December 10, 2023 

” ባልታወቁ ሰዎች በጥይት ከተመቱ በኃላ ህክምና ቢደረግላቸውም ሊተርፉ አልቻሉም ” – ብፁዕ አቡነ ዮሐንስ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የማዕከላዊ ጎንደር ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ በኩረ ትጉኃን ዘርዓዳዊት ኃይሉ ተገደሉ።

ኅዳር 30 ቀን 2016 ዓ.ም ከጠዋቱ በ11 ሰዓት ባልታወቁ ሰዎች በጥይት ተመትተው ህክምና ሲደረግላቸው ቆይተው ሊተርፉ ሳይችሉ ቀርቶ ሕይወታቸው ማለፉን የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ዮሐንስ አሳውቀዋል።

ብፁዕነታቸው የግድያው ምክንያት እንደማይታወቅ ገልጸው በክስተቱ የተሰማቸውን መሪር ኃዘን ገልጸዋል።

መረጃውን የኢኦተቤ ቴቪ ነው።