December 10, 2023 

(ኢትዮ 360- ሕዳር 30/2016) በአዲስ አበባ ከተማ ዛሬ ሰልፍ ይወጣል ተብሎ የተጠበቀውን ወጣት ለመግደልና ለማፈን ተዘጋጅቶ የነበረው ገዳይ ቡድን ሲያዛጋና ጸሃይ ሲጠጣ ውሎ መመልሱን የኢትዮ 360 ምንጮች ገለጹ።

ምንጮቹ ገዳይ ሟች አጥቶ ሲክለፈለፍ የዋለበት ታምረኛ ቀን ህዳር 30/2016 ሲሉ ገልጸውታል።
እነ ሰዉ በላዉ ህልማቸዉ ከሸፈ የሚሉት ምንጮቹ የገደሉትን ገለዉ የተረፈዉን አፍሰዉ ለመዉሰድ ያላደረጉት የዝግጅት አይነት አልነበረም ይላሉ።
ይሄም የሆነው ኢህአፓና ኢዜማ በጥምር ጦርነት ያብቃ በሚል ሰልፍ ጠርተናል ማለታቸውን ተከትሎ መሆኑንም ሳይጠቁሙ አላለፉም።

ነገ ግን ጠዋት ላይ ጎዳናውን የሞላው ሰልፈኛው ሳይሆን ፖሊስና መከላከያ የሚባለዉ የኦነግ ገዳይ ቡድን ነበር ይላሉ።

በየካምፑ የከተማ አዉቶቡስ አሰልፈዉ አስቁመዉ የሟች ያለህ ፥ የታሳርሪ ያለህ ቢሉ በአካባቢው እንኳን ሰው ወፍ ማየት አልቻሉም ሲሉ ተሳልቀውባቸዋል።

አስፓልቱን ሚኒተሪ ለባሽ አጥለቀለቀዉ 6 ስዓት ሲሞላ የታሰበዉ አልሳካ ያለው የገዳዩ ቡድን ሃይልም ውሃ ጥምና ጸሃዩ ገደለን ወደ መጣንበት መልሱን በሚል ሲያጉረመርም እንደነበርም ገልጸዋል።

ለሌላ ነገር ካላሰባችሁን ልቀቁን ቤት ሂደን እንረፍ የሚለውም ድምጽ የወጣውም ከዚሁ አደባባይ ንጹሃንን ሊገል ከተሰማራው ገዳይ ቡድን ነበር ሲሉ ገልጸውታል።