HomeNews Feed postsBook for ALL · Join
Joni Tsegaye · otprodSesncmYsc8et8a ldh:f216665fr8t30a5Aeaa2M435g8a ay0m66 · ሐይለ ጽዮን ገብረዮሐንስ (ጎሞራው) የአማረኛ ቋንቋ ለብዙ ሺ ዓመታት የህዝብ መግባቢያ ቋንቋ ሆኖ የቆየ ስለሆነ የአማረኛ ስነግጥም የንጉሶችን ከሀገር ወደ ሀገር መዘዋወር፣ የጀግንነታቸውን፣ የሀገራቸውን መስፋት፣ የሚገልጹ ስነግጥሞች በጽሁፍ ማስረጃነት ልንጠቅሳቸው የምንችል ቢያንስ በ1303 ለንጉስ አምደጽዮን፣ 1375- 1404 ለአጼ ዳዊት ፣ 1407-1422 ለአጼ ይስሀቅ ፣ 1426 ለአጼ ዘርዕያቆብ፣ 1532-1551 ለአጴ ገላውዲዎስ የተጻፉት ይገኙበታል። ሆኖም የአማረኛ ስነግጥም በ19ኛው ክፍለ ዘመን የህትመት መሳሪያ ሀገራችን ከመግባቱ ጋር የእድገት ለውጥ አሳይቶ ዛሬ የደረሰበት ደረጃ እንዲደርስ፣ ለዚህ ስነግጥም እድገት በቁንጮነት ከሚጠቀሱ የስነጽሁፍ ሰዎች መካከል በተቀዳሚ ስሙ የሚጠራው አቶ ሀይሉ ገብረዮሐንስ ወይም ገሞራው ነው።ሀይሉ ገብረዮሐንስ በ1960ዎቹ አጥቢያ ወደ መድረክ ብቅ ሲል፣ የዘመኑን ህይወት ውስጣዊና ውጫዊ ገጽታዎች እንዲሁም የዘመኑን ሰው ስብእና የመረመረባቸው፣ የተፈጥሮን ውበት የገለጸባቸው ግጥሞች ይገኙበታል። ጥንታዊውን ከዘመናዊው፣ የእኛን ሀገርና የውጭ ሀገር ስነግጥሞችን መርምሮ በአዲስ በገነባው ስነግጥማዊ ስልቱ፤ የአማረኛ ስነግጥም የቋንቋና የአገላለጽ ብርታቱን፣ የላቀ የሀሳብና የስሜት ይዘቶችን ለመግለጽ ያለው ጉልበቱን፣ ረቂቅ ሀሳቦችን ለተራው ሰው እንዲገባ አድርጎ በማቅረብ፣ ከሚስጥርነት ያላለፉ ቁም ነገሮች ግልጽ አድርጎ በማሳየት፣ በስነግጥሙ ለተራወ ህዝብ ህይወት ያለውን ወገናዊነት አሳዬ። ግጥሞቹ ጥልቀት ያላቸው ሀሳቦችንና የህዝቡን ብሶት ለተራው ህዝብ እንዲገቡ ግልጽ አድርገው የሚያሳዩ በመሆናቸው፣ በዘመኑ የተወደዱና ቀጥሎም ለተነሱ ትውልዶች አርአያ ሆኑ፡ለምሳሌ በበረከተ መርገም በሚለው ግጥሙ፤-ከጥንት ጀምሮ ስናየው የኖርነውሲነድ ሲቃጠል የሚስቅ እሳት ነው። ሲል በሌላ ጊዜ ደግሞደረቁ የብስ ዉሃ ጠምቶት በመከራ ስቃዩን ሲያይዝናብ ቢዘንብ ጎርፍ ቢወርድ የብሱን ትቶ ካሮንቋው ላይዝናብ ቢጥል ዘር