስ ነው።

ቦንዱ 6.625 በመቶ ወለድ የሚከፈልበት ነው።