December 12, 2023

ታየ ደንደአ የቀድሞ አለቃውን በተገቢ ቃል ገልጾታል።

“አረመኔ”

መንግስቱ ሙሴ ፡  የአረመኔው አብይ አህመድ ፀሐይ መጥለቅ ጀመረች። የመጀመሪያው ወራጅ ታየ ደንደአ ሆነ ማለት ነው። ይቀጥላል በጣም ብዙ ቀልቀሎ ሆድ የያዙ ተሳፋሪወች በጀልባዋ አሉ። እነዚህ ተሳፋሪወች ሁሌም አይናቸው እና ልቦናቸው ከግል ኑሮ፤ ከእለት ጉርስ ጋር የተቆራኘ በመሆኑ የጀልባዋ መስመጥ አይታያቸውም።

ታየ ደንደአ የጀልባዋን መስመጥ ጅማሮ ተረዳ እና በጥልቅ የሚያውቀውን የአለቃውን ባህርይ የገለጸበት ቃል “አረመኔ” የሚል ነው። አረመኔነቱን ያኔ በወለጋ በሽህ የሚቆጠር የአንድ ትንሽ ከተማ አማሮች ሲጨፈጨፉ አብይ አህመድ ችግኝ ተከላ ወጣ። ታየ ያኔም ያየውን የታዘበውን በሁለት አመቱ ዛሬ “አረመኔ” በሚል አንድ ቃል ገለጸው።

ብዙ ጨካኝ መሪወች አሳልፈናል። ጭከናን ከልክ አሳልፎ ያሳየን ግን አብይ አህመድ ነው። ቃላት የማይገልጠውን የአለቃውን ባህርይ ታየ “አረመኔ” ብሎታል በበኩሌ ቃሉ ያንስብኛል ግን የተሻለ ገላጭ ቃል ከተገኘ ከአረመኔነት ከፍ ያለ እስማማለሁ እስከዚያው ግን ጥሩ ቃል ነው።

ህወሓት በ11 ኛው ሰአት “በስብሰናል” መታደስ አለብን ብላ ወደመቀሌ ሄዳ ለወር ተቀመጠች። ያም ሆኖ የሞተን መመለስ አይቻልም እና የፖለቲካውን ሞት ተጎነጨች። የኦሮሞው ብልጽግና ኦነጋዊው መንግስት ዛሬ አንዱ የመሰረቱትን ስርአት መሪ አረመኔ በሚል ገልጦታል ይህች የስርአታቸውን ሞት ገላጭ ቃል በታሪክ የተመዘገበች ናት። ገራሚው ነገር ግን ዶ/ር አንጋሳ እና ታየ አንድ ፔጅ ላይ ያሉ ይመስላል ለመሆኑ በአዴን የሚባሉት ጉዶች ግን እነ መላኩ አለበል፤ ብናልፍ፤ ወዘተ ዛሬ ምን ይሰማቸው። የአብይ አህመድ አረመኔነት የተገለጠው መጀመሪያ በአማራ ሕዝብ ላይ ያሳየው በሁአላ በትግራይ እና በአፋር ሕዝባችን ላይ ነው። ኦህዴዶች እነ ታየ ደንደአን ጨምሮ የሰሩት ኦነጋዊ ስርአትን መሪ “አረመኔነት” እያንገሸገሸው ታየ ደንደአ ሲናገረው በአዴኖች እንወልክለዋለን በሚሉት ሕዝብ የደረሰው የጥፋት መአት እና አሁንም እየተካሄደበት ያለው ውርጅብኝን ማየት እና መግለጥ ያለመቻላቸው በእውነቱም አንዳንድ ሰወች እንደሚሉት ሁሉም እሬሳወች መሆን አለባቸው። እሬሳ ስል አባባል አይደለም እውነተኛ መቃብር ያልወረደ በድን ማለቴ ነው። በእዝነ ልቦናየ በአዴን የተባሉትን ከነ ብናልፍ እስከነ ጄነራል ተብየው የሬሳ ስብስብ መሆናቸውን ታየኝ።

ለማነኛውም አረመኔዋን ጠ/ሚ የከበቧት ተስፈኞች መውረድ መጀመራቸውን ስራቷም መፍረሱን ታየ አብስሮናል።

ድሮ እኔም እዲህ ብየ ነበር ፋኖ ተሰማራ፤ እንደሆችሚንህ እንደ ቸ ጎቬራ፤ የዚህ ትውልድ ፋኖወች የሚዘምሩም የሚሸልሉም በነበላይ፤ በነአሞራው ውብነህ በነኃይለማርያም ማሞ ነው። የዚህን ትውልድ ትንታግ ፋኖወችን ሳስብ ለዘመናት አንገቴን የደፋሁትን ያህል ኩራት ኩታት እያለኝ መጥቷል። እነዚያን ተርብ ታጋዮች የጁላን ግሳንግስ ጠራጊወችን ባሰብሁ ግዜ አካሄድ አረማመዴን ቀይሬአለሁ። የአረሜነውን ስራትም እድሜ እያሳጠሩት በመሆኑ ፈጣሪ ከነሱ ጋር ይሁን!

ድል ጀኖሳይድ ለተካሄደበት ያማራ ሕዝብ እና ድል ለፋኖ!!!  መንግስቱ ሙሴ