ፈልጎ ውሃ ካለው ከሐይቁ ላይያስጨነቀኝ እንዲህ ያለው እንዲህ ያለው ልዩ ጉዳይ። ይላልየስንኙ ቤት እንዲመታ ተብሎ የሚገጠሙ እኝ – እኝ የሚሉ ግጥሞችን ሲሄስ፣ ”ቃላት በቋንቋ ውስጥ የየራሳቸው ቦታ አላቸው። ቦታቸው ሲናጋ የሉም፤ ሞተዋል ማለት ነው” ይልና፣ የአዲሱ ትውልድ ስነግጥም ከጥንታዊውና ከዘመናዊው ስነጽሁፍ የዳበረ ዘዴና ይትበሀል መቀዳት ይኖርበታል ሲል ይመክራል። የሀይሉ ገብረዮሐንስ ቃላቶች ፍታውራሪ፣ ቀኛዝማች፣ ደጃዝማች ተብለው እንደተሾሙ ሁሉ የየራሳቸውን ቦታ ይዘው ተደላድለው የተቀመጡ መሆናቸውን ለማሳየት ያህል ”ጎጆዬም ጠላችኝ” ከሚለው ግጥሙ ለላሙና በከፊል ልጥቀስ። ግጥሙ ስለራሱ ከሀገሩ ስለመሰደዱና ስለመንገላታቱ፤ ጎጆዬ የሚላትም ሀገሩን፣ አስተዳደሩን ይመስለኛል።እንዴት ታኮርፊያለሽ እንዴትስ ትጠይኝለገዛ ህይወትሽ ተመከሪ ባልሁኝ።ሰዎች ፍረዱልኝ ወይም ፍረዱብኝጎጆዬ ጠላችኝ ተሻሻይ ባልሁኝ።የጎጆዬ መጥላት ሁኔታው ቢጨንቀኝከደጅዋ ላይ ሆኜ በሀዘኔ ሳቅሁኝ።ቀልብን ነካ አድርጎ ልብን የሚሰውርከፍተኛው ሀዘን፣ አሰቃቂው ልቅሶ አለንባ የሚያስቀርመጨረሻው አይነት የሰቆቃው ድንበርሳቅነው ብለውኛል ማስካካት አለነውር።ስቅቅ ላለው ልቅሶ ምርር ላለው ሀዘንበመጨረሻ ላይ መግለጫው ሳቅ ይሆን? ?ሀይሉ ገብረዮሐንስ (ገሞራው)፣ የጥንቱ ስነግጥም በሀሳብና በአገላለጽ ብልሀት የሚያበረክተውን አስተዋጽኦ ቀላል አለመሆኑን የሚያምንና ከግእዝ አስከ አማረኛ ያሉ የስነግጥም ድንጋጌዎች ውርስ በመመርመር የሚደርሳቸው ረቂቅ ሀሳቦችን ያዘሉ ግጥሞች፣ በአይነት፣ በይዘትም በብልሀት የአማረኛን ስነግጥም የላቀ ደረጃ ላይ አድርሰውታል፤ ለምሳሌ ከመጠን በላይ በእውቀት በስለው፣ ይህ ከፍተኛ ብስለታቸው ከአካባቢያቸው አስተሳስባቸው በመናሩ እንደበደል ተቆጥሮባቸው ያለጊዜው ለተቀጩና ለተፈጥሮም ልዩ የማጥፋት ችሎታዋ ትዝብት እንዲሆን ጭምር ሲል ባበረከተው ግጥም፡በመንቃት ላይ ባሉ ፍጡራን መካከልሕይወት የምንለው እንደ ጥሬ እህልበኑሮ ምጣድ ላይ ቢቆላ ቢማሰልየበሰለው ያራል ጥሬው እስኪበስል። ይለናል፤ሀይሉ ግንባር ቀደም ለውጥ ፈላጊ በመሆን ግማሽ ምእተ አመት በስነግጥም ብቻ ሳይሆን በፖለቲካው መድረክም አሳልፏል። ሀይሉ በየግጥሞቹ የዘመኑን