December 10, 2023 – Zemedkun Bekele
ኢንጪኒ እና ዳንግላ
• ኢንጪኒ
“…ከአዲስ አበባ አቅራቢያ ከሆለታና ሙገር ከተማ መሃል በእንጪኒ ከተማ ትናንት ሌሊት ኦነግ ሸኔ ገብቶ ባንክ ዘርፎ፣ እስረኞችም አስፈትቶ፣ 5 የኦህዴድ ብልጽግና አመራሮችንም ገድሎ ከተማዋን ለቅቆ ወጥቷል። ይህ ሁሉ ኦፕሬሽን ሲደረግ የሀገር መከላከያ ተብዬው የኦሮሙማው መከላከያ እዚያው ትንሽ ራቅ ብሎ ቲአትሩን እየሳቀ ይመለከት ነበር ተብሏል። ኦነግ ሸኔዎቹ ዳንጎቴ ሲሚንቶ ፋብሪካ መግባታቸው እንጂ ጥፋታቸው አልተገለፀም።
• ዳንግላ
“…ከሂዊ ፈጠሩ አገው ሸንጎ ጋር በቀጣይ የሞት ሽረት ፍልሚያ ለማድረግ የተዘጋጁት የአገውና ዐማራ ፋኖዎችም ትናንት በተመሳሳይ ከሌሊቱ 10:00 ሰዓት ጀምሮ ባደረጉት የተለየ አስደናቂ ኦፕሬሽን ማረሚያ ቤቱን ሰብረው የፖለቲካ እስረኞችን በማስለቀቅ የጦር መሣሪያም ካወጡ በኋላ የብልፅግናን አድማ ብተና ፖሊስ እና ውኃ አይገቤ ሚሊሻን እጅ ወደ ላይ በማስባል ማርከው በድል ወደ ማዘዣ ጣቢያቸው መመለሳቸው ተነግሯል። ፋኖ እነደ ሸኔ የዘረፈው ባንክ ግን የለም። የዐማራ ክልል ኮማንድ ፖስት ማዘዣ በሆነው ከተማ ይሄ ሁሉ ሱፈጸም የኦሮሙማው መከላከያ ድርጊቱን በርቀት ከማየት በቀር ለትናንት የእሳት ራት መሆን እንዳልፈለገም ተሰምቷል።
“…በቀደም ደብረታቦር ከተማ ላይ የፎከሩት አረጋ ከበደ፣ ጄነራል ብራኑ በቀለ እና አንድ ሌላ የእሳት ራት የሆኑ ሰው በአሚኮ ላይ ድንፋታቸውን ከለጠፉ በኋላ አሚኮ አንስቶታል። በአማሪካ አይዞሽ ባይነት የተበረታታችው የትግሬ ነፃ አውጪዋ ሂዊም ለዳግም ወረራ ዝግጅቷን አጠናክራ ቀጥላለች። በቅርቡ ከወደ ሰሜን ሰማይና ምድር ይጣበቃል። ከታሕሳስ 19 በፊትም ሁሉ ነገር ይለይለታል የሚሉ መተርጉማንም አሉ። የዐማራ ብልጽግና እና የአቢይ መከላከያ ያሉት ዳንኤል ክብረት ፌስቡክ ላይ ብቻ ነው።
• ማኔቴቄልፋሬስ…!