
12 ታህሳስ 2023, 09:42 EAT
በልብስ መስቀያ መንጠቆ መልኩ የተሰሩት የስለላ ካሜራዎች በግዙፉ ኩባንያ አማዞን አማካኝነት ለሽያጭ ቀረቡ።
ካሜራዎቹ ከመወዛገቢያነት አልፈው ግላዊነትን በመጣስ ኩባንያው ክስ ተመስርቶበታል።
በአማዞን በሽያጭ ዝርዝር ውስጥ የተካተተው እና ቢቢሲ የተመለከተው ካሜራ በመታጠቢያ ውስጥ ካለው የፎጣ መስቀያ ጋር ተመሳሳይነት አለው።
በቅርቡ በአማዞን በተሸመተ የልብስ መስቀያ ካሜራ ያለ ፈቃዴ በመታጠቢያ ውስጥ ተቀርጫለሁ ስትል አንዲት ግለሰብ ክስ ማቅረቧን ተከትሎ አንድ የአሜሪካ ዳኛ ኩባንያው ክሱ እንዲቀጥል ውሳኔ አስተላልፈዋል።
እንዲህ አይነት መሳሪያዎችን ላልተገባ ተግባር ማዋል የብሪታንያ ህጎችን የሚጥስ እንደሆነ አንድ ከግል መብቶች ጋር የተያያዘ ባለሙያ ተናግረዋል።
አማዞን በጉዳዩ ላይ አስተያየት ከመስጠት ተቆጥቧል።
በአሜሪካ የአማዞንን ኩባንያ የከሰሰችው የውጭ አገር ተማሪ ናት።
በዌስት ቨርጂኒያ በሚገኝ መኖሪያ ቤት ውስጥ ትኖር በነበረበት ወቅት በመታጠቢያ ቤት ውስጥ በተገጠመ እና የልብስ መስቀያ በሚመስል ካሜራ በድብቅ መቀረጿን ተናግራለች። ግለሰቧ ካሜራው ከአማዞን የተገዛ እንደሆነ የገለጸችው።
የካሜራው ባለቤትም ክስ ተመስርቶበታል።
- አዲሱ የደቡብ አፍሪካ ትውልድ እና የማንዴላ ፍቅር እና ምሬት የተሞላበት ትሩፋቶች12 ታህሳስ 2023
- የዚምባብዌ ዜጎች የገንዘብ ሚኒስትራቸው ‘የአፍሪካ ምርጥ’ ተብለው መሰየማቸው አስገርሟቸዋል12 ታህሳስ 2023
- “ስለእርቅ ስለተናገርኩ፣ ጦርነት ይቁም ስላልኩ እንጂ ሌላ ምክንያት የለም” – አቶ ታዬ ደንደአ11 ታህሳስ 2023
ካሜራው በአማዞን የሽያጭ ድረ ገጽም ላይም ፎጣዎችን ለመስቀል መገልገያነት የሚውል እና “ትኩረትን የማይስብ” ከሚል ሃረግ ማስታወቂያ ጋር መቅረቡንም ግለሰቧ ከክሷ ጋር አያይዛለች።
ካሜራውን ገዝቶ ከገጠመው ግለሰብ በተጨማሪ ኩባንያው “ይህ እንደሚሆን” ያውቅ ነበር በሚልም በአማዞን እና ያልተጠቀሱ የአጋር ኩባንያዎቹም ቅጣት እንዲጣልባቸው ጠይቃለች።
አማዞን በበኩሉ ካሜራው ጥቅም ላይ በሚልውበት መንገድ ተጠያቂ ልሆን አልገባም በሚል የፍርድ ክሱ ውድቅ እንዲደረግ ቢጠይቅም አልተሳካለትም።
የልብስ መስቀያ ካሜራዎቹ በገንዳ ላይ እንዲሁም በአልጋ አጠገብ ሊቀመጡ እንደሚችሉም አማዞን በሽያጭ ዝርዝሩ አካቷቸዋል።
ከነዚህ ካሜራዎች በተጨማሪም በማንቂያ ሰዓት ውስጥ የተደበቀ ካሜራ፣ እንደ ዩኤስቢ ቻርጀር የሚመስል ካሜራ እንዲሁም ‘ታማኝ ያልሆነ የህይወት አጋርን’ ለመከታተል ጥቅም ላይ ሊውል ይላል የተባለ እሳትን የሚቆጣጠር አላርም የሚደበቅ ካሜራ በአማዞን ከቀረቡት ውስጥ ይገኙበታል።