ሕይወት ድቀትና እውነታ እንደ መጽሀፍ ገልጾ እያሳዬ፣ የተሻለ ህብረተሰብን ለመፍጠር የለውጥ አስፈላጊነትን ገልጿል። ሆኖም፣ ለሀገርና ለህዝብ እድገት የሚያስገኝ ለውጥ አስፈላጊነትን ቢያምንም፣ ለውጡ ግን የኛ የሆነውን ሁሉ አገልግሎቱን እንደጨረሰ አሮጌ እቃ አውጦ ጥሎ ሰለጠኑ ከምንላቸው ሀገሮች ምኑንም ምኑንም ከነዝባዝንኬው ማግበስበስ አለመሆኑን በተደጋጋሚ በግጥሞቹ አስነብቦናል። የራስን ማንነትና ምንነት ሳይመረምሩና ግንዛቤ ውስጥ ሳያስገቡ የለውጥ አስፈላጊነት የሚሰብኩትንም ሲሄስ፣”የራሳቸውን መርሀ እውር ለራሳቸው የህሌና ምጣኔ ይቀምራሉ፤፡ ከራሳቸው ግላዊ አስተሳሰብ የራሳቸውን የህሌና አለም ይፈጥራሉ፣ በዘመናትና በትውልዶች አማጭ ረማጭነት ለዘመኑ ትውልዶች የተላለፉትን ባህላዊ ቅርሶች፣ ቫልዩስ፣ ፎርምስ፣ አቲትዩድስ በማርከስ ከግብስብስ መጽሀፍትና ከረጋ ሰራሽ ልምዶች የቃረሙትን ርካሽ አስተሳሰቦች በመደረትና የራሳቸውን የስነህይወት መመሪያ በአየር ላይ ያውጃሉ። አንቀጽ አያስጠቅሱም እንጂ ከእነዚህ ሁሉ አልፈው ተርፈው አካላዊ እነሱነታቸውን ከተራው ሰው ለመለየት የማይነቀሱት፣ የማይኳሉት፣ የማይበጡት ነገር የለም። ይህ ሁሉ ጥረት ከድምሩ ህዝብ አፈንግጦ ለመታየትና ልዩ መስሎ ለመገኘት ስለሆነ የግብዝነት ባህርይነቱ እንደ ታራራ ላይ ፋና ቅልጥጥ ብሎ ይታያል። በሰብአዊነቱ አንጻር የሚያስደንቅ ፍሬ አልባ ሙከራ ነው።” ይልና ስለ እኛ ማንነት ዘወር ብሎ ሲተክዝ ከረዥም ግጥሙ ብቀነጭብ ”እሽሩሩ ድንቡልቦቃ” በሚለው ግጥሙ እንዲህ ይላል።ግን ዋ ያ ቅኔያችን ካልኩለስ በነበርዋ ያ ብሉይ ያ ሐዲስ አልጀብራ በነበርዋ ያ መሳጭ ዜማችን ፊዚክስም በነበርእንዲህ ያርጋጅ አንጓጅ፣ አድናቂ አጨብጫቢ ሆነን ባንቀር። ይላልሀይሉ መጀመሪያ ታወቀበት ከሚባለው ከበረከተ መርገም ጀምሮ ያሉትን ግጥሞች ስናነብ የምንረዳው፣ አጨብጫቢነትን ተጠይፎ እውነትን ለማደን ወጦ ሲንከራተት መኖሩን እናያለን። ስለ እውነትም ሲናገር እንዲህ ይላል።”