(ኢትዮ 360 -ሕዳር 30/2016) ከባህርዳር በዙ 23 ታጅቦ ወደ እንጅባራ ሲገሰግስ የነበረው የብአዴን ርዝራዥ በአዲስ ቅዳም ፋኖዎች ሙትና ቁስለኛ ሆኑዋል ሲሉ የፋኖ አባላቱ ለኢትዮ 360 ገለጹ።
በዙ 23 በመታጀብ ጭምር የገዳዩን ቡድን ተልእኮ ለማስፈጸም ሲጓዝ የነበረው የከሃዲው ቡድን ከነበልባሎቹ የፋኖ አስር አለቃ ኤፍሬም አጥናፋ የአዲስ ቅዳም ፋኖዎች ድንገተኛ ጥቃት ግን ሊያመልጡ አልቻሉም ብለዋል።
የአዲስ ቅዳም ፋኖች ባደረጉት የደፈጣ ኦፕሬሽን በተለምዶ ቻይና ካምፕ ተብሎ በሚጠራው ቦታ ድባቅ የተመታው የባንዳ ስብስብ አብዛኛው ሙትና ቁስለኛ አድርጎታል ብለዋል ለኢትዮ 360 በላኩት መረጃ።
የተረፉት አስከሬናቸውንና ቁስለኞቻቸውን ይዘው ተበትነዋል ብለዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በምዕራብ ጎጃም ወምበርማ ወረዳ የገባው ገዳይ ቡድን በርካታ ንፁን አርሶ አደሮችን በግፍ መጨፍጨፋቸውን የኢትዮ 360 ምንጮች አስታውቀዋል።
በዚሁ ቡድን ከተጨፈጨፉት መካከልም ምጥዋ መቶ ልትወልድ ጤና ጣቢያ የተኛች ነፍሰ ጡር ሙስሊም እናት ከእነ ወላጅ አባቷ ጋር እንደሚገኙበትም ተናግረዋል።
በምስራቅ ጎጃም ቢቸና ከተማ ያለው ገዳይ ቡድን ደግሞ ሴቶችና ህጻናትን በመድፈር አጸያፊ ወንጀል እየፈጸመ መሆኑን ነው የኢትዮ 360 ምንጮች ያመለከቱት።
ይሄ ድርጊት የተፈጸመው በከተማው በሚገኘው ማረሚያ ቤት አጠገብ “የሰንቢ” በምትባል ት/ቤት ውስጥ መሆኑንም ይናገራሉ።