የኔን ልንገራችሁ ፍልስፍናም ኪነትም፣ ጥበብም፣ እውቀትም፣ ትምህርትም (የፈለጋችሁትን በሉ) ሁሉ ነገር እርቃነ እውቀትን ለማስገኘት ነው። አንድም ፍልስፍናም ጥበብም ኪነትም … ሆነች እውነት ናት። እውነት በበኩሏ አንድ ባህሪ ሲኖራት ያም ባህሪዋ ዋህድነት (አንድነት) ብቻ ነው። … የአትላቲክ የፓሲፊክ እውነት፣ የአውሮፓዋ የአፍሪካዋ እውነት፣ የነጩ የጥቁሩ እውነት፣ የእስላሙ የክርስቲያኑ እውነት፣ የሁሉ እውነት … አንዲት ናት።” ይለናል። ግን እውነት በተናገረ፣ እውነትን ባስተማረ፣ እውነትን በመረመረ ከሀገሩ ወንጀለኛ ሆኖ የተባረረበትን እውነታ ለማጥመድ አደን አልቀናው ብሎ ተስፋ ሳይቆርጥ ከሱ ይልቅ ለሀገሩ ሲያንጎራጉር፤እመኘው ነበረ ሞትሽን ለሞቴግን አልሆነልኝም ተቃጠለ አንጀቴሸካራው እድልሽ ሲያጉላላሽም ቢኖርምብታረጂም አንኳ ቀን ሳይወጣ አይቀርምስለዚህ እስከዚያው እያለቀስኩ ላዝግምየሀይሉ ጎሞራው ግጥም አንድን ፍልስፍና፣ ርዮተዓለም፣ ሃይማኖት፣ ወዘተ መስበኪ ወይም ማስተላለፊያ ሳይሆኑ፣ ስሜትን፣ ረቂቅ ሀሳብን፣ ውበትን፣ ወዘተ በመግለጽ ከሙሉነትም በላይ ሞልቶ የሚፈሱበት ግጥሞች ናቸው። ስሙት አዝኖ አሳዝኖን መልሶ ስለኛ ሲጨነቅ፤እስቲ ልናገረው ይውጣልኝ ልተንፍስአልቻለም ያ ልቤ ታምቆ መላወስበኔ የደረሰው በማንም አይድረስ።
All reactions:11
News Feed postsBook for ALL · Join

Book for ALL · Join
Joni Tsegaye · otprodSesncmYsc8et8a ldh:f216665fr8t30a5Aeaa2M435g8a ay0m66 · Join
ሐይለ ጽዮን ገብረዮሐንስ (ጎሞራው) የአማረኛ ቋንቋ ለብዙ ሺ ዓመታት የህዝብ መግባቢያ ቋንቋ ሆኖ የቆየ ስለሆነ የአማረኛ ስነግጥም የንጉሶችን ከሀገር ወደ ሀገር መዘዋወር፣ የጀግንነታቸውን፣ የሀገራቸውን መስፋት፣ የሚገልጹ ስነግጥሞች በጽሁፍ ማስረጃነት ልንጠቅሳቸው የምንችል ቢያንስ በ1303 ለንጉስ አምደጽዮን፣ 1375- 1404 ለአጼ ዳዊት ፣ 1407-1422 ለአጼ ይስሀቅ ፣ 1426 ለአጼ ዘርዕያቆብ፣ 1532-1551 ለአጴ ገላውዲዎስ የተጻፉት ይገኙበታል። ሆኖም የአማረኛ ስነግጥም በ19ኛው ክፍለ ዘመን የህትመት መሳሪያ ሀገራችን ከመግባቱ ጋር የእድገት ለውጥ አሳይቶ ዛሬ የደረሰበት ደረጃ እንዲደርስ፣ ለዚህ ስነግጥም እድገት በቁንጮነት ከሚጠቀሱ የስነጽሁፍ ሰዎች መካከል በተቀዳሚ ስሙ የሚጠራው አቶ ሀይሉ ገብረዮሐንስ ወይም ገሞራው ነው።ሀይሉ ገብረዮሐንስ በ1960ዎቹ አጥቢያ ወደ መድረክ ብቅ ሲል፣ የዘመኑን ህይወት ውስጣዊና ውጫዊ ገጽታዎች እንዲሁም የዘመኑን ሰው ስብእና የመረመረባቸው፣ የተፈጥሮን ውበት የገለጸባቸው ግጥሞች ይገኙበታል። ጥንታዊውን ከዘመናዊው፣ የእኛን ሀገርና የውጭ ሀገር ስነግጥሞችን መርምሮ በአዲስ በገነባው ስነግጥማዊ ስልቱ፤ የአማረኛ ስነግጥም የቋንቋና የአገላለጽ ብርታቱን፣ የላቀ የሀሳብና የስሜት ይዘቶችን ለመግለጽ ያለው ጉልበቱን፣ ረቂቅ ሀሳቦችን ለተራው ሰው እንዲገባ አድርጎ በማቅረብ፣ ከሚስጥርነት ያላለፉ ቁም ነገሮች ግልጽ አድርጎ በማሳየት፣ በስነግጥሙ ለተራወ ህዝብ ህይወት ያለውን ወገናዊነት አሳዬ። ግጥሞቹ ጥልቀት ያላቸው ሀሳቦችንና የህዝቡን ብሶት ለተራው ህዝብ እንዲገቡ ግልጽ አድርገው የሚያሳዩ በመሆናቸው፣ በዘመኑ የተወደዱና ቀጥሎም ለተነሱ ትውልዶች አርአያ ሆኑ፡ለምሳሌ በበረከተ መርገም በሚለው ግጥሙ፤-ከጥንት ጀምሮ ስናየው የኖርነውሲነድ ሲቃጠል የሚስቅ እሳት ነው። ሲል በሌላ ጊዜ ደግሞደረቁ የብስ ዉሃ ጠምቶት በመከራ ስቃዩን ሲያይዝናብ ቢዘንብ ጎርፍ ቢወርድ የብሱን ትቶ ካሮንቋው ላይዝናብ ቢጥል ዘር ፈልጎ ውሃ ካለው ከሐይቁ ላይያስጨነቀኝ እንዲህ ያለው እንዲህ ያለው ልዩ ጉዳይ። ይላልየስንኙ ቤት እንዲመታ ተብሎ የሚገጠሙ እኝ – እኝ የሚሉ ግጥሞችን ሲሄስ፣ ”ቃላት በቋንቋ ውስጥ የየራሳቸው ቦታ አላቸው። ቦታቸው ሲናጋ የሉም፤ ሞተዋል ማለት ነው” ይልና፣ የአዲሱ ትውልድ ስነግጥም ከጥንታዊውና ከዘመናዊው ስነጽሁፍ የዳበረ ዘዴና ይትበሀል መቀዳት ይኖርበታል ሲል ይመክራል። የሀይሉ ገብረዮሐንስ ቃላቶች ፍታውራሪ፣ ቀኛዝማች፣ ደጃዝማች ተብለው እንደተሾሙ ሁሉ የየራሳቸውን ቦታ ይዘው ተደላድለው የተቀመጡ መሆናቸውን ለማሳየት ያህል ”ጎጆዬም ጠላችኝ” ከሚለው ግጥሙ ለላሙና በከፊል ልጥቀስ። ግጥሙ ስለራሱ ከሀገሩ ስለመሰደዱና ስለመንገላታቱ፤ ጎጆዬ የሚላትም ሀገሩን፣ አስተዳደሩን ይመስለኛል።እንዴት ታኮርፊያለሽ እንዴትስ ትጠይኝለገዛ ህይወትሽ ተመከሪ ባልሁኝ።ሰዎች ፍረዱልኝ ወይም ፍረዱብኝጎጆዬ ጠላችኝ ተሻሻይ ባልሁኝ።የጎጆዬ መጥላት ሁኔታው ቢጨንቀኝከደጅዋ ላይ ሆኜ በሀዘኔ ሳቅሁኝ።ቀልብን ነካ አድርጎ ልብን የሚሰውርከፍተኛው ሀዘን፣ አሰቃቂው ልቅሶ አለንባ የሚያስቀርመጨረሻው አይነት የሰቆቃው ድንበርሳቅነው ብለውኛል ማስካካት አለነውር።ስቅቅ ላለው ልቅሶ ምርር ላለው ሀዘንበመጨረሻ ላይ መግለጫው ሳቅ ይሆን? ?ሀይሉ ገብረዮሐንስ (ገሞራው)፣ የጥንቱ ስነግጥም በሀሳብና በአገላለጽ ብልሀት የሚያበረክተውን አስተዋጽኦ ቀላል አለመሆኑን የሚያምንና ከግእዝ አስከ አማረኛ ያሉ የስነግጥም ድንጋጌዎች ውርስ በመመርመር የሚደርሳቸው ረቂቅ ሀሳቦችን ያዘሉ ግጥሞች፣ በአይነት፣ በይዘትም በብልሀት የአማረኛን ስነግጥም የላቀ ደረጃ ላይ አድርሰውታል፤ ለምሳሌ ከመጠን በላይ በእውቀት በስለው፣ ይህ ከፍተኛ ብስለታቸው ከአካባቢያቸው አስተሳስባቸው በመናሩ እንደበደል ተቆጥሮባቸው ያለጊዜው ለተቀጩና ለተፈጥሮም ልዩ የማጥፋት ችሎታዋ ትዝብት እንዲሆን ጭምር ሲል ባበረከተው ግጥም፡በመንቃት ላይ ባሉ ፍጡራን መካከልሕይወት የምንለው እንደ ጥሬ እህልበኑሮ ምጣድ ላይ ቢቆላ ቢማሰልየበሰለው ያራል ጥሬው እስኪበስል። ይለናል፤ሀይሉ ግንባር ቀደም ለውጥ ፈላጊ በመሆን ግማሽ ምእተ አመት በስነግጥም ብቻ ሳይሆን በፖለቲካው መድረክም አሳልፏል። ሀይሉ በየግጥሞቹ የዘመኑን ሕይወት ድቀትና እውነታ እንደ መጽሀፍ ገልጾ እያሳዬ፣ የተሻለ ህብረተሰብን ለመፍጠር የለውጥ አስፈላጊነትን ገልጿል። ሆኖም፣ ለሀገርና ለህዝብ እድገት የሚያስገኝ ለውጥ አስፈላጊነትን ቢያምንም፣ ለውጡ ግን የኛ የሆነውን ሁሉ አገልግሎቱን እንደጨረሰ አሮጌ እቃ አውጦ ጥሎ ሰለጠኑ ከምንላቸው ሀገሮች ምኑንም ምኑንም ከነዝባዝንኬው ማግበስበስ አለመሆኑን በተደጋጋሚ በግጥሞቹ አስነብቦናል። የራስን ማንነትና ምንነት ሳይመረምሩና ግንዛቤ ውስጥ ሳያስገቡ የለውጥ አስፈላጊነት የሚሰብኩትንም ሲሄስ፣”የራሳቸውን መርሀ እውር ለራሳቸው የህሌና ምጣኔ ይቀምራሉ፤፡ ከራሳቸው ግላዊ አስተሳሰብ የራሳቸውን የህሌና አለም ይፈጥራሉ፣ በዘመናትና በትውልዶች አማጭ ረማጭነት ለዘመኑ ትውልዶች የተላለፉትን ባህላዊ ቅርሶች፣ ቫልዩስ፣ ፎርምስ፣ አቲትዩድስ በማርከስ ከግብስብስ መጽሀፍትና ከረጋ ሰራሽ ልምዶች የቃረሙትን ርካሽ አስተሳሰቦች በመደረትና የራሳቸውን የስነህይወት መመሪያ በአየር ላይ ያውጃሉ። አንቀጽ አያስጠቅሱም እንጂ ከእነዚህ ሁሉ አልፈው ተርፈው አካላዊ እነሱነታቸውን ከተራው ሰው ለመለየት የማይነቀሱት፣ የማይኳሉት፣ የማይበጡት ነገር የለም። ይህ ሁሉ ጥረት ከድምሩ ህዝብ አፈንግጦ ለመታየትና ልዩ መስሎ ለመገኘት ስለሆነ የግብዝነት ባህርይነቱ እንደ ታራራ ላይ ፋና ቅልጥጥ ብሎ ይታያል። በሰብአዊነቱ አንጻር የሚያስደንቅ ፍሬ አልባ ሙከራ ነው።” ይልና ስለ እኛ ማንነት ዘወር ብሎ ሲተክዝ ከረዥም ግጥሙ ብቀነጭብ ”እሽሩሩ ድንቡልቦቃ” በሚለው ግጥሙ እንዲህ ይላል።ግን ዋ ያ ቅኔያችን ካልኩለስ በነበርዋ ያ ብሉይ ያ ሐዲስ አልጀብራ በነበርዋ ያ መሳጭ ዜማችን ፊዚክስም በነበርእንዲህ ያርጋጅ አንጓጅ፣ አድናቂ አጨብጫቢ ሆነን ባንቀር። ይላልሀይሉ መጀመሪያ ታወቀበት ከሚባለው ከበረከተ መርገም ጀምሮ ያሉትን ግጥሞች ስናነብ የምንረዳው፣ አጨብጫቢነትን ተጠይፎ እውነትን ለማደን ወጦ ሲንከራተት መኖሩን እናያለን። ስለ እውነትም ሲናገር እንዲህ ይላል።”የኔን ልንገራችሁ ፍልስፍናም ኪነትም፣ ጥበብም፣ እውቀትም፣ ትምህርትም (የፈለጋችሁትን በሉ) ሁሉ ነገር እርቃነ እውቀትን ለማስገኘት ነው። አንድም ፍልስፍናም ጥበብም ኪነትም … ሆነች እውነት ናት። እውነት በበኩሏ አንድ ባህሪ ሲኖራት ያም ባህሪዋ ዋህድነት (አንድነት) ብቻ ነው። … የአትላቲክ የፓሲፊክ እውነት፣ የአውሮፓዋ የአፍሪካዋ እውነት፣ የነጩ የጥቁሩ እውነት፣ የእስላሙ የክርስቲያኑ እውነት፣ የሁሉ እውነት … አንዲት ናት።” ይለናል። ግን እውነት በተናገረ፣ እውነትን ባስተማረ፣ እውነትን በመረመረ ከሀገሩ ወንጀለኛ ሆኖ የተባረረበትን እውነታ ለማጥመድ አደን አልቀናው ብሎ ተስፋ ሳይቆርጥ ከሱ ይልቅ ለሀገሩ ሲያንጎራጉር፤እመኘው ነበረ ሞትሽን ለሞቴግን አልሆነልኝም ተቃጠለ አንጀቴሸካራው እድልሽ ሲያጉላላሽም ቢኖርምብታረጂም አንኳ ቀን ሳይወጣ አይቀርምስለዚህ እስከዚያው እያለቀስኩ ላዝግምየሀይሉ ጎሞራው ግጥም አንድን ፍልስፍና፣ ርዮተዓለም፣ ሃይማኖት፣ ወዘተ መስበኪ ወይም ማስተላለፊያ ሳይሆኑ፣ ስሜትን፣ ረቂቅ ሀሳብን፣ ውበትን፣ ወዘተ በመግለጽ ከሙሉነትም በላይ ሞልቶ የሚፈሱበት ግጥሞች ናቸው። ስሙት አዝኖ አሳዝኖን መልሶ ስለኛ ሲጨነቅ፤እስቲ ልናገረው ይውጣልኝ ልተንፍስአልቻለም ያ ልቤ ታምቆ መላወስበኔ የደረሰው በማንም አይድረስ።
All reactions:
11